Doc Book

Doc Book � Writer only

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 15/ 2018 Marburg Virus Disease Daily update Ethiopia November 24/ 2025
24/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 15/ 2018
Marburg Virus Disease Daily update
Ethiopia
November 24/ 2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 13/ 2018 Marburg Virus Disease Daily update Ethiopia November 22/ 2025  Dr Mekdes Daba, Mini...
22/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 13/ 2018
Marburg Virus Disease Daily update
Ethiopia
November 22/ 2025



Dr Mekdes Daba, Minister of Health

Zewditu Memorial Hospital
Fedila Biya

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 12/2018 ዓ.ምበዛሬዉ እለት 2 ተጨማሪ ሰወች በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ተረጋግጧል Keep in safe sideDr Mekdes Daba, Minister...
21/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 12/2018 ዓ.ም

በዛሬዉ እለት 2 ተጨማሪ ሰወች በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ተረጋግጧል

Keep in safe side

Dr Mekdes Daba, Minister of Health

 ዛሬ 5 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰው በማርበርግ ቫይረስ መያዙ ተገለጸ።የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 2 ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል።በዛ...
20/11/2025



ዛሬ 5 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰው በማርበርግ ቫይረስ መያዙ ተገለጸ።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 2 ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል።

በዛሬው ዕለት 5 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተካሄደ ሲሆን፥ 2 ሰው በቫይረሱ መያዙንና 3 ሰዎች ደግሞ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል።

በሽታው መከሰቱ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስካሁን 33 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን ቫንረሱ በ6 ሰዎች ላይ መገኘቱ በላብራቶሪ ተረጋግጧል።

የጤና ሚኒስትሯ አሁን ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠው ሦስት ሰዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተገለጸ ሦስት ተጠርጣሪዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 10/ 2018 Marburg Virus Disease Daily Update Ethiopia November 19/ 2025
19/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 10/ 2018
Marburg Virus Disease Daily Update
Ethiopia
November 19/ 2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 9 ቀን 2018ዓ.ምMarburg Virus Disease Daily update
18/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 9 ቀን 2018ዓ.ም

Marburg Virus Disease Daily update

Health literacy unit
15/11/2025

Health literacy unit

" የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል " - ጤና ሚኒስቴር የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral ...
14/11/2025

" የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል " - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መከሰቱን እና የበሽታዉን ምንነት በማረጋገጥ ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡

ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል ብሏል።

የዘረመል ምርመራው የተከናወነው በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሄራዊ ሪፈረንስ ላብራቶሪ ነው።

መግለጫው "በዚህም የዘረመል ምርመራ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘዉ ቫይረስ ሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ላይ ከዚህ በፊት ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለዉ መሆኑ ታዉቋል" ነው ያለው።

በተጨማሪም በዛሬው እለትም አዲስ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ወይም በቫይረሱ የተጠረጠረ ሰው ያልተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ ያሳወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ከልሉ በመላከ በሽታዉን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብሏል።

ከነዚህም ውስጥ :-

° የማህበረሰብ አቀፍ የቅኝት ስራዎች፣

° በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለይቶ ማከም፣

° የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና ከተጠረጠሩ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተገልጿል።

በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (Incident Management System) ተቋሞ የፈጣን ምላሽ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ይገኛል ተብሏል።

ጤና ሚኒስቴር:-

➢ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚተላለፉ መረጃዎችንና የጥንቃቄ መልዕክቶችን መከታተልና መተግበር፣

➢ የበሽታው ምልከት የሆኑትን በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልከት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣

➢ ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ግዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣

➢ ሁልጊዜ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

ማንኛውም ጤና ተቋም ለታካሚዎች ልየታ ልዩ ትኩርት በመስጠት የማርበርግ በሽታ (Marburg viral disease) መሰል በሸታ መለየት፣ ማከም እና በአፋጣኝ ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግም በመግለጫው ጠቁሟል።

ለሚመመለከታችሁ ሁሉ
13/11/2025

ለሚመመለከታችሁ ሁሉ

  (Hemorrhagic Fever) ምን ያህል  #ያውቃሉ?  (Hemorrhagic Fever) የሚባለው በሽታ በቫይረስ የሚመጣ ከባድ እና አንዳንዴም ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታ ነው።እነዚህ በ...
13/11/2025

(Hemorrhagic Fever) ምን ያህል #ያውቃሉ?

(Hemorrhagic Fever) የሚባለው በሽታ በቫይረስ የሚመጣ ከባድ እና አንዳንዴም ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታ ነው።

እነዚህ በሽታዎች በሰውነት ውስጥ የደም መርጋት ስርዓት ላይ ተፅዕኖ በማሳደር እና የደም ሥሮችን በመጉዳት ይታወቃሉ፤ በዚህም ምክንያት የውስጥ ደም መፍሰስ (hemorrhage) ያስከትላሉ።

#ዋና ዋና የሄሞራጂክ ፊቨር #አይነቶች

በርካታ የተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ሄሞራጂክ ፊቨር ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል በዓለም ላይ በብዛት የሚታወቁት የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

#ኤቦላ (Ebola)
#ማርበርግ (Marburg)
#ላሳ ፊቨር (Lassa Fever)
#የክራይሚያ-ኮንጎ ሄሞራጂክ ፊቨር (Crimean-Congo Hemorrhagic Fever - CCHFV)
#ዴንጊ ሄሞራጂክ ፊቨር (Dengue Hemorrhagic Fever)
#ቢጫ ወባ (Yellow Fever)

የተለመዱ #ምልክቶች

ምልክቶቹ በቫይረሱ አይነት ይለያያሉ፣ ግን በአጠቃላይ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-

#ድንገተኛ ትኩሳት (Severe Fever)
#ከፍተኛ የሰውነት እና የጡንቻ ህመም (Body Aches and Muscle Pain)
#ድካም (Fatigue)
#ራስ ምታት (Headache)
#ማስታወክ እና ተቅማጥ (Vomiting and Diarrhea)
#የሆድ ህመም (Abdominal Pain)
ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ደግሞ : ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን፣ ከቆዳ ስር የሚወጣ ደም፣ ወይም በሽንት/ሰገራ ውስጥ ደም መታየት።

?

በሽታው የሚተላለፍበት መንገድ በቫይረሱ አይነት ይወሰናል፡-

በተሸካሚ #እንስሳት: እንደ አይጦች፣ የሌሊት ወፎች ወይም ትንኞች (ለምሳሌ ላሳ ፊቨር ከአይጥ፣ ቢጫ ወባ እና ዴንጊ ከትንኝ)።
ከሰው ወደ ሰው: በሽታው ካለበት ሰው ጋር ፣ በተለይም በደም፣ በሰውነት ፈሳሾች (እንደ ምራቅ፣ ሽንት፣ ሰገራ፣ ማስታወክ) ወይም በተበከሉ መርፌዎች።

#ህክምና

ለአብዛኛዎቹ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታዎች የተለየ እና ፈዋሽ የሆነ መድኃኒት የለም። ህክምናው ብዙውን ጊዜ ደጋፊ እንክብካቤ (Supportive Care) መስጠት ላይ ያተኩራል፡-

1. የሰውነት ፈሳሾችን ማካካስ (Rehydration).
2. የደም ግፊትን ማረጋጋት
3. የደም መርጋት ወይም ደም መፍሰስን መቆጣጠር
4. ለአንዳንድ ቫይረሶች (እንደ ኤቦላ እና ላሳ) ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ።

Hakim Mereja ሀኪም መረጃ

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
12/11/2025

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doc Book posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Doc Book:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category