ASCHO Mng

ASCHO Mng Health organization

22/01/2026
 #ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉን?  አብዛኛዎቹ ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊን ሆድ ላይ ለመወጋት ይፈራሉ፣ መርፌው ጽንሱን ይጎዳዋል ብለው ይጨነቃሉ። ...
26/05/2024

#ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉን?
አብዛኛዎቹ ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊን ሆድ ላይ ለመወጋት ይፈራሉ፣ መርፌው ጽንሱን ይጎዳዋል ብለው ይጨነቃሉ። የስኳር ህመም ላለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊን ለመውጋት ተመራጩ ቦታ ሆድ ነው። በእርግዝና ወቅት ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መውጋት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ሆድ ኢንሱሊንን ለመውሰድ ቀላልና አመቺ ቦታ ብቻ ሳይሆን ኢንሱሊን ወደ ሰውነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲገባ (predictable insulin absorption rate) ስለሚረዳ ለኢንሱሊን አወሳሰድ የሚመከር ቦታ ነው። የኢንሱሊን መርፌው ለጽንሱ ምንም አይነት ስጋት አይፈጥርም ምክንያቱም ማህፀኑ ጽንሱን በበቂ ሁኔታ ከለላ ይሰጠዋል። ስለዚህ, የመጀመሪያ ጥያቄያችንን ለመመለስ, አዎ, በእርግዝና ወቅት ኢንሱሊን ሆድ ላይ መውጋት በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።
በእርግዝና ወቅት ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መውጋት ደህንነት ካረጋገጥን በመቀጠል በተለያዩ የእርግዝና ወቅቶች መደረግ ስላለባቸው የተወሰኑ ምክሮችን ስናይ
1. በመጀመሪያው ሶስት ወር የእርግዝና ጊዜ (first trimester) የኢንሱሊን መርፌ በየትኛውም የሰውነት ክፍል ላይ መወጋት ይቻላል:: ከእርግዝና በፊት የነበረ ስኳር ያለባቸውና ኢንሱሊን የሚወስዱ እናቶች የመጀመሪያው ሶስት ወር የኢንሱሊን መውጊያ ቦታ ወይም ቴክኒክ ለውጥ አያስፈልግም።
2. በሁለተኛው ሶስት ወር (second trimester) ጊዜ ሲደርስ የሆድ ገጽታ መለወጥ ይጀምራል፤ ጽንሱ ያድጋል እና ሆድም እንዲሁ። ይሁን እንጂ ኢንሱሊን ሆድ ላይ መውጋት መተው አለብን ማለት አይደለም። ይልቁንስ የመርፌ መወጊያ ቦታን መጠነኛ ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ።በእምብርት ዙሪያ ከጽንሱ ፊት ለፊት ያለውን የሆድ ክፍል ይልቅ ጽንሱ ካለበት በደንብ ራቅ ብለን ከጎን ያሉት የሆድ ክፍሎች ኢንሱሊንን ለመወጋት መጠቀም ይቻላል።
3. በመጨረሻ ሶስተኛው ወር (third trimester) ልጁ እያደገ የመርፌ መወጊያ ቦታ እየጠበበ ይሄዳል እንዲሁም ቆዳ በሆድ ላይ በጣም ጥብቅ ሊል ይችላል። እንዳንዴ ለኢንሱሊን መርፌ መወጊያ የሚሆን ምቹ ቦታ ማግኘት ሊከብድ ይችላል። እንዲህ ሲያጋጥም አይጨነቁ ፣ መፍትሄ አለ ።
መምረጥ ያለብን ቦታ በጎን የሆድ ክፍል ያለውን መሆን አለበት። ቦታውን በአውራ ጣት እና ጠቋሚ ጣት መሀል ቆንጠጥ በማድረግ ቆዳውን ትንሽ በማንሳት መወጋት ይቻላል:: ከሆድ ጋር ጥብቅ ያለውን ሳይሆን በጣቶች መሃከል ላይ ቆዳን ከፍ ማድረግ የሚቻልበት ቦታ በሆድ ጎን ላይ ያግኙ። ከዚያም መርፌውን ከቆዳ በ90 ዲግሪ ቀጥታ አስገብቶ መውጋት ይቻላል።
ይህ ዘዴ ምቹ እና ውጤታማ ሲሆን የኢንሱሊን መርፌን ለመወጋት ተመራጭ መንገድ ነው። ከተገኘ በጣም አጭር የኢንሱሊን መርፌ (በ4 ሚሊ ሜትር) መጠቀም ጥሩ ነው። ይህን የማይመርጡ እና ጽንሱን እንዳልውጋው የሚል ከፍተኛ ፍርሃት ያለባቸው እናቶች እንደአማራጭ ክንድ፣ ታፋ ወይም መቀመጫ ላይ ሊወጉ ይችላሉ።

ፀሐይ አውሮፕላን አዲስ አበባ ደረሰች*****************ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መድረሷን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡እ....
09/02/2024

ፀሐይ አውሮፕላን አዲስ አበባ ደረሰች
*****************

ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መድረሷን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

እ.አ.አ በ1935 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገጣጥማ በረራ ያደረገችው ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ በደመቀ ሁኔታ አቀባበል ተደርጎላታል።

"ፀሐይ" እኤአ በ1935 በጀርመናዊው ኢንጂነር እና የንጉሱ ፓይለት ሄር ሉድዊግ ዌበር ብሎም በወቅቱ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ትብብር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራች አውሮፕላን ናት።

አውሮፕላኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጣሊያን መንግሥት ጋር በተደረሰ ስምምነት በይፋ መረከባቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️የወቅቱ የመስኖ ስንዴ ምርታማነት በጥቂቱ።  የግብርና አቅማችንን በምሉዕ እንጠቀም ዘንድ የጋራ ጥረታችን የጀመርነውን የስራ ፍጥነት ጠብቆ እንዲሄ...
03/02/2024

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

የወቅቱ የመስኖ ስንዴ ምርታማነት በጥቂቱ። የግብርና አቅማችንን በምሉዕ እንጠቀም ዘንድ የጋራ ጥረታችን የጀመርነውን የስራ ፍጥነት ጠብቆ እንዲሄድ እንረባረብ።

ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን በብሔራዊ ገዥ ሀሳብ ሲሰባሰቡ ጠንካራ የማስተባበር፤ የመምራት፤ የመደማመጥና ፈተናዎችን በአብሮነት የመሻገር ችሎታ እንዳላቸዉ ያስመሰከሩበት ታላቅ ታሪክ ነው!
30/01/2024

ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን በብሔራዊ ገዥ ሀሳብ ሲሰባሰቡ ጠንካራ የማስተባበር፤ የመምራት፤ የመደማመጥና ፈተናዎችን በአብሮነት የመሻገር ችሎታ እንዳላቸዉ ያስመሰከሩበት ታላቅ ታሪክ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት፣ በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።ሽልማቱ ክቡር ጠቅላይ ሚ...
28/01/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት፣ በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።

ሽልማቱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ ልዑካን ቡድኖች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ በጣልያን የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ተልዕኮዎች አባላት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት ዓመታት በግብርናው መስክ ቁልፍ ኢንቨስትመንቶችን ያደረገች ሲሆን በስንዴ ምርት ራስን የመቻል ሥራዎችን በማከናወን በዐበይት ምርቶችም ላይ ከፍተኛ ዕድገት አስመዝግባለች።

In a ceremony hosted by the United Nations Food and Agriculture Organization in Rome, Italy, Prime Minister Abiy Ahmed has been awarded the prestigious FAO Agricola Medal, according to the organization, for his vision, leadership and commitment to food security and nutrition as well as the pursuit of innovative solutions in wheat self-sufficiency in the context of fast-changing and challenging circumstances.

The Prime Minister received the Agricola Medal in the presence of high-level delegates of various countries, representatives of international organizations, diplomatic missions in Italy and private sector representatives.

For the past five years, Ethiopia has been making critical investments in the agricultural sector and pursuing wheat self sufficiency endeavors marking significant growth across major commodities.

ሚዲያዎች በመንግስት አሰራር ውስጥ ግድፈቶች እንዲታረሙ የማሳየት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል - የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ሚዲያዎች በመንግስት አሰራር ውስጥ ግድ...
28/01/2024

ሚዲያዎች በመንግስት አሰራር ውስጥ ግድፈቶች እንዲታረሙ የማሳየት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል - የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ

ሚዲያዎች በመንግስት አሰራር ውስጥ ግድፈቶች እንዲታረሙ የማሳየት እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የማገዝ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ አሳሰቡ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያስገነባውን የፋና ላምሮት ስቱዲዮ እያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ቦርድ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ መገናኛ ብዙኃን በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ማኖር እንዲችሉ ሁነቶችን ከመዘገብ አልፈው ትኩረታቸውን በአሰባሳቢ ትርክት እና በትውልድ ግንባታ ስራ ላይ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ባለብዝሃ መልክ በሆነችው ኢትዮጵያ ህዝቦችን ከሀገራቸውም ሆነ እርስ በእርስ የሚያስተዋውቁ ይዘቶች ላይ በማተኮር የስነ ልቦና መቀራረብ መፍጠር እንዲሁም አብሮነትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር የሚዲያዎች ዋና ትኩረት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ሚዲያዎች እርስ በእርሳቸውም ሆነ ከሲቪል ማህበራት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸውን ድርሻ በሚገባ መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉም ጠቁመዋል።

በተለይም በተልዕኮ፣ በይዘት እና በአሰራር ተቀራራቢ የሆኑ ሚዲያዎች ተገቢነት ከሌለው ፉክክር ወጥተው ትብብርን፣ ተቀራርቦ ተሞክሮ መለዋወጥን በማዳበር እና ለበለጠ ውጤታማነት ሰብሰብ ብለው በመቀናጀት የሀገሪቱን ገጽታ በተሻለ መልኩ መገንባት አለባቸው ብለዋል።

ስቱዲዮው በዋናነት የመዝናኛ ፕሮግራሞችን እና አሳታፊ መድረኮችን እንዲያስተናግድ ታስቦ የተገነባ ነው ተብሏል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ASCHO Mng posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram