ሲና የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Sina home based health care service

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ሲና የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Sina home based health care service

ሲና የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት  Sina home based health care service Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሲና የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Sina home based health care service, Medical and health, አዲስ አበባ, Addis Ababa.

12/03/2026

እስትሮክ (stroke) ምንድን ነዉ?

💥እስትሮክ የሚፈጠረው ወደ አንጎል የሚሄደው የደም ፍሰት ሲቀንስ ወይም ሲቋረጥና በዚያ ምክንያት ኦክስጂን (oxygen) እና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ወደዛ የአንጎል ክፍል መሄድ ሲያቅታቸውና የአንጎል ክፍል ደግሞ ሲሞት ማለት ነው

💥እስትሮክ (stroke) በሁለት ይከፈላል
1 እስኬሚክ ( Ischemic)
2 ሔሞሮጂክ(Hemorrhgic)

💥እስኬሚክ (Ischemic) የምንለው ወደ አንጎላችን የሚሔደው የደም ፍሰት በረጋ ደም ወይም በስብ ክምችት ሲዘጋ ማለት ነው

ይህም ሊከሰት የሚችሉባቸው ምክንያቶች ከፍተኛ የደም ግፊት, ማጨስ,የልብ ህመም የመሳሰሉት ሲሆኑ

💥ሔሞሮጂክ( hemorrhagic) የምንለው ደግሞ በአንጎላችን ውስጥ የሚገኝ የደም ስር ሲፈነዳ ማለት ነው

ሊያስከስቱ የሚችሉት ምክንያቶች ውስጥ
💥አንደኛውና ዋነኛው ከፍተኛ የሆነ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የደም ግፊት ሲኖር
💥አኖርዝም (Aneurysm) የምንለው የደም ስር ችግር ሲኖር
💥በአደጋ ጊዜ ጭንቅላታችን በተለያዩ ምክንያቶች ተጋጭቶ በጭንቅላት ውስጥ ደም ሲፈስ

የእስትሮክ ዋነኛ ምልክቶች
💥 ፊት በአንድ በኩል እኩል አለመሆን(face drop)
💥የእጅ ወይም የእግር በአንድ በኩል መዛልና አለመታዘዝ
💥ለመናገር መቸገር
💥ከፍተኛ የራስ ምታት, የሰውነት ክብደትን አለመቆጣጠር እንዲሁም የእይታ ችግር ሊሆኑ ይችላሉ

እንግዲህ ይህንን ሁሉ ካልን እስትሮክ (stroke)በድንገት የሚፈጠር ሲሆን ባፋጣኝ እርዳታ ከተደረገለት መዳን ሒደቱ ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል
ታዲያ እንዴት ልንከላከለው እንችላለን ካልን:
💥የደም ግፊት ካለ
💥የስኳር በሽታ ካለ
💥ኮልስትሮል ካለ እነዚህን በአግባቡ መቆጣጠር እና በደንብ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል

ሌላው ደግሞ አመጋገብን ማስተካከል እንቅስቃሴ ማድረግ
ከተለያዩ ሱሶችና መጠጦች ,ሲጋራና የመሳሰሉት መቆጠብ

💥ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ሲስተዋሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ችግሩ ሳይባባስ መፍትሔ ለማግኘት ዋነኛና ተመራጭ ነው

10/03/2026

ማይግሬን(Migraine)የራስ ምታት ህመም

ማይግሬን በአብዛኛው ጊዜ በአንድ በኩል ከፍሎ የሚይዝ የራስ ምታት አይነት ሲሆን ይህም ከ4 እስከ 72 ሰአት ሊቆይ ይችላል

ማይግሬን ራስምታት በአንድ ሰው በህይወት ዘመኑ የሚቆይ ግልጽ ምክንያት የሌለው በሽታ ነው

ማይግሬን ሙሉ በሙሉ አይድንም ነገር ግን የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል እና የጤና ተቋም ክትትል በማድረግ ማይግሬንን ለመቆጣጠር ይቻላል

ማይግሬን ያለባቸው ሰዎች የሚያሳዩት ምልክቶች ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት: ማቅለሽለሽ :ማስመለስ :የአይን ብዥታ የእጅና የእግር መዛል ድባቴና ቁጣቁጣ ማለት ናቸው

ማይግሬን የሚባያባብሱ ነገሮች
👉ከልክ ያለፈ ጭንቀት እንቅልፍ ማብዛትና ማጣት
👉ከፍተኛ የሆነ ድምጽ ወይም ጩኸት ያለበት ቦታ መሆን
👉እንደ አልኮል: ሻይ: ቡናና ኮካኮላ በብዛት መውሰድ
👉በሆርሞናል ለውጦች (hormonal change)
👉በወር አበባ ጊዜ
👉በእርግዝና ጊዜ
👉 አድካሚ ስራ ከነበረ
👉መስኮቶች ስር ቁጭ ተብሎ የሚሰሩ ከሆነ ከፍተኛ የአየር ግፊት ከነካን
👉ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም በቤተሰብ ያለበት ሰው ካለ ሊከሰት ይችላል

መፍትሔው
🌴የራስ ምታት ማስታገሻዎች መውሰድ (paractamol,Ibuprofine)
🌴ህመም ከሚያባብሱ ነገሮች ራስን መጠበቅ
🌴ጸጥ ባለና ጨለማ ቦታዎች መቀመጥ
🌴አንገትና ግንባርን በሙቅ/በቀዝቃዛ በተነከረ ፎጣ መጠቅለል
🌴የራስ ጭንቅላትን ማሳጅ ማድረግ
🌴መድሀኒቶችን ሳያበዙና ሳያቋርጡ በትክክል መውሰድ
🌴ማይግሬን ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች መቆጠብ
🌴ጤናማ የሆነ የእለት ተለት የአኗኗር ዘዴና አመጋገብ ማዳበር

10/03/2026

Address

አዲስ አበባ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሲና የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት Sina home based health care service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share