Dr Getaneh Dejen

Dr Getaneh Dejen Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr Getaneh Dejen, Addis Ababa.

01/08/2023
14/05/2023

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት
_________

▪የበሽታው ምንነት

የማህፀን በር ካንሰር በሽታ በአለም ላይም ሆነ በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ለሴቶች ሞት ዋና ምክንያት ነው፡፡ በሽታው (Human Papilloma Virus) በተባለ በአይን በማይታይ ረቂቅ ህዋስ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

የማህፀን በር ካንሰርን የሚያመጣው ቫይረስ ብዙ ዝርያዎች ያሉት ሲሆን በሽታውን የማምጣት አቅም ያላቸው በጣም ትንሾቹ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያም በየዓመቱ በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ብዛት ከ7500 በላይ የሚደርስ ሲሆን በበሽታው ከተጠቁት ውስጥም ከ5000 በላይ የሚሆኑት ይሞታሉ፡፡ በሽታው ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በወንዶች ላይ በፊንጢጣ እና በብልት አካባቢ እንደ ኪንታሮት አይነት ችግሮች ሲያመጣ በሴቶች ላይ ደግሞ ለማህፀን በር ካንሰር መከሰት ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡

የማህፀን በር ካንሰር በሽታን የከፋ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ሴቶች የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩት ከ15-20 ዓመት በኋላ ነው፡፡ ምንም ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን በውስጣቸው ይዘው ለረጅም ጊዜ ይኖራሉ፡፡

▪የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች:

በሽታው በግብረስጋ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፍ ሲሆን በሽታው ከአለበት ሰው ወደ ጤነኛ ሰው የሚተላለፈው ጥንቃቄ በጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ነው፡፡ ይበልጥ ለበሽታው የሚጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች:
▫እድሜያቸው ሳይደርስ የግብረስጋ ግንኙነት የሚጀምሩ ሴቶች፣
▫ከቡዙ ሰዎች ጋር ግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ፣
▫በብልት አካካቢ ሌሎች ቁስለቶች መኖር፣
▫በሽታ የመከላከል አቅም ማነስ፣
▫ሲጋራ መጠቀም የመሳሰሉት ናቸው፡፡

▪የበሽታው መከላከያ መንገዶች

የማህፀን በር ካንሰርን ከምንከላከልባቸው መንገዶች አንዱና ዋናው እድሜያቸው 9-14 ዓመት የሆናቸውን ሴት ልጆች መከላከያ ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግ ነው፡፡ አንዲት ሴት ልጅ ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ራሷን ለመከላከል 2 ጊዜ ክትባቶችን ከ6 እስከ አንድ አመት በሆነ ልዩነት መውሰድ አለባት፡፡

በኢትዮጵያም የማኅጸን በር ካንሰር በሽታን ለመከላከልና ለመግታት የማኅጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ሴት ልጃገረዶች ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና ለክትባት በተመረጡ ጊዜያዊ የክትባት ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሴት ልጆች የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረጋቸው በፊት ቢከተቡ በበሽታው ከመጠቃት ይድናሉ፡፡

ሌሎቹ መከላከያ መንገዶች:
▫እድሜያቸው ለአቅመ ሂዋን ከመድረሱ( ከ18 ዓመት) በፊት ግብረስጋ ግንኙነት ከመፈፀም መቆጠብ፣
▫አንድ ለአንድ መወሰን፣
▫ልቅ ከሆነ የግብረ -ስጋ ግንኙነት እራሳቸውን በመታቀብ ▫ሲጋራ አለማጨስ፣
▫የወንዶች ግርዛት በወቅቱ እንዲካሄድ ማድረግ፣ ▫የስነተዋልዶ ጤና ትምህርት መስጠት ይገኙበታል፡፡

በሌላ መንገድ እድሜያቸው መከተብ ከሚችሉበት እድሜ ክልል ያለፉና ከ30-49 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች የቅድመ ማህፀን በር ካንሰር በሽታ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ምርመራውን በማድረግ ችግሩ የተገኘባቸው ነገር ግን ምንም ዐይነት የህመም ምልክት የሌላቸው ሴቶች ( ካንሰር ደረጃ ላይ ያልደረሱ) መታከምና መዳን ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለበሽታው የተጋለጡና የታመሙ ሴቶችን እስከመጨረሻው ድረስ የእንክብካቤና ፍቅር መስጠት ይገባል፡፡

ኢትዮጵያም የማህፀን በር ካንሰር የህብረተሰቡ የጤና ችግር ከማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ አለማቀፋዊ ስምምነት ገብታለች ፡፡ በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ በ2030 90% የሚሆኑ ሴት ልጆችን የክትባቱ ተጠቃሚ ማድረግ፣ 70% የሚሆኑትን እድሜያቸው ከ30-49 ዓመት የሆኑትን ሴቶች የቅድመ ማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ማድረግ፣ እና የማህፀን በር ካንስር የተገኘባቸውን 90% የሚሆኑትን ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡

አዘጋጅ: አቶ መንግስቱ ቦጋለ፣ ፐብሊክ ሄልዝ ፕሮፌሽናል እና ከፍተኛ የክትባት ባለሙያ

14/05/2023

Happy Mother's Day!!

Take the advantage of fasting
06/03/2023

Take the advantage of fasting

24/02/2023

በቫይታሚንና ማዕድን ያልበለፀገ የስንዴ ዱቄት ለገበያ እንዳይቀርብ ሊከለከል ነው
በዳዊት ታዬ
February 15, 2023

በቫይታሚንና በማዕድን ያልበለፀገ የስንዴ ዱቄትን በማምረትም ሆነ በማስመጣት ለገበያ ማቅረብ እንደማይችል፣ የወጣው አስገዳጅ ድንጋጌ ከሰኔ 2015 ጀምሮ ስለሚተገበር አምራቾችና አስመጪዎች ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሱቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ለዱቄት አምራቾችና አስመጪዎች በላከው ሰርኩላር፣ የስንዴ ዱቄት በተመረጡ ቫይታሚንና ማዕድን ማበልፀግ አስገዳጅ እንዲሆን በተወሰነው መሠረት፣ አስገዳጅ ደረጃውን በመተግበር በተሰጠው ጊዜ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተገልጿል፡፡ አምራቾች ዱቄቱን ለማበልፀግ የሚያስችላቸውን መሠረተ ልማት በተሰጠው ጊዜ አሟልተው፣ በተፈለገው ደረጃ ማምረት ካልጀመሩ ምርታቸውን ለገበያ ማቅረብ እንደማይችሉም አስታውቋቸዋል፡፡

ቀደም ብሎ ለዚህ አስገዳጅ ደረጃ ተፈጻሚነት የሁለት ዓመት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ አስገዳጅ ደረጃውን ያፀደቀው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ምክር ቤት በማዕድን የበለፀገ የስንዴ ዱቄት የእፎይታ ጊዜ ሁለት ዓመት የሚለው ስህተት በመሆኑ፣ ወደ አንድ ዓመት ዝቅ እንዲል ማስተካከያ በመሰጠቱ አስገዳጅ ድንጋጌው ሰኔ 2015 የሚተገበር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህንን ማስተካከያ በሰርኩላሩ ያስታወቀው ኢንስቲትዩቱ፣ በዚሁ መሠረት አምራቾች በቀሪዎቹ ወራት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ማምረት ተግባራቸው ይግቡ ብሏል፡፡

ይህ አስገዳጅ ደረጃ ቀደም ብሎ በፈቃደኝነት እንዲተገበር የፀደቀ ቢሆንም፣ አንድም አምራችና አስመጪ ሊተገብረው ባለመቻሉ በአስገዳጅነት እንዲተገበር ሊወሰን ስለመቻሉ ታውቋል፡፡

የስንዴ ዱቄት ለማበልፀግ አስገዳጅ ደረጃን በተመለከተ በባለሙያዎች ከተሰጠ ማብራሪያ መረዳት እንደተቻለው፣ ይህ አስገዳጅ ደረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሠራበትና በኢትዮጵያ ዘግይቶ የተተገበረ ነው፡፡ አስገዳጅ ደረጃው እስካሁን ያለመተግበሩም ቀላል የማይባል ጉዳት ያስከተለ ስለመሆኑ አኃዛዊ መረጃዎች ተጠቅሰው የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ግን አምራቾች ለቫይታሚን ማበልፀጊያ የሚሆነውን ምርት በማስገባትና የመደባለቂያ መሣሪያውን በመትከል፣ የበለፀገውን ምርት ማምረት ግዴታቸው ይሆናል ተብሏል፡፡ የማበልፀጊያ ግብዓቶቹም የተለዩ ስለመሆናቸውም ታውቋል፡፡

አገራዊ የሥነ ምግብ ችግሮችን ለመቅረፍ በተለይም በትንሽ መጠን ለሰውነት የሚያስፈልገው (Micronutrients) ነገር ግን ጠቀሜታቸው እጅግ ብዙ የሆኑትን የቫይታሚንና ማዕድን እጥረት ለመቀነስ፣ ምግብን ማበልፀግ አዋጭና ውጤታማ ስትራቴጂ መሆኑ ታምኖበት በተግባር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ከ425 በላይ ዱቄት አምራቾች ያሉ ሲሆን፣ ኢንስቲትዩቱ ባለፈው ሳምንት በጻፈው ደብዳቤ ይህንን አስገዳጅ መመርያ ተፈጻሚ እንዲያደርጉ በስም ዝርዝር የገለጻቸው 199 አምራቾች ናቸው::

ምንጭ :- ሪፖርተር ጋዜጣ

04/10/2022

“. . . they also have pre-eclampsia in the
developed countries, but they don’t die the
way our own patients are dying, not because
we do not know how to manage them but
[because] they don’t come early and by the
time they come, it is so late”.

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913292030

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Getaneh Dejen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram