13/10/2023
የደም ግፊት/"ደም ብዛት"-HYPERTENSION
ምንድነው?
👉ክንድዎ ላይ በሚደረግ የግፊት መለኪያ መሠረት የደምዎ መጠን ከ140/90ና ከዚያ በላይ ከሆነ የደም ግፊት አለብዎት እንላለን። (JNC 8, STG-2021 two measurments)
መንስኤው ምንድነው?
👉በተፈጥሮ ተጋላጭነት ሲኖር (Genetically predisposed የምንለው)
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት; የአልኮል መጠጥ ማዘውተር; ሲጃራ ማጨስ; ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ ወዘተ...(Sedentary life style)
👉ሌሎች በሽታዎችን ተከትሎ (የኩላሊት; የሆርሞን;የስኳር; የልብ ና የደምስር በሽታዎች) ሊከሰት ይችላል።
የሕመሙ ምልክቶች
👉ደም ግፊት በራሱ የተለየ ምልክት የለውም።
👉የደም ግፊት መጠኑ ከፍ ሲል ከሚየስከትለው ውጤት አንፃር እንደተጎዳው የሰውነት ክፍል የተለያዩ ምልክቶች ይኖሩታል➡️ራስምታት; የባሕሪ ለውጥ; ድካምና ለመተንፈስ መቸገር; እግር/እጅ መደንዘዝ ወይም አለመታዘዝ ወዘተ...
የሚያስከትለው ውጤት
👉የልብ ሕመምን ተከትሎ ድንገተኛ ሞት
👉ስትሮክ(የአንጎል ውስጥ ደምስሮችን በማፈንዳት/ በማጥበብ ምክንያት)
👉 ኩላሊትን ይጎዳል
👉የደም ስሮች ውስጥ የስብ ክምችትን ያስከትላል
ምርመራ
👉የደም ግፊት ልኬትን ማዘውተር
👉የልብ; የኩላሊት ና የኮሌስትሮል ምርመራዎችን ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።
መፍትሔዎች
👉ውፍረት መቀነስ (BMI
Address: Adaamaa, Ganda 01, Sillaasee maazooriyaa, Cinaa baankii Abisiiniyaa አዳማ,01, ስላሴ ማዞሪያ, አቢሲንያ ባንክ አጠገብ 0936239911/0973909096