15/06/2023
ምግብ እንደተመገቡ ወዲያውኑ ማደረግ ያሌለብዎ 7 ነገሮች
ቀበቶ ማላላት፤ ምግብ እንደተመገቡ እንደተመገቡ ቀበቶ vማላላት ለአላስፈላጊ ክብደት ለመጨመር ይዳርጋል፡፡
የእግር ጉዞ ማድረግ፤ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ የእግር ጉዞ ማድረግ ጨጓራችን አሲድ አብዝቶ እንዲረጭ ስለሚያደርግ ከምግብ በኋላ የእግር ጉዞ ካቀዱ 30 ደቂቃ መቆየት ይኖርቦታል፡፡
መተኛት፤ ምግብ እንደተወሰደ ወዲያውኑ መተኛት የጨጓራ ችግርና የአንጀት እንፌክሼን ሊያስከትል ይችላል፡፡
ፍራፍሬ መመገብ፤ ምግብ እንደተወሰደ ፍራፍሬ መመገብ ምግብ በአግባቡ እንዳይፈጭ በማድረግ በጨጓራ ላይ ጉዳት ያመጣል፡፡ ከምግብ በኋላ ፍራፍሬን ለመመገብ አንድ ሰዓት መቆየት ያስፈልጋል፡፡
ገላን መታጠብ፤ ገላን መታጠብ በጨጓራ አከባቢ ያለውን የደም ዝውውር እንዲቀንስ ስለሚያደርግ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ገላን መታጠብ ጨጓራችን ምግብ በአግባቡ እንዳይፈጭ ያደርጋል፡፡
ገላን ምግብ ከመመገብ በፊት ወይም ከምግብ በኋላ ከ1 እስከ 2 ሰዓታት መቆየት ያስፈልጋል፡፡
ሻይ መጠጣት፤ ሻይ ከምግብ የሚናገኛቸው የፕሮቲን ንጥረ ነገሮች በቀላሉ እንዳይፈጩ የሚያደርግ አሲድ በውስጡ ይዟል፡፡
ለዚህም ሻይ መጠጣት ከፈለጉ ሻይን የመጠጫ ትክክለኛው ጊዜ ከመመገቦ ከአንድ ሰዓት በፊት መሆን አለበት
ሲጋራ ማጤስ፤ በማንኛውም ጊዜ ሲጋራ ማጤስ ጉዳት እንዳለው ግልጽ ቢሆንም ምግብ ከተወሰደ በኋላ ወዲያውኑ ሲጋራ መውሰድ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
ከምግብ በኋላ የሚወሰድ 1 ሲጋራ የ10 ሲጋራዎች ያህል ጉዳት አለው፡፡