Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS

Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS, Orthotics & Prosthetics Service, Mikililand Center, Addis Ababa.

ለመላዉ የክሪስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉ የሰላም፣የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት መልካም ም...
26/09/2025

ለመላዉ የክሪስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
መልካም በዓል !

23/09/2025

Ethiopia 🇪🇹 has begun building East Africa’s biggest rehabilitation center in Gefersa, Sheger City, near Addis Ababa.

The state project will merge 17 facilities into one, offering full care for physical, mental, cognitive, and psychological issues, including accident injuries and long-term illnesses.

When complete, it will be the region’s largest rehab center, helping make Ethiopia a leader in recovery services and health tourism.

21/09/2025

እነደ ሀገር የመጀመሪያ የሆነዉ ሀገር አቀፍ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ለአገልግሎት ስበቃ በአለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣዉን የአዕምሮ ህመም በመከላከል ለአዕምሮ ጤና ምቹ ሁነታን መፍጠር የሚችል መሆኑ ተመላከተ።

20/09/2025

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉ ሀገር ሀገር አቀፍ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር

ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተጀመረ************************************************የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የአ...
19/09/2025

ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተጀመረ
************************************************
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ገፈርሳ ሳይት የሚገነባውን የተቀናጀ ማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ታሪኩ ታደሰ እንደገለጹት፤ አገልግሎቱ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎት በመስጠት የአእምሮና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን በተለይም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ተደራሽ በማድረግና ለአእምሮ ጤና ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ ውጤታማ ተግባራትን እንደሚያከናውን ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የማገገሚያ የህክምና አገልግሎት ፕሮጀክት ስራውን ይበልጥ ለማሳለጥ ወሳኝ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የገለፁት ዶክተር ታሪኩ ታደሰ በዘርፉ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ላለፉት አራት አስርት አመታት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ መሆኑንም ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስቴር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ግንባታው መጀመር መንግስት የጤና መሰረተ ልማትን ለማሟላት የጀመረውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ገፈርሳ ሳይት የሚከናወነው ግንባታ በኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ወጪ የሚሸፈን ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው መሆኑን ተመላክቷል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡

የጤና መሰረተ ልማቶችን በማጠናከር የተሟላ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የመከላከል እና አክሞ የማዳን አቅም እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል መገንባቱ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ የማገገሚያ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ገፈርሳ ሳይት የተጀመረው ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ግንባታ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ላይ የሚገነባ ሲሆንጨግንባታው በ17 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን በመግለጽ፤ በተያዘለት ጊዜ መስፈርቱን አሟልቶ ተገንብቶ ስራ እንዲጀምር ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመረሃ- ግብሩ በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገፈርሳ ጉጄ እና ለቡራዩ ክ/ከ ተማሪዎች እንድሁም አነስተኛ ገቢ ላላቸዉ የተቋሙ ሰራተኞች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ የተበረከተ ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ለአዲስ ከተማ ክ/ከ፤ለገፈርሳ ጉጄ እና ለቡራዩ ክ/ከ የአካል ጉዳት ላለባቸዉ የዊልቼርና የክራንች ድጋፍ በማድረግ ከአገልግሎቱ ታካሚዎች ጋር የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታዎች የማዕድ ማጋራት ስነ-ስርዓት ያከናወኑ መሆኑንን ለመረዳት ተችለዋል።

11/09/2025

እንኳን ለ2018 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

BAGA BACAQII GANNAA IRRAA GARA BOOQA BIRRAATTI NAGAAN CEETAN !

መልካም አዲስ ዓመት
AYYAANA GAARII

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት
Tajaajila Deggersa Qaamaa Itoophiyaa

Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል  ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከታካሚዎች  ጋር አከበረ።********************************የኢትዮጵያ የአካ...
09/09/2025

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከታካሚዎች ጋር አከበረ።
********************************
የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ታሪኩ ታደሰ ባደረጉት የእንኳን አደረሳችሁ የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት ተቋሙ በአካልና በአእምሮ ጤና ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና ባጠናቀቅነዉ 2017 ዓ.ም. አመርቂ ዉጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ጠቅሰዉ በቀጣይም የአካባቢዉን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እንደታቀደና አዲሱን ዓመት ስንቀበል ባንድ ጎኑ ለ3000 ዓመታት በሩቅ ስንመኝ የነበረዉን የዕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በማስመረቅ ደስታችንን በጋራ የገለፅንበት ታሪካዊ ቀን ሲሆን በሌላ ጎኑ ደግሞ እንደ ሀገር የመጀመርያ የሆነዉን የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ማስጀመርያ መሰረተ ድንጋይ በገፈርሳ ሳይት የሚናስቀምጥበትና የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጅማሮ እዉን የምናደርግበት ዓመት ላይ የምንገኝ በመሆኑ የዘንድሮ የዘመን መለወጫ በዓል ለየት ያደርገዋል በማለት ተናግረዋል።

ዶ/ር ታሪኩ አያይዘውም መጪው አዲስ ዓመት መፃሂ እድል የሚታይበትና በጤናዉ ዘርፍ የተመዘገቡትን ስከቶች በማላቅና በማጽናት የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚናረጋግጥበት ዓመት መሆኑን አስረድተዉ፤ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የብልግናና የኢትዮጵያን ከፍታ እዉን የምናደርግበት እንድሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ነጋሽ በበኩላቸው አዲሱ ዓመት የአእምሮ ህሙማንን በመንከባከብ በእምሮ ህመም ምክንያት በሰዎች ላይ የሚደርሰውን መገለልና መድሎ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በማስቀረት የሱስ እና የአዕምሮ ህሙማን መደበኛ ህይወታቸዉን እንድመሩና በአዕምሮ የበለጸገ ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የዜጎች ሁሉ አስተዋጽኦ አይተኬ ሚና እንዳለዉ ገልፀዉ ፤አዲሱ ዓመት የጤና፣ የብልጽግና እንዲሆን በመመኘት፤ ይህን ፕሮግራም ለማሳካት ለተረባረቡ አካላት ሁሉ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

በመጨረሻም ክብረ-በዓሉ በፓናል ውይይት፣ በግጥም፣ በሙዚቃዊ ዝግጅቶችና ውዝዋዤ የደመቀ ሲሆን፤የበዓሉ ታዳሚዎችም የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የታካሚ ቤቴሰቦች የበዓሉ ታዳሚዎች መሆናቸዉን ለመረዳት ተችሏል።

ጳጉሜን-4 የማንሰራራት ቀን  “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት” የኢትዮጵያን የማንሠራራት ጅማሮ በዘላቂ የኢትዮጵያ ብልጽግና እናረጋግጣለን፡፡የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት
09/09/2025

ጳጉሜን-4 የማንሰራራት ቀን

“ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት”

የኢትዮጵያን የማንሠራራት ጅማሮ በዘላቂ የኢትዮጵያ ብልጽግና እናረጋግጣለን፡፡

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት

ጳጉሜን 3           የእመርታ ቀን!የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና!የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት
08/09/2025

ጳጉሜን 3
የእመርታ ቀን!
የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና!

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት

ጳጒሜን -2  የኅብር ቀን       ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ እና ዐቅም ነው!       ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የሚትኖር፣ የብዝኃ ተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነ...
07/09/2025

ጳጒሜን -2 የኅብር ቀን

ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ እና ዐቅም ነው!

ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የሚትኖር፣ የብዝኃ ተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነች ድንቅ ሀገር ናት፡፡

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት

ጳጉሜን-1 የጽናት ቀን         "ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር"ኢትዮጵያ መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ብልጽግናዋን ታረጋግጣለች፡፡                  የኢትዮጵያ የአካል ድጋ...
06/09/2025

ጳጉሜን-1 የጽናት ቀን

"ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር"

ኢትዮጵያ መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ብልጽግናዋን ታረጋግጣለች፡፡

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ ሙሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣የፍቅር፣ የመተሳሰብና የኢትዮጵያን የማንሰራራ...
03/09/2025

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ ሙሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣የፍቅር፣ የመተሳሰብና የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጅማሮ የምናረጋገጥበት ዓመት እንድሆንሎ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት
++++++++++++++++++++++++++

Address

Mikililand Center
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram