National Medium Clinic

National Medium Clinic We are ready to serve you !

14/07/2022
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለኢድ አል-አድሐ  በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ!በዓሉ የጤናና የፍቅር እንዲሆን ምኞታችን ነው!
08/07/2022

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለኢድ አል-አድሐ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
በዓሉ የጤናና የፍቅር እንዲሆን ምኞታችን ነው!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ፤እንኳን ለኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም፣የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ።
01/05/2022

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ፤እንኳን ለኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም፣የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ፤ አደረሰን ።
24/04/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ፤ አደረሰን ።

ረመዳን ሙባረክ !
01/04/2022

ረመዳን ሙባረክ !

17/03/2022

ሞቅ ያለ ውሃን መጠጣት አስገራሚ ጠቀሜታዎች
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አብዛኛዎቻችን ከአልጋችን ከተነሳን በኋላ ሰውነታችንን ለማነቃቃት እራሳችንን በትኩስ ቡና ወይም ሻይ ቀኑን እንጀምራለን፡ ውሃ በምንጠጣበት ጊዜም ቀዝቃዛ እንዲሆን እንመርጣለን ነገር ግን በአዩርቬዲክ ህክምና መሰረት ሁሉም ስህተት ናቸው።

በተለይም በጠዋቱ ሞቅ ያለ ውሃን መጠጣት ሰውነታችን የተፈጥሮ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳችን ውስጥ ሊገነባ የሚችል ሜታክቢክ ፈሳሽ በመፍጠር ሰውነታችንን መዳን ይችላል

ሞቅ ያለ ውሃ መጠጣት አፋችን ባይጣፍጠንም ካፌይን እና ሻይ የመሳሰሉትን ለጤንነትዎ በእጅጉ መቀነሱ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።. ለዚህም ስድስት ምክንያቶችን ማስቀመጥ ይቻላል።

1. ጠዋት ላይ አንድ ሞቅ ያለ ኩባያ ዉሃ ከሰውነትዎ ዉስጥ መርዛማ ነገሮችን ለማፅዳት ይረዳል። ውሃ እና ሌሎች ፈሳሾች በሆድዎ ውስጥ ያለውን ምግብ ይሰብራሉ እና የምግብ መፍጫ ስርዓቱ በሂደት ላይ ያስጉዛሉ።

2.በባዶ ሆድ የሞቀ ዉሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትንም ይከላከላል::

3. ተፈጥሯዊ ከፍተኛ ኃይል ያለው የቤት ውስጥ መድሐኒት ተብሎ የሚጠራው የሞቀ ውሃ, ከወር አበባ እና የራስ ምታ ህመምን ለማስታገስ ሊረዳ ይችላል።

4. አንድ ብርጭቆ ሞቃት ውሃን ማለዳ ማለዳ መጀመሪያ ላይ መጠጣት ክብደትን ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም የጨጓራና ትራክት እና ኩላሊት የተሻለ ጤንነት ወይም አገልግሎት እንዲኖረው ይረዳል::

5. የደም ዝውውርን ያሻሽላል፡ ይህም ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ, ደካማ የደም ዝውውርን እና ፍሰትን ያስወግዳል ::

6. ከእድሜ ቀድሞ የሚመጣን እርጅና ያዘገያል። በሰውነታችን ውስጥ መርዛማ ነገሮች መኖራቸው ወደ እርጅና በፍጥነት እንዲያመራ ያረገዋል, ነገር ግን የሞቀ ውሃው ሰውነታችንን ከነዚህ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ለማጽዳት ይረዳል። የቆዳ ሴሎችን በመጠገን የቆዳችንን የመሳብ /elasticity ይጨምራል::

28/02/2022

#የልጆች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

🔷 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የምንለው ከኩላሊት እስከ የውሃ ሽንት ማስወገጃ(urethra) ጫፍ ድረስ የሚከሰተውን የኢንፌክሽን ዓይነት ነው፡፡

🔷 በአብዛኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃው የውሃ ሽንት የሚከማችበት እና ፊኛ በመባል የሚታወቀውን የሽንት ማጠራቀሚያ ክፍል ነው፡፡

** ሴት ልጆች በተፈጥሮ የሽንት ቧንቧቸዉ አጭር በመሆኑ ምክንያት ከወንዶች ይልቅ ተጠቂነታቸው እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

** ያልተገረዙ ወንድ ልጆችም ከፍ ያለ ለሽንት ቧንቧ የመጋለጥ ዕድል አላቸው።

ምክንያቱ ምንድነው❓️

🔘 የልጆች የ ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በበሺታ አምጪ ባክቴርያዎች ሲሆን ረጅም ሰአት ሺንትን መያዝ እና የንፅህና ጉድለት ሊከሰት እንድሁም በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት ይቺላል ይቺላል::

👉 ምልክቶቹ ምንድናቸው❓️

🔺 ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት ስሜት
🔺 ስመጣ ደሞ ትንሽ ትንሽ መሽናት
🔺 በሽንት መሽናት ጊዜ ህመም
🔺 በሽንት መሽናት ጊዜ ማልቀስ
🔺 ትኩሳት
🔺 የሆድ ህመም /ቁርጠት

$ ሕክምናው ምንድነው❓️

✔️ ሕክምናው ሀኪም የሚያዛቸው ፀረ ባክቴርያ መድኃኒቶች (Antibiotics)

✔️ የህመም ማስታገሻዎች እንደ አስፈላጊነቱ ሊታዘዙ ይቺላሉ

👉 መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው ❓️

🔹 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሙሉ በሙሉ መከላከል ባይቻልም ተጋላጭነትን መቀነስ ይቻላል፤ ከነዚህም ዉስጥ፤

# ወላጅ ወይም ልጆች ከሽንት ቤት በኋላ በሶፍት ሲያፀዱ ከፊት(ከብልት) ወደ ኋላ(ፊንጢጣ) መሆን አለበት

🔹 ይህም ዘዴ ሠገራ ላይ ያሉ ባክቴሪያዎች ወደ ሽንት ቧንቧ እንዳይገቡ ያረጋል

#ድርቀት ካለ በ አግባቡ ማከም

#ልጅዎ በቂ ፈሳሽ እንዲወሰድ ያበረታቱት::

#ህፃናት ጨዋታቸዉን ላለማቋረጥ ሽንታቸዉን ይዘዉ ብዙ የመቆየት ባህሪ አላቸው በመሆኑም ቶሎ ቶሎ እንዲሸኑ እና ልምዱን እንዲተዉ ያድርጉ።

#ትምህርት ቤትም ሽንታቸውን እንዲሽኑ በቂ ጊዜ መስጠት

#ከሰዉነታቸዉ በጣም የሚጣበቁ እንደ ስኪኒ ጂንስ ያሉትን አያልብሷቸዉ።

21/02/2022

☑️ ሳንባ ምች እንዴት ይከሰታል?

የሳንባ ምች በባክቴሪያ እና በቫይረስ አማካይነት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ በፈንገስ እና የኬሚካል ሽታ በሚበዛበት ቦታ የሚሰሩ ሰዎች ላይም በሽታው ሊከሰት ይችላል፡፡

በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ የደከመ የስኳር ፣የኤች አይ ቪ እና የካንሰር በሽተኞችንም በብዛት ያጠቃል፡፡ የተበከለ አየር ወደሰዎች የመተንፈሻ አካል በሚገባበት ሰዓት በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ኢንፌክሽን በመፍጠር ለሳንባ ምች ያጋልጣል፡፡

የሳንባ ምች በሽታን በተመለከተ ጠቅላላ ሀኪም አደራው ካሳሁን ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተውናል፡፡ ጉንፋን ቶሎ ቶሎ የሚያጠቃቸው ፣የአስም በሽተኞች ፣ሲጋራ የሚያጨሱ እና አልኮል አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡

የሳንባ ምች በሽታ ዕድሜያቸዉ ከአምስት ዓመት በታች እና ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን በብዛት ያጠቃል፡፡

☑️ የሳንባ ምች በሽታ ምልክቶች

🔹 ከሶስት እስከ አምስት ቀን አክታ የቀላቀለ ሳል መሳል፣
🔹 የሰውነት ትኩሳት መጨመር ፣
🔹 ትንፋሽ ማጠር፣
🔹 የራስ ምታት ስሜት መኖር፣
🔹 ብርድ ብርድ ማለት፣
🔹 በሳል ወቅት የደረት ውጋት መባባስ፣
🔹 ላብ ላብ ማለት፣
🔹 የልብ ምት መጨመር፣
🔹 የሰውነት ድካም መኖር፣
🔹 የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣
🔹 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ናቸው፡፡

☑️ የሳንባ ምች በሽተኛ ማድረግ ያለበት ነገር

በተገቢው መንገድ በባለሙያ የታዘዘውን መድሃኒት መውሰድ፡፡ በቂ እረፍት ማድረግ፣ አልኮል አለመጠጣት፣ አለማጨስ፣ ጉንፋን የሳንባ ምችን የመቀስቀስ ባህሪ ስላለው ተገቢውን ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

☑️ በሽታውን ለመከላከል መደረግ ያለበት

ተገቢውን የአመጋገብ ስርአት በመከተል መመገብ፣ የሚሰጡ ክትባቶችን ተቆጣጥሮ ማስከተብ፣ የግል እና የአካባቢን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ፣ ሳል እንደተከሰተ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እና ተገቢውን ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

Address

Shegole In Front Of Anbesa Garage
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when National Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram