Aki Speech Therapy

Aki Speech Therapy Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aki Speech Therapy, Alternative & holistic health service, Addis Ababa.

ከተማሪዎቻችን ወላጆች የተሰጠ የምስጋና ምስክር ወረቀትመስከረም 14, 2018 ከተማሪዎቻችን ወላጆች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተቀብለናል። ይህ እውቅና ለምንሰጠው ነፃ የንግግር ሕክምና ልጆቻቸ...
11/10/2025

ከተማሪዎቻችን ወላጆች የተሰጠ የምስጋና ምስክር ወረቀት

መስከረም 14, 2018 ከተማሪዎቻችን ወላጆች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተቀብለናል። ይህ እውቅና ለምንሰጠው ነፃ የንግግር ሕክምና ልጆቻቸው እያመጡ ያለውን አስደናቂ ለውጥ የሚያሳይ እውነተኛና ተጨባጭ ማስረጃ ነው ። በልጆቹ ላይ የምናያቸው አስደናቂ ለውጦች የስኬታችን እውነተኛ መለኪያ ነው።

Deborah Foundation Honored by Parents

September 24, 2025, We were honored to receive a certificate of appreciation given to us by grateful parents of our students. This recognition is for the free speech therapy services we provide, and it's a testament to the incredible progress the children are making. Seeing their progress and the joy on their faces is the greatest reward of all. Thank you to all the parents for trusting us with your children.

👶የእድገት ምዕራፎች ምንድን ናቸው?90% የሚሆን የአንጎል እድገት በ ልጆች የመጀመሪያው 5 አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ያውቃሉ? ወሳኝ የእድገት ምዕራፎችን መረዳት የልጅዎን እድገት በቀላሉ እ...
10/09/2025

👶የእድገት ምዕራፎች ምንድን ናቸው?
90% የሚሆን የአንጎል እድገት በ ልጆች የመጀመሪያው 5 አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ያውቃሉ?
ወሳኝ የእድገት ምዕራፎችን መረዳት የልጅዎን እድገት በቀላሉ እንዲከታተሉ እና ማንኛውንም ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ ምልክቶችን አስቀድመው እንዲለዩ ያግዝዎታል።

💡Tip፡ እንደ እንቅስቃሴ፣ ተግባቦት እና ማህበራዊ ችሎታ ባሉ ዘርፎች የልጅዎን እድገት ለመከታተል በጽሁፍ ያስቀምጡ ወይም ዲጂታል መከታተያ (Tracker) ይጠቀሙ።

🌟ትናንሽ እርምጃዎች ወደ ትልቅ ስኬቶች ይመራሉ!

አኬ የስነ ልሳን(speech therapy clinlic )ደረጃውን ከፍ በማረግ ቁጥር ( 2 ) SPEECH THERAPY CLINLICመክፈቱን በደስታ ይገልፃል  በተጨማሪም የህፃናት መዋያም መክፈ...
05/11/2024

አኬ የስነ ልሳን(speech therapy clinlic )ደረጃውን ከፍ በማረግ ቁጥር ( 2 ) SPEECH THERAPY CLINLIC
መክፈቱን በደስታ ይገልፃል በተጨማሪም የህፃናት መዋያም መክፈታችንን በደስታ እንገልፃለን !!!👏👏👏👏
አድራሻችን:-

-ቁጥር 1 ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ በሚወስደው መንገድ በስተ ግራ በኩል ዳሽን ባንክ ህንፃ ላይ 2ፎቅ ላይ
-ቁጥር 2 24 40/60 ኮንዶሚኒይም ገባ ቡሎ
ስልክ ቁጥር 0903242838/0985365590/0978806778 ይደዉሉ ማንኛዉንም የንግግር ችግሮችን መፍትሄ እንስጣለን የብዙ አመት ልምድ ባላቸው ባለ ሀኪሞች መፍትሄ እንሰጣለን!!!
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፡-
* የህፃናት ማቆያ (ከ6ወር ጀምሮ)
*ማንኛዉም የህፃናት የንግግር ችግር(speech Therapy)
*ማንኛዉም የአዋቂ የንግግር ችግር(speech Therapy)
*የባህሪ ህክምና(ABA Therapy )
*Art Therapy
*ቤት ለቤት speech Therapy
*የአምሮ ህክምና (Psychiatriy )
# የሚሰጥበት ቋንቋ፡-
አማርኛ
ኦሮምኛ
እንግሊዘኛ

በልጆች ላይ የትኩረት ማነስ እና እረፍት የለሽ እንቅሰቃሴ ወይም Attention deficit hyperactive disorder (ADHD) ምንድን ነው? -ADHD ልጆች ላይ በጣም በብዛት የሚ...
03/06/2024

በልጆች ላይ የትኩረት ማነስ እና እረፍት የለሽ እንቅሰቃሴ ወይም Attention deficit hyperactive disorder (ADHD) ምንድን ነው?

-ADHD ልጆች ላይ በጣም በብዛት የሚስተዋል የአእምሮ ጤና እክል ሲሆን ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሲሆኑ በአብዛኛው በልጆች ላይ ይስተዋላል እስከ ጎልማሳነት እድሜ ሊቀጥል የሚችል ችግር ነው።

አይነቶቹስ?

-ይህ ችግር ከፍተኛ የሆነ የትኩረት ማነስ ወይም ማጣት (inattention) እና እረፍት የለሽ እንቅስቃሴ ማሳየት (hyperactivity)፣ የሚያስከትለውን ችግር ወይም ብዙ ሳያስቡ ግብታዊ መሆን (impulsivity)፣ ወይም የሁለቱ ውህድ ሊሆን ይችላል።

ማንን ያጠቃል?
-ከሴቶች ይልቅ ወንዶችን በብዛት የሚስተዋል ችግር ነው።

ምልክቶቹስ?

-በአካባቢያቸው ወይም በሌላ ሀሳብ መረበሽ
-ለጥቃቅን ነጠሮች ትኩረት መስጠት አለመቻል

-በግድየለሽነት ስህተት መስራት
-አንዳንድ ተግባራትን ከጀመሩ በዃላ የማስቀጠል ፣ የመጨረስ ችግር ለምሳሌ በክፍል ውስጥ አሰተማሪ እያስተማረ መከታተል ጀምረው ወዲያውኑ ሀሳባቸው መበተን

-ትእዛዝ ያለመቀበል ችግር
-አእምሮን ከሚፈትሹ ስራዎች መራቅ

-ንብረቶቻቸው በአግባቡ መያዝ አለመቻል፣የመጣል ችግር
-የእለት ተእለት እቅስቃሴ የሚደረጉ ነገሮችን የመርሳት ሁኔታ

-እረፍት የለሽ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማሳየት ወይም ከመጠን በላይ መወራጨት ፣ አርፎ አለመቀመጥ፣ መቅበጥበጥ፣ ማውራት መቆም አለመቻል፣ ረጋ ብሎ ለመጫወት መቸገር፣ በሰው ወሬ፣ በጨዋታ መሀል ያለ ፍቃድ ጣልቃ መግባት፣

አጋላጭ ምክንያቶቹስ?

-ተመራማሪዎች ይህ ነው የሚባል መንሰኤ ባያሰቀምጡም ነገር ግን በዘረመል (genetics) አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል።

-ያለ ጊዜ የተወለዱ ልጆች ፣ በእርግዝና ጊዜ የሚያጨሱ ፣ አልኮል መጠጥ የሚጠጡ እናቶች ፣ በእርግዝና ጊዜ ከመጠን በላይ ጭንቀት

-በአካባቢ የሚገኙ መርዛማ ኬሚካል ተጋላጭ መሆን
-በአንጎል ላይ የሚደርስ ጉዳት

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች በቂ እርዳታ ካላገኙ ውሳኔዎችን ለመወሰን መቸገር፣ በትምህርት እና ስራ ላይ ደካማ መሆን፣ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ መሆን፣ ስራ ማጣት፣ ገንዘብን በአግባቡ መጠቀም አለመቻል፣ ለሱስ ተጋላጭ መሆን፣ ራስን ማጥፋት፣ ደካማ የሆነ ማህበራዊ ሂወት ሊያመጣ ይችላል።

ህክምናውስ?

-የአሰተሳሰብን እና የባህርይ ህክምና ይህ ህክምና እንዴት እነዚህን ልጆች መንከባከብ እንደምችል ቤተሰብን እና መምህራን ማስተማርን ያካትታል። ይህ ህክምና ልጆች እዴት ባህሪያቸውን መቆጣጣር እንደሚችሉ፣ ይረዳል ተብሎ ይታሰባል።

-መድሀኒቶች ለምሳሌ stimulants እና non stimulants የሚባሉ ምልክቶቹን ለመቀነስ ይረዳሉ። stimulants መድሀኒቶች የሚሰሩት አንጎል ውስጥ የሚገኙ Dopamine እና Norepinephrine የሚባሉ ኬሚካሎች መጠን በመጨመር ነው። non stimulants የሚሰሩት ደግሞ የNorepinephrine መጠን በመጨመር ነው።

ከወላጅ እና መምህራን ምን ይጠበቃል?

-ADHD ያለባቸው ልጆች ለማስተካከል አጫጭር እና ትኩረት የሚጠይቁ ጨዋታዎችን እና ተግባራትን ማዘጋጀት ፣ ማሳተፍ እና ማበረታታት ከወላጆች እና ከመመህራን የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው።

-ልጆችን በቅጣት ሳይሆን በምክር ለማስተካከል መሞከር፣ ቁጣ እና ስድብ ማስወገድ ለልጆች ስነ ልቦና የተሻለ ነው።

-የልጆቹን ትኩረት ሊበትኑ የሚችሉ ነገሮችን ከአካባቢያቸው ማራቅ እና የጭንቀት መንፈስ ሲታይባቸው ረጋ ባለ መንፈስ ማወያየት የተረጋጉ እና አስተዋይ እንዲሆኑ ያግዛል።

-በሞባይል ስልክ ፣ቴሌቪዥን፣ እና ኮምፒዩተር ላይ የሚያሳልፋትን ጊዜ መቀነስ

-በቂ እንቅልፍ እንዲያገኙ ማገዝ፣የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴ ለምሳሌ ዮጋ፣ ታይ ቺ የሚባሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የመርሳት በሽታን ለመከላከል የሚረዱ 5 ነጥቦች==========================1) እግርን ሸራ ጫማ ወይም እስኒከር ውስጥ መክተት። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አእምሮ ውስጥ የሚዘዋወረ...
23/05/2024

የመርሳት በሽታን ለመከላከል የሚረዱ 5 ነጥቦች
==========================
1) እግርን ሸራ ጫማ ወይም እስኒከር ውስጥ መክተት። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አእምሮ ውስጥ የሚዘዋወረውን የደም መጠን እና ኦክስጅን ስለሚጨምር አእምሮ እንዳያረጅ ይረዳል።

2) የአእምሮ እንቅስቃሴ ማድረግ። ስፖርት ስንሰራ አካላችን እንደሚፈረጥመውና እንደሚጠነክረው አእምሯችንም እንደዚሁ ነው። አዳዲስ ነገሮችን ስንማር አእምሯችንን ስፖርት እያሰራን ነው።

3) አመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ። እድሜያቸው 65 አመት ከሆናቸው አስር ሰዎች አንዱ የመርሳት በሽታ ይይዘዋል። አንዳንዶቹ የመርሳት በሽታ መንስኤዎች በቀላሉ የሚድኑ አካላዊ ህመሞች ናቸው። ስለዚህ አመታዊ ምርመራ በማድረግ እነዚህን ህመሞች በጊዜ መለየትና ታክሞ መዳን ይቻላል።

4) ስኳርና የደም ግፊትን መቆጣጠር። ከአልዛይመር ህመም ቀጥሎ የመርሳት ህመምን የሚመጣው አእምሮ ውስጥ ደም ሲፈስ ነው።ለዚህ ዋነኛ አጋላጮቹ የስኳር ህመም እና የደም ግፊት ስለሆኑ የደም ግፊትና የስኳር ህመምን መቆጣጠር የመርሳት ህመም እንዳይከሰት ይከላከላል።

5) በእድሜ የገፉ ሰዎች ድባቴ ወይም የእንቅልፍ ችግር ሲያጋጥማቸው የአእምሮ ሀኪም ማማከር። በእድሜ የገፉ ሰዎች ብስጭት ወይም ድብርት ሲሰማቸው ወይም እንቅልፋቸው ሲቀንስ "እርጅና ነው" ብሎ ችላ ከማለት ይልቅ የአእምሮ ሀኪም ማማከር

ያለ አእምሮ ጤና፤ጤና የለም!!!!

11/01/2024

አኪ የስነ ልሳን ሕክምና ክሊኒክ አሁን ደሞ ደረጃውን ከፍ በማድረግ
በ speech therapy nተጨማሪ የብዙ አመት ልምድ ባላቸዉ ሐኪሞች እና ነርሶች
ልዩ እንክብካቤ በሚያደርጉ ነርሶ
ቤት ለቤት የነርስግ አገልግሎት መጀመራችንን በደስታ እንገልፃለን !!! 0903242838 በመደወል ያናግሩን

09/12/2023

ታዲያስ ሁሉም ሰው በቀላል ጊዜ ውስጥ 'የንግግር ሕክምና' ምን እንደሆነ ይረዱ.
በንግግር ሕክምና ውስጥ ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች ንግግር, ቋንቋዎች እና መግባባት በመገንባት ላይ እናተኩራለን. እኛ እነዚህን ነገሮች ለማሳካት ቀላል አዝናኝ አፍቃሪ ተግባሮችን እና የአፍ የሞተር እንቅስቃሴ እናደርጋለን.

Aki Speech TherapyHow to prevent Stroke easily1. Know ur blood pressure2. Eat healthy diet🍎3. Maintain healthy weight🏋4....
29/10/2023

Aki Speech Therapy
How to prevent Stroke easily
1. Know ur blood pressure
2. Eat healthy diet🍎
3. Maintain healthy weight🏋
4. Quit smoking🚭
5. Stay active👟
6. Avoid drinking too much alcohol

October 29 world stroke day

Address

Addis Ababa

Telephone

+251978806778

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aki Speech Therapy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Aki Speech Therapy:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram