ALERT Comprehensive Specialized Hospital

ALERT Comprehensive Specialized Hospital This is the official Facebook account of ALERT Comprehensive Specialized Hospital

በአለርት ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማገልገል ላይ ካሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ለዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ዶ/ር ሩት አለሙ የሕፃናት የዓይን ሕክምና፣ የአዋቂዎችና የሕፃናት መንሸዋረር እና ...
05/01/2026

በአለርት ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማገልገል ላይ ካሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ለዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ዶ/ር ሩት አለሙ የሕፃናት የዓይን ሕክምና፣ የአዋቂዎችና የሕፃናት መንሸዋረር እና ኒውሮ-ኦፕታልሞሎጂ ሰብ ስፔሻሊስት ናቸው።

ስለ ክፍሉ የበለጠ ለማወቅ👉🏼 https://alerthospital.gov.et/department/ophtalmology.php

***
Introducing the specialist doctors serving at Alert Comprehensive Specialized Hospital.

Today, we feature Dr. Ruth Alemu a Pediatric Ophthalmology, strabismus and Neuro-ophthalmology subspecialist

To know more about the department👉🏼 https://alerthospital.gov.et/department/ophtalmology.php

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ የስራ ክፍል በተቋሙ ምስጋናና እውቅና ቀረበለት!ይህ እውቅና የተሰጠው የስራ ክፍሉ በሴቶች፣ በህፃናት፣ በአ...
02/01/2026

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ የስራ ክፍል በተቋሙ ምስጋናና እውቅና ቀረበለት!

ይህ እውቅና የተሰጠው የስራ ክፍሉ በሴቶች፣ በህፃናት፣ በአረጋውያን፣ በአካል ጉዳተኞችና በሌሎች ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ያከናወነው ውጤታማ እና ተደራሽ አገልግሎት ምክንያት ነው።

በክቡርት ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን እና የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት...
02/01/2026

በክቡርት ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን እና የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ እና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የልዑካን ቡድኑ የTrauma Center ሕንፃ ግንባታ፣ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሕክምና ሕንፃ ግንባታ፣ ግንባታው የተጠናቀቀው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ሕንፃ፣ የህክምና እቃዎች መጠገኛና መገጣጠሚያ (ባዮሜዲካል) ሕንፃ ግንባታ፣ የሰራተኞች ካፍቴሪያ ሕንፃ ግንባታ፣ የከርሰምድር ውሃ ማውጫ ስራዎችን እንዲሁም በቀጣይ በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች የተዘጋጀ የመሬት አቀማመጥ ሁኔታን በዝርዝር ተመልክቷል።

በምልከታው መጨረሻ የልዑካን ቡድኑ እነዚህ ወሳኝ ፕሮጀክቶች በጥሩ ደረጃ ላይ መገኘታቸውን በመግለፅ፣ ስራዎቹ በተጀመረበት ፍጥነትና ጥራት እንዲቀጥሉ ቀጣይ ክትትል እንደሚደረግ ገልጿል።

ALERT Comprehensive Specialized Hospital በሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችና ሌሎች ተጋላጭ ቡድኖች ላይ የተከናወኑ አጠቃላይ አገልግሎቶችና ተግባራትን መሠ...
01/01/2026

ALERT Comprehensive Specialized Hospital በሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችና ሌሎች ተጋላጭ ቡድኖች ላይ የተከናወኑ አጠቃላይ አገልግሎቶችና ተግባራትን መሠረት አድርጎ በተካሄደው የአካቶ ትግበራ ምዘና በተሳካ ሁኔታ በመወጣት፣ ከጤናና ግብርና ሚኒስቴሮች ተጠሪ ተቋማት መካከል የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ እውቅና አግኝቷል።

ይህ ውጤት በተቋማችን ውስጥ ፍትሃዊነትን፣ ማካተትንና ማህበራዊ ፍትህን መርሆ አድርጎ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በተደረገ የተባበረ እና ቀጣይነት ያለው ጥረት ውጤት ነው።

ALERT Comprehensive Specialized Hospital ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላቀረቡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ክፍል ሰራተኞች ሁሉ ልባዊ ምስጋናውንና እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልእክት ያስተላልፋል።

ይህ እውቅና ተቋማችን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።

ALERT Comprehensive Specialized Hospital
Your Health Is Our Mission!

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት፣ የጥራትና ኢኖቬሽን ክፍል፣ የህሙማን ቅብብሎሽ ክፍል እና የህክምና ክፍል አስተባባሪዎች በጋራ በመሆን በኢትዮ ጠቢብ ...
01/01/2026

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት፣ የጥራትና ኢኖቬሽን ክፍል፣ የህሙማን ቅብብሎሽ ክፍል እና የህክምና ክፍል አስተባባሪዎች በጋራ በመሆን በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ተገኝተው፣ ከግል ጤና ተቋማት ጋር ያለውን የታካሚዎች የቅብብሎሽ ስርዓት (Private Health Institution Catchment Referral Linkage) እና በቀጣይ በጋራ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ያተኮረ ሁለተኛውን የጋራ የውይይት ፎረም በስኬት አካሂደዋል።

ይህ ፎረም የታካሚ ቅብብሎሽን ለማጠናከር፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና ከግል ጤና ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር አስፈላጊ መድረክ ሆኖ ተገልጿል።

Senior management members of ALERT Comprehensive Specialized Hospital, together with the Quality and Innovation department , the Patient admission & Discharge Unit, and Clinical Department Coordinators, conducted the second joint consultative forum at Ethio Tebib Hospital.

The forum focused on strengthening the patient referral linkage with private health institutions (private health institution catchment referral linkage) and discussed priority areas for continued collaboration and joint actions moving forward.

This engagement serves as an important platform to enhance referral coordination, improve service quality, and reinforce partnerships between public and private health institutions.
https://linktr.ee/Alert_Hospital
Linktree (https://linktr.ee/Alert_Hospital)
Alert Comprehensive Hospital | Facebook, TikTok | Linktree
Your Health, Our Mission – Excellence in Specialized Care.
Join our social media

🎥 የጤና ትምህርት | ALERT CSH👉 የኪንታሮት በሽታ• ምንነቱ• የሚታዩ ምልክቶች• የህክምና አማራጮችና መፍትሄዎችበዶ/ር በለጠ ሽኩርየጠቅላላ ቀዶ ህክምና ክፍል ኃላፊአለርት ኮምፕርሄንሲቭ...
01/01/2026

🎥 የጤና ትምህርት | ALERT CSH

👉 የኪንታሮት በሽታ
• ምንነቱ
• የሚታዩ ምልክቶች
• የህክምና አማራጮችና መፍትሄዎች

በዶ/ር በለጠ ሽኩር
የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ክፍል ኃላፊ
አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

📺 ቪዲዮውን ሙሉ በሙሉ ይመልከቱ፦
🔗 https://youtu.be/BxW5Gzj1Oxs?si=KzllXb6U72mT5w9T

✅ ይከታተሉን | ያጋሩ | አስተያየትዎን ይስጡ
“Your Health Is Our Mission!”

በአለርት ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማገልገል ላይ ካሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ለዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ዶ/ር ሀይመት ሰለሞን ራድዮሎጂስት እና ቦዲ ኢሜጂንግ ሰብስፔሻሊስት ናቸው።ስለ ክፍ...
29/12/2025

በአለርት ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማገልገል ላይ ካሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ለዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ዶ/ር ሀይመት ሰለሞን ራድዮሎጂስት እና ቦዲ ኢሜጂንግ ሰብስፔሻሊስት ናቸው።

ስለ ክፍሉ የበለጠ ለማወቅ👉🏼 https://alerthospital.gov.et/department/radiology.php

***
Introducing the specialist doctors serving at Alert Comprehensive Specialized Hospital.

Today, we feature Dr. Haymet Solomon a Radiologist body imaging sub-specialist

To know more about the department👉🏼 https://alerthospital.gov.et/department/radiology.php

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምርምር፣በስልጠና እና በህክምና አገልግሎት  ለማህበረሰቡ ተደራሽ እያደረገ ያለውን የጤና አገልግሎት አበረታች መሆኑን የሚዲያ ፎረም   ተሳታፊዎች...
27/12/2025

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምርምር፣በስልጠና እና በህክምና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እያደረገ ያለውን የጤና አገልግሎት አበረታች መሆኑን የሚዲያ ፎረም ተሳታፊዎች ገለፁ፡፡
ሆስፒታሉ ከሚዲያ ባለሙያዎች፣ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የፌዴራል ሆስፒታሎች የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ውይይትና የተግባር ስራዎችን ምልከታ አካሄዷል፡፡
በዚህም የማዋለጃ ህክምና ክፍሉ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑ፣የጽዱ ጤና ተቋም ምሳሌ እንደሆነ፣ለሚዲያ አካላት መረጃዎችን የመስጠት አቅምና ፍጥነቱ የሚበረታታና ተሞክሮ መሆኑ፣የሰራተኞችና የተገልጋዮች እርካታ መጨመሩ፣ተቋሙ ከህክምና በተጨማሪ የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እያከናወነ መሆኑ እና ከ500 በላይ አልጋዎች ያሉትና በወር ከ45 ሺ በላይ ተገልጋዮች የሚታከሙበት ተቋም መሆኑን እንዲሁም የዲጅታል ህክምና አገልግሎትና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቅም ተሞክሮዎች ቀርበዋል፡፡
በመጨረሻም ከሚዲያና ከተቋማት ጋር በጋራ በመስራት አገልግሎቶቹን ማሰፍትና ማስቀጠል እንደሚገባ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡

የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የፌዴራል ሆስፒታሎች የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተዘጋጀው የሚዲያ ፎረም ላይ ተሳት...
26/12/2025

የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የፌዴራል ሆስፒታሎች የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተዘጋጀው የሚዲያ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል።

በፎረሙ ቀጥሎ ተሳታፊዎቹ ሆስፒታሉ እያከናወናቸው ያሉ ዋና ዋና የተግባር ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ ተደራሽና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት እያከናወነ ያለውን ከፍተኛ ተግባራዊ ስራዎች፣ እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን፣ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን እንዲሁም የተቋሙን የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ለይ እየተሰራ ያለውን ስራ ተመልክተዋል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ሆስፒታሉ እያከናወነ ያለውን ተቋማዊ ለውጥና የአስተዳደር ስርአትን አድንቀዋል።

አለርት ሆስፒታል፡ ከቲቢና ስጋደዌ ማቆያነት ወደ ቀጠናዊ የህክምና የልህቀት ማዕከል!የጤና ተቋማት አለምአቀፋዊ ተልዕኮ ሰብአዊነትን መሠረት ያደረገ፣ ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና ጥራቱን የጠበቀ የህ...
25/12/2025

አለርት ሆስፒታል፡ ከቲቢና ስጋደዌ ማቆያነት ወደ ቀጠናዊ የህክምና የልህቀት ማዕከል!

የጤና ተቋማት አለምአቀፋዊ ተልዕኮ ሰብአዊነትን መሠረት ያደረገ፣ ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነው። በዚህ አውድ ውስጥ፣ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአለርት (ALERT) ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ ጠንካራ ታሪክ፣ የተረጋገጠ ተልዕኮ እና ዘርፈ-ብዙ አስተዋጽኦ ያለው ተቋም ነው።

1. ታሪካዊ ዳራና የሰብአዊነት ተልዕኮ

አለርት ሲመሰረት፣ ዋና ተልዕኮው በወቅቱ “የማይድንና ከፍተኛ ፍርሃት የነበረበት” የስጋደዌ (Leprosy) በሽታ መከላከል፣ ታካሚዎችን መንከባከብ እና የሰው ክብርን መጠበቅ ነበር። ዛሬ ግን ተቋሙ ያንን ታሪካዊ መነሻ በመጠናከር፣ የሰውን ልጅ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጤና በሙሉ የሚመልሱ ውስብስብ እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎቶች ማዕከል ሆኗል።

2. አለምአቀፋዊ ደረጃን የጠበቁ ዋና አገልግሎቶች

አለርት ከአለምአቀፍ የጤና ተልዕኮዎች (Global Health Missions) ጋር ተጣጣሚ በሆነ መንገድ የሚከተሉትን ቁልፍ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፦

•የመልሶ ማቋቋም ህክምና (Rehabilitation): በአደጋ ወይም በበሽታ ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሰው ሰራሽ አካላት መገጣጠም፣ ፊዚዮቴራፒ እና አጠቃላይ የመመለሻ እንክብካቤ በመስጠት ወደ ሙሉ እና ንቁ ህይወት እንዲመለሱ በግንባር ቀደምነት ይሰራል።

•የቆዳ ህክምናና ቀዶ ህክምና:
በቆዳ ህክምና (Dermatology) እና በፕላስቲክና መልሶ ማቋቋም ቀዶ ህክምና (Plastic & Reconstructive Surgery) ዘርፍ የአገሪቱ ዋነኛ እና የተመረጠ የሪፈራል ማዕከል ነው።

•የምርምርና ስልጠና ማዕከል (AHRI):
ከአርማወር ሃንሰን ሪሰርች ኢንስቲትዩት (Armauer Hansen Research Institute – AHRI) ጋር በቅርብ ትብብር በአለምአቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የምርምር ስራዎችን በማካሄድ ለሳይንሳዊ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

3. ፈተናዎችና የወደፊት ተስፋ

እንደ ማንኛውም ታላቅ የጤና ተቋም፣ አለርት በቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ በሰው ሃይል ልማት እና በዘላቂ ፋይናንስ ረገድ ያሉ ፈተናዎችን እየተቋቋመ ሲሆን፣ በተለይ ለደሃና ለተጋላጭ ማህበረሰቦች ተደራሽ እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። “ማንንም ወደ ኋላ አለማስቀረት” (Leaving No One Behind) የሚለውን ዓለምአቀፋዊ መርህ በተግባር የሚያሳይ ተቋም ነው።

“ጤናማ ማህበረሰብ የጠንካራ ሀገር መሠረት ነው!”

የአለርት ሆስፒታል ጉዞ ከበሽታ መከላከል በላይ ተሻግሮ፣ የሰውን ልጅ ሙሉ ጤና፣ ክብር እና ራስን መቻል ወደ መመለስ አድጓል። ይህን ተቋም መደገፍና ማጠናከር የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው።

#አለርት #ጤና

24/12/2025
24/12/2025

ከሦስተኛ ፎቅ ላይ ወድቃ በገጠማት አደጋ ለ5 ወራት ያህል ከወገቧ በታች መንቀሳቀስ አትችልም ነበር፡፡ አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች

Address

Kolfe Keranyo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ALERT Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category