Dr. Solomon werku

Dr. Solomon werku Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Solomon werku, Doctor, Addis abeba, Addis Ababa.

23/02/2020

ሪህ​—መንስኤውና ለበሽታው የሚያጋልጡ ነገሮች

ሪህ በጣም ከተለመዱት የአርትራይተስ በሽታ ዓይነቶች አንዱ ሲሆን ከፍተኛ ሥቃይ ሊያስከትል ይችላል። “ሪህ፣ ሰውነት ዩሪክ አሲድን በተገቢው መንገድ ማስወገድ ባለመቻሉ ምክንያት የሚመጣ ችግር” እንደሆነ አርትራይተስ የተባለው መጽሐፍ ገልጿል። መጽሐፉ አክሎም እንዲህ ብሏል፦ “ሪህ መንስኤው በግልጽ የሚታወቅ ሕመም ነው፤ ይህ ሕመም የሚከሰተው በመገጣጠሚያዎች መሃል ባለው ፈሳሽ (ሲኖቪያል ፍሉይድ) ውስጥ የዩሪክ አሲድ ቅንጣቶች ሲኖሩ ነው። ሪህ የሚያጠቃው መገጣጠሚያዎችን በተለይም በእግር አውራ ጣት ውስጥ የሚገኙትን ነው።”

ዩሪክ አሲድ፣ የሪህ በሽተኛ በሆኑ ሰዎች ደም ውስጥ የሚገኝ ከሰውነት ሊወገድ የሚገባ ነገር ነው፤ ዩሪክ አሲድ የሚፈጠረው ፕዩሪን ከተባሉት ንጥረ ነገሮች ነው። አብዛኛውን ጊዜ ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ የሚጠራቀመው በሽንት አማካኝነት በተገቢው መጠን ባለመወገዱ ነው። በዚህ ጊዜ መርፌ መሰል የዩሪክ አሲድ ቅንጣቶች በእግር አውራ ጣት መገጣጠሚያ ላይ ሊከማቹ ይችላሉ፤ እርግጥ ነው፣ እነዚህ ቅንጣቶች በሌሎች የሰውነት መገጣጠሚያዎች ላይም ሊጠራቀሙ ይችላሉ። በዚህ ምክንያት መገጣጠሚያው ስለሚቆጣ ያብጣል ብሎም ከፍተኛ ሥቃይ ያስከትላል፤ እንዲሁም ሲነኩት ያተኩሳል።* አልፍሬድ የሚባል አንድ የሪህ ሕመምተኛ የታመመው ክፍል “በትንሹ ቢነካ እንኳ በጦር የተወጋ ያህል በጣም ያሠቃያል” ብሏል።

አርትራይተስ አውስትራሊያ ያወጣው መረጃ እንዲህ ይላል፦ “የሪህ ሕመም አንድ ጊዜ ከተቀሰቀሰ በኋላ ሕክምና ካላገኘ በአብዛኛው ለአንድ ሳምንት ያህል ይቆያል። ከዚያ በኋላ ለወራት እንዲያውም ለዓመታት ሕመሙ ድጋሚ ላይነሳ ይችላል። የሪህ ሕመምተኛ ተገቢውን ጥንቃቄ ካላደረገ ሕመሙ ቶሎ ቶሎ ሊቀሰቀስ፣ እያየለ ሊሄድ እንዲሁም በመገጣጠሚያዎች ላይ ዘላቂ የሆነ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ሪህ ሥር የሰደደ ሕመም የሚሆንበት ጊዜም አለ።”

ሪህ በሕክምና ልንቆጣጠራቸው ከምንችል የአርትራይተስ ዓይነቶች አንዱ ነው። በሽታውን ለማከም በአብዛኛው የሚወሰዱት መድኃኒቶች ስቴሮይድ ያልሆኑ የሕመም ማስታገሻዎች ናቸው፤ በሽታው በተደጋጋሚ የሚያገረሽና ከፍተኛ ሥቃይ የሚያስከትል በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ አሎፑሪኖል የተባለው ዩሪክ አሲድ እንዳይፈጠር የሚረዳ መድኃኒት ይወሰዳል። ሪህ እንዳያገረሽ ማድረግ ይቻላል? አዎ፣ ሕመምተኛው በሽታውን የሚያባብሱትን ነገሮች ካወቀ እንዳያገረሽበት ማድረግ ይችላል።

ሪህ እንዲያገረሽ የሚያደርጉ ነገሮች

ለሪህ በሽታ ዋነኛ መንስኤ የሚሆኑት ዕድሜ፣ ፆታና የዘር ውርስ ናቸው። አንዳንድ ሊቃውንት እንደሚሉት ከሆነ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሕመምተኞች በበሽታው የሚሠቃይ የቤተሰብ አባል ያላቸው ናቸው። ቀደም ሲል የተጠቀሰው አልፍሬድ “አባቴም ሆነ አያቴ ሪህ ነበራቸው” ብሏል። ከዚህም በላይ፣ ሪህ አብዛኛውን ጊዜ የሚያጠቃው ወንዶችን በተለይ ደግሞ በ40 እና በ50 ዓመት መካከል ያሉትን ነው። ወንዶች በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ከሴቶች በሦስት ወይም በአራት እጥፍ ይበልጣል፤ እንዲያውም ሴቶች ከማረጣቸው በፊት በበሽታው የመያዝ አጋጣሚያቸው እጅግ አነስተኛ ነው።

ከመጠን ያለፈ ውፍረትና አመጋገብ፦ ኢንሳይክሎፒድያ ኦቭ ሂውማን ኒውትሪሽን እንዲህ ይላል፦ “በአመጋገብ ሪህን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት በአሁኑ ጊዜ እያተኮረ ያለው ከፍተኛ የፕዩሪን ይዘት ያላቸው ምግቦችን በማስወገድ ላይ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ከሪህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና ችግሮችን ለምሳሌ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን፣ ሰውነት ኢንሱሊንን በአግባቡ ጥቅም ላይ ባለማዋሉ ምክንያት የሚመጣ ሕመምን እንዲሁም ዲስሊፒዲሚያን በ

23/02/2020

/INSOMNIA



ይህ ማለት ለመተኛት መቸገር፡በቂ ለሆነ ጊዜ በእንቅልፍ አለመቆየት ወይም ተኝተን ስንነሳ ምንም አይነት እረፍት የማይሰጥ ከሆነ የዚህ እክል ምልክት ነው ማለት እንችላለን።በአጠቃላይ የዚህ ችግር ተጠቂ የኖኑ ግለሰቦች ጥቂት ሰአታት የሚተኙ ወይም የተመቻቸ ቦታ ኖሮ መተኛት ሚቸገሩ ናቸው።ይህም እንቅልፍ ማጣት በቀን ተቀን እለታዊ ክንዉናችን ላይ ተጽኖ ይፈጥራል።ይህ ችግር በተወሰነ የሰአት ገደብ ከፍለን ከዚ በታች የሚተኙ ይህ እክል አለባቸው ለማለት እንቸገራለን ምክንያቱም የተለያዩ ግለሰቦች የተለያየ የእንቅልፍ ጊዜ ስለሚኖራቸው ነው።አብኛዉን ጊዜ ይህ ችግር ብቻዉን የሚመጣ ሳይሆን ከተለያዩ የጤና ችግር እና እለት ተእለት ከሚገጥሙን ስንክሳር ጋር የሚያያዝ ነው #ለምሳሌ ህመም፡ጭንቀት እና የተላያዩ የጤና ሁከቶች ጋር ይዛመዳል እነዚህ ተዛማጅ ባሉበት ወቅት ይህን እክል ለማስወገድ እና ለማከም ቀለል ይላል ምክንያቱም እነዙህ ምክንያቶች ከታወቁ እነሱን ማከም ያንን እክል ለማስወገድ ይረዳል።በአጋጣሚ ግን ምንም አይነት ተጓዳኝ ችግር ሳይኖር የእንቅልፍ ማጣት ችግር እራሱ ዋነኛ ችግር ሆኖ ሊመጣ ይችላል በዚህ ወቅት እራሱን እንቅልፍ ማጣትን ማከም ይኖርብናል ማለት ነው።በህክምና የተለያዩ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ መንገዶች ሲኖሩ ለዛሬ ከነዚህ መካከል በቀላሉ ቤት ወስጥ መተግበር የምንችላቸዉን መንገድ እናያለን እሱም ፦ጤናማ የእንቅልፍ መርህ ፡ የሰዉነታችን ጡንቻዎች የማዝናናት/ሪፍሬሽ ማድረግ ፡ እራስን መቆጣጠር ነው
በህክምናው ወደ ተወሳሰቡ የህክምና መንገድ ከመሄዳችን በፊት ይህን ህክምና ማድረግ ይመከራል

1 ጤናማ የእንቅልፍ መርሆች መከተል
👇👇👇
#እረፈት እስኪሰማን ብቻ መተኛት ከዛም ከአልጋል ላይ መነሳት
#ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ጊዜ ማበጀት ለምሳሌ ሁሌ 3 ሰአት ወደ መኝታ ማምራት
#እንቅልፍ ሳይመጣ ወደ አልጋ በማምራት ለመተኛት መሞከርን ማወገድ
#ከምሳ በኋላ የሚወሰዱ አነቃቂ መጠጦችን ማስወገድ ለምሳሌ ቡና
#የመተኛ ጊዜያችን ሲደርስ ምንም አይነት አልኮል አለመዉሰድ
#አለማጨስ በተለያ ማታ ላይ
#ለመተኛት በምንሰናዳበት ወቅት የተለያዩ ሀሳቦች ሚያስጨንቁን እና ሚረብሹን ከሆነ የምናስበዉን ነገር በወረቀት ላይ መጻፍ እና ሲነጋ ለዛ ነገር መፍትሄ መፈለግ
#መተኛት ሲያቅተን የተለያዩ መጻፍት ወይም አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ መመልከትን ማስወገድ
#አልጋ ላይ ሆኖ ምግብ መመገብን ማስወገድ
#አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማናገርን ማስወገድ
#በቀን ላይ ለአጭር ጊዜ የሚወሰዱትን ናፕ ማስቀረት
#እንቅልፍ አልወስደን በሚል ወቅት በተደጋጋሚ ሰአታችንን በማየት መጨነቃችን ማስወገድ ይኖርብናል
#እየራበን ወደ መኝታ አለማምራት
#የመተኛ ክፍላችንን በተቻለ መጠን አመቺ እና ለእንቅልፍ እንዲጋብዝ አድርጎ ማዘጋጀት ለምሳሌ መብራት ፡ጫጫታን ማወገድ
#ቋሚ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረገ

2 የሰዉነታችን ጡንቻዎች የማዝናናት/ሪፍሬሽ ማድረግ
👇👇👇
ይህን ለመከወን በመጀመርያ የፊታችን ላይ ያሉትን ጡንቻ ለቀቅ ለማድረግ እና ለማዝናናት ለ5-6 ሰኮንድ ለሚያህል ጊዜ ጥርስትን ነክሶ/ጡንቻን በመወጠር/ መቆየት በመቀጠልም ለ20-30 ሰኮንድ ለቀቅ ማድረግ።ይህን መጀመርያ ከፊታችን ጡንቻዎች ጀምረን እስከ እግራችን ድረስ ይህንን መንገድ መከወን። ይህን በተደጋጋሚ መሞከር ይህም መንገድ ዉስጣዊ ስሜታችን ረጋ ሲለሚያደርገው ቶሎ እንቅልፍ እንዲወስደን ይረደናል።
3 እራስን መቆጣጠር፦ይህ ሀሳብ እንደ አንድ የህክም

23/02/2020

የጡት ካንሰር

ከአንዳንድ ለጡት ካንሰር መጋለጥ እድልዎን ይቀንሱ።
የጡት ካንሰር ማለት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የጡት ሴሎች ዕድገት ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ በሽታ የሚጠቁት ሴቶች ቢሆኑም የጡት ካንሰር በወንዶችም ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡

የጡት ካንሰር ዋነኛ ምልክቶች

ዕጢ፣ እብጠት እና የቆዳ ለውጥ ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ ሊከሰት ይችላል፡፡ እነዚህ ምልክቶችም የሚከሰቱባቸው ሰዎች ግዴታ በጡት ካንሰር በሽታ ተይዘዋል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህን ምልክቶች ካዩ ወደ ክሊኒክ በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡

በጡት ላይ የሚደረግ የግል ፍተሻ
በየወሩ ቢደረግ ጠቃሚ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በማንኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች ይህን በማድረግ ራሳቸውን ከጡት ካንሰር መጠበቅ እንደሚችሉም ይመክራሉ፡፡ ይህን ለማድረግ ምቹ ጊዜ የወር አበባ መጥቶ ከሄደ በኃላ በሚከቱሉት ቀናት ቢሆን ይመከራል፡፡ አብዛኞች ሴቶች የራሳቸውን የጡት ካንሰር የሚያገኙት በጡቶቻቸው ላይ ያለውን ለውጥ በመመልከትና በጡታቸው አካባቢ ያለውን ስሜታቸውን በመረዳት ነው።

የጡት ካንሰር ምርመራ

መጀመር ያለበት ምንም ዓይነት የበሽታው ስሜት ባይሰማዎትም ጭምር ነው፡፡ በተለይ ከ40 ዓመታቸው በላይ ያሉ ወይም በቤተሰባቸው ውስጥ የጡት ካንሰር ታሪክ ያለባቸው ሴቶች በየሁለት ዓመቱ አንዴ የማሞግራም ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡ ማሞግራም አነስተኛ ጨረር በመጠቀም ጡቶችን በሁለት ከፕላስቲክ በተሰሩ ጠፍጣፋ ትሪዎች መሃከል አድርጎ በመጫን ከተለያየ አቅጣጫ ምስልን በማንሳት የሚደረግ የጡት ምርመራ ነው፡፡

በጡት ላይ በሚደረግ ፍተሻ ወቅት የጡት እባጭ የሚገኝባቸው ታካሚዎች በተጨማሪ የአልትራ ሳውንድ እና የኤም.አር.አይ (MRI) ምርመራ ሊታዘዝላቸው ይችላል፡፡ ከነዚህ የተገኘውም ውጤት አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ ከእባጩ ላይ በመርፌ ናሙና በመውሰድ (Fine Needle Assessment ወይም Biopsy) ካንሰር መሆኑን ወይም አለመሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እባጩ ካንሰር ያልሆነ እጢ (benign tumor) ሆኖ ይገኛል፡፡ ካንሰር የሆነ እባጭም (malignant tumor) በሚገኝበት ጊዜ በቶሎ እርምጃ በመውሰድ በዘመናዊ ህክምና ታክሞ መዳን ይቻላል፡፡



የጡት ካንሰር ህክምና

አብዛኛውን ጊዜ የሚጀመረው የቀዶ ጥገና በማድረግ ካንሰር የሆነውን እባጭ በማስወገድ ሲሆን ይህን ደግሞ የሚወስነው እባጩ የደረሰበት ደረጃ ነው፡፡

የጡት ካንሰር ሶስት አይነት ህክምና ይኖረዋል

1- ጨረር (Radiotherapy)
2- ኬሞ ቴራፒ (Chemotherapy)
3- ቀዶ ጥግና (Surgery)
አንዱ ወይም ሁሉም አይነት ህክምና ለአንድ ሰው ሊሰጥ ይችላል።
ጤና ይስጥልን

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
DOCTOR

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Solomon werku posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category