የጠቢባን ዓለም

የጠቢባን ዓለም Welcome

09/10/2022

እውቁ ቻይናዊ ፈላስፋ ኮንፊሽየስ እንዲህ ይለናል...

" ጥበብን ከተግባር መማር ጥሩ ነው። ነገር ግን ረጅምና መራራ ነው። ጥበብን ከሰው በመኮረጅም መማር ይቻላል። ነገር ግን ቀላልና ርካሽ ነው። ጥበብን በልቦና መርምሮ መማር ከባድ ነው። ነገር ግን ከዘዴዎች ሁሉ እጅግ የተከበረው ዘዴ ነው። "
/ ኮንፊሽየስ /

በኔ አረዳድ...
ልቦናውን መመርመር ያልቻለ ሰው ወይ ልቦናውን ደፍኖ ከተግባር መማርን ይመርጣል በዛም ረጅም እና መራራ ትግልን እና ትምህርትን ይጎነጫል አልያም በመኮረጅ እራሱን ለማስተማር ይሞክራል ግን ዘወትር ተከታይ ብቻ ይሆናል አልያም የሚከተላቸው በቀደዱለት ቦይ ብቻ የሚፈስ ውሃ ይሆናል።

25/08/2022

#ከሱፊዝም መንደር
ሩሚ
"መምህር ሆይ! ፍቅርን ፈልጎ ለማግኜት መንገዱን
ይምሩኝ ይላቸዋል። ሩሚም "የአንተ ድርሻ ፍቅርን መፈለግ አይደለም ነገር ግን ከእሱ ጋር እንዳትገናኝ ያገደህንና በልብህ
የገነባኸውን የጥላቻ ግንብ ማፍረስ ነው " ። ለሩሚ ፍቅር
ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታ በመሆኑም ይህንን ስጦታ የምናገኝበት ቀላሉ መንገድ ሰጭውን አጥብቆ መፈለግ ነው። ለዚህም ሩሚ ሲናገሩ፦ በፈጣሪ ብርሀን ፍቅር አገኜሁ፤
ከእሱም ውበት ቅኔን ተቀኜሁ፤ የሰው ልጅ ዓይኖች ሊያዩህ በማይቸሉት ልቤ ውስጥ ሆነህም ዘወትር አሸበሽባለሁ፤ እናም አንዳንዴ በአንተ ታጅቤ ስወዛወዝ ሰዎች ይመለከታሉ
ይህንን ደግሞ ጥበብ በማለት ይጠሩታል ሱፊው ሩሚ አንድ ወዳጃቸው ቤት ተጋብዘው እጅግ ደስ የሚል የፍቅር ታሪክ ሰምተው ሲጨርሱ ጋባዣቸው፦ "ፍቅር በእርግጥም እውር ነው፤ ሰዎችን ባልጠበቁት ስፍራ ወስዶ ያገናኛቸዋል" አለ። ሩሚ ግን እንዲህ በማለት አስተካከሉት፦ "ፍቅረኞች በመጨረሻ የሚገናኙበት ስፍራ የሚባል ነገር የለም፤ አስቀድሞ አንዳቸው በሌላው ውስጥ ነበሩና "። በመጨረሻም የምትገርመኝን ሀሳብ ልጨምር
"
"ጠያቂ ፡ እግዚአብሔርን ትውጂዋለሽ?
መልስ፡ አዎ እወደዋለሁ ።
ጠያቂ ፡ ሴጣንንስ ትጠይዋለሽ?
መልስ፡ አልጠላውም፤
ጠያቂ ፡ እንዴ ለምን?
መልስ ፡ እግዜብሄርን 24 ሰዓት ሙሉ ከወደድኩት ሴጣንን
የምጠላበት ጊዜ የለኝም ።"
#ጥላቻችን የበዛው መዋደዳችንን ቀንሰን ነውና ጥላቻችንን ያጥፋልን ሳይሆን መዋደዳችንን ይጨምርልን ።
አንድ ቀን የሱፊው መምህር ቢያዚድ ቢስታሚን አንድ ሰው በዱላ ይመታቸውና ዱላው ይሰበራል ። መምህሩ ግን ሌላ አዲስ ዱላ ያነሱና ማር ከሞላው ስልቻ ጋር ለመታቸው ሰው ይሰጣሉ ።
መምህሩ ይህን ሲያደርጉ ለሠውዬው እንዲህ አሉ ፦ " በዱላው ጨንቅላቴን በመምታትህ ዱላው ተሠበረ ፤ ለዚህም በተሰበረው ዱላ ምትክ አዲስ ዱላ እነሆ ፣ ለወደፊቱም ስትማታ ኃይልና ጉልበት ይሰጥህ ዘንድ ደግሞ ማር አቀረብኩልህ ። ማንም በስጦታው ተደስቶ ነገር ግን ስጦታውን የሰጠውን ሰው የማይመለከት (ከሱ የማይማር) እሱ ለስጦታው እንጂ ለሰጪው ግድ የሌለው ነው ። "
"አንድ ሰው እጅግ የተዋበና ውድ የሆነ ባርኔጣ ቢሰጥህ በስጦታው ደስ አይልህምን? ነገር ግን ከባርኔጣው ይልቅ እሱን የምታስቀምጥበትን ጭንቅላት በሰጠህ ፈጣሪ ደስ ይበልህ "
" አሉ ጥበበኛው የሱፊ መምህር

https://t.me/ABmedia_tube

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

22/08/2022

ሰንበትን እረፉ የተባለው በምክንያት ነው ። የስራችን ሁኔታ እንኳን ባይፈቅድ ትንሽም ቢሆን የእረፍት ጊዜ ማግኘት በጣም ወሳኝ ነገር ነው ። የሰራነውን የምንገመግምበት ፣ የቤተሰብ ጊዜ የምናሳልፍበት ፣ ራሳችንን ዘና የምናረግበት ፣ ለተቸገሩ የምንረዳበት መልካም ስራ የምንሠራበት ቀን ለህይወታችን ትክክለኛ ጣዕም ይሰጠናል ።

ምርጥ እሁድ ተመኘን🙏

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

22/08/2022

ላኦ ዙ (Laozi) ማን ነው? ቁጥር_2

"ከማጣት ብዙ ይገኛል፤ ከማግኘት ብዙ ይታጣል፡፡"

"ሀያልነት የፈለገውን ያህል ምክንያታዊ ቢሆንም፣ አጥቂውን መልሶ ማጥቃቱ አይቀርም፡፡"

"ሁሉም ወንዞች ከተራሮች ፈልቀው ወደ ባህር የሚፈሱት፣ ባህሩ ዝቅ ብሎ ስለሚገኝ ነው።"

"ዳዋው መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ ነው፡፡"

"ታላቁ ዳዋ ወደ ሁሉም ይፈሳል፣ ሁሉም ነገሮች ከእርሱ የተፈጠሩ ናቸው፤ ይሁን እንጂ አልወለዳቸውም፡፡"

"ዳዋውን ማእከል ያደረገች፣ ወደ ፈለገችው ቦታ ያለስጋት ትሄዳለች፡፡"
"ዳዋው መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ ነው፡፡"
"ታላቁ ዳዋ ወደ ሁሉም ይፈሳል፣ ሁሉም ነገሮች ከእርሱ የተፈጠሩ ናቸው፤ ይሁን እንጂ አልወለዳቸውም፡፡"

"ዳዋውን ማእከል ያደረገች፣ ወደ ፈለገችው ቦታ ያለስጋት ትሄዳለች፡፡"
"የሰው ልጅ በአምላኩ ስራ ጣልቃ ይገባል፣ ሰማይ ይቆሽሻል፣ መሬት ሀብቷ
ያልቃል፣ ሚዛኑ ይዛባል፣ ፍጥረታትም ይጠፋሉ፡፡"

"የጦር መሳሪያዎች በበዙ ቁጥር፣ የሰዎች ደህንነት ስጋት ላይ ይወድቃል፣
ለዜጎች ብዙ ድጋፍ ባደረግህ ቁጥር የሰዎችን ራስ የመቻል ጉዞ ይቀንሳል።"

"አንዲት ሀገር ትልቅ ሀይል ሲኖራት እንደ ባህር ትሆናለች፣ ሁሉም ወንዞች ወደ እርሷ ይፈሳሉ።"

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

22/08/2022

ላኦ ዙ (Laozi) ማን ነው? ቁጥር_1

ከመጀመሪያዎቹ የቻይናውያን ፈላስፎች አንዱ፣ የታኦይዝም ትምህርቶች መሥራች ላኦ ዙ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ በቁሳዊ ቅንጣቶች ላይ የተመሰረቱ የሚታዩ የተፈጥሮ ክስተቶች የእርሱ አስተምህሮ መሰረቶች ናቸው፡፡ እንደተገለጸው፣ ላኦ ዙ የቻይና ጥንታዊ ፈላስፋ እና የታኦይዝም መስራች አባት ነው፡፡ “ላኦ ዙ” የሚለው ቃል የእንግሊዝኛ ትርጉም ጥንታዊ ፈላስፋ እንደማለት ነው፡፡ "የጥንቱ ሕፃን" ተብሎም የሚታወቅ እንደሆነ ተጽፏል። በጥልቅ ጥበቡና በታዋቂ ተጫዋችነቱ በታኦኢስት የቻይና ነገስታት ዘንድ በሰፊው ይታወቃል፡፡

ስለ ላኦ ዙ ታሪካዊ ሕይወት እምብዛም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የሚታውቀው ነገር ቢኖር፣ ትክክለኛ ስሙ ሊ ኸር ሲሆን፣ በደቡባዊው የዙፋን ዘውድ ቤተሰብ ውስጥ የተወለደ መሆኑ ነው፡፡ በእድሜ ትልቅ ሰው በነበረበት ጊዜ፣ በመንግሥታዊው ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ የቤተ-መጻህፍት ባለሙያ በመሆን ከማገልገሉ በተጨማሪ አነስተኛ የመንግስት ቦታን ይዞ እንደነበር ተጽፏል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ በቻይና ንጉሳዊ አገዛዝ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ፣ የታኦይዝም ፍልስፍና አንደኛው መንገድ፣ ሀገርን ማስተዳደር ጥበብ ላይ የተመሠረተ ነው። ከሰራቸው ታዋቂ የጥበብ ስራዎች መካከል፤ ግዛትን ለማስተዳደር የተገለጹ አራቱ ጥበቦችንና መንገዶችን የተመለከቱ ነበሩ። እነሱም፣ የንጉሠ ነገሥት መንገድ፣ የንጉሠ ነገሥታዊ መንገድ፣ የንጉሳዊ መንገድ እና የሄግሜኒንግ መንገድ የተሰኙት እንደሆነ ተዘግቧል።

በማሰላሰል ላይ የተመረኮዘ፣ ሙሉ በመሉ ኦፊሴላዊ ያልሆነ ዶክትሪን የሚያስተምረው ላኦ ዙ፣ በዘመናዊው አነጋገር ምስጢራዊ እና ጸጥተኛ መሆንን የሚያስተምር አስተሳሰብ እንደነበረው አሁን ካሉ የጽሑፍ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል። “ሰው በራሱ ውስጥ ካሉ ውሸቶች ሁሉ ራሱን በማውጣት እውነትን ያገኛል” የሚለው አስተሳሰቡ የሚታወቅበት አስተሳሰቡ ነው:: ላኦዙ በአስተምህሮው እንዲህ ሲል ተናግሯል “ከሰማይና ከምድር በፊት የነበረ ማለቂያ የሌለው ፍጡር አለ፡፡ እንዴት የማይደፈር፣ እንዴት የተረጋጋ! እሱ ብቻውን የሚኖር እና የማይለወጥ ነው። ሁሉንም ነገር ያንቀሳቅሳል፣ ግን አይጨነቅም። እንደ ሁለንተናዊ እናት ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ስሙን አላውቅም፡፡ ታኦ ብዬ እጠራዋለሁ” በማለት አስተምሯል፡፡

የፍልስፍና እሳቤዎቹ

"እኔን ማወቅ ከፈለግህ፣ በልብህ ውስጥ አንተነትህን ተመልከት።"

"አንድ ሀገር በጥበብ ከተመራች ኗሪዎቿ ባላቸው የረኩ ይሆናሉ፡፡ "

"የሰውን ልጅ ለመረዳት አለምን ተረዳ፣ አለምን ለመረዳት ደግሞ ሰማየ ሰማያትን እወቅ።"

"ሙሉ ለመሆን ከፈለግህ ጎደሎ ለመሆን ፍቀድ፣ ቀጥ ያለ ለመሆን ካሻህ ጎባጣ ለመሆን ፍቀድ፣ እንዳትጠግብ ከፈለግህ ለመራብ ፍቀድ፣ ለመወለድ ከፈለግህ ለመሞት ፍቀድ፣ እንዲሰጥህ ከፈለግህ ያለህን ስጥ።"

"አብረቅርቆ ለመታየት የሚሞክር የራሱን ብርሀን ያደበዝዛል፣ ለራሱ የማይገባውን ክብር የሚሰጥ እውነተኛ ማንነቱን ያጣል፡፡"

"ሁሉም ነገር የተገኘው ከመሆን ነው፣ መሆን እራሱ የተገኘው ደግሞ ካለመሆን ነው፡፡"

"ጥሩ ተጓዥ የተወሰነ መድረሻ የለውም፣ ጥሩ አርቲስት ምእናቡ ወደ ወሰደው ይሄዳል፤ ጥሩ ሳይንቲስት አእምሮውን ለሆነውና ለሚሆነው ሁሉ ክፍት ያደርጋል፡፡"

"መደበኛ ህልሞችህንና ከንቱ ሀሳቦችህን ተዋቸው፣ አለም ራሷን ታስተዳድራለችና፡፡"

"ህጉን ስትተወው ሰዎች ሀቀኛ መሆን ይጀምራሉ፣ ምጣኔ ሀብትን ስትተወው ሰዎች ሀብታም መሆን ይጀምራሉ፣ ሀይማኖትን ስትተወው ሰዎች በመንፈስ መርካት ይጀምራሉ፡፡"

"ሁሉም ነገር እንደሚለወጥ ከተረዳህ፣ እንዲኖር የምትፈልገው ነገር አይኖርም።"

"ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ሲጋጩ አሸናፊነት የምትሄደው መረታትን ወደተቀበለው ጎራ ነው።"

"እውነተኛ ቃላት ማራኪ አይደሉም፣ ማራኪ ቃላትም እውነተኛ አይደሉም።"

"አለም ብጽእት ናት፣ ልትሻሻል አትችልም፤ ከነካሃት ታወድማታለህ፣ እንደ እቃ ከቆጠርሀት ታጠፋታለህ።"
:
:
:
ቁ. 2 ይቀጥላል።

22/08/2022

ቆራጥ ሁን!

የትም አያደርስህም እንጂ የስሜትህ ባሪያ መሆን ቀላል ነው፤ ጊዜያዊ ደስታ የሚሰጡህን ነገሮች በጥበብ እለፋቸው፤ ለእውነተኛ ደስታህ ስትል አሁን የማይጠቅሙህን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ሁኔታዎች፣ ቦታዎች ሁሉ ከህይወትህ አውጣቸው!

የተመረዘ እጅ ወይም እግር የሚቆረጠው ባለቤቱ ስለማያስፈልገው አይደለም ግን ሌሎቹን የሰውነት ክፍሎች ስለሚመርዝ ነው፤ ስኬትና ደስታ መስዋዕትነት ይጠይቃል! ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ ቆራጥ ሁን!

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

22/08/2022

ራስን መገምገም!

ፈጣሪ በህይወት ዘመናችን ሙሉ ልንጠቀመበት ከምንችል በላይ ድንቅ አቅምና ስጦታ ሰጥቶናል፣ ይህ የፈጣሪ ስጦታ ለኛ ነው፡፡ ፈጣሪ ልንሰጠውም ባንችል አንዱ ልናመሰግንበት ከምንችልበት መንገድ የተሰጠን አቅምና ችሎታ በህይወት ዘመናችን እስከምንችለው ድረስ መጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ የተሰጠን ድንቅ አቅምና ችሎታ እንዴት እየተጠቀምንበት እንዳለን ራሳችን እንፈትሽ፡፡ ልክ እንደኛ የሆኑ የሰው ልጆች በዉስጣችን ያለ ድንቅ አቅም በመጠቀም ብዙ ተዓምር ሰርተዋል፡፡ እኛስ ይህ እፁብ ድንቅ የሆነ አቅማችን በመጠቀም ምን እየፈጠርን፣ ምን እየሰራንና ምን ዓይነት ህይወት እየኖርን ነው የምንገኘው?

አሁን የምንፈትሸው ድንቅ አቅማችንን አይደለም ምክንያቱም በአቅምና በአፈጣጠራችን ደረጃ ሁላችንም የሰው ልጆች ድንቅ ነን፡፡ አሁን የምንፍተሸው በህይወታችን በምን ያክል ፈተና እና ችግር እየተፈተንን እንዳለንም አይደለም። ምክንያቱም ድንቅ ሰዎች በየትኛውም አይነት ፈተና ወይም መከራ ውስጥ ቢገቡም ሁሌ የሚያሸኑፈበት መንገድ በመፈለግና በማሸነፍ ነው የሚታወቁት፡፡

ድንቅ የሆነ አቅማችንን በመጠቀም ምን እየሰራን፣ ምን እየፈጠርን፣ ምን እያሻሻልን እንገኛለን? አሁን የምንኖረዉ ያለን ህይወት፤ የምናገኘዉ ገቢ፤ የምናደረገው እንቅስቃሴ፤ የምንፈጥረው መፍትሄ፤ በህይወታችን የምናፈራው ያለን ውጤት ስንፈትሽ ድንቅ አቅማችንን የምንጠቀመበት መንገድ ድንቅ ነዉ ወይስ ተራ? እባክዎ አንዴ ረጋ ብለዉ ድንቅ አቅሞትን የሚጠቀሙበት ደረጃ የት እንደሆነ እራሷን ይፈትሹ፡፡

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

አብዝቶ መቀመጥ ለአእምሯችን ለምንድነው አደገኛ የሚሆነው?በብዙ የህይወት መንገዶች አእምሯችንን መጠቀም በምንፈልግበት ቦታ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በፈተና እና በተለያዩ ቦታዎች መቀመጥን...
22/08/2022

አብዝቶ መቀመጥ ለአእምሯችን ለምንድነው አደገኛ የሚሆነው?

በብዙ የህይወት መንገዶች አእምሯችንን መጠቀም በምንፈልግበት ቦታ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በፈተና እና በተለያዩ ቦታዎች መቀመጥን እናዘወትራለን፡፡ በአንድ ወቅት በወጣ ጥናት ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የአእምሮ ነዳጅ (brain’s fuel) አቅርቦት ላይ ተጽኖ ከማሳደር ባሻገር በአእምሮም ጤና ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡

አእምሯችን ጉሉኮስ የተራበ አካል ነው፡፡ ምንም አንኳ የሰውነታችንን ክብደት 2% ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም 20% የኛን ሀይል/ኢነርጂ የሚጠቀመው እርሱ ነው፡፡

ይህ ሀይል ደግሞ በአብዛኛው የመጀመሪ ደረጃ የአዕምሮ ነዳጅ በሆነው ጉሉኮስ መልክ የሚገኝ ነው፡፡ የዚህ ሀይል ስርጭት ከተቋረጠ የአዕምሯችንን ሴሎች ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ የጉሉኮስ በበቂ ደረጃ መኖር ከአይምሮ ጤንነት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡

አይሞሯችን ለከፍተኛ ጉሉኮስ መጠንም ይሁን ለአነሰተኛ ጉሉኮስ መጋለጥ (dementia) ዲሜንሺያ ለተሰኘው ህመም የመጋለጥ አደጋን ይጨምርበታል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በተገቢው መንገድ ጉሉኮስን መቆጣጠር ለአእምሮ ጤና እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡

አብዝቶ መቀመጥ ከሚያመጠው የጤና እክል ውስጥ፡-

• በለጋ ዕድሜ ለሞት የመጋለጥ (early death) አደጋን ከፍ ያደርገወል በግምት 60-75 መጠነኛ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ በቀን ስምንት ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣን በለጋ አድሜ ለሞት የመጋለጥ አደጋን ለማጥፋት ይረዳል፡፡

• አብዝቶ መቀመጥ የጉሉኮስ መጠንን በማዛባት ለአእምሮ ጤና ችግር ያጋልጥል አብዘኛው ጥናቶች መቀመጥ በመቀነስ በተወሰነ መጠን መራመድ ከምግብ በኋላ ጉሉኮስ መጠንን ይቆጣጠራል፡፡

• አብዝቶ መቀመጥ በአእምሯችን የደም ስርጭትን ሊቀንስ ይችላል ከመቀመጥ ይልቅ መራመድ በአእምሯችን የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር ይረዳል፡፡ የአእምሮ የደም ዝውውር ለአእምሮ የሚቀርበውን የጉልኮስ መጠን በመቆጣጠር አእምሮ ጤና ላይ አወንታዊ ተጽኖ ይፈጥራል፡፡ በአእምሮ የደም ዝውውር መቀነስ የአእምሮ ስራ በፍጥነት እንዲቀንስ የማድረግ እና ከመርሳት በሽታ (Alzheimer’s disease) ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡

ስለዚህ ምን እናድርግ ካለችሁ? አብዝቶ መቀመጥ ስለሚያመጣው የአእምሮ ጤና ጉደት ሁሉንም የሚያስማማ አንድ የሆነ ጥናት ባይኖርም አብዝቶ መቀመጥ የጉሉኮስ መቆጣጠር መጠን በመቀነስ የአእምሮ ጤናችን ላይ እክል ስለሚፈጥር

• ከምግብ በኋላ የመቀመጥ መጠናችንን ብንቀንስ መልካም ነው
• ከራት በኋላ በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴ ማድረግ (ለምሳሌ፡- የተበላበትን እቃ በማጠብ ሊሆን ይችላል)
• ጠዋት ወደ ስራ ስንሄድ ወይም ከስራ በኋላ በእግር መጓዝ

የምንቀመጥበትን ሰዓት በመቀነስ የአዕምሯችንም ሆነ የአካላችንን ጤና እናስጠብቅ፡፡

ምንጭ፡- የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ከ the Conversation ጋር በመተባበር።
ከተመቻችሁ ሼር አድርጉ
https://t.me/ABmedia_tube

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

"......መጀመሪያ እራስሽን ውደጂው፣ ከዛ በኋላ ሰውን መውደድ ጀምሪ። ከዚያ አካባቢሽን ሀገርሽን በእራሱ ጊዜ ትወጃለሽ። ችግሩ የሰው ልጅ መጀመሪያ መውደድ የሚጀምረው እራሱን ሳይሆን ሌሎች...
22/08/2022

"......መጀመሪያ እራስሽን ውደጂው፣ ከዛ በኋላ ሰውን መውደድ ጀምሪ። ከዚያ አካባቢሽን ሀገርሽን በእራሱ ጊዜ ትወጃለሽ። ችግሩ የሰው ልጅ መጀመሪያ መውደድ የሚጀምረው እራሱን ሳይሆን ሌሎችን ነው። ከዚያ ባደገ ቁጥር ሰዎችን ጠልቶ እራሱን መውደድ ይጀምራል።
.....እና እንዳልኩሽ አንድ ሰው ሀገር ከመግዛት እራሱን መግዛት ይከብደዋል፣ እራሱን የገዛ ሰው ግን አለምን መግዛት ይችላል። ስለዚህ እራስን መውደድ፣ መግዛት እና ማሸነፍ ከሁሉም ይቀድማል።....."

".......ሁሌም ከማንም እንደማታንሺ አስቢ፣ ለእራስሽ ክብር ስጪ፣ ራስሽን ውደጂ፣ ሁሉንም እችላለው ብለሽ ተነሺ፣ ፈተናዎችን በጥበብ እንደምትወጪ እመኚ፣ አንብቢ፣ ሁሌም ለነገሮች ዝግጁ ሁኚ፣ ያኔ ሁሉም ሰው ያከብርሻል። ሁሉንም ታሸንፊያለሽ፣ ሁሉም ይወድሻል።

ሰነፍ አትሁኚ፣ የሰው ልጅ ውድቀት የሚጀምረው በስንፍናው ነው። ሰነፍ ሰው መጥፎ ነገሮችን ሁሉ በጫንቃው ይሸከማል። ምክንያቱም በስንፍናው ስጋው የሚበላው ያጣልና። ሰው ሰነፍ ከሆነ የሰውን ይመኛል። ሌባ ይሆናል፣ ውሸትን ይናገራል፣ ነውርንም ይፈጽማል። ስለዚህ ብርቱ ሰው መሆን አለብሽ።

አንቺ ማንንም መፍራት እና እንደዚህ ይሉኛል ማለት የለብሽም!! አንቺ በትክክል መልእክትሽን ካስተላለፍሽ ምን ችግር አለው ሰው የፈለገውን ቢል?? ሰውን አክብሪ!!!....."

ከ ''ውብ'' መፅሐፍ የተቀነጨበ፤

https://t.me/ABmedia_tube

🇪🇹ለሌላው ደግ ደጉን እናስብ ኑሮዋችን ደስተኛ ትሆናለችና።🙏

Address

Addis Ababa
103

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጠቢባን ዓለም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category