ጤናማ ህይወት

ጤናማ ህይወት ፎሎው እና ሼር በማድረግ ጤናማ ትውልድ እንፍጠር

ደም መለገሶ ለእርሶም ጤና ጥቅም እንዳለው ያውቃሉ?ደም መለገስ ከስጦታዎች ሁሉ የበለጠ ስጦታ ሲሆን በመለገሳችን የሚወልዱ እናቶችን፣ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችን፣ ካንሰር እና ሌላ የረጅም ጊዜ...
16/10/2025

ደም መለገሶ ለእርሶም ጤና ጥቅም እንዳለው ያውቃሉ?

ደም መለገስ ከስጦታዎች ሁሉ የበለጠ ስጦታ ሲሆን በመለገሳችን የሚወልዱ እናቶችን፣ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችን፣ ካንሰር እና ሌላ የረጅም ጊዜ የጤና ችግር ያለባቸው እህት ወንድሞቻችን በቂ ደም ወይም የተወሰኑ የደም ሴሎች ሳያገኙ ከመሞት እንታደጋለን

ደም መለገስ ታዲያ ከጤና አንፃር ለሚለገስላቸው ብቻ ሳይሆን ለለጋሾቹም ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታ አለው፡፡ እንደ አሜሪካ ቀይ መስቀል ማህበር መረጃ መሰረት አዘውትሮ ደም በመለገስ የሚያገኟቸውን የጤና ጠቀሚታዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ

✦ ጭንቀትን ይቀንሳል
✦ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳዎታል
✦ የደም ሕዋስ ምርት እንዲጨምር ያደርጋል

✦ በደሞ የሚገኘውን ከፍተኛ የብረት ክምችት በመቀነስ የልብ ምቶ የተስተካከል እንዲሆን፣ ጡንቻዎት እንዳደክም፣ ጉበቶና ጣፊያዎ እንዳይጎዳ እንዲሁም ለካንሰር እንዳይጋለጡ ይረዳዎታል
✦ በልብ በሽታ የመጠቃት እድልን ይቀንሳል
✦ የኮሌስትሮል (የደም ቅባት) መጠንን ይቀንሳል
✦ በሰውነቶ ያለው ካሎሪ እንዲቃጠል ይረዳል

✦ ነፃ የጤና ምርመራዎች ( የልብ ምት ፣ የደም ግፊት፣ የሰውነቶ የሙቀት እና የሂሞግሎቢን መጠን እንዲሁም የደም አይነቶን ማወቅ ይችላሉ)

✦ የተለያዩ የበሽታ ምርመራዎችን በነፃ (ሂፐታይተስ -ቢ እና ሲ፣ኤች አይቪ፣ዌስት ናይል ቫይረስና የቂጥኝ)

ከእርስዎ የተወሰደው 1 ከረጢት ደም እስከ 3 ሰዎች ያህል ሕይወት በመታደጉ የደስታ ስሜትን ይጎናፀፋሉ

አብዛኞቻችን ደም በመለገሳችን ለችግር ተጋላጭ እንሆን ይሆን ብለን እናስባለን እውነታው ግን ደም መለገስ የሚያመጣው ምንም ችግር የለም፤ ለእያንዳንዱ ለጋሽ አዲስና ጤንነቱ የተጠበቀ ዕቃዎች ስለሚጠቀሙ ደም በመለገስዎ በደምና በደም ንኪኪ ሊተላለፉ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች ሊይዝዎ አይችሉም። እርስዎ ጤናማ ከሆኑ ጤንነትዎ ላይ ምንም አይነት ችግር ሳይከተል ደም መለገስ ይችላሉ

ደም ለመለገስ የሚደረጉ ዝግጅቶች :

✦ ሙሉ ጤነኛ መሆን
✦ ቢያንስ 18 አመትና ከዚያ በላይ መሆን
✦ ክብደትዎ ቢያንስ 45 ኪሎግራም መሆን
✦ አካላዊና ሌሎች የጤና ምርመራ ማለፍ የሚችል መሆን አለበት
✦ እርግዝና፣ በቅርቡ የተደረገ ውርጃ እና የቀዶ ህክምና አለመኖሩን ማረጋገጥ
✦ የሚለግሰው ሰው በቅርቡ ክትባቶችንም ሆነ መድሃኒቶችን ያልወሰደ መሆን አለበት

ደም ለመለገስ ካሰቡበት ቀን በፊት ባለው ምሽት በቂ እንቅልፍ ማግኘት የሚያስፈልግ ሲሆን ከመለገስዎ በፊት ጤናማ ምግብ መመገብ፤ ስብነት ያለቸውን (ለምሳሌ የአሳማ ስጋ) እና እንደ አይስ ክሬም ያሉ ምግቦችን አለመመገብ ይመከራል

ከመጠን ያለፈ የረሀብ ስሜት የጤና ችግር ሊያመላክት እንደሚችል ያውቃሉ?ከመጠን ያለፈ የረሃብ ስሜት በተለያየ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደ ጤናማ ሁኔታ ይወስዱታል መንስኤዎቹ...
14/10/2025

ከመጠን ያለፈ የረሀብ ስሜት የጤና ችግር ሊያመላክት እንደሚችል ያውቃሉ?

ከመጠን ያለፈ የረሃብ ስሜት በተለያየ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደ ጤናማ ሁኔታ ይወስዱታል

መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?

⋄ እርግዝና ካለ
⋄ ማስቀመጥ
⋄ የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት
⋄ የጨጓራ ህመም
⋄ ከባድ ስራዎችን አዘውትሮ መስራት
⋄ የእንቅልፍ እጦት
⋄ በደም ውስጥ የስኳር መጠን ማነስ
⋄ የስኳር ህመም
⋄ ጭንቀት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ
⋄ የወር አበባ (ከመምጣቱ በፊት)
⋄ አልኮል መጠጣት ማዘውተር

መፍትሄው

⋄ ጭንቀት ካለ መቀነስ
⋄ አልኮል መጠጣት አለማዘውተር
⋄ የስኳር ህመም እና ሌሎች ችግሮች ካሉ ያንን ማከም

መቼ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ አለብን?

⋄ የማዞር ስሜት ካለው
⋄ የቆዳ መገርጣት
⋄ ራስን መሳት
⋄ ማንቀጥቀጥ ካለው

የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ሲሆን የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አ...
12/10/2025

የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?

የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ሲሆን የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚቋቋሙ ክፍሎች ናቸው ።ዲስኩ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ አለው

የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው።ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል

አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። የተንሸራተተው ዲስክ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም

✔ መንስኤዎች

የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል::
የዲስክ መንሸራተት መቼ እንደተፈጠረ ማወቅ ያስቸግራል ነገር ግን የሚከተሉት እንደ መንስኤ ይገለጻሉ

▸ ጉልበታችንን ሳናጥፍ ከባድ እቃ ለማንሳት ስንሞክር
▸ ከባድ እቃ ይዘን ከጀርባችን ስንታጠፍ ነው
▸ ባልተስተካከለና በተጣመመ አኳሀን ከባድ ነገር ስናነሳ ወይም ስንሸከም

✔ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች

▸ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት
▸ እድሜ
▸ ከባድ ስራ መስራት
▸ በዘር ተመሳሳይ ችግር ካለ

✔ የሚታዩ ምልክቶች

▸ የታችኛው ጀርባ ህመም
▸ በትከሻዎ ፤ በጀርባዎ ፣ በእጆችዎ ወይም በእግሮችዎ ላይ የመደንዘዝ ስሜት
▸ የአንገት ህመም
▸ ጀርባዎን ማጠፍ ወይም ለማስተካከል ሲጥሩ ህመም
▸ የጡንቻ ድክመት
▸ ከወገብ በታች የዳሌ ህመም

✔ ሊያመጣ የሚችላቸው ውስብስብ ችግሮች

▸ ህመም ፣ መደንዘዝ ወይም ድክመት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎን እስከሚያደናቅፉ ድረስ ሊጨምር ይችላል
▸ የፊኛ ወይም የአንጀት ችግር

✔ መከላከያ መንገዶች

▸ ትክክለኛ የሰዉነት አቋም እንዲኖር ማድረግ
▸ ከባድ እቃ በሚያነሱበት ወቅት ጫናዉን/ክብደትዎን ከጀርባዎ ይልቅ በእግሮችዎ ላይ ማድረግ
▸ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
▸ ለረጅም ጊዜ የሚቀመጡ ከሆነ ቀጥ ብለዉ ለመቀመጥ መሞከር
▸ የሚተኙበትን ሁኔታ ምቹ ማድረግ
▸ ክብደትዎን መቆጣጠር

✔ መፍትሄ እና ህክምናዉ

▸ ሙቅ ነገር መያዝ ህመምን ለማስታገስ ይረዳል
▸ ከመጠን ያለፈ እረፍት ማስወገድ/ መጠነኛ እንቃስቃሴ ማድረግ
▸ የህመም ማስታገሻ መድሐኒቶች
▸ ጡንቻን የሚያፍታቱ መድሐኒቶች
▸ በባለሙያ የታገዘ የፊዚዮቴራፒ ህክምና
▸ በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል

የአቮካዶ የጤና ጠቀሜታዎችአቮካዶ ባለው ከፍተኛ የሆነ የቫይታሚንና የሚነራል ይዘት፣ በውስጡ የያዘው ፋይበርና እጅግ አነስተኛ የስብ መጠን የዓለማችን ተመራጭ የፍራፍሬ ዓይነት እንዲሆን አድርጎ...
10/10/2025

የአቮካዶ የጤና ጠቀሜታዎች

አቮካዶ ባለው ከፍተኛ የሆነ የቫይታሚንና የሚነራል ይዘት፣ በውስጡ የያዘው ፋይበርና እጅግ አነስተኛ የስብ መጠን የዓለማችን ተመራጭ የፍራፍሬ ዓይነት እንዲሆን አድርጎታል

✧ አቮካዶ በሰውነታችን የሚገኝን የኮሌስትቶል መጠን ዝቅ በማድረግ ረገድ አቻ የለውም

አቮካዶ በውስጡ የያዘው ከፍተኛ የፋቲ አሲድ መጠን በሰውነታቸን ያለውን የኮሌስትቶል መጠን ዝቅ እንዲል ያስችላል።
በአንፃሩ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆነው የኮሌስትሮል መጠን ከፍ እንዲል ያደርጋል

✧ አቮካዶ በውስጡ የያዘው ቫይታሚን ኢ ለልብ ህመም ወይም ስትሮክ የመጋለጥ ዕድላችንንም በእጅጉ ይቀንሳል

✧ እርጅናን ለመከላከል እና የቆዳ ውበት ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳል

በአቮካዶ ውስጥ በብዙ መጠን የሚገኘው አንቲ ኦክሲዳንት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና የሞቱ የቆዳ ሴሎች እራሳቸውን እንዲተኩ ሲያግዝ፥ ካሮቲኖይድስ የተባለው ንጥረ ነገርም በቆዳ ላይ የሚታዩና የቆዳን ውበት የሚቀንሱ ምልክቶች እንዳይከሰቱ ያደርጋል

አቮካዶን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች ከማያዘወትሩት የተሻለ ለስላሳ ቆዳ እና ፀጉር፣የሰውነት ጠረን፣ የአዕምሮ ዕድገት እንደሚጎናፀፉም ጥናቶች ያመላክታሉ

✧ ክብደት ለመቀነስ ፍቱን ነው፣

አቮካዶ ሙቀት ሰጪ ምግብ ከምንላቸው የምግብ አይነቶች እንደመመደቡ፥ በየማዕዳችን በቂ የጊዜ ልዩነት እንድናደርግ ዕድል ይሰጠናል ፤ በዚህም ቶሎ ቶሎ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማን በማድረግ የምግብ ፍጆታንና ክብደታችንን እንድንቀንስ ያስችላል

✧ ለስኳር ህመምተኞች ተመራጭ ነው

በአቮካዶ ውስጥ በጥሩ መጠን የሚገኘው ፖታሺየም በደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን በማመጣጠን በሰውነት ውስጥ የልብ ስራንና የስኳር መጠንን የተረጋጋ እንዲሆን ያስችላል

✧ ለፅንስ ጤንነት ወሳኝ ነው

አቮካዶ ጥሩ የቫይታሚን ኤ ፣ ቢ ኮምፕሌክስ፣ ሲ፣ ኢ፣ ኤች፣ ኬ እና ፎሊክ አሲድ መገኛ ነው።
በተጨማሪም በውስጡ የሚገኙት እንደ ማግኒዢየም፣ ኮፐር፣ አይረን ፣ ካልሲየም እና ፖታሲየም የመሳሰሉትን ንጥረ ነገሮች ለፅንሱ ዕድገት እጅግ ወሳኝ ናቸው

የእርስዎ የፍቅር ቋንቋ የትኛው ነው?የፍቅር ቋንቋ ዓይነቶች♥️ አካላዊ ንክኪየመጀመሪያ ደረጃ የፍቅር ቋንቋቸው አካላዊ ንክኪ የሆነባቸው ሰዎች አካላዊ ንክኪ የበለጠ ፍቅርን እና አድናቆት እን...
03/10/2025

የእርስዎ የፍቅር ቋንቋ የትኛው ነው?

የፍቅር ቋንቋ ዓይነቶች

♥️ አካላዊ ንክኪ

የመጀመሪያ ደረጃ የፍቅር ቋንቋቸው አካላዊ ንክኪ የሆነባቸው ሰዎች አካላዊ ንክኪ የበለጠ ፍቅርን እና አድናቆት እንዲሰማችው ያደርጋል

ይህ የግድ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን እጅን መያያዝን፣ ማቀፍ፣ ክንድ/ፊትን መነካካትን እና በመንገድ ላይ ሲሆዱ ክንዶን ትከሻቸው ላይ ማድረግን ሊያካትት ይችላል።በቀላል አነጋገር አካላዊ ንክኪን የሚመርጡ ሰዎች ከአጋራቸው ጋር ለመግባባት አካላዊ ንክኪ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ እና ከአጋራቸው ጋር በአካል መቀራረባቸው አስፈላጊ ሊሆን ይችላል

♥️ ስጦታዎችን መቀበል

የመጨረሻው የፍቅር ቋንቋ ስጦታዎችን መቀበል ነው፡፡ ይህ ቀዳሚ የፍቅር ቋንቋ ላላቸው ሰዎች የግድ ትልቅ ወይም ውድ ስጦታ አይጠብቁም ነገር ግን የስጦታዎን ሀሳብ ያደንቃሉ

ይህ የፍቅር ቋንቋ ያላቸው ሰዎች ስጦታውን መውደድ ብቻ ሳይሆን ሰጪው ስጦታውን ለማዘጋጀት የሚያደርገውን ጥረት ያደንቃሉ። ስጦታዎችን መቀበልን የሚያስደስተው ሰው የተቀበሉትን እያንዳንዱን ስጦታ ሊያስታውሱ ይችላሉ

♥️ የማረጋገጫ ቃላት

የፍቅር ቋንቋው የማረጋገጫ ቃላት የሆነ ፍቅርን በንግግር፣በምስጋና ወይም በአድናቆት መግለፅን ይመርጣል።በአጋሮት የተፃፉ ደግ ቃላቶች ፣አነቃቂ ጥቅሶች፣ የፍቅር ማስታወሻዎች፣ ወይም የምስጋና የጽሁፍ መልዕክቶች ያስደስቶታል። ይህን የፍቅር ቋንቋ የሚመርጡ ሰዎች ደግነት ለጎደላቸው ቃላቶች አሉታዊ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል እና ከአጋራችው ለሚሰነዘሩ ትችቶች ከመጠን በላይ ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ

የፍቅር ቋንቋው የማረጋገጫ ቃላት የሆነ አጋር ካሎት ምስጋናዎችን ማቅርብ ፣ አጋሮት በሚናገረው ነገር ላይ ፍላጎት ማሳየት እና ላከናወነው ነገር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ደስተኝ ማድረግ ይችላሉ።በጥልቅ ደረጃ ከአጋራችው ጋር ለመግባባት 'እወድሻለሁ/ው'፣ 'በአንተ/ቺ እኮራለሁ' እና 'አደንቅሃለሁ/አደንቅሽለው' ሊሉ ይችላሉ

♥️ ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ

የፍቅር ቋንቋዎ ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ ከሆነ፣ፍቅርን የሚግልፁት ያልተከፋፈለ ትኩረቶን ለአጋሮ በመስጠት ነው፡፡ ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ የዓይን ንግግርን፣በንቃት ማዳመጥ፣በትኩረት መቆየት እና በአጋሮት ላይ ማተኮርን ያካትታል፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ሀሳቦችን፣ ልምዶችን፣ ስሜቶችን ጥልቅ ግላዊ ፍላጎቶችን፣ የማንነት ተቀባይነትን እና ያልተቋረጠ አውድን መጋራት ያሉ ጥራት ያላቸውን ውይይቶችን ሊያካትት ይችላል

ይህ የፍቅር ቋንቋ ያለው ሰው ጋር አብረዎ በሚሆኑበት ጊዜ ስልኮት ላይ የሚያተኩሩ ከሆነ፣ ሲናገር የሚያቋርጡት ከሆነ ወይም ስሜቶትን የማያከፍሉት ከሆነ እንደማይወዱት ሊሰማው ይችላል።ይልቁንም አሳቢ መሆን ፣ድጋፍ መስጥት፣ማዳመጥ እና መሳተፍ እንደሚወዱት እንዲሰማው ያደርጋል

♥️ የአገልግሎት ተግባራት

የአንድ ሰው ዋና የፍቅር ቋንቋው የአገልግሎት ተግባራት ከሆነ፣ ፍቅራቸውን ለመግለፅ ወይም አጋራቸው ፍቅሩን ለመግለፅ ከፈለገ የእርዳታ አገልግሎት መቅርብ አለበት

ይህ አጋራቸው ያልተጠበቁ ጥሩ ነገሮችን ሲያደርግ፣ ልዩ ፕሮጀክቶችን በጋራ መስራትን፣ የቤት ውስጥ ስራዎችን ማጠናቀቅ እና በአገልግሎት መረዳዳትን ይጨምራል

እነዚህ ብዙውን ጊዜ ጫናን ወይም ጭንቀትን ለማስታገስ ከመደበኛው የኃላፊነት ድርሻዎ በላይ በመሥራት አጋሮን መርዳት ሊሆን ይችላል። ይህ የፍቅር ቋንቋ ያላቸው ሰዎች አጋራቸው ነገሮችን ለማቅለል ሲል አንድ መስራት የማይወዱትን ስራ በመስራት ማስደስት ይቻላል/ፍቅርን ለመግለፅ ጥሩ መንገድም ነው

ሁሌ ለምን ብርድ ብርድ ይለኛል?እነዚህ የጤና ችግሮች የብርድ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርጉ ይችላሉ ◈ የደም ማነስ የደም ማነስ የሚከሰተው በደማችን ውስጥ በሚፈጠር የቀይ ደም ሴሎች እጥረት ነው...
30/09/2025

ሁሌ ለምን ብርድ ብርድ ይለኛል?

እነዚህ የጤና ችግሮች የብርድ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርጉ ይችላሉ

◈ የደም ማነስ

የደም ማነስ የሚከሰተው በደማችን ውስጥ በሚፈጠር የቀይ ደም ሴሎች እጥረት ነው ፤ ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጅን ለሰውነታችን የሚያስተላልፉ ሲሆን መጠናቸው ሲያንስ ሰውነታችን የሚገባውን ያህል ኦክስጅን አያገኝም ይህ ሲሆን የብርድ ስሜት በተለይ በእጅ እና እግር ላይ ፣ የድካም ስሜት ፣ የማዞር ስሜት እና የትንፋሽ እጥረት ሊከሰት ይችላል

◈ ሃይፖታይሮዲዝም (የታይሮይድ መጠን ማነስ)

አንገታችን ውስጥ የሚገኘው የታይሮይድ እጢ በቂ ሆርሞን ማመንጨት ሲቸገር የብርድ ስሜት ይፈጥራል

◈ ኩላሊት በሽታ

ኩላሊት ሲታመም በሰውነታችን ውስጥ አደገኛ የቆሻሻ ክምችት ሊፈጠር ይችላል ይህ ሲከሰት የሰውነታችንን ሙቀት ሊቀንስ ይችላል። ኩላሊት በሽታ አልፎም የደም ማነስ በማምጣት ይበልጥ የብርድ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል

◈ ስኳር በሽታ

በስኳር ምክንያት የሚፈጠር የነርቭ ጉዳት ብርድ ብርድ እንዲለን ምክንያት ይሆናል

◈ የደም ቧንቧ መጥበብ

የደም ቧንቧ ውስጥ የሚከማች ቆሻሻ የደም ቧንቧ እንዲጠብ በማድረግ ደም በቅጡ መዘዋወር እንዳይችል ያደርጋል ይህ ሲሆን እጅ እና እግር ተገቢውን ያህል ደም ስለማያገኙ ቅዝቃዜ ስሜት ሊፈጠር ይችላል

◈ የነርቭ ህመም

በቂ የሆነ መልእክት ወደ ሰውነታችንን ማስተላለፍ ስለማይቻል የነርቭ ህመም ያጋጠማቸው ሰዎች ላይ ብርድ ብርድ ማለት ፣ መደንዘዝ እና የማቃጠል ስሜት ሊፈጠር ይችላል

◈ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት

የቫይታሚን ቢ12 እጥረት የደም ማነስ በመፍጠር ብርድ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል

◈ ሃይፖፒቱታሪዝም

ይህ ህመም የሚከሰተው አእምሮ ውስጥ ያለው ፒቱታሪ እጢ በቂ ሆርሞን ማመንጨት ሳይችል ሲቀር ነው። የብርድ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።

◈ መድሃኒቶች

አንዳንድ መድሃኒቶች ብርድ ስሜት ያስከትላሉ ቤታ ብሎከርስ የተባሉ የልብ መድሃኒቶች የብርድ ስሜት፣ የማዞር ስሜት፣ የማቅለሽለሽ ስሜት እና ድካም ይፈጥራሉ

◈ ጉንፋን

ጉንፋን አፍንጫ፣ ጉሮሮ እና ሳንባን ጨምሮ መላ ሰውነታችንን የሚያጠቃ ቫይረስ ሲሆን በዚህ ወቅት ብርድ ብርድ እንዲለን ያደርጋል

ከመጠን በላይ ስኳር መጠቀም የጤና ችግር ያመጣል?በቀን መጠቀም ያለብን የስኳር መጠን ስንት እንደሆነ ብዙዎቻችን አንረዳም ነገር ግን ለወንዶች በቀን ውስጥ እስከ 9 የሻይ ማንኪያ ሲሆን ለሴቶ...
28/09/2025

ከመጠን በላይ ስኳር መጠቀም የጤና ችግር ያመጣል?

በቀን መጠቀም ያለብን የስኳር መጠን ስንት እንደሆነ ብዙዎቻችን አንረዳም ነገር ግን ለወንዶች በቀን ውስጥ እስከ 9 የሻይ ማንኪያ ሲሆን ለሴቶች ደግሞ 6 የሻይ ማንኪያ ድረስ መጠቀም እንችላለን ነገር ግን እዚም መድረስ የሌለበት ሲሆን ከዚህ በላይ የሚጠቀሙ ከሆነ ከመጠን በላይ እንለዋለን

የሚያመጣቸው ችግሮች ፡-

✦ የበሽታ መከላከል አቅምን ይቀንሳል

✦ ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ላልተፈለገ ውፍረት እና ለደም ግፊት ስለሚያጋልጠን ወደ ልብ ህመም ይመራናል

✦ ኢንሱሊን በአግባቡ እንዳይስራ በማድረግ አይነት 2 ለሆነው የስኳር ህመም ያጋልጣል

✦ የካንሰር ተጋላጭነታችንን ይጨምራል

✦ ስኳር አብዝተን በምንጠቀምበት ጊዜ ስሜታችን እንዳይነቃቃ እና ድብርት ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል

✦ ቆዳችን ቶሎ እንዲሸበሸብ እና ያረጀን እንድንመስል ያደርጋል ምክንያቱም ኮላጅን እና ኢላስቲን ቆዳ እንዲለጠጥ የሚያደርጉ ሲሆኑ ስኳር በምናበዛበት ወቅት ግን ስራቸው ይስተጓጎላል

✦ በደማችን ውስጥ ያለውን ቅባት ስለሚጨምረው የጉበት ስብ እንዲከሰት ያድርጋል

✦ ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን እንዲጨምር ያደርገዋል ስለዚህ የደም ቧንቧዎች ላይ ጫና እንዲፈጠር በማድረግ ወይም ለመለጠጥ የሚያስችላቸውን አቅም በማሳጣት የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል

✦ በሰውነታችን ውስጥ ሌኘቲን የሚባል ንጥረ ነገር መጥገባችንን የሚነግረን እና የረሃብ ስሜትን የሚቆጣጠር ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን በምንጠቀምበት ወቅት ስራውን እንዳይሰራ በማድረግ ረሃብ እንዲባባስ እና መብላት ከሚገባን በላይ ተመግበን ለአላስፈላጊ ውፍረት እንድንጋለጥ ያደርጋል

✦ ስኳር ሰውነታችን ወዝ እንዲያመርት ስለሚያደርግ ቡጉር ያመጣል

የምግብ አለርጂ ከዚህ በፊት ያለ ምንሞ ችግር ሲበሉት በነበረ ምግብ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ?የምግብ አለርጂ የሚፈጠረው የሰውነታችን የበሽታ የመከላከል ስርዐት አንድ ምግብ ...
26/09/2025

የምግብ አለርጂ ከዚህ በፊት ያለ ምንሞ ችግር ሲበሉት በነበረ ምግብ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ?

የምግብ አለርጂ የሚፈጠረው የሰውነታችን የበሽታ የመከላከል ስርዐት አንድ ምግብ ወስጥ ሊገኝ የሚችል ፕሮቲንን በስህተት እንደ መጥፎ አካል ቆጥሮ በሚሰጠው ምላሽ ምክንያት ነው

ይሄም ምላሽ በሰውነታችን ውስጥ ቀለል ካሉ ምልክቶች ጀምሮ ለህይወት አስጊ እስከመሆን የሚደርሱ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል

መንስኤዎች

አብዛኛዎቹ የምግብ አለርጂዎች በተወሰኑ ምግቦች ይነሳሉ ከነዚህም ውስጥ

⋄ ኦቾሎኒ
⋄ እንቁላል
⋄ የላም ወተት
⋄ ስንዴ
⋄ አኩሪ አተር
⋄ አሳ

ምልክቶች

ለአንዳንድ ሰዎች የምግብ አለርጂ ምላሽ ከባድ ላይሆን ይችላል። ለሌሎች ሰዎች ፣ የአለርጂ የምግብ ምላሽ አስፈሪ አልፎ ተርፎም ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል። ምግብ ከበሉ በኋላ ብዙውን ጊዜ የምግብ አለርጂ ምልክቶች ከጥቂት ደቂቃዎች እስከ ሁለት ሰዓታት ውስጥ ይታያል

የተለመዱ የምግብ አለርጂ ምልክቶች :

⋄ በአፍ ውስጥ ማሳከክ
⋄ የሆድ ህመም
⋄ ተቅማጥ
⋄ ማቅለሽለሽ
⋄ ማስታወክ
⋄ የከንፈር የፊት ፣የምላስ እና የጉሮሮ ወይም ሌሎች የሰውነት ክፍሎች እብጠት
⋄ አተነፋፈስ የአፍንጫ መታፈን ወይም የመተንፈስ ችግር
⋄ መፍዘዝ
⋄ ራስ ምታት
⋄ ችፌ
⋄ በአንዳንድ ሰዎች የምግብ አለርጂ አናፍላሲስ የተባለ ከባድ የአለርጂ
ምላሽን ሊያስነሳ ይችላል። ይህ ለሕይወት አስጊ የሆኑ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል። ከነዚህም ውስጥ :

⋄ የአየር መተላለፊያ ቱቦዎች መዘጋት
⋄ ለመተንፈስ የሚያስቸግር የጉሮሮ እብጠት
⋄ በከፍተኛ ሁኔታ የደም ግፊት መቀነስ
⋄ ፈጣን የልብ ምት
⋄ የንቃተ ህሊና ማጣት
⋄ አጋላጭ ሁኔታዎች
⋄ በቤተሰብ የምግብ አለርጂ ከነበረ
⋄ ዕድሜ
⋄ አስም

መከላከያ መንገዶች

⋄ ምን እንደሚበሉ እና እንደሚጠጡ ይወቁ፡፡የታሸጉ የምግብ ላይ መለያዎችን በጥንቃቄ ማንበብዎን እርግጠኛ ይሁኑ

⋄ በምግብ ቤቶች ውስጥ በሚመገቡበት ጊዜ ጥንቃቄ ያድርጉ

ህክምናውስ ምንድን ነው?

⋄ ምግቡን መብላት ያቁሙ

⋄ በሐኪም የታዘዙ ፀረ-ሂስታሚን መድኃኒቶች የመለስተኛ ምላሾችን ምልክቶች ለመቀነስ ይረዳሉ

⋄ ከባድ የአለርጂ ምላሽ ወይም አናፍላሲስ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የኤፒነፍሪን ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል

የእግር ህመም መንስኤዎችአብዛኛው የእግር ህመም በመገጣጠሚያዎች ፣ በአጥንቶች ፣ በጡንቻዎች ፣ በጅማቶች ወይም ሌሎች ህብረ ህዋሶች መዳከም እና ከመጠን በላይ መጠቀም ወይም በአደጋ ምክንያት ...
23/09/2025

የእግር ህመም መንስኤዎች

አብዛኛው የእግር ህመም በመገጣጠሚያዎች ፣ በአጥንቶች ፣ በጡንቻዎች ፣ በጅማቶች ወይም ሌሎች ህብረ ህዋሶች መዳከም እና ከመጠን በላይ መጠቀም ወይም በአደጋ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። አንዳንድ የእግር ህመም ዓይነቶች በታችኛው አከርካሪ ላይ ካሉ ችግሮች ጋር ሊያያዙ ይችላሉ፡፡ የእግር ህመም በደም መርጋት ፣ ቫሪኮስ ቬን ወይም በቂ የደም ዝውውር ባለመኖሩ ምክንያት ሊከሰት ይችላል

የእግር ህመም ምክንያቶች

▸ የሪህ በሽታ
▸ የደም መርጋት ችግር
▸ የአከርካሪ ችግር
▸ የሳያቲካ ችግር
▸ የአጥንት ኢንፌክሽን
▸ ውልቃት
▸ ቫሪኮስ ቬን
▸ የኩላሊት በሽታ
▸ የነርቭ ችግር
▸ ኢንፌክሽኖች
▸ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አደጋዎች

የእግር ህመም አይነቶች

▸ ሺን ስፕሊንት (Shin splints) ፡- ፊት እግርዎ ወይም ቁርጭምጭሚትዎ ላይ ህመም ከጀመረዎ ብዙ ጊዜ የሺን ስፕሊንት ምልክት ነው ። ይህ ህመም የሚፈጠረው በእንቅስቃሴ እግራችን ላይ ጫና ስንፈጥር ነው። ሰውነታችን ከለመደው ደረጃ በላይ እንቅስቃሴ ስናደርግ ስሜቱ ይፈጠራል

▸ የእግር እስትራፖ ፡- ከፍተኛ እንቅስቃሴ ወይም የውሃ ጥማት እግር ላይ የጡንቻ መሳሳብ ወይም እስትራፖ እንዲፈጠር ያደርጋል አንዳንድ ግዜ ከተለመዱ ነገሮች ወጣ ያሉ ነገሮችን ስናደርግ ለእንደዚህ አይነት ችግር እንድንጋለጥ ያደርገናል

▸ የቁርጭምጭሚት ህመም ፡- ሲንቀሳቀሱ ወይም ቁርጭምጭሚትን ሲጫኑ የህመም ስሜቱ የሚጨምር መቅላት ወይም እብጠት ካለው የቁርጭምጭሚት ህመም ሊኖርብዎ ይችላል

▸ ሳያቲካ (Sciatica) ፡- ጀርባዎ እና የእግርዎ ጀርባ ላይ የሚወረወር ህመም የሚሰማዎት ከሆነ ችግሩ ሲያቲክ ነርቭ ላይ ሊሆን ይችላል። ሲያቲክ ነርቭ ከታችኛው ጀርባ ላይ ጀምሮ በመቀመጫ በማለፍ ወደ እግር የሚሄድ ነርቭ ነው

▸ የአኪሊስ ቴንደን ጉዳት ፡- ከተረከዝ በላይ የሚፈጠር ህመም ብዙ ግዜ የአኪሊስ ቴንደን ጉዳት ምልክት ነው። ከፍ ያለ የሂል ጫማ ማዘውተር ይህንን ህመም ይፈጥራል ፡፡ እንዲሁም ልጆች ከእንቅልፋቸው በእግር ህመም እና ስትራፖ ምክንያት ሊነሱ ይችላሉ የልጅ አጥንት ሲያድግ የጡንቻ ቴንደኖች በመለጠጥ ከአጥንት ጋር ሲያያዙ ህመም ሊፈጠር ይችላል

▸ የታፋ ህመም ፡- የቀን ሰራተኞች እና ሌሎች ከፍተኛ ጭነት የሚሸከሙ ሰዎች በታፋ ህመም በመጠቃት ይታወቃሉ ። የዚህ ምክንያት ዳሌ ዙሪያ የሚገኝ ነርቭ ላይ ጫና በመፈጠሩ ነው

የመከላከያ መንገዶች

▸ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል
▸ የሰውነት ክብደትን መቀነስ
▸ ቀለል ያሉና ምቾት የሚሰጡ ጫማዎችን መጠቀም
▸ የኩላሊት ፣ የጉበት ፣ የልብና የደም ግፊት በሽታዎችን በወቅቱ መታከም ዋንኞቹ የእግራችንን ጤና መጠበቂያ መንገዶች ናቸው

ለእግር ህመም የሚሰጡት የህክምና ዓይነቶች ከቀላል የነርቭ ህክምና እስከ ቀዶ ህክምና ድረስ የሚዘልቁ ሲሆን በደም ዝውውር መዘጋት ሳቢያ ለተከሰተ የእግር ህመም የተዘጋውን የደም ዝውውር በመክፈት የታማሚውን ጤና ወደነበረበት ለመመለስ የሚያስችል የህክምና ዘዴ አለ

የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ቅጠል የጤና ጠቀሜታዎች :-✧ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቀንሳል ✧ የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል✧ ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቅባት መጠን ያስተካክላል✧ አስ...
21/09/2025

የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ቅጠል የጤና ጠቀሜታዎች :-

✧ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቀንሳል

✧ የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል

✧ ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቅባት መጠን ያስተካክላል

✧ አስም እንዳይባባስ ያደርጋል

✧ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ ሰዎች የሰውነት ክብደት መጠን ያስተካክላል ነገር ግን የመከላከል አቅምን አያስተካክልም

✧ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ላለባቸው ጠቃሚ ነው

✧ በማረጥ ምክንያት የሚመጡ ድንገተኛ የሙቀት ስሜት እና እንቅልፍ የማጣት ችግርን ጤናማ ያደርጋል

✧ የደም ማነስ ላለባቸው ተመራጭ ነው

✧ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች

ነፍሰ ጡር ሴት እና የሚያጠቡ እናቶች ባይጠቀሙት ይመከራል

የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ግልፅ ምልክት ሳያሳዩ ለብዙ አመት በመቆየት ለከባድ የጤና ችግር ሊዳርጉን እንደሚችሉ ይውቃሉ?የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ህፃናትንና አዋቂዎች ላይ ይከሰታሉ፡፡ በጣም የተለያዩ...
18/09/2025

የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ግልፅ ምልክት ሳያሳዩ ለብዙ አመት በመቆየት ለከባድ የጤና ችግር ሊዳርጉን እንደሚችሉ ይውቃሉ?

የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ህፃናትንና አዋቂዎች ላይ ይከሰታሉ፡፡ በጣም የተለያዩ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ያሉ ሲሆን የተለመዱትና በብዛት ከሚገኙት ዉስጥ ወስፋት፣ የመንጠቆ ትል፣ ጊኒ ትል ፣ ስተሮንግሎይድስ፣ የኮሶ ትል፣ ጃርድያ እና አሜባ ይገኛሉ

የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነታችን የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫና በተበከለ ዉሃና ምግብ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ በመራባት የህመም ስሜቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ

✔ ምልክቶች

◈ የአንጀት ስርዓት ለዉጥ መኖር (የሆድ ድርቀት፣ ተቅማጥ ወይም ልል ሰገራ)
◈ የምግብ ፍላጎት መለወጥ
◈ ማቅለሽለሽና ማስመለስ
◈ የሆድ ህመም
◈ አንጀት ዉስጥ ከነበሩና ከአንጀት ዉጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች ከተሰራጩ ህመሙ ከአንጀት ዉጪ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል እንዲከሰት ያደርጋሉ
◈ ጉንፋን መሰል የህመም ምልክቶች፣ የሆድ መነፋትና ጋዝ መብዛት፣ በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት፣በፊንጥጣ ዙሪያ ማሳከክና የመሳሰሉት ናቸዉ

✔ መንስኤዎች

◈ በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
◈ የተበከለ ዉሃ
◈ ቆሻሻ የእጅ ጣቶች ጥፍር በአግባቡ ለመቆረጥ
◈ በደንብ ያልበሰለ/ ያልተቀቀለ/ ለብ ለብ የተደረገ ስጋ መመገብ
◈ ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ባህሪይ መኖር
◈ እንደ መንጠቆ ትል ያሉ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በባዶ እግር የምንሄድ ከሆነ ትሉ የእግር ቆዳን በስቶ ወደ ሰዉነታችን ይገባል
◈ የግል ንፅህና አጠባበቅ አነስተኛ መሆን
◈ የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ መሆን
◈ በጥገኛ ትላትሎች የተያዘ የቤት እንስሳ ጋር መኖር

✔ የመከላከያ መንገዶች

◈ ሁሉንም አትክልትና ፍራፍሬዎች ከመመገብዎ በፊት በደንብ ማጠብ
◈ ከመመገብዎ በፊት ምግብዎን በደንብ ማብሰል ፓራሳይቶችን ለመግደል ይረዳል
◈ ፈልቶ የቀዘቀዘ አልያም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
◈ የግልና የአካባቢ ንፅህ መጠበቅ
◈ ከመመገብዎ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅዎን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ/ካጫወቱ በኃላ እጅዎን በደንብ መታጠብ

✔ ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚደረገዉ ህክምና እንደጥገኛ ትላትሉ አይነት የሚለያይ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎን በማማከር አስፈላጊዉን ህክምና ማግኘት ይገባል

ተገቢውን ህክምና ሳያገኝ የቆየ የሆድ ትላትል እስከ ሞት ሊያደርሱ የሚችሉ የውስጥ የሰውነት አካላት ጉዳቶች እና የጤና ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል

የድድ መሸሽ ምንድን ነው?የድድ መሸሽ ወይም ጂንጂቫል ሪሴሽን የድድ ሴሎች ሲጠፉ የጥርስ ስር የሚሸፍነው ድድ ተገፍቶ የጥርስ ስር የሚያጋለጥበት ሁኔታ ነው መንስኤዎች▸ ከፍተኛ ፍትጊያ የሚያመ...
16/09/2025

የድድ መሸሽ ምንድን ነው?

የድድ መሸሽ ወይም ጂንጂቫል ሪሴሽን የድድ ሴሎች ሲጠፉ የጥርስ ስር የሚሸፍነው ድድ ተገፍቶ የጥርስ ስር የሚያጋለጥበት ሁኔታ ነው

መንስኤዎች

▸ ከፍተኛ ፍትጊያ የሚያመጣው መሳሳት
▸ የጥርስ ኢንፌክሽን
▸ ያልተስተካከለ የጥርስ አቀማመጥ
▸ ጥርስ ስንቦርሽ ድድ ላይ ጫና ከተፈጠረ
▸ ፔሪዮዶንታል በሽታ
▸ በዘር የሚመጣ የድድ መሳሳት
▸ የስኳር ህመም
▸ የሆርሞን ለውጥ
▸ ሲጋራ ማጨስ

ምልክቶች

▸ ጥርስ ከቦረሹ በኋላ መድማት
▸ ቀይ ያበጠ ድድ መኖር
▸ መጥፎ የአፍ ሽታ
▸ የድድ ህመም
▸ የጥርስ መነቀል
▸ የድድ መሸብሸብ

መከላከያ መንገዶች

▸ ጥርስን በጣም ሳይጫኑ በስሱ መፋቅ
▸ ሳሳ ያለ ዘመናዊ መፋቂያ መጠቀም
▸ በጣም ቀጭን የጥርስ ማፅጃ ገመድ በመጠቀም ድድን ሳይጫኑ ጥርስ መሀል ያሉ ክፍተቶችን ማፅዳት
▸ የድድን ሴንስቲቪቲ የሚቀንሱ የጥርስ ሳሙናዎች መጠቀም
▸ ሲጋራ ማጨስን ማቆም
▸ ጥርስን ለሊት ለሊት የማፋጨት ወይም በሀይል የማጋጠም ሁኔታ ካለ የጥርስ መሸፈኛ ማድረግ

💊 ህክምናው መንስኤው እና ያለበት ደረጃው ላይ ተመስርቶ እስከ ሰርጀሪ የሚደርስ ሊሆን ይችላል

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጤናማ ህይወት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram