Dr. Seid Arage

Dr. Seid Arage Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Seid Arage, Medical and health, Addis Ababa.

Maternal Fetal Medicine sub specialist
( በእናቶችና ጽንስ ህክምና አደጋ ላይ ወይም ውስብስብ ችግሮች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ህክምና )
ረዳት ፕሮፌሰር
አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በረካ የእናቶችና ህጻናት ማእከል
+ 251910161920

With College of Health Sciences Addis Ababa University – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
23/01/2026

With College of Health Sciences Addis Ababa University – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

ሾተላይ እና ሳይንሳዊ መፍትሄው ጥንዶች አንድ ልጅ ብቻ ወልደው በቀጣይ የተወለደው ልጅ ሕይወት ሲያልፍ ወይም ሴቶች ለእርግዝና ሲቸገሩ በተለምዶ ሾተላይ አለባቸው ሲባል ይስተዋላል። ሾተላይ ተ...
18/01/2026

ሾተላይ እና ሳይንሳዊ መፍትሄው

ጥንዶች አንድ ልጅ ብቻ ወልደው በቀጣይ የተወለደው ልጅ ሕይወት ሲያልፍ ወይም ሴቶች ለእርግዝና ሲቸገሩ በተለምዶ ሾተላይ አለባቸው ሲባል ይስተዋላል። ሾተላይ ተብሎ የሚጠራው ችግር በሕክምና አር ኤች ፋክተር (RH factor) ወይም አር ኤች ኢንኮምፓቲቢሊቲ (RH incompatibility) የሚል ስያሜ እንዳለው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፅንስ እና ማሕፀን ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በማተርናል ፌታል ሜዲስን ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ሰኢድ አራጌ ይናገራሉ።

ሾተላይ (RH incompatibility) ሕመም

በጽንስ ጊዜ የሚከሰት ሾተላይ ተፈጠረ የሚባለው አባት ፖዘቲቭ፣ እናት ኔጌቲቭና ልጅ የአባቱን የደም አይነት ወስዶ ፖዘቲቭ በሚሆንበት ወቅት ብቻ ነው። እናት አር ኤች ፋክተር ሳይኖራት (ኔጌቲቭ ሆና) ፅንስ አርኤች ፋክተር ሲኖረው (ፖዘቲቭ ሲሆን) የእናት የበሽታ መከላከያ ስርዓት የፅንሱን አርኤች እንደባዕድ ይቆጥረዋል ይላሉ ዶ/ር ሰኢድ።

ቀጥሎም መከላከያ በማመንጨት ፅንሱ ላይ ችግር ይፈጠራል። የተፀነሰው ልጅ ለዚህ ችግር ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆነው ከ28 ሳምንት የእርግዝና ጊዜ በኋላ (ሊወለድ በተቃረበበት) ነው። በደማቸው ውስጥ አር ኤች ፋክተር የሌላቸው ማለትም የደም አይነታቸው ኤ ኔጌቲቭ፣ ቢ ኔጌቲቭ፣ ኤቢ ኔጌቲቭ እና ኦ ኔጌቲቭ የሆኑ ሴቶች የደም አይነቱ ፖዘቲቭ (positive) ከሆነ ወንድ ሲፀንሱ እንዲሁም የፀነሱት ልጅ የደም አይነት ፖዘቲቭ (የአባቱን ሲይዝ) አር ኤች ፋክተር ወይም ኢንኮምፓቲቢሊቲ ተፈጠረ ይባላል።

አባት ፖዝቲቭ፤ እናት ኔጌቲቭ ሆኖ ፅንሱ ኔጌቲቭ የሚሆንበት (የእናቱን የሚይዝበት) አጋጣሚ ምንም ችግር አይፈጥርም ይላሉ ዶ/ር ሰኢድ።
የሰው ልጅ ባጠቃላይ ስምንት ዓይነት የደም አይነት ሲኖረው፤ አራቱ አር ኤች ፖዘቲቭ፤ አራቱ ደግሞ አር ኤች ኔጌቲቭ ናቸው። ትልቁ ጉዳይ የሚመጣው እናትየዋ በተፈጥሮዋ አር ኤች ኔጌቲቭ የሆነች እለት ነው።
የሚወለደው ልጅ የአባቱን ከያዘ ለናትየዋ የደም አይነት አዲስ እንግዳ ይሆናል። የልጁ የደም ዓይነት ሳይወለድ በማሕጸን ውስጥ እያለ ወይንም በወሊድ ሰዓት ከልጁ ደም ወደ እናትየዋ ይደማል (ይቀላቀላል)። በሚቀላቀልበት ጊዜ ደግሞ የልጁን የደም ዓይነት የናትየዋ የደም ዓይነት ስለማያውቀው እንደ በሽታ ይቆጥረዋል። ስለሆነም በመጀመሪያ እርግዝና ላይ በሽታ ብሎ ይመዘግበዋል።

እንደገናም እናት እርግዝና ስትይዝ ያንን የደም አይነት ቀጣይ ላይ በእርግዝና ከያዘች መጀመሪያ ላይ በሽታ ተብሎ የተመዘገበ ልጅ ስለሆነ የእናትየዋ የበሽታ መከላከያ ስርዓት ያን ልጅ ያጠፋቸዋል። ሳይወለድ ካጠፋቸው ልጁ ውስጥ እያለ የደም ማነስ ይኖረዋል። እድሉን አግኝቶ መወለድ ከቻለ እና ደም ማነስ ካልገጠመው ቢጫ ሆኖ እንዲወለድና አደጋ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል።

በመጀመሪያ እርግዝና ወቅት ሾተላይ የማጋጠም እድል አነስተኛ ነው። ይህ ችግር በይበልጥ የሚስተዋለው 2ኛ እና ከዛ በላይ በሆነ ፅንስ ላይ ነው። የመጀመሪያ ፅንስ ላይ የእናት የመከላከያ ስርዓት እንደ በሽታ የቆጠረውን የጽንስ የደም አይነት የሚለይበት የሚሰጥበት በመሆኑ ነው።

ነገር ግን የመጀመሪያ እርግዝና ሲባል ከዚህ ቀደም ፅንስ ማቋረጥ እና መሰል ችግር ያላጋጠማት (እርግዝና ሙሉ በሙሉ ተፈጥሮ የማያውቅ) መሆን አለበት። ከዚህ ቀደም እናት ባላወቀችበት መንገድ እርግዝና ተፈጥሮ የነበረ ሊሆን ይችላል። ስለሆነም የመጀመሪያ እርግዝና በእርግጠኝነት ላይታወቅ ስለሚችል እንዲሁም በቀጣይ (2ኛ) እርግዝና ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል ሕክምና መሰጠት የሚጀምረው በመጀመሪያ እርግዝና ወቅት ነው።

አርኤች ፋክተር (ሾተላይ) የሚያስከትለው ችግር ፅንሱ ሆድ ውስጥ እያለ የደም ማነስ ማጋጠም፣ ፅንስ መቋረጥ፣ ወቅቱ ሳይደርስ መወለድ፣ ከተወለደ በኋላ የደም ማነስ ችግር፣ የተወለደ ልጅ ቢጫ መሆን፣ ሾተላይ እና ሳይንሳዊ መፍትሄው የተወለደ ልጅ ላይ የአእምሮ ችግርና ልጅ ከተወለደ በኋላ ሕይወት ማጣት ናቸው።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደየ ሀገሩ የተለያየ ቢሆንም የደም አይነታቸው ፖዘቲቭ ማለትም አር ኤች ፋክተር ያላቸው ሰዎች ብዛት ኔጌቲቭ የደም አይነት ካላቸው ሰዎች አንፃር ከፍተኛ ነው። እንደ ዶክተር ሰኢድ ንግግር፤ የአር ኤች ፋክተር ችግር በመቶኛ ሲቀመጥ ከ100 ሰዎች መካከል በ16 ላይ ያጋጥማል። የቅርብ ጥናት ባይኖርም በኢትዮጵያ ከ100 ሰዎች ምናልባት ከስድስት እስከ አስር በመቶ ሰው ላይ ይከሰታል።

ስለሆነም ኔጌቲቭ የሆነች (አር ኤች ፋክተር የሌላት) እና ፖዘቲቭ አር ኤች ካለው የፀነሰች ነፍሰ ጡር ሴት 28ኛ ሳምንት ላይ ሕክምና ይሰጣታል። ይህም ጽንሱ ፖዘቲቭ ከሆነ ችግር አንዳይፈጠር ያደርጋል። ኔጌቲቭ ከሆነ ደግሞ ጥቅም ባይኖረውም ጉዳት አያስከትልም።
ይህ ሕክምና ምንም አይነት ተጓዳኝ ችግር ስለማያስከትል ተጋላጭ ለሆኑ እናቶች በሙሉ እንዲሰጥ ይደረጋል።

አንዲት ሴት ይህ ችግር አጋጥሟታል የሚባለው የአባት የደም አይነት ፖዘቲቭ (አር ኤች ፋክተር ያለው)፣ የእናት ኔጌቲቭ (አር ኤች ፋክተር የሌለው) እና የተፀነሰው ልጅ ፖዘቲቭ (አር ኤች ፋክተር ያለው) ሲሆን ነው።

የአባት የደም አይነት ፖዘቲቭ ቢሆንም 40 በመቶ የሚሆነው ፅንስ የእናትን የደም አይነት ኔጌቲቭ ስለሚይዝ ችግር አያጋጥመውም። በተመሳሳይ የጥንዶቹ (የሁለቱም) የደም አይነት ኔጌቲቭ ከሆነ የሚፀነሰው ልጅም ኔጌቲቭ ስለሚሆን የሾተላይ ችግር አይፈጠርም።

ከዚህ ቀደም የሾተላይ ችግር ያጋጠማቸው ጥንዶች በቀጣይ እርግዝና ላይ ፅንሱ የእናትን የደም አይነት (ኔጋቲቭ) የመያዝ እድል ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን ፅንሱ በድጋሚ የአባቱን የደም አይነት ከያዘ ሕክምና እንዲያገኝ ይደረጋል። አር ኤች ኢንኮፓቲቢሊቲ (ሾተላይ)ና ሕክምናው
በጥቅሉ ከዚህ ቀደም የሾተላይ ችግር ያጋጠማቸው እናቶች በቀጣይ እርግዝና ለችግሩ ተጋላጭ መሆን ወይም አለመሆናቸውን ለማወቅ የሚደረግ የላብራቶሪ ምርመራ፣ 28ኛ የእርግዝና ሳምንት ላይ የሚሰጥ መድሃኒት፣ ከወሊድ በኋላ የሚሰጥ መድሃኒት፣ ፅንስ ሆድ ውስጥ እያለ ደም እንዲሰጠው ማድረግና ልጅ ከተወለደ በኋላ የሚሰጥ ሕክምና ይጠቀሳሉ።

ሾተላይ /አር ኤች ኔጋቲቭ (RH-)/ ችግርን መከላከል ይቻላል። 28ኛ ሳምንት ላይ ሲደርሱ ወይንም ሰባት ወር መግቢያ ላይ ሲደረስ የዚህን በሽታ መከላከያ መርፌ መወጋት ይቻላል። ይህ በቂ አይደለም። ዋናው ተከላካይ እናት እንደወለደች በሰዓታት ውስጥ የልጁ የደም ዓይነት ይታይና የእናትየውን ከመሰለ ይቀራል፣ የአባትየውን ከመሰለና ከታወቀ ድጋሚ ያንኑ መድሃኒት ሁለተኛ ዙር መድሃኒቱን እንዲወስድ ይደረጋል።

በሽታ የሚባለውም ይህንን እድል ያላገኙ እናቶች ላይ ነው። በኢትዮጵያ ይህ መድሃኒት በጣም ውድ ከመሆኑም ባሻገር በቀላሉ ላይገኝ ይችላል። ይህ ሆኖም አልፎም አንዳንድ ሰዎች መድሃኒቱንም ወስደው ውስን ሰዎች ለዚህ ችግር ይጋለጣሉ።

ብዙ ጊዜ ችግር ላይ የሚወድቁት ግን መድሃኒቱን ያላገኙት፣ በክትትላቸውም ያንን እድል ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች ናቸው። መድሃኒቱ ማቀዝቀዣ የሚፈልግ በመሆኑ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ ለጸሃይ ከተጋለጠ አያገለግልም። እንደገናም ሀገር ውስጥ የሚመረት መድሃኒት ባለመሆኑና ከውጭ ሀገር ስለሚመጣ በተለያየ መንገድ አላግባብ የሚመጣባቸው ሁኔታዎች ስለሚኖሩ መድሃኒቱ ውጤታማ ያለመሆን ባህሪም ሊኖረው ይችላል።

ሾተላይ ያጋጠማቸውን እናቶች በማዕከሉ እርግዝናቸውን ካወቁ አራት ወራት ጀምሮ ክትትል ይደረግላቸዋል። ደም ካነሳቸው ደም ይሰጣቸዋል። ለቢጫነት የሚጋለጡ ሆነው ከተገኙ ደግሞ ከተወለዱ በኋላ በሆስፒታሉ ውስጥ ባለ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተመደቡ ባለሙያዎች የሾተላይ ሕክምና ይደረግላቸዋል።

የሾተላይ ሕመም ጽንሱ ላይ ይታወቃል። የመጀመሪያው የልየታ መንገድ እናትየዋ /አር ኤች ኔጋቲቭ (RH-)/ መሆኗ ነው። ይህንን ተከትሎ የላቦራቶሪ ምርመራ ከእናትየው ደም ተወስዶ በሚደረገው ምርመራም ውጤቱ ጥቆማ ይሰጣል።

የደም ማነስ መኖርና አለመኖሩን ለማወቅ ሙያዊ ሥራ ይሠራል። ሥራውም የሚሠራው በአልትራ ሳውንድ ነው። ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከቀድሞው በተሻለ እና በቀላል መንገድ የልጅን የጭንቅላቱን የአእምሮ ክፍል በአልትራ ሳውንድ በማየት ደም ማነስ እንዳለበት እና እንደሌለበት ማወቅ ይቻላል።

አንዲት እናት ሳታውቅ እንኳን እርግዝና ብትይዝ ሾተላይ ያለበት ሰው ልጅ አይወልድም የሚለውን አባባል ማስቀረት ያስፈልጋል። በሆስፒታሉን ወደፊት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሪፈራል በመቀበል ማከም እንፈልጋለን። ለዚህም ብቁ የሰው ኃይል እና የሕክምና መሳሪያዎች አሉ። መማር ማስተማሩም ይህንን ተግባር ማስፋፋት ዓላማ ማድረጉን ይጠቁማሉ።

እስካሁን ባሉ ጥናቶች ደሙን ወስደው ካደጉ በኋላ የተሰሙ ችግሮች የሉም። በርግጥ ሳይንሱ ለሌላውም ዓለም አዲስ ነው። ነገር ግን በተሻለ ሁኔታ ርቀው ሄደዋል። ተሞክሮ ያለው ባለፉት ከስምንት እስከ 10 ዓመታት ውስጥ ነው። የእስካሁንን በመሰብሰብ ጥናት ውስጥ እናስገባለን።

ፅንስ ሆድ ውስጥ እያለ የደም ማነስ ሲያጋጥመው ደም እንዲሰጠው ይደረጋል። ይህም የደም አይነታቸው ኔጊቲቭ (አር ኤች ፋክተር ከሌላቸው) ሰዎች የተወሰደ ነው። በይበልጥ ኦ ኔጌቲቭ የደም አይነት ለፅንሱ እንዲሰጥ ይደረጋል።

ስለሆነም የፅንሱና የእናት የደም አይነት ኔጌቲቭ (ተመሳሳይ) እንዲሆን ማድረግ ችግሩን ያስተካክላል። እናት ኔጌቲቭ እና አባት ፖዝቲቭ የደም አይነት ላለው ፅንስ በሙሉ 28ኛ የእርግዝና ሳምንት ላይ ሕክምና ይሰጣል። ነገር ግን በዚህ ወቅት የሚሰጥ ሕክምና በድጋሚ ከወሊድ በኋላ እንዲሰጥ የሚደረገው ፅንሱ ከተወለደ በኋላ ፖዝቲቭ የደም አይነት እንዳለው ሲረጋገጥ ነው።

ከእናቱ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ኔጌቲቭ ከሆነ ሕክምና (መድሃኒት) አያስፈልገውም። ፅንስ ሆድ ውስጥ እያለ የደም አይነቱን ማወቅ ይቻላል። ነገር ግን የደም አይነቱን ለማወቅ በሚደረግ ምርመራ ችግሩን ላለማባባስ ሲባል በ28ኛ የእርግዝና ሳምንት ላይ ተጋላጭ ለሆኑ እናቶች በሙሉ ሕክምናውን መስጠት ተመራጭ ተደርጓል። ፅንስ ሲቋረጥ ወይም ልጅ ሕይወቱን ሲያጣ ከአር ኤች ችግር ጋር የማማያዝ ሁኔታዎች አሉ።
አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም ፖዘቲቭ የሆኑ እናቶች በእርግዝና ወቅት በተለያየ በሽታ (ችግር) ምክንያት ልጅ ሊያጡ ይችላሉ። ነገር ግን ከአር ኤች ፋክተር (የሾተላይ ችግር) ጋር ሊያያዝ እንደማይገባው ያመለክታሉ።

በሾተላይ ላይ ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ የእናቶችን ትክክለኛ ችግር እንዳይታወቅ በማድረግ አስፈላጊውን ሕክምና እናዳያገኙ ያደርጋል። እንደገናም የስነልቦና ችግር በማስከተል በቀጣይ እርግዝና ላይ ጫና ያስከትላል።

አር ኤች ኔጌቲቭ የሆኑ ሰዎች ጤናማ ናቸው። ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች ችግሩን አስቀድሞ በመከላከል እና በሕክምና መውለድ ይችላሉ።
የአር ኤች ፋክተር ችግር (ሾተላይ) መከላከያ መንገድ
ትዳር ሲመሰረት የአር ኤች ፋክተር ምርመራ ማድረግ፣ ኔጌቲቭ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች ደም ቢለግሱ፣ ተጋላጭ የሆኑ እናቶች በማንኛውም ችግር ፅንስ መቋረጥ ሲያጋጥማቸው ሕክምና ማድረግ (መድሃኒት መውሰድ) መፍትሄ መሆኑንም ይጠቅሳሉ።

አር ኤች ኔጋቲቭ ሆነው እርግዝና ያላቸው ክትባቱን ለማግኘት በ28 ኛ ሳምንት እና ከወሊድ በኋላ መውሰድ አለባቸው። ገንዘብ ቢጎድል እንኳን ከወሊድ በኋላ ወዲያውኑ ሲወለድ የሚወሰደውን መውሰድ ያስፈልጋል።
በእርግዝና ጊዜ የሾተላይ በሽታ ያለባቸው እናቶች ልክ እንደማንኛውም እርግዝና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በብቁ ባለሙያዎች በነጻ ሕክምና ያገኛሉ። የሕክምና ባለሙያዎች ችግሩ የተባባሰ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ወደ ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ቢልኩ ሆስፒታሉ ለማከም ዝግጁ ነው።

14/01/2026
01/01/2026

የፅንስ ልብ ህመሞች ደህንነት ክትትል
በ EBS TV
ዛሬ አንድ ሰአት ምሽት ላይ ይከታተሉ።

About our department , AAU, CHS , department of Obstetrics and Gynecology 5th floor.
25/12/2025

About our department , AAU, CHS , department of Obstetrics and Gynecology 5th floor.

ከጅማ እስከ አዲስ አበባ፣ከተስፋ መቁረጥ እስከ ሕይወት።  ሾተላይ ሲነሳ ብዙ ሰዎች ይፈራሉ፣ ይጨነቃሉ፣ እንዲሁም ተስፋ ይቆርጣሉ። ቢሆንም ሾተላይ በቀድሞ ምርመራ እና በዘመናዊ ሕክምና መከላ...
15/12/2025

ከጅማ እስከ አዲስ አበባ፣
ከተስፋ መቁረጥ እስከ ሕይወት።

ሾተላይ ሲነሳ ብዙ ሰዎች ይፈራሉ፣ ይጨነቃሉ፣ እንዲሁም ተስፋ ይቆርጣሉ። ቢሆንም ሾተላይ በቀድሞ ምርመራ እና በዘመናዊ ሕክምና መከላከልና መታደግ የሚቻል ሕመም ነው።
ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ግን፣ በፅንሱ ውስጥ ከባድ የደም ማነስ (severe fetal anemia) እና የልብ ድካም (heart failure) ሊያስከትል ስለሚችል፣ ብዙ ፅንሶች በጊዜያቸው እንዳይወለዱ ምክንያት ይሆናል።ነገር ግን በዘመናዊ የሕክምና ቴክኖሎጂ እና በልዩ ሙያ ባለሞያዎች እጅ፣ ይህ ችግር መፍትሄ እያገኘ ነው። በሀገራችን አንጋፋና መሪ የሕክምና ተቋም በሆነው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ በሾተላይ የተጎዱ ብዙ ፅንሶችን በጥንቃቄ እየተከታተልን፣ እናታቸው ሆድ ውስጥ እያሉ የደም ልገሳ (intrauterine blood transfusion) በማድረግ በሰላም እንዲወለዱ ማድረግ ተችሏል።
ከእነዚህ ባለ ጉዳዮች መካከል አንዷን ለእናንተ ለማጋራት ፈለግን።
ይህች እናት በቀድሞ እርግዝናዎቿ ሾተላይ ምክንያት ፅንስ ለተደጋጋሚ ጊዜ ያጣች ሲሆን፣ በዚህኛው እርግዝና በስድስተኛው ወር መጨረሻ (27 ሳምንት) ከጅማ ከተማ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሪፈር መጣች።
በመጣችበት ጊዜ የፅንሱ ሔሞግሎቢን መጠን 3.1 g/dl ነበር፣ ይህም እጅግ ከባድ የደም ማነስ መኖሩን ያመለክታል። በዚህ መሠረት የመጀመሪያው የማህፀን ውስጥ የደም ልገሳ ተፈጸመ።
ከሁለት ቀናት በኋላ፣ ሁለተኛው የደም ልገሳ ከመደረጉ በፊት ሔሞግሎቢኑ 4.1 g/dl ሲሆን፣ ከልገሳው በኋላ 13.2 g/dl ደረሰ። በቀጣይ ክትትል ውስጥ፣ በአጠቃላይ አራት ጊዜ የማህፀን ውስጥ የደም ልገሳ ተካሄደ።
የመጨረሻው ልገሳ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሲደረግ፣ ከልገሳ በፊት የፅንሱ ሔሞግሎቢን 10.7 g/dl ነበር፣ ከልገሳ በኋላ ደግሞ 14.1 g/dl ደርሶ ፅንሱ በሰላም ተወለደ።
ከተወለደ በኋላ፣ ሕፃኑ በህፃናት ጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል (NICU) ውስጥ ለብዙ ቀናት በጥንቃቄ ተከታተለ፣ በመጨረሻም በፎቶው ላይ የምታዩት ሕፃን በሙሉ ጤንነት እናት ከወራት ቆይታ ህጻንም ከአስራ አምስት ቀን የጽኑ ህሙማን ክፍል ቆይታ በኋላ ከሆስፒታላችን ወጥቶ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ በ ተሟላ ጤንነት ተመለሰ።
ይህ ዓይነት ሕክምና በሆስፒታላችን(በ ጥቁር አንበሳ) በትምህርትና በአገልግሎት መልክ እየተሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በሾተላይ ችግር ያጋጠማችሁ እናቶች ከየትኛውም አካባቢ ብትመጡ ተገቢውን ሕክምና ማግኘት ትችላላችሁ።
ዶር ሰይድ አራጌ
ረዳት ፕሮፌሰር ፣ የእናቶች እና ጽንስ ህክምና ሰብስፔሻሊስት
የማህጸንና ጽንስ ክፍል ኃላፊ

Am excited to share attending the 23 rd fetal Medicine Congress at UK, London,at Wembley stadium Great hall.It is one of...
07/12/2025

Am excited to share attending the 23 rd fetal Medicine Congress at UK, London,at Wembley stadium Great hall.
It is one of the world Congress with world wide experts presenting the latest updates , research findings.
It is a great experience to me as well to have updated knowledge and skills on the area of Maternal and fetal medicine.

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በክረምት ወቅት ሲሰጥ የነበረው ነጻ ህክምና አገልግሎት  በመላ አድስ አበባ ባሉ ክፍለ ከተማዎች ያዳረሰ ሲሆን  በዚህ ፕሮግራም የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ...
15/09/2025

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በክረምት ወቅት ሲሰጥ የነበረው ነጻ ህክምና አገልግሎት በመላ አድስ አበባ ባሉ ክፍለ ከተማዎች ያዳረሰ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ማድረግ ከነበረብኝ በታችም ተሳትፌ ይህን እውቅና ስለተሰጠኝ ከልብ እያመሰገንኩ ወደፊትም ለእንደዚህ አይነት በጎ ተግባር ከዚህ ይበልጥ ብተባበር ደስተኛ ነኝ።
I am truly honored by the recognition of my participation to the Summer Volunteers Medical Services program of AAU titled እሽ ለበጎ. It was a privilege and a responsibility to contribute, and I deeply appreciate the dedication of the volunteers and medical professionals who made such an impact.

ክቡራና ክቡራት ነገ በሚደረገው ደም ልገሳ ፕሮግራም ቤተል አደባባይ አድስ አበባ የምትችሉ ይህን ያነበባችሁየሚመቻቸውን በተለይ ደም ሰጥተው የማያውቁትን ይዛችሁ ኑ።ከጥዋት 3:30 ጀምሮ እንጠ...
06/09/2025

ክቡራና ክቡራት
ነገ በሚደረገው ደም ልገሳ ፕሮግራም
ቤተል አደባባይ አድስ አበባ የምትችሉ ይህን ያነበባችሁ
የሚመቻቸውን በተለይ ደም ሰጥተው የማያውቁትን ይዛችሁ ኑ።
ከጥዋት 3:30 ጀምሮ እንጠብቃችዋለን ።
በመምጣታችሁ ከልብ እናመሰግናለን ።
ያልቻላችሁ ደግሞ መስጠት ይልመድባችሁ።

ነጻ የደም ግፊትና ስኳር ምርመራም በእለቱ ይኖራል።
04/09/2025

ነጻ የደም ግፊትና ስኳር ምርመራም በእለቱ ይኖራል።

Address

Addis Ababa
7080

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Seid Arage posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram