27/02/2025
Polycystic Ovarian Syndrome (PCOS) ምንድን ነው?
👉🏽 PCOS የሆርሞን መዛባት ችግር ሲሆን የሚያጠቃው የማህፀን እንቁላል ማምረቻ (ovaries) ሲሆን ፤ የሚከሰተውም በሴት ልጅ የመውለጃ እና የወር አበባ ዘመን ላይ ነው።
PCOS ለምን ይከሰታል?
👉🏽 PCOSን የሚያመጡ ነገሮች በጥናት ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ ባይቻልም ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ምክንያቶች መሀከል
⚡️ ለinsulin ለተባለው ሆርሞን ሰውንታችን ስሜት ማጣጣት (loss of sensitivity) ወይም መቋቋም (resisitance) - ይህም ለስኳር ህመም ያጋልጣል
⚡️ Androgen የተባለው የወንድ ሆርሞን በሰውነት መጨመር ይጠቀሳሉ - ይህም እንቁላል በየወሩ እንዳልይለቀቅ ያደርጋል። በተጨማሪም በማይጠበቁ ቦታዎች ላይ ፀጉር እንዲበቅል ያደርጋል
የPCOS ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
👉🏽 የተዛባ የወር አበባ:- ይህም ማለት እየቆየ የሚመጣ የወር አበባ, ሲመጣ ደግሞ በጣም የሚበዛ መሆን
👉🏽 መውለድ መቸገር
👉🏽 ውፍረት :- PCOS ካለባቸው ከ 5 ሴቶች 4ቱ ወፍራም የሚባሉ ናቸው
👉🏽 ፀጉር በማይጠበቅ ቦታ መውጣት :- በፊት፣ ደረት፣ ሆድ፣ ጭን እና እግር ላይ
👉🏽 በጎልማሶች ላይ ብጉር :- ብዙን ጊዜ ለህክምናዎች በቀላሉ የማይድኑ
👉🏽 እጅግ ወዛማ የሆነ ቆዳ
👉🏽 በአንገት፣ ብብት እና በተወሰኑ የቆዳ አካባቢዎች መጥቆር ከሌላው አካባቢ ጠንከር እና ሻከር ማለት
👉🏽 በማህፀን እንቁላል ማምረቻ ላይ ትንንሽ ውሀ የቋጠሩ ከረጢቶች መፈጠር
PCOS ሊያመጣ የሚችላቸው ተጓዳኝ የጤና እክሎች
👉🏽 የስኳር በሽታ ( type 2 DM)
👉🏽 Metabolic syndrome- ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ የደም ግፊት መጨመር፣ መጠን መጨመር እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን መኖር
👉🏽 ለልብ ህመም ማጋለጥ
👉🏽 የማህፀን የውስጠኛው ግድግዳ መወፈር እና ለማህፀን የውሰጠኛው ግድግዳ ካንሰር ማጋለጥ
👉🏽 በእንቅልፍ ጊዜ አየር ማጠር እና እንቅልፍ መቸገር
👉🏽 ለድባቴ (depression) መጋለጥ ናቸው።
የPCOS ህክምና ምን ይመስላል?
👉🏽 የPCOS ህክምና የሚወሰነው እንደ ሴቲቱ የህመም ምልክት ፣ ተጓዳኝ የጤና ሁኔታዎች እና የእርግዝና ፍላጎቶትን ባማከለ መልኩ ይሆናል
👉🏽 የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች - የወር አበባን ለማስተካከል ፣ ባለተገባ ቦታ የሚወጡ ፀጉሮችን ለመከላከል ፣ ብጉርን ለመከላከል እና የማህፀን ግድግዳ ካንሰርን(endometrial cancer) ለመከላከል ይጠቅማሉ።
👉🏽 ለስኳር ህመም የሚሰጡ መድሀኒቶችም ለPCOS የህክምና መንገድ ይሆናሉ፤ ይህም androgen የተባለውን ሆርሞን በመቀነስ እንቁላል እንዲለቀቅ እና የወር አበባ ጊዜውን ጠብቆ እንዲመጣ ያደርጋል።
🗣️🗣️ ጠቃሚ ነጥቦች!
⚡️ ለማርገዝ በሚፈለግ ጊዜ መደረግ ካለባቸው ነገሮች ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው የሰውነት ክብደትን(ውፍረትን) መቀነስ ነው ፤ ይህም የወር አበባን እንዲስተካከል እና እንቁላል በሚጠበቅበት ጊዜ እንዲለቀቅ ያደርጋል።
⚡️ ሀኪምሽ በተወሰነ መልኩ እንቁላል እንዲለቀቅ የሚረዳ መድሀኒትም ሊሰጥሽ እና እርግዝና የመከሰት እድልን ሊጨምርልሽ ይችላል።
https://t.me/DrDawitMOBGYN