Alem Ketema Enat General Hospital

Alem Ketema Enat General Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alem Ketema Enat General Hospital, Hospital, Merabete, `Alem Ketema.

14/02/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ።ዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል
18/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ።
ዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል

በቀን 05/05/2018 ዓ/ም የአለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ የሆስፒታሉን የ2018  ዓ/ም ግማሽ አመት(6 ወራት) እቅድ አፈፃፀም ገመገመ።መድረኩን የመሩት :_1. ...
17/01/2026

በቀን 05/05/2018 ዓ/ም የአለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ የሆስፒታሉን የ2018 ዓ/ም ግማሽ አመት(6 ወራት) እቅድ አፈፃፀም ገመገመ።
መድረኩን የመሩት :_
1. አቶ ያቤፅ ንጉሴ - የሆስፒታሉ ስራ ኘመራር ቦርድ ሰብሳቢና የአለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ
2. አቶ ጌታው በላይግዛው -የሆ/ሉ ም/ቦርድ ሰብሳቢና የመርሐቤቴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
3. አቶ አለባቸው አብወይ - የሆስፔታሉ ስራ አስኪያጅ
ተሳታፊዎች:_
1. ተጋዥ እንግዳ አቶ ብርቃብርቅ ---በአብክመ የሰሜን ሸዋ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ
2. የሆስፒታሉ ስራ አመራር ቦርድ አባላት
3. የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አባላት
4. የስራ ክፍል አስተባባሪዎች ሰሆኑ
የሆስፒታሉ አፈፃፀም በፖርፖይንት ከቀረበ ቡኋላ በጥንካሬና ወደ ፊት መስተካከል ባለባቸው አሰራሮች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የእለቱ መርሀ ግብር ተጠናቋል፡፡

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
06/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ

መልካም ዜናበቀን 17/04/2018 ዓ/ም የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል የህሙማን መርጃ ማህበር ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ከመደገፍና ምንም ነገር የሌላቸውን ህሙማን ከ...
27/12/2025

መልካም ዜና
በቀን 17/04/2018 ዓ/ም የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል የህሙማን መርጃ ማህበር ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ከመደገፍና ምንም ነገር የሌላቸውን ህሙማን ከማሳከምም በላይ መክፈል ለማይችሉ ሃምሳ (50) የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባልነት ክፍያ በመክፈል የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አደረገ።
የህሙማን መርጃ ማህበሩን አባላት እንድሁም በተለያዬ ጊዜ የምትረዱትን በተገልጋይ ማህበረሰቡ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ይህንን የተቀደሰ ስራ መርዳት ለምትፈልጉ:_
=ወ/ሮ ውባለም ፀጋዬ=0924788772
=CBE Account =1000255383648 /ዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል ህሙማን መርጃ ማህበር/
//ዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል//

30/11/2025
28/11/2025

| ‎

‎የጤና ባለሙያዎችን የመጀመሪያው ዲግሪ ስልጠና ምልመላን ይመለከታል

28/11/2025

ህፃናት እንደ ተወለዱ የሚሰጥ የጉበት በሽታ መከለከያ ክትባት
__________

ከወሊድ በኋላ የሚሰጥ የሄፐታይተስ ቢ ክትባት ወይም የጉበት በሽታ መከለከያ ክትባት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍና ሕፃናት ወደፊት እንደ የጉበት ጠባሳ እና የጉበት ካንሰር ያሉ ሥር ለሰደዱ የጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ ይከላከላል።

በተለይም እናት የቫይረሱ ተሸካሚ ከሆነች፥ ከወሊድ በኋላ ክትባቱን መስጠት ኢንፌክሽኑን ለመከላከል በጣም ውጤታማው መንገድ ነው።

የሄፐታይተስ ቢ ክትባት ህፃናት ከተወለዱ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ይሰጣል። በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓት ውስጥ ክትባቱ መስጠት አስተማማኝ እና ውጤታማ ነው ።

ከሆስፒታል ውጭ ለተወለዱ ህጻናት ክትባቱን ከተወለዱ በኋላ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ መከተብ አለባቸው።

ክትባቱ በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት እና በተወሰኑ የግል ጤና ተቋማት ውስጥ ይሰጣል!

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

28/11/2025

(Amebiasis)
======
አሜባ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ረቂቅ ጥገኛ ተዋሲያን ነው ፡፡ አሜባ በዋነኝ አንጀትን የሚያጠቃና አንጀት ውስጥ የሚኖር ሲሆን ከአንጀት ውጭም እንደጉበት ያሉ አካላትን ያጠቃል፡፡ አብዛኛው ሰው አሜባ አምጭ የሆነው ትል አንጀታቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ሰዎች የበሽታውን ምልክት ሳያሳዩ ይኖናሉ ነገር ግን ምልክቱን የሚያሳዩም አሉ፡፡

#መንስኤው
=====
አሜባ ኢንታሜባ ሂስቶሎቲካ (E. Histolytica) በተባለ አሜባን አምጭ በሆነ ጥገኛ ትላትል ይከሰታል፡፡

?
======
☑️የተበከለ ውሃ እና ምግብ ዋና መተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው፡፡
☑️ከሰገራ ጋር ከሰውነት ከወጣ በኋላ ለሳምንታት ምንም ሳይሆን የመቆየት ችሎታ ያለው ሲሆን ያልበሰሉ ምግቦች በተለይም አትክልት መመገብ ለበሽታው ያጋልጣል፡፡

?
=====
👉የሆድ ቁርጠት
👉ደም የቀላቀለ ተቅማጥ
👉ድካም
👉ራስ ምታት
👉የሰውት ፈሳሽ እጥረት
👉ትኩሳት እና በአጠቃላይ የጤና ችግር ፡

☑️አንጀት ውስጥ የነበረው አሜባ በደም አማካኝነት ተሰራጭቶ ጉበትን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ጉበት ውስጥ ከገባ በኋላ መግል ይፈጥራል፡፡ በቀኙ የላይኛው የሆድ ክፍል የሚሰማ ህመም እና ትኩሳት ዋናዎቹ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በሽታው ከአንጀት ቢነሳም ተቅማጥ የሚታየው በጣም ጥቂት በሽተኞች ላይ ነው፡፡ ጉበት ውስጥ የተፈጠረው መግል ወደ ሳምባም ሊዛመት ይችላል፡፡ ለአሜባ የሚሰጡ መድሃኒቶች የሚያድኑት ሲሆን ተጨማሪ መዘዞችን ካመጣ ወይም ደግሞ በመድሃኒቶቹ ካልዳነ ኦፕሬሽን መሰራት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡


=====
የአንጀት የአሜባ በሽታ ሰገራ ተወሰዶ በሚደረግ የማይክሮስኮፕ ምርመራ ይታወቃል።
ከአንጀት ውጭ የሆነ በአሜባ ምክንያት የተከሰተ የጉበት መግል ማከማቸት ደግሞ አልትራሳውንድ ወይም ሲቲ ስካን በመስራት ማወቅ ይቻላል።
የአሜባ በሽታ በምርመራ ከታወቀ በኋላ አሜባውን አከንጀት እና ከሌሎችም የሰውነት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚረዱ መድሀኒቶች (Metronidazole ,Tinindazole, Paramomycine,Pyrantel Pamoate...)ይታዘዛሉ።


=====
👉ምግብን በንፅህና ማዘጋጀት
👉የሚጠጣ ውሃን ማፍላት
👉 ምግቦችን በተለይ አትክልትን በደንብ አብስለሎ መመገብ
👉 ንፁህ ውሃ መጠጣት
👉 ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብ
👉የህመሙ ምልክቶች ካሉ ቶሎ ውድ ህክምና ቦታ መሄድ፣ መመርመር እና የታዘዙልዎትን መድሀኒቶች በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል።

ምንጭ
1.CDC
2.Mediscape

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

Address

Merabete
`Alem Ketema

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alem Ketema Enat General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category