02/04/2026
➕➕ የወገብ ህመም ለሚያስቸግረው➕➕
🖲 የወገብ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ ሀኪምጋ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ የወገብ ህመም ያለበት ሰው ላይ፣ አንዳንድ ተጨማሪ ምልክቶች ከታዩ፣ በቶሎ ህክምና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል።
🖲 የዲስክ መንሸራተት ብቸኛው የወገብ ህመም አምጪ በሽታ አይደለም፣ የአከርካሪ አጥንት፣ የጡንቻ ፣ የነርቭ እና የውስጥ ደዌ ህመሞችም፣ የወገብ ህመምን ሊፈጥሩ ይችላሉ
🖲 አንድ ሰው ላይ ፣የወገብ ህመም መኖሩ ብቻ ሁልግዜ አሳሳቢ ችግር ነው ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ አንዳንድ ግዜ ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች፣ የወገብ ህመሙ አደገኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው
🖲 የወገብ ህመም እንደቆይታ ግዜው በ 4 አይነት መንገድ ይከፈላል፣ ማለትም፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምት በታች የቆየ ከሆነ የአጭር ግዜ የወገብ ህመም ወይም ( acute back pain) ተብሎ ይጠራል።
🖲 ወይም ደሞ፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምንት እስከ 3 ወር ድረስ የቆየ ከሆነ ፣( subacute back pain) ተብሎ ይጠራል: ሲተረጎም፣ ከፍያለ ደረጃ ያለው የአጭር ግዜ የወገብ ህመም እንደማለት ነው።
🖲 የወገብ ህመሙ ፣3 ወር እና ከዛ በላይ የቆየ ከሆነ፣ (chronic back pain) ወይም ስር የሰደደ የወገብ ህመም እንደሆነ ያመላክታል።
🖲 ከዚህ ውጪ ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም፣ በመሀል ለተወሰነ ግዜ እረፍት እየሰጠ የሚመላለስ እና ለረጅም ግዜ የሚቆይ የወገብ ህመም ያጋጥማቸዋል፣
🖲 ይህ አይነቱ የወገብ ህመም በህክምናው (recurrent back pain ) ተብሎ ይጠራል ወይም ተመላላሽ የወገብ ህመም ማለት ነው።
🖲 የወገብ ህመምን በዚህ መልኩ በቆይታ ግዜው መከፋፈል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክኒያት፣ የወገብ ህመም መንስኤ የሆነውን በሽታ ለመለየት እና ትክክለኛውን ምርመራ እና ህክምና ለመስጠት ታስቦ ነው።
🖲 ምክኒያቱም፣ ከ 30 በላይ የሚሆኑ የበሽታ አይነቶች፣ የወገብ ህመም ስሜትን የመፍጠር አቅም ስላላቸው ማለት ነው
🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ ከ 6 ሳምንት በታች የሚቆይ የወገብ ህመም በቀላል ህክምና ወይም በቀላል የህመም ማስታገሻዎች ብቻ የሚድን ሆኖ ይገኛል።
🖲 80 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚያጋጥመው የወገብ ህመም አይነትም፣ ይሄው አጭር የግዜ ቆይታ ያለው የወገብ ህመም ነው፣ ከነዚህ ውስጥ፣ 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በ 6 ሳምንት ውስጥ ሲሻላቸው ይታያል።
🖲 የወገብ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው ታዲያ መቼ ነው? አንድ ሰው በራሱ ላይም ሆነ፣ በቤተሰብ አባል ላይ የሚታይ የወገብ ህመም ሲያጋጥመው ፣ሀኪም ጋር ከመምጣቱ በፊት ምን ማድረግ አለበት?
ሙሉውን መረጃ በቪዲዮ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ።