ጊዜ የባህል ሕክምና አገልግሎት/ Gize traditional medical center

ጊዜ የባህል ሕክምና አገልግሎት/ Gize traditional medical center አድራሻ
ቦሌ ቦሌስኩል አጠገብ👈
አያት ባቡር 40/60 ቤቶች ዋናው መንገድላይ 👈
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲው አካባቢ 👈
09 88 95 47 64

11/08/2025

ጊዜ የባህል ሕክምና ማዕከል✅

09 88 95 47 64📞

01/08/2025

በመዲናዋ 2ተኛው መስሪያቤታችን አያት አደባባይ የሚገኘው ጊዜ የባህል ሕክምና ማዕከል እንዲህ በተደራጀና ባማረ መልኩ ተጠናቆ ስራውን ጀምሯል ☘️

18/07/2025
በአዲስአበባ አያት አደባባይ የሚገኘውን መስሪቤታችን በተያያዘው ሊንክ አማካይነት ያገኙታልጊዜ የባህል ሕክምና ማዕከል🌿🌱☘️
14/07/2025

በአዲስአበባ አያት አደባባይ የሚገኘውን መስሪቤታችን በተያያዘው ሊንክ አማካይነት ያገኙታል

ጊዜ የባህል ሕክምና ማዕከል🌿🌱☘️

Find local businesses, view maps and get driving directions in Google Maps.

 #ጥቁሯ ሐምሌ ሰባት ስትታወስዓለማየሁ ገላጋይ ለሟች ብቻ ሳይሆን ለገዳይም ማዘን ይገባል የምትል ቆንጆ አባባል አለችው። በርግጥም ለገዳይ ማዘን ከተገባ የእኔ ሐዘን ለኮለኔል ዳንኤል አስፋው...
14/07/2025

#ጥቁሯ ሐምሌ ሰባት ስትታወስ

ዓለማየሁ ገላጋይ ለሟች ብቻ ሳይሆን ለገዳይም ማዘን ይገባል የምትል ቆንጆ አባባል አለችው። በርግጥም ለገዳይ ማዘን ከተገባ የእኔ ሐዘን ለኮለኔል ዳንኤል አስፋው ያደላል። ይህ ሰው ሦስት የአገር መሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። በዚህ ሳያበቃም ከሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አሳዛኝ ሕልፈት ጋር ስሙ ይነሳል።

መጋቢት ሦስት ቀን 1968 ዓ.ም ኮለኔል ዳንኤል በመራው ቡድን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ጵጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በአሳዛኝ ሁኔታ የተገደሉት ከ46 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር። የቅዱስነታቸው ሞት በሕይወት እያሉ እንደ ተቀኟቸው ቅኔያት ሰምና ወርቅ ነው። ቁምነገሩ ግን ይህ አይደለም። ዋናው ጉዳይ አራት አስርታት የተሻገረው የጭካኔ ቅኔ አሁንም በወጉ አለመፈታቱ ይመስለኛል።

ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን ለመግደል ያሰበው በሥጋ ብቻ አልነበረም። ከሞቱም በኋላ ስማቸው በበጎ እንዳይታወስ ለማድረግ የሚቻለውን ሞክሯል። አንዱና ዋናው ቅዱስነታቸው ከእስር ቤት አምልጠው በአንዲት ሴት መነኩሴ ቤት ተደብቀው ተያዙ የሚለው ዜና ነው። የደርግ ሰዎች ይህን ፖለቲካዊ ቴአትር ሊያሰሩ ለምን እንደፈለጉ ግልጽ ባይሆንም ተውኔቱ ግን እዚህ ግባ የሚባል ሤራ የለውም።

ሁለት ነገሮችን ብቻ ልጥቀስ። የመጀመሪያው አንድ የስድሳ ዘጠኝ ዓመት የሐይማኖት መሪ በጥብቅ ከሚጠበቀው ቅፅር አመለጡ መባሉ ነው:: እንዲህ ያለው ኩሸት ለስልጣን ለሚታገል አልያም ለምድራዊ ኑሮ ለሚተጋ ወጣት ይመጥን ይሆናል። ምድራዊውን ሞት አስቀድሞ ለሞተ አባት ግን አመለጡ የሚለው ቃል የተገባ አይደለም።

ቅዱስነታቸው ለምድሩ ሕይወት ቢጓጉ አስቀድመውም ከደርግ ጋር መስማማትና ለፖለቲከኞች ሎሌ መሆን ይችሉ ነበር። የእርሳቸው ምርጫ ግን በግልፅ እንደታየው ከቤተ መንግስቱ በተቃራኒ ሆነ:: ከደርግ ውድቀት በኋላ በተቋቋመው ልዩ አቃቢ ሕግ ውስጥ በመረማሪነት የተሳተፉ አንድ ግለሰብ እንዳጫወቱኝ ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ለወታደራዊው መንግስ አሳልፈው ያስረከቡት በቤታቸው ደበቁ የተባሉት ሴት መነኩሴ ናቸው። ይህ መረጃ እውነት ከሆነ ቅዱስነታቸው ባልጠበቁት ሴራ ተተብትበው ለሞት የተጋዙ አባት ሆነዋል::

ወታደራዊው መንግስት የእኝህን አባት ሥጋ ገድሎ ላለመርካቱ ሌላው ማሳያ ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በኢጣሊያን ወረራ ወቅት አቡነ ጴጥሮስ እንዲገደሉ ፈርመዋል መባሉ ነው:: ደርግ ለዚህ የሀሰት ውንጀላው የውሸት ደብዳቤ አዘጋጅቶ የቅዱስነታቸው ይሁንታ መኖሩን ለታሪክ ለመተው ብዙ ደክሟል:: ይህም ቢሆን ግን በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት በእውነት ንፋስ ሲፈርስ ብዙ አልቆየም:: የወቅቱ ሰነዶች እንደሚያስረዱት በቅደመ ስማቸው አባ መልዕክቱ ይባሉ የነበሩት አቡነ ቴዎፍሎስ በፋሽሽት ዘመን ለእንዲህ ያለ ውሳኔ የሚያበቃ ስመ ሥልጣን አልነበራቸውም::

የደርግ ከሁሉም የከፋው ተግባር ግን ሁለተኛውን ኢትዮጵያዊ ጳጳስ የገደለበት መንገድ ነው። የኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ቅዱስነታቸውን ወግ ላለው ሞት እንኳን አላጫቸውም:: የሞት መልዕክተኞቹ እኝህን ትልቅ አባት ቀጭን ሽቦ አንገታቸው ላይ አስገብተው በተራዘመ ስቃይ ነበር ለህልፈት ያበቋቸው::

ዘግይቶ እንደተሰማው ደግሞ በዚች ጥቁር ቀን የተገደሉ ሌላም የሐይማኖት መሪ ነበሩ:: ስማቸው ቄስ ጉዲና ቱምሳ ሲባል ፤ እንደ ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ሁሉ አብዮቱ እግዚአብሔርን መግፋቱ ተገቢ አይደለም ብለው በአደባባይ የተቹ ናቸው:: ቄስ ጉዲና ክርስቶስ የመጣው ለተገፉትና ለጭቁኖች ነው ብለው የኮሚኒዝምን አማላክ አልባነት አውግዘዋል:: የኮለኔል መንግስቱ አማካሪ የነበረውን ታናሽ ወንድማቸው ባሮ ቱምሳን ሳይቀር ባኮ ከተማ በተካሄደ ሙግት አምርረው ወቅሰዋል::

ታዲያ ይህ ፕሮቴስታንታዊ ክርክራቸው በደርግ ሳይወደድ ቀርቶ ከብጹዕነታቸው ጋር የሞት ጽዋን እንዲጎነጩ ተደረጉ:: ቁመተ መለሎው ቄስ ጉዲና በዛሬዋ ዕለት ለምድሩ ሞት ሲሞሸሩ የነበረው ሂደት ከቅዱስነታቸውም የከፋ ነበር:: የደርግ ነፍሰ ገዳዮች ባገኙት ነገር ሰቅለው ሕይወታቸውን ለማጥፋት ቢሞክሩም የቄስ ጉዲና ቁመት ግን ለዚህ አልተመቸምና ጣሩን አበዛባቸው:: በዚህ ሂደትም ነፍሳቸው ሳይወጣ በብዙ ስቃይ ውስጥ ቆይተዋል:: አንዳንዶች እንደሚሉትም የመጨረሻ ህልፈታቸው እውን የሆነው አንገታቸን በመስበር ነበር::

የዛሬዋ ቀን ሁለቱን የሃይማኖት አባቶች ብቻ ሳይሆን ሁለቱን የኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም መንበር ተቀናቃኞች ኃይሌ ፊዳና ብርሃነ መስቀል ረዳንም ያጣንበት ነው። የደርግ መንግስት እነዚህ ሰዎች በተመሳሳይ ዕለት የገደለው ባጋጣሚ አይመስልም። ግድያው ትዕምርታዊ ነበር::

የታሪክ ድርሳናት እንደሚያትቱት ደርግ ብርሃነመስቀል ረዳና ሃይሌ ፊዳን በተመሳሳይ ጉድጎድ ፤ ቅዱስነታቸውንና ቄስ ጉዲናን በሌላ ጉድጎድ እንዲቀበሩ ካደረገ በኇላ ሁሉንም ጠላቶቹን ከምድር በታች እንዳዋለ ያስብ ነበር:: የሆነው ግን ከዚህ ይለያል:: የፈራቸው ትልልቆቹን ሲገድል የተናቁት አራት ኪሎን በእጃቸው አስገቡ::

ይህም ሆኖ ወታደራዊው መንግስት አንድ ነገር አሳክቷል:: እርሱም ለልጆቹ ወግኖ በሃይማኖቱ ታምኖ ለመሞት የተዘጋጀ አባት ከአምስት ኪሎ መጥፋቱ ነው:: ዛሬ እነዛ ለእምነታቸው ታምነው በአንድ የደርግ ጉድጎድ የተከተቱ አባት ልጆች ፖለቲካ መሀላቸው ገብቶ ያነታርካቸዋል :: እሳዛኙ ነገር ከዚህም ከፍ ይላል:: አሁን ይችን ዕለት የተንተራሰው አረጋዊ የሃይማንት ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የመግደል ፖለቲካ ከገዳም ደጃፍ ደርሷል::

እነሱ አንዴ የሥጋን ሞት ሙተዋልና ሀዘናችን ለገዳይ ነው:: እንዴት ያለ ልቡና የአንድን አርጋዊ ስቃይና ሕልፈት እያየ ተደሰተ? ምንስ ሕሊና በአባቱ አንገት ላይ ገመድ አስገብቶ የሰላም እንቅልፍ ተኛ? እንጃ!

#የቅዱስነታቸው በረከት ይደርብን!

Maereg Getachew

12/07/2025

በዌብሳይት አድራሻችን gize1.wordpress.com ያገኙናል

11/07/2025

ጊዜ የባህል ሕክምና ማዕከል

0988954764

09/07/2025

Giza traditional medical center
በጊዜ ይታከሙ🌱🌱

07/07/2025

ጊዜ የባህል ህክምና ማዕከል

ለስንፈተ -ወሲብ
ለአይነ-ጥላ
ለዕደሰብ(የሰውጂ)
ለኪንታሮት
ለደምግፊት
ለሪህ
ለጉበት
ለሚጥል በሽታ
ለመካንነት
ለአስም
ለአልማዝ ባለጪራ

እና ሌሎችንም አገልግሎቶች እንሰጣለን

አድራሻችን አያት ባቡር ጣቢያ 40/60 ቤቶች አማራባንክ ያበት ህንፃ ዋናው መንገድ ላይ ያገኙናል

ስልክ 09 88 95 47 64

በጊዜ ይታከሙ !

Address

ቦሌ ሆምስ/ጉርድ ሾላ/ደ/ብርሃን ያገኙናል
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጊዜ የባህል ሕክምና አገልግሎት/ Gize traditional medical center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category