GoodCare home health care & consultancy services

  • Home
  • GoodCare home health care & consultancy services

GoodCare home health care & consultancy services Medical home care

26/06/2024

አስደሳች ዜና

በኢትዮጲያ የመጀመሪያ የሆነው የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በኘራይቤት ዊንግ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ ።

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በሚሰጠው ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎት በርካታ የማህበረሰቡ ክፍልን እያገለገለ ይገኛል።

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከዚህ በፊት በኘራይቤት ዊንግ የመሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና መጀመሩ ይታወሳል

በዛሬው እለትም በኢትዮጲያ የመጀመሪያ የሆነው የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በኘራይቤት ዊንግ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል ።

ከፍተኛ ቀዶ ጥገናውን ያከናወኑት የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም የአርትሮስኮፒ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት
ዶ/ር ሰኢድ መሃመድ ቀዶ ጥገናው የተሳካ እንደነበር ገልፀው በቀጣም አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጠባበቁ ታካሚዎች ስለሚገኙ ስራውን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት የሃገር ውስጥ የህክምና ግብአት ምርት እና ኢኖቬሽን አውደ-ርእይ ተከፈተ ____________በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነው የሃ...
22/06/2024

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት የሃገር ውስጥ የህክምና ግብአት ምርት እና ኢኖቬሽን አውደ-ርእይ ተከፈተ
____________

በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነው የሃገር ውስጥ የህክምና ግብአት እና ምርቶች ኢኖቬሽን አውደ-ርእይ “ጤናችን በምርታችን” በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀምሯል፡፡

በግርብናው ዘርፍ የተገኘውን የሃገር ውስጥ ምርት የማሳደግ ስኬት የህክምና ግብአት እና ምርትንም በማሳደግ ይደገማል ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤ የሃገር ውስጥ የህክምና ምርቶችን ማሳደግ አስፈላጊነትን በተመለከተም የኮቪድ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሃገራት ክትባትንና ሌሎች ግብኣቶችን ማግኘት መቸገራቸውን በማስታወስ ከዚህ ቀደም ከሀገር ዉስጥ አምራቾች ሲቀርብ የነበረዉ የህክምና ግብኣት 8 በመቶ ብቻ የነበረዉ አሁን ላይ ወደ 36 ፐርሰት በጥቂት አመታት ውስጥ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የሃገራችን የህክምና ምርቶች ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ አቅም ያላቸው ግለሰቦች ቢሳተፉ ትርፋማ እንደሚሆኑ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ እንደ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዘመናት የባህል መድሃኒት እውቀት ያላት ሃገር በመድሃኒት ምርት ከራሷ አልፋ ለሌሎች ሃገራትም መትረፍ ትችላለች ብለዋል፡፡

ጊዜው ክረምት በመሆኑ በተለይም ኢትዮጵያውያን ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ አውደ-ርእዩ በማምጣት እና በማስጎብኘት የልጆቻቸውን ተነሳሽነት እንዲያሳድጉ ጥሪ ያቀረቡት ዶ/ር አብይ፤ አውደ ርእዩን ያሰናዳው ጤና ሚስቴር እንዲሁም መድሃኒት በማምረት የዜጎችን ህይወት በመታደግ ላይ ለሚገኙ አምራቾች ምስጋና በማቅረብ የኢትዮጵያ መንግስትም ለዘርፉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር የሃገር ውስጥ የህክምና ግብአት እና ምርትን ማሳደግን በፖሊሲው ውስጥ አካቶ እየተገበረ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በአውደ-ርእዩ መክፈቻ የተናገሩ ሲሆን፤ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ የሃገር ውስጥ የመድሃኒትና ሌሎች ግብአቶች ምርትን ማሳደግ መሆኑን በመግለጽ አዳዲስ ምርቶችን በማምረት ወደ ገበያ እንዲገቡ ለባለሃብቶች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው አውደ ርእዩ ከ110 በላይ የሃገር ውስጥ የህክምና ግብአቶች እና ምርቶች አምራቾች የተሳተፉ ሲሆን፤ አውደ ርእዩ ለቀጣይ ስድስት ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

11/06/2024
02/06/2024
ለሴቶች...የማህፀን ውስጥ ዕጢ መንስኤ፣ ምልክቶችና መፍትሄው ፡-የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለውና ወደዛ የመለወጥ ዕድሉ እጅግ በጣም አናሳ የሆነ የማሕፀን ውስጥ ዐባጭ ሲ...
31/05/2024

ለሴቶች...
የማህፀን ውስጥ ዕጢ መንስኤ፣ ምልክቶችና መፍትሄው ፡-
የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለውና ወደዛ የመለወጥ ዕድሉ እጅግ በጣም አናሳ የሆነ የማሕፀን ውስጥ ዐባጭ ሲሆን በአብዛኛው የሚከሰተውም በወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው፡፡

የማሕፀን ዕጢ ከማሕፀን ግድግዳ ጡንቻዎች የሚነሳ ሲሆን ሴሎች ጤናማ ባልሆነ ሆኔታ ሲከፈሉ የሚከሰት ችግር ነው፡፡

ይህ የማሕፀን ዕጢ በፍጥነት የሚያድግ ወይንም በዝግታ የሚያድግ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተመልሶ በራሱ ሊጠፈም ይችላል፡፡

የማሕፀን ዕጢ በሴቶች ላይ እጅግ የተለመደ በመሆኑ ምክንያት ከ4 ሴቶች ሦስቱ በሕይወት ዘመናቸው የማሕፀን ዕጢ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ምልክት ስለማያሳዩ እንዳላቸውም የማወቅ ዕድል የላቸውም፡፡ በአብዛኛው የሚገኘው በድንገት በሚደረግ ምርመራ ነው፡፡

>> የማሕፀን ዕጢ ምልክቶች -

በአብዛኛው ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ላይ እነዚህ ይስተዋላሉ :-

• ከፍተኛ የሆነ የወር አበባ መብዛት
• ከሰባት ቀናት በላይ የሚቆይ የወር አበባ ማየት
• ማሕፀን አካባቢ ግፊት መሰማት ወይንም ሕመም
• ቶሎ ቶሎ የውሃ ሽንት መምጣት
• የሆድ ድርቀት
• የጀርባ እና የዕግር ሕመም ስሜት
• አልፎ አልፎ ከፍተኛ የሆነ ሕመም የሚያስከትል ሲሆን ይህም የሚሆነው የደም ዝውውር በሚቀንስ (በሚቋረጥ) ጊዜ ነው፡፡

>> የማሕፀን ዕጢ መንስኤው -

ይህ ነው የሚባል ዕርግጥ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ጥናቶች የሚያመለክቷቸው ከሆርሞኖች እና ከዘር ግንድ ሁኔታዎች ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው ነው፡፡

>> ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች -

• ከዘር፡-
እናት ወይንም እህት የማሕፀን ዕጢ ካላቸው ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡

• ጥቁር ዘር፡-
ጥቁር ሴቶች በአብዛኘው ተጋላጭነታቸው ይጨምራል፡፡

• በልጅነት የወር አበባን ያዩ ከሆነ
• አመጋገብ ናቸው፡፡

የማኅፀን ዕጢ ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ ባይሆንም የደም ማነስ እና ምቾት ማጣትን ግን ሊያስከትል ይችላል፡፡

>> የማሕፀን ዕጢ እና እርግዝና -

የማሕፀን ዕጢ በአብዛኛው እርግዝናን የማይቃረን ቢሆንም አንዳንዴ ዕጢው በሚገኝበት ቦታምክንያት በጥቂት ሰዎች ላይ እርግዝናን እንዳይፈጠር መንስዔ ይሆናል፡፡ ይህ በሚሆን ጊዜ ሐኪምን በማማከር ከእርግዝና በፊት መደረግ ያለባቸውን ቅድመ ሆኔታዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

>> ሐኪም ማማከር አስፈላጊ የሚሆነው -

• የማያቋርጥ የማሕፀን አካባቢ ሕመም ካለ
• ከፍተኛ ሕመም ያላቸውና በብዛት የሚያስቸግሩ የወር አበባ ጊዜያት
• ከወር አበባ ቀናት ውጪ የደም መፍሰስ
• በግብረ ስጋ ግኝኑነት ጊዜ የሕመም ስሜት ከተሰማዎ
• የሆድ ዕብጠት ካለዎ
• የውኃ ሽንትን ማስወገድ መቸገር
• እጅግ ከፍተኛ የሆነ ድንገተኛ የማኅፀን አካባቢ ሕመም ካለዎትና ከፍተኛ የደም መፍሰስ የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡
ምንጭ:- Doctor Alle

***የስኳር ህክምና ግቦች (therapeutic goals of diabetes care) ምንድን ናቸው? ***=========ዶ/ር መላኩ ታዬ (ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል) በሁሉም የህይ...
30/05/2024

***የስኳር ህክምና ግቦች (therapeutic goals of diabetes care) ምንድን ናቸው? ***
=========
ዶ/ር መላኩ ታዬ (ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)

በሁሉም የህይወታችን ዘርፎች አሸናፊ እንድንሆን ማቀድና ግብ ማስቀመጥ አንዱ የስኬት ቁልፍ ነው። ማቀድና ግብ ማውጣት ህይወታችንን በተቻለ መንገድ ለመምራት ያግዛል። ከሁሉም የሚበልጠው ደግሞ ጤናችን ነው። ስለሆነም ጤናችንን ለመጠበቅ ማቀድ፣ ግብ ማስቀመጥና በጽናት ዘወትር ራሳችንን መንከባከብ ያስፈልጋል። በተለይም የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ጤናቸውን ለማሻሻል አበክረው መትጋት ይኖርባቸዋል። ይህን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ለዛሬ ውይይታችን የመረጥነው ርዕስ የስኳር ህክምና ግቦች ምንድን ናቸው የሚለውን ነው።

እንደሚታወቀው የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠርና የስኳር ተጓዳኝ የጤና እክሎችን ለመቀነስ መደበኛ ክትትል እና ቀጣይነት ያለው ሕክምና ያስፈልጋቸዋል። ሕክምናው የአኗኗር ለውጦችን ማድረግ፣ በጤና ባለሙያ የታዘዙ መድሃኒቶችን በአግባቡ መውሰድና ዘወትር ራስን የመጠበቅ እርምጃዎች ማድረግን ያጠቃልላል። ይህም የስኳር በሽታ የሚያስከትላቸውን የልብና የደም ቧንቧ ውስብስብ ችግሮች ስጋት ይቀንሳል። ነገር ግን ስኳርን ብቻ በማስተካከል ችግሮችን ማጥፋት አይቻልም።

ይልቁንም ዘርፈ ብዙ የተቀናጀ የአደጋ ተጋላጭነት ቅነሳ ማድረግ ይፈልጋል። ይህም ሲባል ስኳር ማስተካከል፣ የደም ግፊትን በተገቢ ሁኔታ ማከም፣ የጎጂ ኮሌስትሮል መጠንን መቀነስ እንዲሁም የሰውነት ክብደት በተለይም ቦርጭን መቀነስ ያካትታል። እነዚህን አራት የስኳር ህክምና ግቦችን ማሳካት አዳጋች ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ ሁሉንም ግቦች መምታት የቻሉት ከ10% ያነሱ ታካሚዎች ብቻ ናቸው። በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሰሩ ጥናቶችም የሚያሳዩት የህክምና ግቦቹን ያሳኩት ታካሚዎች ቁጥር ከ3% የማይበልጥ መሆኑን ነው።

የስኳር እንክብካቤን የሕክምና ግቦች ለማሳካት ከሚያግዙ መሰረታዊ መፍትሄዎች ውስጥ ታካሚን ያማከለ የስኳር ትምህርትና ግንዛቤ ማስጨበጫ እውቀትን ማሻሻል እና ራስን መንከባከብ ይገኝበታል።

የታካሚዎች ስለስኳር ህክምና ግቦች ያላቸው እውቀት ማነስ ራሳቸውን እንዳይጠብቁ፣ የስኳር ቀጥጥሩ እንዲባባስ፣ እንዲሁም የስኳር ተጓዳኝ የጤና እክሎች ስር እንዲሰዱ ያደርጋል። በተቃራኒው ደግሞ የታካሚዎች ስለ ስኳር ሕክምና ግቦች እውቀት መሻሻል እራስን መንከባከብን ፣ የመድኃኒት አወሳሰድን እና የስኳር ቁጥጥርን እንደሚያሻሽል በርካታ ጥናቶች ያሳያሉ።

የስኳር ህክምና ግቦች ዋና ዋናዎቹ አራት ናቸው።

የመጀመርያውና ዋናው ግባችን በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን መቆጣጠር ነው። ይህም ማለት በባዶ ሆድ የሚሰራው የደም መጠን ከ80 እስከ 130 mg/dl ፣ ከምግብ በኋላ የሚለካው የስኳር ልኬት ከ180 mg/dl በታች፣ እንዲሁም የ3 ወር አማካኝ የስኳር ክምችት መጠን ከ7% በታች እንዲሆን ይመከራል።

ነገር ግን የግሉኮስ መጠን በጣም መቀነስ በሁሉም ታካሚዎች ውስጥ የተሻለው ስልት ላይሆን ይችላል። የምናስቀምጠው ግብ ታካሚውን ያማከለ መሆን ይኖርበታል። እድሜያቸው በጣም የገፋ ከሆነ፣ የልብና የደም ሥር ሕመም ከፍተኛ ተጋላጭነት ካላቸው፣ ጥሩ ማህበራዊ ድጋፍ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ እየታየ የስኳር ግባችንን ማላላት ሊያስፈልግ ይችላል። ምክንያቱስ ቢባል አሳሳቢ የሆነ የስኳር ማነስ በራሱ ችግሮች ስለሚያመጣ ነው።

በተጨማሪም ግሉኮስን ብቻ መቆጣጠር በቂ አይደለም። የስኳር ተያያዥ እክሎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቀነስ ሌሎች በርካታ ማስተካ

29/05/2024

ምላሳችን ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?

ምላሳችን እንደ አንድ የሰውነታችን ክፍል ስለ ጤናችን በርካታ ጉዳዮችን ይናገራል።የምላሳችን ቀለም በመመልከት ብቻ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣችንን መረዳት እንችላለን።ይሁን እንጂ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የምላስ ቀለም ለውጦች ሲያጋጥሙን ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋማት በማምራት ሀኪሞችን ማማከር ተገቢ ነው።

1. ቀላ ያለ ምላስ

– ምላሳችን ይህን አይነት ቀለም ሲኖረው ሰውነታችን እንደ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ እና አይረን ያሉ ንጥረ ነገሮች እጥረት እንዳጋጠመው የሚያሳይ ነው።
– አንዳንድ የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎች ደግሞ ይህ ሁኔታ በአንድ በተወሰነ የሰውነታችን ክፍል ሙቀት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ይላሉ።
– የጥርስ ሳሙና፣ መድሃኒት አልያም አሲዳማ ምግቦች በአፍ ውስጥ ከሚፈጥሩት ውህደት ጋር ተያይዞም ሊከሰት ይችላል።

2. ሀምራዊ ምላስ

– ለጉሮሮ ቁስል (ብሮንካይትስ) መጋለጥን የሚያሳይ ነው።
– ሰውነታችን በቂ ኦክስጂን አለማግኘቱንም ያመላክታል።
– ዝቅተኛ የደም ዝውውር እና ከፍተኛ የኮሊስትሮል መጠንንም ይጠቁማል።
– በጣም የቀዘቀዙ ምግቦችን እንዲሁም ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል መውሰድ ደግሞ ለችግሩ ሊያጋልጥ ይችላል።

3. ሻካራ እና ቢጫ ምላስ

– አነስተኛ የሆሞግሎቢን መጠንን ያሳያል።
– ድካም እና መዛል፣ ከሳንባ እና ትልቅ አንጀት ጋር የተያያዙ ችግሮችንም ያመለክታል።
– ዝንጅብል፣ ቀረፋ እና ነጭ ሽንኩርት መጠቀም ከዚህ ችግር ለመውጣት ይረዳል።
– የሄሞግሎቢን መጠንን ከፍ ለማድረግ እንደ ስፒናች፣ ቀይ ስር፣ አፕል፣ ቀይ ስጋ፣ ዘቢብ፣ ማንጎ፣ ለውዝ እና የመሳሰሉ የምግብ አይነቶችን መመገብ ይመከራል።

4. ጥቁር ምላስ

– ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰው ልጆች ምላስ ወደ ጥቁርነት እና ጸጉር የበዛበት መሆን ይሸጋገራል።
– ጥቁርና ጸጉር የሚያወጣ ምላስ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ነው የሚነገረው።
– በምላስ ላይ የሚወጣው ጸጉር በአፍ ውስጥ ለባክቴሪያዎች መራባትና ለቆሻሻዎች መጠራቀሚያነት በማገልገል በርካታ የጤና ችግሮችን ያስከትላል።

5. ነጭ ምላስ

– በምላስ ጸጉሮች ባክቴሪያዎች መሰግሰጋቸውን ያመለክታል።
– የሞቱ ህዋሳት እና ቆሻሻዎች በምላሳችን ጸጉሮች መመሸጋቸውንም ያመለክታል።
– ሲጋራ ማጨስ፣ የውሃ ጥም፣ የአፍ መድረቅ እና መሰል ምክንያቶች ለችግሩ
በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

6. ቀይ ምላስ

– በአብዛኛው በህጻናት ጤና ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ያሳያል።
– የእንጆሪ ቀለም ያለው ምላስ ደግሞ ህጻናት ለትኩሳት እና የደም ስሮችን ለሚያጠቃ በሽታ መጋለጣቸውን ያመለክታል።
– ይህ አይነት ቀለም ያለው ምላስ በወጣቶች ላይ ብዙ ጊዜ አይታይም።
– ምላሳችን በጣም ለስላሳና ቀይ ከሆነ የቫይታሚን ቢ በተለይም የኒያሲን እጥረት እንዳጋጠመን ያሳያል።

7. ግራጫ ምላስ

– ይህ ደግሞ ሜላኖማ ለተባለ የቆዳ ካንሰር በሽታ መጋለጥን ያሳያል።

8. ቀይ ነጠብጣቦች የበዙበት ምላስ

– በምላስ ላይ የሚታዩ ቀይ ነጠብጣቦች የበርካታ ችግሮች ምልክት መሆናቸው ይነገራል።
– ከቫይታሚን ሲ የሚገኙ ባዮፍላቮዶይሶችን በበቂ ሁኔታ አለማግኘትን ያመለክታል።
– ትኩስ መጠጦችን ማዘውተር ለችግሩ በምክንያትነት ይጠቀሳል።
– የአስም እና የተለያዩ አለርጂዎች ምልክትም ነው።

9. ደረቅ ምላስ

– ሰውነታችን በርካታ ንፍጥ እያመረተ መሆኑን ያሳያል።
– ችግሩን ለመፍታት ከስኳር ምርቶችና ከወተት ተዋጽኦዎች መራቅ ያስፈልጋል።
– ጭንቀት ምራቅ አመንጪ እጢዎች እንዲያብጡ በማድረግ ምላስ እንዲደርቅ የማድረግ አቅም አለው።
– አንድ ብርጭቆ የሎሚ ውሃ መጠጣት የምላስ ድርቀትን ለማስወገድ ይረዳል።

26/05/2024

ለ አጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሸ
09 94 80 45 23
07 13 33 32 59

25/05/2024

አለም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እንድትሆን…….
___________

ሲስተር አይናለም ሃይሌ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ወረዳ ጂንካ ከተማ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በክሊኒካል ነርስነት ለበርካታ አመታት ስታገለግል ኖራለች፡፡ ሲ/ር አይናለም በነርስነት ሙያዋ ምስጉን፤ በታካሚዎችም ተወዳጅ ነበረች፡፡ ይህ ግን ብዙም አለዘለቀም፡፡ ከአምስት አመት አገልግሎት በኋላ የጤና ችግር ገጠማት፡፡ እግሮቿ መራመድ ተሳናቸው፡፡ እጆቿም እንደልብ አልታዘዝላት አሉ፡፡

የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የስራ ባልደረቦቿም ሲ/ር አይናለምን ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ ተረባረቡ፡፡ እንዳለመታደል ሆነ እና ዘመናዊ ህክምና የህክምና መሳሪያዎች ጥገኛ ስለሆነ የስራ አጋሮቿ እንዳሰቡት አክመው ሊያድኗት ይቅርና ችግሯን እንኳ በአግባቡ ለይተው ህመሟን ለማወቅ ተቸገሩ፡፡ ሆስፒታሉ እንደ ኤምአርአይ፣ ያሉ የዲያግኖስቲክስ ማሽኖች የሌሉት በመሆኑ ወደ ሌላ ሆስፒታል ለህክምና ላኳት፡፡

በተደረገላትም ህክምና የነርቭ ችግር እንዳለበት ተነገራት፡፡ በተደረገላት ህክምና እጆቿን ዳግም ማዘዝ ብትችልም እግሮቿ ግን እንደቀድሞው አላራምድም ስላሏት፤ በዊልቸር ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ የአካል ጉዳተኛ መሆኗ ግን ሲ/ር አይናለምን ተስፋ አላስቆረጣትም፡፡ ኧረ የታባቱ ብላ ስራ ካልጀመርኩ አለች፡፡ የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታልም ለዊልቼር መንቀሳቀሻነት የሚያስችል መንገድ እና ሌሎች ሁኔታዎችን በማመቻቸት ወደ ስራዋ እንድትመለስ አደረገ፡፡

ዛሬ ላይ ሲ/ር አይናለም በጂንካ ሆፒታል በሴንትራል ትራያጅ ክሊኒካል ነርስነት እያገለገለች ትገኛለች፡፡ 14 አመታትም አለፉ፤ የልጆች እናት የሆነችው ሲ/ር አይናለም፤ ቤት ውስጥ እና መንገድ ላይ በዊልቸር መንቀሳቀስ ከሚያጋጥማት ችግር ውጪ ስራዋን በአግባቡ ጥንቅቅ አድርጋ በመከወን ላይ ትገኛለች፡፡

“አለም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አይደለችምና ማህበረሰባችን ሁኔታዎችን ለአካል ጉዳተኞች በማመቻቸት ከሌሎች ዜጎች እኩል ፍሬያማ እንዲሆኑ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል” ብላናለች፡፡

የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሲ/ር አይናለም ላደረገው ድጋፍ ሁሉ ምስጋና ይገባዋል፡፡ በጥቂት ድጋፍ የአጋል ጉዳተኞች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሊለወጡ እንደሚችሉ የሲ/ር አይናለም ታሪክ እማኝ ነው፡፡

የአካል ጉዳት በየትኛውም ጊዜ፤ በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት እንደሚችል ተረድተን ሁላችንም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተን የበኩላችንን እንወጣ የሚለው ደግሞ የኛ መልዕክት ነው፡፡

Address


4523

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GoodCare home health care & consultancy services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram