Al-Afia

Al-Afia Health consultancy agency

25/09/2022
20/07/2022

Dry Mouth ( Xerostomia)
የአፍ መድረቅ ችግሮች ምክንያቶችና መፍትሄዎቻችው

የአፍ መድረቅ ችግር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ምራቅ (saliva) አመንጪ እጢዎች (salivary glands) ምራቅን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።

ምራቃችን በ አፋችን ውስጥ በባስቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የጥርስ መቦርቦር እንዳይፋጠር የሚራዳ ሁኔታን ይስመቻቻል። ከዚህም በተጨማሪ ምግብን አላምጦ የመዋጥ ሂደትን እንድናድርግና ልምግብ መፈጨት ሂደት የሚያስፋልጉ ኤንዛየምስ የማመንጨት ተግባርን ይስከናውናል።

የምራቅ መመንጨት በሚቀንስ ጊዜ የ አፍ መድረቅ ይከሰትና ጤናችንን ሊይስቃውስ ይችላል።

የአፍ መድረቅ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

* አፋችን ውስጥ የማጣበቅ ስሜት ሲሰማን

*መጥፎ የአፍ ጠረን

*ለማላመጥ ፣ ለመዋጥ እና ለመናገር መቸገር

*የጉሮሮ መሻከር ወይንም ቁስለት

*የምግብ ጣዕም ማጣት ናቸው።

የአፍ መድረቅ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

የአፍ መድረቅ የሚመጣው አመንጪ እጢዎች በሚፈለገው መጠን ምራቅን ማመንጨት ሲያቆሙ ነው ለዚህም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እናያለን።

* መድሃኒቶች
አብዛኛዎቹ መድሀኒቶች የአፍ መድረቅ የጎንየሽ ጉዳታቸው እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ለመደበት፣ጭንቀት እና አንዳንድ የአለርጂ መድሀኒቶች ይጠቀሳሉ።

*እድሜ
እድሜአችን በጨመረ ቁጥር የተለያዩ አካላዊ ለውጦችን ተከትሎ የ አፍ መድረቅም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።

*የነርቭ ጉዳት
በጭንቅላት እና አንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች በሚጎዱ ጊዜ የአፍ መድረቅ በተያያዥነት ሊመጣ ይችላል።

*ሲጋራ ማጤስ፣ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መውሰድና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የአፍ መድረቅን ያስከትላል።

*ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ
ካንሰርን ለማከም የሚሰጡ ህክምናዎች የ አፍ መድረቅን ለጊዜያዊ ወይንም በቋሚነት ሊያስከትሉ ይችላል።

*ሌሎች የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ፣የስኳር ህመም፣ስትሮክ፣የፈንገስ ኢንፌክሽን ይስሉ ህመሞች ለአፍ መድረቅ ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።

*ማንኮራፋትና አፍን ከፍቶ መተንፈስ ሌሎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።

ከአፍ መድረቅ ጋር በተያያዘ የሚመጡ ሌሎች ችግሮች ምንድን ናቸው?

* የጥርስ መቦርቦር እና የድድ ህመም
*የከንፈር ቁስለት
*የፈንገስ ኢንፌክሽን
*የከንፈር መሰነጣጠቅ
*የክብደት መጠን መቀነስ ናቸው።

አንድ ሰው የአፍ መድረቅ ሲያጋጥመው ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። ከዛም እንዳስፈላጊነቱ መድሀኒት እንዲውስዱ ይደረጋል።

የአፍ መድረቅ እንዲቀንስልን በቤት ውስጥ ልንጠቀማቸው የምንችላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

*ውሀን ይጎንጩ ውሀን መጎንጨት የዘወትር ልማር ማድረግ፣ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ ለማላመጥ እና ለመዋጥ እንዳይችሉ በውሃ ማወራረድ።
*በአፍንጫዎ ብቻ ይተንፍሱ የማንኮራፋት ችግር ካለብዎና ሌሊት አፍዎን ገጥመው መተኛት ካልቻሉ ለማንኮራፋቱ ሀኪምን ያማክሩ።
*ከስኳር ነጻ የሆኑ ማስቲካ ወይንም ከረሜላ መጠቀም
*ከንፈርዎን ቫዝሊን ወይንም የከንፈር ቅባት በመቀባት ያለስለሱ።

20/07/2022

ምች የሚባል በሽታ ግን ምንድነው ?
( ምች በፀሐይ ይመጣል ወይስ አይመጣም?)

🔘 ምች የሚባለው በሽታ በእንግሊዘኛው herpes labialis የሚባለው ሲሆን ዋናው የበሽታው ምልክት ደሞ ሄድ መጣ የሚሉ ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ በከንፈር ዙሪያ የሚወጡ ቁስሎች ናቸዉ።

የምች መንስኤው ምንድነው?

የበሽታው ዋናው መንስኤው herpes simplex የሚባለው ቫይረስ ሲሆን በመሳሳም ወይም በ ሌሎች አካላዊ ግንኙነቶች አማካኝንት ከአንድ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ::

ምልክቶቹ

- የመጠቅጠቅና የማሳከክ ስሜት
- ዉሃ የቋጠሩ ቁስሎች
- ትኩሳት
-የራስ ምታት
- የጡንቻ ላይ ህመም
-የአንገት ላይ ንፍፊትቶች እብጠት

-ለምች የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድናቸው?

1. ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ

ፀሐይ ብርሃን ለብቻው ምች አያመጣም።
ነገር ግን ምች የሚያመጣው ቫይረስ (herpes simplex 1) ቀድሞ ይዞን እራሱ ነርቭ ህዋሶች ዉስጥ ይደብቃል ።

የፀሐይ ብርሃን ዉስጥ ባለው ultraviolet የሚባለው ጨረር ደሞ ሊነሳሳው (re activate ሊያረገው) እና ከተደበቀበት የነርቭ ስር ዉስጥ በ መውጣት ድጋሚ ወደ ቆዳ አካባቢ በመሄድ ሄድ መለስ የሚል ቁስል ሊያመጣ ይችላልይችላል
2. ቅባት ያለዉ ምግብ መመገብ
3. ጭንቀት
4. ኤች አይ ቪ ኤድስ
5. የካንሰር ህክምና
6. የወር አበባ ዑደት ጊዜ የሆርሞን መለዋወጥ

የጤና ባለሙያ ማማከር ያለብን መቼ ነው ?

- የበሽታ መከላከል ብቃት መቀነስ/የተዳከመ ከሆነ
- ቁስሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ካልዳነ
- የህመሙ ምልክቶች ከፍተኛ ከሆኑ
- ህመሙ በተደጋጋሚ ከተከሰተ
-በአይን የመቆጥቆጥ ስሜት ሲሰማ

ሕክምናውስ ምንድን ነው?
-ጸረ- ቫይረስ መድሃኒት እና የህመም ማስታገሻ መድሐኒት መዉሰድ
- በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ብርቱካን እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን
-በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ
- የአእምሮ ዉጥረትን/ ጭንቀትን መቅነስ
- ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ተክል ቅጠል በማሸት ቁስሉ ላይ ማድረግ/መቀባት

-ዉሃ የቋጠረ ቁስል ባለበት ወቅት የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር መከላከል፤
- ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዛመተዉ በሚያዥበት/ዉሃ በሚቋጥርበት ጊዜ ስለሆነ ሌላዉን የሰዉነት ክፍልዎን እንዳይነኩ መጠንቀቅ :- በተለይ አይንንና የብልት አካብቢ ለቫይረሱ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ላለመንካት መጠንቀቅ፤
- የመገልገያ ዕቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም፡- እንደ ፎጣ፣ መመገቢያ ዕቃዎችንና የመሳሰሉትን
-የእጅን ንፅህና መጠበቅ፡- ሌላ ሰዉ ከመንካት በፊት እጅዎን በደንብ ይታጠቡ ።

20/07/2022

ለአንቺ
በእርግዝናሽ ወቅት ማወቅ ያለብሽ ሰባት ነገሮች።

1. በ እርግዝናሽ ወቅት በቂ የሆነ የፅንስ ክትትል አድርጊ።

ማርገዝሽን ካወቅሽበት ቀን ጀምሮ ተገቢውን የእርግዝና ክትትል ማድረግ ይኖርብሻል ።
በክትትል ወቅትም አስፈላጊ የሆኑ የደም የሽንት የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብሻል::

2. አይረን እና ፎሊክ አሲድ መውሰድ አለብሽ ። ምክንያቱም ፎሊክ አሲድ በበቂ ከወሰድሽ የቀይ ደም ህዋስ እንዲመረት እና የደም ማነስ እንዳይከሰትብሽ ያደረጋል።

ፎሊክ አሲድ በበቂ ከወሰድሽ ሕፃኑ ላይ የ ነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) እንዳይከሰት ይከላከላል ።

ፎሊክ አሲድን የሚይዙ ምግቦች ፡- ብርቱካን ፣ ወይን ፣ ፓፓያ ጎመን ፣ሩዝ ፣ ባቄላ ፣ ስኳር ድንች ፣ እንቁላል ፣ ዳቦ ፎሊክ አሲድን ከነዚህ ውስጥ ማግኝት እንችላለን ፡፡

3. የደም አይነትሽን ማወቅ ይጠቅምሻል ።የ የሚጠቅምሽም ባንቺ እና በ ልጅሽ የደም አለመመሳስል ምክንያት ፅንሱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዳይደርስ እንድትከላከይ ይረዳሻል ::

በተለይ ያንቺ የደም አይነት ኔጌቲቭ የሚባለው ከሆነ

ለምሳሌ A negative, B negative, AB negative ወይም O negative ከሆነ የሾተላይ መከላከያ ወይም አንታይ ዲ (Anti - D) የሚባለውን መድሃኒት እርግዝናው ከታወቀ በ 7 ተኛ ወር ላይ እና ከወሊድ በኋላ በ 72 ሰአት ወሰጥ መውሰድ ይኖርብሻል።

4. ለህመም ማስታገሻ ተብለው የሚወሰዱ መድሀኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ አትውሰጂ።

በተለይ በመጀመሪያዎቹ 16 ሳምንታት የእርግዝና ወቅት የህፃኑ ዋና ዋና የሚባሉ የሰውነት ክፍሎች የሚፈጠርበት ግዜ ስለሆነ ፅንሱ ላይ ጉዳት ያደርሳያደርሳል

5. በእርግዝና ግዜ የአተኛኘትሽን አስተካክይ።

በእርግዝና ወቅት መተኛት ያለብሽ በግራ ጎንሽ መሆን አለበት።
በግራ ጎንሽ ስትተኚ ወደ ፅንሱ የሚሄደውን ምግብ እና የደም ዝውውርን እንዲጨምር ያደርጋል:: በጀርባሽ የምትተኚ ከሆነ ግን በተቃራኒው ወደ ልጅሽ የሚሄደው ምግብ እና የደም ዝውውር ሊቀንስ ይችላል።

6. ምግብሽን ሳታበስይ አትመገቢ!

በእርግዝና የሚከለከሉ ምግቦች ብዙም የሉም ። እንደውም ጤናማ ከሆኑ(ማለትም የበሰሉ እና በንፅህና የተዘጋጁ) ከሁሉም የምግብ አይነት እናት እንድትመገብ ይመከራል ።
ጣፋጭ እና የ ታሽጉ ምግቦችን አታዘውትሪ።

7. በ እርግዝና ወቅት በቂ እና ጤናማ የሆነ ኪሎ መጨመር ይኖርብሻል።

ከእርግዝና በፊት ከምትመገቢው ምግብ ተጨማሪ ምግብ ያስፈልግሻል።

20/07/2022

የጡት ካንሰር በሽታ ምንድን ነው?
የጡት ካንሰር በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ወንዶችንም የሚያጠቃ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡የጡት ካንሰርም በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ያስከትላል፡፡

ጡት በተፈጥሮ በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡
እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጡት ካንሰር ጅማሬው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው፡፡ የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛ ያልሆነ ህዋስ በሰውነታችን ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው፡፡ የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ህብረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል፡፡
ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች
የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሚከሰትበት ምክንያት በውል አይታወቅም፡፡ የሚከተሉት ሴቶች ግን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

• ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ፡፡ የእድሜ መጨመር ለጡት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ፣
• ከዘር/ከቤተሰብ በጡት ካንሰር የተያዘ ካለ ለበሽታው የመጋለጥ እድል ከፍተኛ
• ካንሰር ያልሆኑ ሌሎች የጡት በሽታዎች አጋጥሞ ከነበረ፣
• የአልኮል መጠጥ የሚያበዙ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡ አልኮል መጠጥ አዘውትራ የምትወስድ ሴት አልኮል ከማይጠቀሙት ይልቅ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከፍተኛ ነው፡፡
• የወር አበባቸውን ቀድመው/በልጅነት ያዩ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡
• ከ30 ዓመት በኋላ ልጅ የሚወልዱ ወይም ከነጭራሹ የማይወልዱ፣
የወር አበባ ማየት ከማቆም(ከማረጥ) በኋላ የሚመጣ የሰውነት ክብደት መጨመር ለጡት ካንሰር ያጋልጣል፡፡
• ከሚገባው ዕድሜ በጣም ዘግይተው ያረጡ፣
• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያዘወትሩና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው፣
• በስራ ገበታቸው ላይ በከፍተኛ ጨረር ውስጥ ያለምንም መከላከያ የሚሰሩ
• ሰራተኞች በበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡፡፡



የጡት ካንሰር ምልክቶች

የጡት ካንሰር ሲጀምር ህመምም ሆነ ምልክቶች የሉትም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የጡት ላይ እብጠቶች ካንሰር ባይሆኑም ዋነኛው የጡት ካንሰር ምልክት ግን በጡት ላይ የሚከሰት ጠጣር እብጠት ነው፡፡ የሚከተሉት ደግሞ ተጨማሪ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
• ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት፣
• የጡት ጫፍ አካባቢዎች መቅላትና ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣
• በጡት አካባቢና በብብት ውስጥ እብጠት መከሰትና ሙቀት ያለው መሆን፣
• የጡት ቆዳ መሸብሸ/ወደ ውስጥ መግባት ወይም እንደብርቱካን ልጣጭ ዓይን ማውጣት፣
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምናና ምርመራ ማድረግ ነው፡፡

የጡት ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች
የጡት ካንሰር ተሰራጭቶ ወደ ሌላ የሰውነት አካል ከመድረሱና ከመባዛቱ በፊት ከተደረሰበት ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ ነው፡፡ በመሆኑም የጡትን ችግር በየወቅቱ ወይም በየጊዜው ለማወቅ ሴቶች በተወሰነ ጊዜ በጡታቸው ላይ የሚከሰተውን እብጠት በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው፡፡ የኸውም፣-

1. የማሞግራም ምርመራ ማድረግ
ይህ ምርመራ ጡትን ራጅ በማንሳት የሚደረግ የምርመራ ዘዴ ሲሆን አስተማማኝ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴ ነወ፡፡ በመሆኑም ብዙ ሐኪሞች ማንኛዋም ሴት ከ40 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም ከ20 እስከ 40 ዓመት ያሉ ደግሞ በየሦስት ዓመቱ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡

2. ሐኪም በመዳሰስ የሚያደርገው ምርመራ
ሐኪም ጋር በየስድስት ወሩ በመቅረብ፣ የሚሰማን ስሜት በመግለጽና ጡትን በማሰዳሰስ ምርመራ ማድረግም ተገቢ ነው፡፡
3. የራስን ጡት በራስ የመመርመር ዘዴ

የራስ በራስ የጡት ምርመራ በየወሩ ማድረግ ህይወትን ከሞት ለመታደግ ያስችላል፡፡ጡት በወር አበባ ምክንያት በቅርጽ፣ በመጠንና በስሜት ስለሚቀያየር ሁልጊዜ በየወሩ በተለመደ ቀን መመርመር አለበት፡፡ ይህን ማድረግ ጡት ላይ የሚከሰት ማንኛውንም ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡

20/07/2022

ሕጻናት ድንገተኛ የነስር ሕመም ሲያጋጥማቸው ማድረግ የሚገባዎ 7 ነገሮች

• ነስርን ብዙ ጊዜ ቤት ዉስጥ በቀላል ዘዴዎች ማቆም ይቻላል፡፡ ወላጆች ግን መረጋጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡የልጅዎን ጭንቀላቱን ትንሽ ወደ ፊት ዘንበል አርጎ አፍንጫው አጥንት በታች ያለውን ለስላሳ የ አፍንጫ ክፍል ቢያንስ ለ10 ደቂቃ ጫን አርጎ መያዝ :: ቶሎ ከለቀቁ መልሶ ሊደማ ይችላል፡፡
• በዚህ መንገድ ቀላል ነስር ከሆነ ይቆማል፡፡ ካልተሳካ ግን ለተጨማሪ 10 ደቂቃ አሁንም ደግሞ አፍንጫውን ጫን አርጎ መያዝ ይገባል፡፡
• በነዚህ ሁለት ሙከራዎች ወይም በ 20 ደቂቃ ዉስጥ ካልቆመ በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ልጅዎን ሐኪም ዘንድ
• በዚህ ወቅት ልጆዎ በአፉ እንዲተነፍስ ይንገሩት፡፡
• ይጠንቀቁ!በፍፁም ልጆዎን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ወይም ማንጋጠጥ የለበትም:: ምክንያቱም ቀና ስላለ ደሙ ወደ ውጭ አይፍሰስ እንጂ ወደ ዉስጥ በምግብ ቱቦ በኩል በብዛት እንዲፈስ እና ወደ ጨጓራው እንዲገባ ያረጋል ይሄ ደሞ ከፍተኛ የደም ማነስ እና ትውከት ሊያስከስት ይችላል::
• ሶፍት ወይም ሌላ ነገር ወደ አፍንጫ አይክተቱ! ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መድማቱን ሊጨምሩት ይችላሉ፡፡
• የልጅዎን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉ፡፡ነስሩ ከቆመ በዋላ ለተወሰነ ሰዓት ልጆ አፍንጫውን እንዳይነካካ እና በኃይል እንዳይናፍጥ ከባድ ነገር እንዳያነሳ ያርጉት

የልጆች ነስርን መከላከል ይቻላል ?
አዎ መከላከል ይቻላል፡፡ ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ግን የሚቻለው በሐኪም ሲታከም ነው::
መከላከያ መንገዶቹ ምንድናቸው?
 ልጆች አፍንጫቸውን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ነገሮች ማራቅ
 አፍንጫቸውን እንዳይነካኩ ማስተማር
 የልጆች ጥፍርን ማሳጠር
 የአየር ንብረቱ ደረቅ ከሆነ አፍንጫቸው ዉስጡን ቫዝሊን በመጠኑ መቀባት ወይም እንፋሎት መታጠን
 ጉንፋን እና አለርጂን በአግባቡ መታከም
 መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ትእዛዝ አለመውሰድ
 ቋሚ የህፃናት ሕክምና ክትትል ማድረግ
በነስር ሕመም የታመመ ልጅዎን መቼ ነው ሆስፒታል መውሰድ የሚገባዎ?
 ከላይ እንደ እንደተጠቀሰዉ የማይቆም ከሆነ
 ባንዴ ብዙ ደም መፍሰስ ካለ(ከ1 ስኒ በላይ)
 ልጆዎ ራስ ማዞር እና መሳት ካጋጠመው
 ተደጋጋሚ ነስር እና የጥርስ መድማት ካለ
 ቆዳው በቀላል ምት(አደጋ) የሚበልዝ ከሆነ
 ከ 2 ዓመት በታች ነስር ከተከሰተ
 ልጆዎ ከዚህ በፊት የደም ማነስ ካለበት
 ተከታታይ ደም የቀላቀለ ትውከት ካለ

Address

Betel
Addis Ababa

Telephone

+251918473761

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Al-Afia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Al-Afia:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram