Dr Mark

Dr Mark To support our society by giving updated information on different health issues.

በእርግዝና ጊዜ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ ምን ያህል ያውቃሉ? | Exercise in pregnancyበዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስትበእርግዝና ጊዜ የሚደረግ እንቅስቃሴ ጥቅሞች...
10/04/2022

በእርግዝና ጊዜ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ ምን ያህል ያውቃሉ? | Exercise in pregnancy
በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

በእርግዝና ጊዜ የሚደረግ እንቅስቃሴ ጥቅሞች

⁃ 👉በእርግዝና ጊዜ ያለ የጀርባ ህመም ይቀንሳል
⁃ 👉የሆድ ድርቀትን ይቀንሳል
⁃ 👉በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ሰኳር ፣ ግፊት እና በኦኘራሲዎን የመውለድ እድልን ይቀንሳል
⁃ 👉የልብንና የደም ቧንቧን ጥንካሬ ይጨምራል

እንቅስቃሴ ስናደርግ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

⁃ 👉ውሀ በደንብ እንቅስቃሴ ከመጀመራችን በፊት እንቅስቃሴ እያደረግን እና ከጨረስን በውሀላ መጠጣት አለብን።
⁃ 👉በተቻለ አቅም ቀለል ያለ ሙቀትን የማይስብ ልብስ አድርገን እንቅስቃሴ እናድርግ
⁃ 👉ሞቃት በሆነ አየር ወይም ክፍል እንቅስቃሴ አናድርግ
⁃ 👉ለብዙ ሰዐት መቆም እና ለብዙ ሰዐት ለጥ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ አይመከርም ምክንያቱም ደም ወደ ልባችን እንዳይመለስ ሰለሚከለክል

ነፍሰጡር እናት በሳምንት ምን ያህል ጊዜ መንቀሳቀስ አለባት?

⁃ 👉150 ደቂቃ መጠነኛ የሆነ ኤሮቢክስ(aerobics) መስራት ትችላለች ይህ ማለት 30 ደቂቃ በቀን እንደማለት ነው። ( መጠነኛ ሲባል ያለምንም ችግር ማውራት የምትችል ከሆነ ነገር ግን መዝፈን የሚከብዳት ከሆነ እንደማለት ነው)

እንቅስቃሴ ማድረግ የሌለባቸው ነፍሰ ጡሮች!

⁃ 👉ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ውርጃ ካጋጠመሽ
⁃ 👉በበፊት እርግዝናሽ ከ9 ወር በፊት ምጥ መቶብሽ የሚያውቅ ከሆነ
⁃ 👉የደም ምልክት በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት ከማህፀን ደም አይተሽ ከሆነ
⁃ 👉የእንግዴ ልጁ ከልጁ ቀድሞ የመጣ ከሆነ
⁃ 👉የማህፀን ጫፍ መሳሳት ወይም መቅጠን አለ ከተባልሽ
⁃ 👉የአስም በሽታ ፣ የስኳር በሽታ እና የልብ በሽታ አለብሽ ከተባልሽ
⁃ 👉መንታ እና ከዛ በላይ ያረገዝሽ ከሆንሽ

በእርግዝና ጊዜ የሚመከሩ የእንቅስቃሴ አይነቶች!

⁃ 👉ዋና
⁃ 👉ፈጠን ያለ እርምጃ
⁃ 👉የቤት ውስጥ ወይም በጂም ቤት ያለ ሳይክል መንዳት
⁃ 👉ከባድ ያልሆኑ የaerobics እንቅስቃሴዎች
⁃ 👉የጠረቤዛ ቴኒስ
⁃ 👉ዮጋ

የተከለከሉ እንቅስቃሴዎች!

⁃ 👉የፈረስ ግልቢያ
⁃ 👉እግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ እና የመረብ ኳስ
⁃ 👉ፈጣን ሩጫ፣ ዝላይ
⁃ 👉ከከፍታ ቦታ ላይ ዘሎ ዋና መግባት
⁃ 👉Gymnastic እንቅስቃሴዎች
⁃ 👉የሜዳ ቴኒስ

እንቅስቃሴ እያደረኩ ማቆም የሚገባኝ መቼ ነው?

⁃ 👉ደም ከማህፀን ከወጣ
⁃ 👉የማዞር ወይም እራስን መሳት ካለ
⁃ 👉አየር ማጠር
⁃ 👉የደረት ህመም
⁃ 👉እራስ ምታት
⁃ 👉የጡንቻ መዛል
⁃ 👉የምጥ ስሜት (ከእምብርት በታች ወደታች ጫን የሚል ስሜት ካለ)
⁃ 👉ውሀ የመሰለ ፈሳሽ ከማህፀን ከወጣ

ዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

 #ህፃናትን ካጠባን በዋላ እንዴት አርገን ማስገሳት አለብን❓️  #ህፃናትን ማስገሳትስ  #ጥቅም አለው ❓️🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸❤️  #ጨቅላ  #ህፃናትን ደስተኛ ለማድረግ በሰላም እንዲተኙ ጡ...
09/04/2022

#ህፃናትን ካጠባን በዋላ እንዴት አርገን ማስገሳት አለብን❓️ #ህፃናትን ማስገሳትስ #ጥቅም አለው ❓️
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸

❤️ #ጨቅላ #ህፃናትን ደስተኛ ለማድረግ በሰላም እንዲተኙ ጡት ማጥባት ወይም መመገብ ብቻ ሳይሆን ማስገሳትም ያስፈልጋል‼️

❤️ #ህፃናት የእናት ጡት ስጠቡም ሆነ ጡጦ ሲጠቡ አብረው አየር ሊስቡ እና ከወተቱ ጋር ሊውጡት ይቺላሉ::

🔷 ይህ አየር ወደ ጨጓራቸው ከገባ በዋላ በማስገሳት ካልወጣ ላቸው በከፍተኛ ሁኔታ ሊረብሻቸው ይቺላል

🔷 ማንኛዉም ህፃን ልጅ ከ 60-90 ሲሲ በላይ ከጠባ ማስገሳት ይመከራል

🔷 ህፃናት እየጠቡ ቢተኙ እንኩዋን ከ እንቅልፋቸው ሳንቀሰቅሳቸው ማስገሳት ይመከራል ‼️

🔷 በአግባቡ ከያዝናቸው አብዛኞቹ ህፃናት በጥቂት ደቂቃዎች ዉስጥ ያገሳሉ ሆኖም አንዳንድ ህፃናት ግን እስከ 20 - 30 ደቂቃ ሊፈጅባቸው ይቺላል እና ትንሽ ይታገሱ‼️

🔷 በተለይ እድሜያቸው ከ 1 አመት በታች የሆኑ ህፃናት የጨጓራቸው መጠን ዝቅተኛ ስለሆነ ከምግቡ ተጨማሪ አየሩ ገብቶ ካልወጣ ወይም ካላገሱ የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል

🔺 መነጫነጭ
🔺 ትውከት
🔺 ተደጋጋሚ ቅርሻት
🔺 ኃይለኛ ስቅታ
🔺 ሆድ ቁርጠት
🔺 ማልቀስ
🔺 እንቅልፍ ማጣት
🔺 የሆድ መንፋት እና የመሳሰሉት ምልክት ይኖራቸዋል

💙 ስለዚህ ማስገሳት ይሄንን ሁሉ የሚከላከል ከሆነ ካጠቡ በዋላ እንዴት አርገን እናስገሳ ቸው

🔷 ህፃናትን ለማስገሳት ሶስት አይነት ዘዴዎች አሉ ‼️

👉 #1. ካጠባን በዋላ ወደ ላይ ቀጥ አርጎ መቀፍ በመቀጠል

📌 የልጆዎን አገጭ የእርሶ ትከሻ ላይ ያሳርፉት
📌 ጀርባቸውን በእጃችን መታ መታ ማድረግ
📌 በመቀጠል ቀስ ብሎ ከፍዝቅ (ዘጭ ዘጭ)ማድረግ
📌 ይሄ ዜድ ለተኙ ህፃናት በጣም ተመራጭ ነው

👉 # 2. ልጅዎን እግርዎ ላይ ቁጭ በማድረግ በ አንድ እጅዎ አንገቱን እና ጭንቅላቱን ይደግፉ በሌላው እጅዎ ጀርባውን መታ መታ ያርጉ
📌 ይሄ ዜድ ለሁሉም ህፃናት ላይሆን ወይም ላይመቻቸው ይቺላል ሆኖም ከላይ ያለው የመጀመሪያው ዜድ ካልሰራ ይሄኛውን ዜድ ይሞክሩት
📌 አንዳንድ ህፃናት ልክ ሲያገሱ አብረው ትንሽ ቅርሻት(wet burning) ሊኖራቸው ይቺላል አንዳንዱ ደሞ ላይኖረው ይቺላል

👉 #3. ልጆን በሆዱ ጉልበቶ ላይ ያስተኙ እና በመቀጠል ጭንቅላቱን እና አንጀቱን ይደግፉ
📌 በመቀጠል ጀርባውን መታ መታ ያርጉ
📌 እግሮን ወደ ጎን ወደ ላይ ወደ ታች ማንቀሳቀስ
📌 ይሄ ዜድ ለሁሉም ህፃናት ላይሆን ወይም ላይመቻቸው ይቺላል
📌 በተለይ ለተኙ ህፃናት አይመከርም

👉 #4. ልጅዎን በእጅዎ ክንድ ላይ ያስተኙ እና ቀስ ብለው ያንቀሳቅሱ (በመጠኑ ከፍዝቅ ያድርጉት)

📞 "ሰላም ዶክተር ልጄ 1 ወሩ ነው አላገሳ ብሎኝ ተቸግሬያለሁኝ ምን ላድርግ ❓️" ይሄ ጥያቄ የ ብዙ እናቶች ጥያቄ ነው

🛑 አንዳንድ ህፃናት 20 -30 ደቂቃ ተይዘውም ላያገሱ ይቺላሉ ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው

🔘 የጡት/ጡጦ አያያዝ ችግር(ስያጠቡ)
🔘 ከላይ ያሉትን ዘዴዎችን በደንብ አለመተግበር
🔘 በቂ ወተት አለማግኘት
🔘 በተፈጥሮም ሊሆን ይቺላል
👉 ስለዚህ በጣም ከተቸገሩ ሀኪሞን በቅርበት ያማክሩ ‼️

"ህፃናትን በማከም ብዙ እድሜዬን ያሳለፍኩ ቢሆንም ለራሴ ልጅ ግን አልሆንኩለትም"ሰላም የሀኪም ገፅ ቤተሰቦች ፤ ስሜ ዶ/ር ሰገን ዮሐንስ ሲሆን የምሰራው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የ...
09/04/2022

"ህፃናትን በማከም ብዙ እድሜዬን ያሳለፍኩ ቢሆንም ለራሴ ልጅ ግን አልሆንኩለትም"

ሰላም የሀኪም ገፅ ቤተሰቦች ፤ ስሜ ዶ/ር ሰገን ዮሐንስ ሲሆን የምሰራው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትነት ነው።

ልጄ ሚካኤል ዳንኤል ከሁለት ሳምንት በፊት 8ተኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን 1 ዓመት ከ7 ወር በፊት ኤ ኤል ኤል (ALL) በሚባል የደም ካንሰር አይነት ከተገኘበት በኅላ ለህክምና ወደ ቱርክ በመሄድ ብዙ ወጪ በማውጣት ለ8 ወራት ኬሞቴራፒ ህክምና የወሰደ ሲሆን ከዛ ከተመለሰ በኀላም ህክምናውን በመከታተል ላይ ነበር።

ነገር ግን የዛሬ 3 ሳምንት አካባቢ እንደገና በሽታው መመለስ በማሳየቱ ይከታተሉት የነበሩ ሀኪሞኘች በአሁኑ ግዜ ኬሞቴራፒ ፣ ጨረር ህክምና እና የመቅኔ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልገው ተነግሮናል። ይህም ህክምና በሀገራችን የሚሰጥ ባለመሆኑ የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቦርድ ውሳኔ ወደ ውጭ ሄዶ እንዲታከም ወስኗል።

ለመቅኔ ንቅለ ተከላ የተጠየቅነው ዋጋ እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ እኔም የመንግስት ሰራተኛ በመሆኔ እና ለጤና ባለሞያ ምንም የጤና ኢንሹራንስ ባለመኖሩ ይህንን ለመሸፈን ተቸግሬአለሁ።

ህፃናትን በማከም ብዙ እድሜዬን ያሳለፍኩ ቢሆንም ለራሴ ልጅ ግን አልሆንኩለትም። በአቅማችሁ የተቻላችሁን እንድታግዙኝ ስል በትህትና ጠይቃለሁ። አመሠግናለሁ።

ዶ/ር ሰገን ዮሐንስ
1000155156965
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Gofundme: https://gofund.me/eaaac63b

02/05/2021

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል አደረሰን ፤ መልካም በዓል!!

የአስም በሽታና እርግዝናየአስም በሽታ በመላው ዓለም የሚታይ ሲሆን በአየር ብክለት ምክንያት መጠኑ እየጨመረ ይገኛል። አስም ያለባት ሴት ማረወገዝ ትችላለች ወይ?አዎንእርግዝና በአስም ላይ የሚ...
15/12/2020

የአስም በሽታና እርግዝና
የአስም በሽታ በመላው ዓለም የሚታይ ሲሆን በአየር ብክለት ምክንያት መጠኑ እየጨመረ ይገኛል።
አስም ያለባት ሴት ማረወገዝ ትችላለች ወይ?
አዎን
እርግዝና በአስም ላይ የሚያመጣው ችግር
አስም ካለባቸው ነፍሰ-ጡሮች ውስጥ
· ሲሶዎቹ (1/3)- ከበፊቱ የተለየ ህመም አይታይባቸውም
· ሲሶዎቹ - ይሻላቸዋል
· ሲሶዎቹ - ደግሞ በጣም ይታመማሉ።
በዚህ ምክንያት አስም ያለባት እናት በእርግዝና ጊዜ መድኃኒቷን እንዳታቋርጥ ይመከራል።
አስም በእርግዝና ላይ የሚያመጣው ችግር
አስም ያለባት እናት ከጤነኛዋ በበለጠ
· ለደም ግፊት
· ያለጊዜው መውለድ
· ክብደቱ ትንሽ የሆነ ወይም በማህፀን ውስጥ የቀጨጨ ህፃን
· ሲወለዱ የመታመምና የመሞት እድላቸው ከፍ ያሉ ህፃናትን የመውለድ እድል አላት።
መፍትሄው ፦ አስሙን በተቻለ አቅም እየተቆጣጠሩ ጥሩ የሆነ የእርግዝና ክትትል ማድርግ ይኖርባታል።
ቸር እንሰንብት
በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት. ጤና

Orthopaedic Surgeons @ Black Lion Hospital 🇪🇹.Medical Heroes
17/11/2020

Orthopaedic Surgeons @ Black Lion Hospital 🇪🇹.
Medical Heroes

"ልጆች እየተጫወቱ የባዕድ ነገር ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?" - ዶ/ርአቤል ግደይ ፤ የህፃናት ሐኪምባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦ ሲገባ ትንታን ያስከትላል። ይህ የአየር ወደ ሳንባመግባት...
01/11/2020

"ልጆች እየተጫወቱ የባዕድ ነገር ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?" - ዶ/ር
አቤል ግደይ ፤ የህፃናት ሐኪም
ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦ ሲገባ ትንታን ያስከትላል። ይህ የአየር ወደ ሳንባ
መግባትን በመከላከል እና ትንፋሽን በመቁረጥ የአተነፋፈስ ስርዓትን በማቆራረጥ
ለአዳጋ ያጋልጣል።
ለየት የሚያደርገው የአየር መግባት በመከልከል በአጭር ጊዜ ለሞት ሊያደርስን
ስለሚችል ነው። ለምሳሌ፦ አጥንት ፣ ክኒን ፣ ውሃ ፣ ኦቸሎኒ ፍሬ ፣ ስንዴ…
ሌሎችን ጠጣር ነገሮች ወደ አየር ቱቦ ሊገቡ እና ትንታን ሊያስከትሉ የሚችሉ
ናቸው።
የትንታ ምልክቶች
ልክ ባዕድ ነገሮች ወደ መተንፈሻ አካላት ሲገቡ የሚኖሩ ምልክቶች እነዚህ ናቸው
1. በሃይል ማሳል
2. መናገር አለመቻል
3. ጮክ ያለ ድምፅ
4. መጥቆር
5. ትንፋሽ ማጠር
6. ማላብ
7. ድንጋጤ
8. አንገት ማሳከክ
9. መፍጨርጨር
10. ቀልብን መሳት
11. ማንቀጥቀጥ
ግዜ ከወሰደ
•ተደጋጋሚ ሳል
•ሽታ ያለው ዓክታ
•ክብደት መቀነስ
•ትንፋሽ ማጠርና መድከም
የትንታ የመጀመርያ እርዳታ አሰጣጥ
1. ሁኔታውን መታዘብ
2. መጠየቅ
3. ሰዎች እንዲረዱን መጣራት
4. ጀርባ መምታትና ሆድን መጫን
አንድ ከእናንተ ጋር እየተመገበ የነበረ ሰው ድንገት ትን ቢለው በእነዚህ ከላይ
በተዘረዘሩ መንገዶች ማገዝ ይቻላል።
ልጆች እየተጫወቱ ቆይተው ክኒን ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?
1. ሁኔታን መታዘብ
• ምን እንደዋጡ መታዘብ
• ይህም ህክምና ሂደን ለማስረዳት ይረዳናል
• እርዳታ ሰጪ የአደጋ ምስክር እንደሆነ አስቡ።
2. መጠየቅ
• ምን እንደዋጠ መጠየቅ
ለምሳሌ ፍሬ ፣ ምግብ ፣ ድንጋይ
3. ሰዎች ለእርዳታ መጣራት
• እሪ ብሎ መጮህ እና ሰዎችን እርዳታ መጠየቅ
4. ጀርባ መምታትና ሆድ መጫን
• ሁኔታውን በፍጥነት በመረዳት ወደ እርዳታ መግባት ያስፈልጋል።
ሀ. ጀርባ መምታት
ትልልቅ ሰዎች እንዲያጎነብሱ በማድረግ ከታች ከሚታየው ስዕል አድርገን 5 ግዜ
ጀርባቸው መምታት ደጋግመን መተን ተስፈንጥሮ ከወጣ ጥሩ ካልሆነ ወደ ሆድ
መጫን መቀጠል።
ለ. ሂልማች ማኑቨር / ሆድ መጫን
ጀርባ ደጋግመን 5 ግዜ ከመታን በኃላ ቀጥለን ሆድን መጫን ያስፈልጋል። ይህ
መቆም በሚችሉ ሰዎች ጀርባ ከመምታት በኃላ የምንፈፅመው ይህ ባዕድ ነገር
መውጣት አለመውጣቱን ማየትና ካልወጣ እንዲወጣ እየመላለስክ መሞከር
ወሳኝ ነው።
ትንታ በማይቆሙ ህፃናት
ልክ ባዕድ ነገር ሲገባባቸው ቁልቁል ደፍተን ጀርባቸውን 5 ግዜ በመምታት
ከዛም ደረታቸውን እየደጋገምን ሌላ ጉዳት በማያስከትል መልኩ መጫንና
መጠፍጠፍ ይጠበቅብናል።
5. ህክምና መሄድ
አንድ ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦው የገባበት ሰው ወደ ህክምና መሄድ አለበት።
ሳንባ ቁስለት እንዳይፈጥርበት ሃኪም ሊያየው ይገባል።
የመጀመርያ እርዳታ የመጨረሻ አይደለም!

"የህጻናት አስም" - በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ : የህጻናት እስፔሻሊስት ሀኪም- አስም ምንድን ነው?አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎችተጽእኖ ከሚገባው በላይ ...
31/10/2020

"የህጻናት አስም" - በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ : የህጻናት እስፔሻሊስት ሀኪም
- አስም ምንድን ነው?
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች
ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገት ለተወሰነ ጊዜ መጥበብ ነው። ይህ የአየር
ቧንቧ ጥበት መድሀኒት ሲዎስዱ ወደ ነበረበት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል
ነው።
- ምክንያተ መንስኤ
ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ፣ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ በሆኑ ምክንያቶች ይነሳል።
የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ቁስለት/ብግነት በማጋለጥ
አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋጭ ጥበት እና
የቆሸሸ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ አለመውጣት ሳል እና የመታፈን
ምክንያትን ያመጣል። ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ ምክንያቶችን መቀነስ ይቻላል።
- የአስም አይነቶች
1. በተደጋጋሚ የሚነሳ አስም/recurrent asthma/seasonal
ይህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚያስነሱት አስም ነው። ቀስቃሽ ምክንያቶችን
በመቀነስ ድግግሞሹን መቀነስ እና ደረጃውንም መቆጣጠር ይቻላል።
2. ረጅም ጊዜ የቆየ አስም /chronic asthma
ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስም
- አለርጅ/አስም ቀስቃሾች ምንድን ናቸው?
1. የሲጋራ ፣ የከሰል እና የማገዶ ጭስ
2. የአበባ፣ቆሻሻ፣ የፅዳት መጠበቂያ/ዴቶል/ ፣ የሽቶ እና ላበት ማጥፊያዎች ሽታ
3. ላባ እና ጸጉር ያላቸው የቤት እንስሳት
4. የከብቶች ሽንት እና አዛባ
5. በረሮ የሚረጨው ኬሚካል
6. እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
7. የጉንፋን ቫይረስ
8. የኬሚካል ሽታ
9. ጭንቀት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
10. ሻጋታ
11. የጨጓራ አሲድ ቅርሻ/Gastro esophageal reflux disease
12. የአፍንጫ አለርጅ እና ሳይነስ ህመም
- ለአስም አጋላጭ ሁኔታዎች
1. የቆዳ አለርጅ/የቆዳ አስም
2. የአፍንጫ እና አይን አለርጅ
3. የምግብ አለርጅ
4. አስም ያለበት እናት ፣ አባት ፣ እህት ወይም ወንድም
5. ከጉንፋን ጋር የማይያየያዝ ሳል
- የህመም ምልክቶች
1. በቅዝቃዜ ወቅት እና ማታ ማታ የሚባባስ ደረቅ ሳል
2. የደረት መጨነቅ/የመታፈን ስሜት
3. የትንፋሽ መፍጠን
4. የድካም ስሜት
5. የሰውነት መዛል እና ላበት
6. ሙዚቃዊ ትንፋሽ
7. ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣ እና አቅልን መሳት
- አስም አመላካች ነገሮች ምን ናቸዉ
1. በጥርጣሬ የአስም መድኃኒት ሲሰጥ በቶሎ የሚሻል ከሆነ
2. ወላጅ አስም ወይም አለርጅ ካለበት
3.ነባር የትንፋሽ አለርጅ ካለ
4. ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አለርጅ:
- ህጻናት ላይ አስም ይምንለው በአመት ውስጥ ሶስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የሆነ
ሀኪም ያረጋገጠው የመተንፈሻ አለርጅ ካለ ነው።
- አስምን በምን እናረገግጣለን
1. የሳንባ ምርመራ:
በጤንነታቸው ወቅት ያላቸው የሳንባ አየር የማስገባት እና የማስወጣት
የመጨረሻ አቅም ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል በህመሙ ምክንያት ቀነሰ የሚለውን
በመለካት።
2. የአየር ቧንቧ ለትንፋሽ ቧንቧ አስፊ ህይዎት አድን መድሀኒት ያለውን ፈጣን
ምላሽ በማየት።
3. በአለርጅ አምጭ/ቀስቃሽ መድሃኒት አስም የመከሰት እድሉን መሞከር(ይህ
ምርመራ ብዙ አይመከርም)
4. በእስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያለውን የተቃጠለ አየር የማስውጣት አቅም
በመለካት።
- የአስም ህክምና
1. የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች
2. የአየር ቧንቧ ቁስለትን/ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒት
3. አለርጅን የሚቀንስ መድሃኒት
4. አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
5. ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ
መከላከል
6. በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል
መድሃኒት መስጠት
- እንደ መውጫ
የህጻናት የመተንፍሻ ቱቦ በተፈጥሮ ጠባብ በመሆኑ ምክንያት አስም ጋር
የሚመሳሰሉ ብዙ ህመሞች ስላሉ አስም አለ የምንለው በታፈኑ ወቅት በአስም
መድሀኒት ያላቸው ለውጥ አመርቂ ከሆነ እና ለአስም ተጋላጭነት ካላቸው ነው።
እድሜያቸው ከ4 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሳንባን በአግባቡ መስራት ወይም
አለመስራት ለማወቅ ለምርመራ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ በብዛት በክትትል
ብቻ ነው መለየት የሚቻለው። አካባቢያዊ አስም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን
በማስተካከል አስምን መከላከል ዉጤታማ ነው።

28/10/2020

የጡት ካንሰር በወንዶች ላይ ይከሰታልን?የወንዶች የጡት መጠን አንዲት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ሴት የሚኖራትንያህል ጡት ነው፡፡ በዚህም የተነሳም መጠኑ ከሴቶች በጣም ያነሰ ይሁን እንጂወንዶች...
24/10/2020

የጡት ካንሰር በወንዶች ላይ ይከሰታልን?
የወንዶች የጡት መጠን አንዲት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ሴት የሚኖራትን
ያህል ጡት ነው፡፡ በዚህም የተነሳም መጠኑ ከሴቶች በጣም ያነሰ ይሁን እንጂ
ወንዶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድል አላቸው፡፡
የወንዶችን የጡት ካንሰር ከሴቶች አቻወቻቸው በምን ይለያል?
1.የወንዶች የጡት ካንሰር ከጠቅላላው የጡት ካንሰር 5% ወይም አንድ ወንድ
የጡት ካንሰር ሲከሰት በሴቶች ደግሞ ከ150-200 ሴቶች ላይ ድረስ ይከሰታል
(1∶150-200) ፡፡
2.በወንዶች ላይ የሚከሰተው የጡት ካንሰር በአብዛሃኛው ጊዜ የሚታወቀው
(Diagnose) የሚደረገው ዘግይቶ ነው፡፡ ለዚህም እንደዋነኛ ምክንያት
የሚቀመጠው ወንዶች በጡት ካንሰር እንያዛለን ብለው ስለማያስቡና ተገቢውን
ምርመራ በጊዜ ስለማያደርጉ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው
የሴትና የወንድ የጡት ካንሰር ተማሳሳይ ህክምናና የመዳን እድል አለው፡፡
የወንዶች የጡት ካንሰር አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
የእድሜ መጨመር (ብዙው የጡት ካንሰር የሚከሰተው ከ 60 አመት በላይ
በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው)
የጡት ካንሰር በቤተሰብ (አባት፤ እናት፤ እህት፤ወንድም) ውስጥ መኖር
ጡት ወይም ደረት አካባቢ በልጅነት የጨረር ህክምና ማድረግ
በተለያዩ መድሀኒቶች ወይም ኢንፌከሽን ምክንያት የጡት መጠን መጨመር
(Gynecomastia)
ኢስትሮጅን የሚባል መድሀኒትን መውሰድ
ከልክ ያለፈ ውፍረት
እና ሌሎችም
( በዶር አብዱ አደም - የካንሠር ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም)

የልጆች ስቅታ (Hiccup) መንስኤው ምንድነው እንዴትስ ማቆም እንችላለን?ስቅታ በአዋቂም ሆነ ልጆች ላይ ሊታይ የሚቺል ብዙ ጊዜ ጤናማ እና ተፈጥሯዊ ምላሽ (reflex) ሲሆን አዋቂ ሰዎችን...
23/10/2020

የልጆች ስቅታ (Hiccup) መንስኤው ምንድነው እንዴትስ ማቆም እንችላለን?
ስቅታ በአዋቂም ሆነ ልጆች ላይ ሊታይ የሚቺል ብዙ ጊዜ ጤናማ እና ተፈጥሯዊ ምላሽ (reflex) ሲሆን አዋቂ ሰዎችን እንደሚረብሽው ግን ህፃናትን ብዙ ጊዜ አይረሻቸውም እንደውም ህፃናት ስቅ እያላችው ጥሩ እንቅልፍ መተኛት ይቺላሉ።
ህፃናት ስቅታ የሚጀምራቸው ገና በእናት ማህፀን እያሉ ነው (ከ6 ሳምንት ጀምሮ) ስለዚህ ለነሱ በጣም ቀላል እና የለመዱት ነገር ነው ስለዚህ ብዙ መቸነቅ አይገባም።
ስቅታ የሚመጣው እንዴት ነው? ስቅታ የሚከሰተው ዲያፍራም የሚባለው ሳንባችን ከታች ደግፎ የሚገኘው ጡንቻ ድንገት ስኮማተር እና ቮካል ኮርድ የሚባለው የአየር መግቢያ ድንገት ሲዘጋ ነው።
ልጆች ስቅታስ መንስኤው ምንድነው?
1. ቶሎ ቶሎ እና ብዙ ምግብ መመገብ: ቶሎ ቶሎ ብዙ ጡት ወይም ጡጦ መጥባት ይህም ብዙ አየር ወደ ጨጓራ እንዲገባ እና ዲያፍራም የሚባለው ሳንባችን ከታች ደግፎ የሚገኘው ጡንቻ ድንገት እንዲኮማተር ያደርጋል።
2. ህፃናት የሚያስደስታቸውን ወይም ለየት ያለ ነገር ሲያገኙ( excitement)
3. ህፃናት ሙቀት በተለይ ሆድ አካባቢ ያለ ሙቀት በድንገት መቀነስ እና የመሳሰሉት ናቸው
ልጆች ስቅታስ መፍትሄው ምንድነው?
1. ጡት ወይም ጡጦ ቀጠባ በዋላ በደንብ ማስገሳት የአሜሪካ የህፃናት ሕክምና ማህበር አንድ ህፃን ከ60 ሚሊ ሊትር በላይ ተጠባ በደንብ ማስገሳት እና ልጁን ከ 20-30 ደቂቃ ቀና አድርጎ(upright position) ማስቀመጥን ይመክራል።
2.ልጆች በጣም ሳይርባቸው መመገብ ወይም ማጥባት መሃል ላይ ስቅታ ከጀመራቸው ማጥባቱ ቆም አድርጎ ማስገሳት እና ትንሽ ቆይቶ ማጥባት
3. የእንጀራ እናት (Pacifier, dummy) መስጠት: ይሄ መፍትሄ እድሜያቸው ከ1 ወር በታች ላሉ ህፃናት እና ባጠቃላይ እንደኛ ላሉ ሃገራት ላይ ከንፅሕና ጋር ተያይዞ ብዙም አይመከርም ሆኖም ልጅን ለማረጋጋት ተብሎ እንድ አማራጭ ይቀርባል
4. ዋናው መፍትሄ ግን ወላጆች ስቅታ ቀላል እንደ ሆነ ልጁ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ማወቅ እና 5-10 ደቂቃ ዉስጥ እንደሚቆም ማወቅ እና በመረጋጋት ልጃቸውን ማጫወት ማዝናናት አለባቸው። ከነዝህ ዉጭ ያሉት ባህላዊ መንገዶችን ባንጠቀም ይመከራል
ስቅታ መቼ ነው መታከም ያለበት?
1. የተከሰተው ልጁ 1 ዓመት እድሜ በላይ ከሆነ እና ስቅታው በጣም ተከታታይ ከሆነ
2. ህፃኑ እድሜው ከ1 ዓመት በታች ሆኖ ከ ስቅ ታው ጋር ተደጋጋሚ ትውከት ቅርሻት ሳል እና መነጫነጭ ካለው ምን አልባት ከ ጨጓራ ችግር (GERD) ጋር ሊያያዝ ይቻላል እና ሀኪምን ማማከር ተገቢ ነው።
ዶ/ር ፋሲል መንበረ ፤ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም
Hello ጤና

በእርገዝና ወቅት የሚታዩ 7 ጤናማ ለውጦች1. በደቂቃ ውስጥ ያለው የልብ ምት እና የትንፋሽ መጠን ይጨምራል2. በመጀመሪያውና በመጨረሻው የእርግዝና ወራት የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት3. የእግር ...
23/10/2020

በእርገዝና ወቅት የሚታዩ 7 ጤናማ ለውጦች

1. በደቂቃ ውስጥ ያለው የልብ ምት እና የትንፋሽ መጠን ይጨምራል
2. በመጀመሪያውና በመጨረሻው የእርግዝና ወራት የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
3. የእግር ማበጥ
4. የእንቅልፍ መዛባት
5. የምግብ ፍላጎት
ሀ. የመጀመሪያዎቹ ወራት - መቀነስ
ለ. የመጨረሻዎቹ ወራት - መጨመር
6. የምግብ ቶሎ አለመፈጨት
7. የሆድ ድርቀት ብዙ ነፍሰ-ጡሮች ላይ የሚታዩ ለውጦች ናቸው፡፡

(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት) ፡፡
Hello ጤና

Address

Bo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Mark posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram