29/11/2025
ዋሌትን ከኃላ ኪስ አድርጎ መቀመጥ በግዜ ሂደት ለ ከፍተኛ የጀርባ ህመም ያmጋልጣል ።
ዋሌትን ከኃላ ኪስ ሳያወጡ እላዩ ላይ መቀመጥ በግዜ ሂደት የጀርባ አጥንት አቀማመጥን ይጎዳል እንዲሁም በምንቀመጥበት ወቅት ከኃላ ኪሳችን ዋሌት ካለ አቀማመጣችን እንዲዛባ ሰለሚያደርግ ዋሌቱ በሌለበት በኩል እንዲያጋድል
ያደርገዋል ።
ይህም ያለተደላደለ አቀማመጥ በታችኛው ጀርባችን አካባቢ ያልተገባ አቀማመጥን ይፈጥራል በተለይ ሳያቲክ ነርቭን ( sciatic nerve) ለከፍተኛ ጫና አንዲጋለጥ
ያደርገዋል ።
ሳያቲክ ነርቭ በሰው ውስጥ ትልቁና ረጅሙ ነርቨ ሲሆን ። ከታችኛው ጀርባ ጀምሮ በመቀመጫችን አቋርጦ በ እያንድ አንዱ እግር በማለፍ የእግራችን ጫፍ ድረስ የሚሄድ ነርቭ ነው ።
ዋሌት ከኃላ ኪስ አድርገን ስንቀመጥ የሚፈጠረውም ጫና ውጤቱ ከፍተኛ ህመምን ሲኖረው በተለይ በታችኛው ጀርባ ፣ ዳሌ እና እግር አካባቢ የመደንዘዝ ስሜት ያስከትላል ።
እንደዚህ አይነት አጉል ልማድ በግዜ ሂደት አካላዊ ቁመናን ከማበላሽቱ በተጨማሪ በምንቀመጥበት እና በምንራመድበት ሰዓት ምቾት እንዳይሰማን ያደርጋል ።
ለበለጠ መረጃ በ 7797 በ ነፃ በመደወል የጤና ባለሙያ ማማከር ይችላሉ
https://t.me/droga_pharmacies
https://www.facebook.com/share/19ofNccgYV/