Heal Africa Dialysis Clinic

Heal Africa Dialysis Clinic Heal Africa Dialysis Clinic located Around Enkulal Fabrica, Addis Ababa. Please call 0974040531 / 32

May Allah bless your life with joy and prosperity. Eid Mubarak! Wishing you a happy and peaceful Eid filled with love an...
21/04/2023

May Allah bless your life with joy and prosperity. Eid Mubarak! Wishing you a happy and peaceful Eid filled with love and happiness!
ኢድ ሙባረክ! መልካም እና ሰላማዊ የኢድ በዓል በፍቅር እና በደስታ የተሞላ እንዲሆን እንመኛለን።
Iid Mubaarak! Iida baga nagaa jaalalaa fi gammachuun guutame isiniif hawwaa.
Ciid Mubaarak! Waxaan idin rajeynayaa Ciid farxad leh oo nabad ah oo ay ka buuxaan jacayl iyo farxad.

عيد مبارك! أتمنى لكم عيداً سعيداً وهادئاً مليئاً بالحب والسعا

በአጠቃላይ ጤናማ ሰዉነት የኩላሊታችን ደህንነት እጅጉን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ኩላሊትም ከሰዉነት ዉስጥ አላስፈላጊ እና የተከማቸን ቆሻሻ በሽንት እንድናስወግድ ያገለግላል። በሰዉነታችንም ዉስጥ...
07/04/2023

በአጠቃላይ ጤናማ ሰዉነት የኩላሊታችን ደህንነት እጅጉን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ኩላሊትም ከሰዉነት ዉስጥ አላስፈላጊ እና የተከማቸን ቆሻሻ በሽንት እንድናስወግድ ያገለግላል። በሰዉነታችንም ዉስጥ ያሉ ንጥረ ቅመሞች፣ ጨዉን እና የዉሃን መጠን በማመጣጠን ሰዉነታችን ጤናማ እንዲሆን ያስችላል። እነዚህ ንጥረ ቅመሞች ወይም ዉሃ መመጣጠን ካልቻለ ጤናማ የሆነ የሰዉነት ስርዓት ይናጋል። ስለዚህ የኩላሊታችንን ጤናማነት ማስጠበቅ አስፈላጊ ይሆናል።
ሳናዉቀዉ የምናደርጋቸዉ ኩላሊታችንን የሚጎዱ 10 ባህርያትን ከስር አስቀምጠንላችኋል። ከነዚህ ድርጊቶች በመቆጠብ የኩላሊታችሁን ደህንነት ማስጠበቅ ይቻላል።

1. የህመም ማስታገሻ በብዛት መጠቀም
አብዛኛዉን ጊዜ የህመም ማስታገሻዎች ያለ ሃኪም ማዘዣ ስለሚሸጡ ሰዎች በቀላሉ በመግዛት ለቀላልም ሆነ ከባድ ህመም እንደማስታገሻነት ይጠቀማሉ። እነዚህም ማስታገሻዎች መካከል ነን ስቴሮይዳል የሚባሉቱ ማስታገሻዎች በብዛት ከመጠን በላይ ለረጅም ጊዜ መጠቀም ኩላሊታችንን አደጋ ላይ ይጥለዋል። ስለዚህ እነዚህን የህመም ማስታገሻዎች አስፈላጊ ከሚሆኑባቸዉ ሁኔታዎች ዉጭ ያለመጠቀም ይመከራል።

2. ብዙ ጨዉ መመገብ
በዉስጣቸዉ ብዙ ጨዉ ያላቸዉ ምግቦች የደም ግፊትን በመጨመር ኩላሊትን ለበሽታ ሊዳርጉ ይችላሉ። ስለዚህ ምግቦቻችንን ብዙ ጨዉ በማድረግ ከማጣፈጥ ይልቅ መጠነኛ ጨዉ በማድረግ በሌሎች የምግብ ማጣፈጫዎች ማለማመድ ይመከራል።

3. በቂ ዉሃ ያለመጠጣት
ከምክንያቶቹ ሁሉ ቀዳሚ የሆነዉ እና የአብዛኛዉ ሰዉ የማያስተዉለዉ ስህተት በቂ ዉሃ ያለመጠጣት ነዉ። በቂ ዉሃ መጠጣት ኩላሊታችን የሚያደርገዉን የቆሻሻ ማጣራት ሂደት ያግዛል። ያ ካልሆነ ግን ኩላሊታችን ላይ ጫና ያበዛል። የኩላሊትን ጠጠርም ለማስወገድ ዋነኛዉም መፍትሄም በቂ ዉሃ መጠጣት ነዉ። ለአዋቂ በቀን በቂ ዉሃ የሚባለዉ በትክክል የሚለካዉም በቀን ቢያንስ ከ ሁለት እስከ ሶስት ጊዜ ሽንት በመሽናት ነዉ።

4. ማጨስ
ብዙ ጊዜ ማጨስ ለሳምባ እና የልብ ጤና ጠንቅ መሆኑ ቢነገርም ኩሊትንም ይጎዳዋል። የሚያጨሱ ሰዎች ኩላሊታቸዉ ፕሮቲን የተባለዉን ንጥረ ነገር በሽንት እንዲወገድ ሊያደርግ ይችላል፡ ይሄም የኩላሊትን መጎዳት ያሳያል።

5. አልኮሆል መጠጣት
ከዚህ ቀደም ብዙ አልኮሆል መጠጣት ኩላሊት የጎዳል የሚል አመለካከት ያለ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ለሰዉነት አይጎዳም የሚባል የአልኮል መጠን እንደሌለ ጥናቶች ያመለክታሉ። ስለዚህ አልኮል መጠጣትም ኩላሊት ላይ የራሱ የሆነ ጉዳት ላይ ይዳርጋል።

6. በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አዘዉትሮ መመገብ
በፋብሪካ ተቀነባብሮ የሚወጡ ምግቦች በብዛት በዉስጣቸዉ ሶዲየም እና ፎስፈረስ የተሰኙ ንጥረ ቅመሞችን በብዛት ስለሚይዙ እነዚህን ምግቦች አዘዉትሮ መመገብ ንጥረ ቅመሞቹ ኩላሊታችንን ከረጅም ጊዜ በኋላ እንዲጎዱ ያደርጋቸዋል።

7. እንቅልፍ በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት
የእንቅለፍ ስርዓት መጠበቅ ባጠቃላይ ለሰዉነታችን ጤና አስፈላጊ ነዉ። ነገር ግን ኩላሊታችን የስራ ጫናዉ በእንቅልፍ ኡደታችን ላይ ስለሚመሰረት በቂ እንቅልፍ ያለመተኛት በጊዜያት ኩላሊታችንን ሊጎዳዉ ይችላል።

8. ብዙ ስጋ መመገብ
ከመጠን በላይ የሆነና በአትክልት እና ፍራፍሬ ያልታከለበት ስጋ አዘዉትሮ መመገብ ደማችንን ይበልጥ አሲዲክ እንዲሆን ሰለሚያደርገዉ ይሄ ደግሞ ኩላሊታችንን ይጎዳዋል።

9. ጣፋጭነት ያላቸዉን የታሸጉ ምግቦች በብዛት መመገብ
ጣፋጭነት ያላቸዉን ምግቦች በብዛት መመገብ የስኳር እና ደም ግፊት ህመምን ያመጣል። እነዚህ ህመሞች ደግሞ በተዘዋዋሪ ኩላሊለታችንን ስለሚጎዱ፡ ከመጠን በላይ የሆኑ ጣፋጭነት ያላቸዉን ምግቦች መመገብ አይመከርም።

10. የሰዉነት እንቅስቃሴ ያለማድረግ
እንቅስቃሴ ማድረግ ለሁለንተናዊ የሰዉነት ጤንነት አስፈላጊ ቢሆንም፡ በቂ እንቅስቃሴ ያለማድረግም ኩላሊታችንን ከሚጎዱ ልማዶች አንዱ ነዉ።
ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ኩላሊታችንን ሊጎዱ የሚችሉ ባህርያት በማስወገድ ጤንነቱን መጠበቅ ይቻላል።

ጤናችሁ ይብዛ!
ኩላሊት በመጎዳቱ የተነሳ ለሚያስፈለግ የዳያሊሲስ አገልግሎት ወይም ማማከር የ ሂል አፍሪካ ዳያሊሲስ ማዕከልን ቀድመዉ ቢያማክሩ ይሻላል ብለን እናምናልን። ለአገልግሎቱ 0974040531 ወይም 0974040532 ይደዉሉ።

👉 የሽንት መጠን ማነስ ፣ ወይም በጭራሽ አለመሽናት፡፡ ይህም ማለት በ 24 ሰዓት ውስጥ ያለን ሽንት ተለክቶ ከ 400 ሚሊ ሊትር ያነሰ ከሆነ። ይህም የሚያመለክተው ኩላሊት የማጣራት አቅሟን ...
26/09/2021

👉 የሽንት መጠን ማነስ ፣ ወይም በጭራሽ አለመሽናት፡፡ ይህም ማለት በ 24 ሰዓት ውስጥ ያለን ሽንት ተለክቶ ከ 400 ሚሊ ሊትር ያነሰ ከሆነ። ይህም የሚያመለክተው ኩላሊት የማጣራት አቅሟን እንዳጣች ነው። ይህም በሰውነት ውስጥ ውኃ እንዲጠራቀም ምክንያት ይሆናል። ይህም ሁለተኛውን ምልክት እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም የሰውነት ማበጥ ነው።

👉 የሰውነት ማበጥ በብዛት የሚከሰተው ጠዋት ጠዋት በፊት እና አይን አካባቢ ሲሆን እየቆየ ሲሄድ ደግሞ በሆድ እና በእግር ላይ እብጠት ሊታይ ይችላል።

👉 ውኃው የተጠራቀመው በደረት አካባቢ ከሆነ የደረት ሕመም ወይም ግፊት እና የትንፋሽ እጥረት ሊኖር ያችላል።

👉 በሰውነት ውስጥ ያለው የውሃ መጠን በመጨመሩ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ሊኖር ይችላል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የራስ ምታት እና የአይን ብዥታ ሊኖር ይችላል።

👉 ደም የቀላቀለ፣ ቀይ ወይም ቡናማ የሆነ ሽንት ልናይ እንችላለን።ይህም ሽንትን የኮካ ኮላ ቀለም እንዲኖረው ያደርጋል። ይህም የኩላሊት መጎዳትን ያመላክታል።

👉 ማስታወክ እና የምግብ ፍላጎት አለመኖር ሲሆን የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ዩሬሚያ የሚባል መርዛማ ኬሚካል በሰውነታችን ውስጥ ስለከማች ነው።

👉 በቀላሉ የመድከም ስሜት ነው።

👉 እንዲሁም ሽንት ከመጠን ያለፈ አረፋ ካለው በሽንት ውስጥ ፕሮቲን እንዳለ ሊያመላክት ይችላል። ጤነኛ ሰው ላይ በሽንቱ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፕሮቲን እንዲኖር አይጠበቅም፤ ኩላሊት አጣርቶ ወደ ደም ይመልሰዋል። ነገር ግን ኩላሊት ሲጎዳ በሽንት ውስጥ ፕሮቲን ሊገኝ ይችላል።

ለዳያሊሲስ፡- 09 74 04 05 31 / 09 74 04 05 32
እንቁላል ፋብሪካ፣ አዲስ አበባ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Heal Africa Dialysis Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Heal Africa Dialysis Clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram