Woba Ari Worda Health Office page 2012

Woba Ari Worda Health Office page 2012 Boyka

15/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ዘዴዎች

‎🔴 #አስቸኳይ  #ጥንቃቄ መልዕክት‼️‎‎በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰ...
13/11/2025

‎🔴 #አስቸኳይ #ጥንቃቄ መልዕክት‼️

‎በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ ጋዜጣዊመግለጫ

‎የጤና ሚኒሰቴር፥ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን እንዳይከሰቱ የመከላከል እና ከተከሰቱም በአፋጣኝ የማረጋገጥና የተቀናጀ የቅኝትና የምላሽ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

‎በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrከagic Fever) በሽታ መከሰቱን የቅኝት መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች (08) በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑ ታውቋል።

‎በዚህም መሰረት የጤና ሚኒሰቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብኢትዮጵያ ክልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደ ቦታው በመላክ የመስከ ግምማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እያከናወነ ሲሆን በተጨማሪም የማህበረሰብ ቅኝት፣የንክኪ ልየታ፡የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ ይገኛል።

‎በመሆኑምመላዉ ሕብረተሰባችንና የሚመለከታቸዉ የባለድርሻ አካላት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ፣ድረስ፤ ለመከላከል የሚከተሉትን ምከረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡

‎ #በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ

‎ #ምልከት ሲኖር ወደ ህከምና፣ተቋማትና መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንከኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣

‎ #ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት፣

‎ #ማንኛውም ጤና ተቋም በታካሚዎች ልየታ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሻይራል ሄሞሬጅክ ፊሸር (ViralHemmoragic Fever) መሰል በሸታ መለየት፣ መመርመር፣ማከም እና ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል።

‎ተጨማሪ መረጃዎችን ወደ 8335 እና 952 ነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ማግኘት ይቻላል።

‎ዶ/ር መቅደስ ዳባ
‎የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር
‎ህዳር 03/2018 ዓ.ም
‎አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  ምንድን ነው?‎‎ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላት...
13/11/2025

ምንድን ነው?

‎ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላትን በማጥቃት እና በሰውነት ውስጥ ያሉ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ፣ በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው።

#‎የበሺታው_መንስኤ እና የቫይረስ ዓይነት

‎. Ebola and ,Rift Valley Fever (RVF) & Yellow Fever ተብሎ የሚከፈል ሲሆን እንደ #ኢቦላቫይረስ ፣ #ደንጉ እና #የለውፊቨር የተባሉ ቫይርሶች የበሺታው መንስኤ ሲሆኑ #በትንኝ ንክሻም የሚመጡ ናቸው ።

‎ በሽታው ስሙ እንደሚያመለክተው በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም እንዲፈስ በማድረግ ለሞት የሚዳርግ ህክምና አልባ አደገኛ በሺታ ነው።

‎በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም መድማት እና መፍስሥ ከተከሰተ የበሽታው ከባድ ደረጃ ምልክት ነው።

‎በሽታው እንዴት ይተላለፋል?

‎1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
‎2· በነፍሳት ንክሻ፡
‎3· ከሰው ወደ ሰው፡ ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።



‎ምልክቶቹ በድንገት ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ በተጠቃ ከ 2-21 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ

‎መጀመሪያ ላይ የሚታዩ ምልክቶች
‎ምልክቶቹን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን
‎የመጀመሪው ቀለል ያሉ ምልክቶች እና የመጨረሻው አደገኛ //አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚታዩ ናቸው


‎· ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
‎· ድካም እና የመዛል ስሜት
‎· የጡንቻ፣ የአጥንት ህመም እና ቁርጥማት
‎· ራስ ምታት
‎· የጉሮሮ ህመም

‎ (በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ)፡

‎· በቆዳ ስር ደም መውጣት
‎. ከአፍ፣ አፍንጫ፣ ከዓይን ወይም ከጆሮ ደም መፍሰስ።
‎· የጭንቅላት አዕምሮ መናጋት ፣ መደንገጥ፣
‎. ራስን መሳት ኮማ ውስጥ መግባት)
‎· የኩላሊት እና የጉበት መጎዳት እና ስራ ማቆም
‎· ከፍተኛ ድካም እና ሾክ/Shock
‎· የበርካታ አካላት አለመሥራት

‎እንዴት መከላከል ይቻላል ?

‎በሽታው በትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በመሆኑ ነፍሶን ከሞት መታደግ ስለሆነ በአግባቡ ይጠቀሙት ። ከታማሚ ሰው ጋር ያልዎትን ንክክ መከላከል እና
‎አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ሆኖ ፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ፣
‎መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !

‎ የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል !!

‎1. እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
‎2. ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣ ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
‎ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
‎3. ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
‎4.ከ ነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር መጠቀም፡ ነፍሳት እና ወረርሽኙ ወደተከሰተበት ቦታ ፈጽሞ አይሂዱ ፣ ደገኛ ነው ፣ የመተላለፍ እድሉ አደገኛ ነው። ለህክምና ባለሙያዎች መከላከያ ይጠቀሙ እና ሙሉ አካላትዎን የሚደብቁ ልብሶች ይልበሱ

የአጥንት መሳሳት ምንድን ነው?👉በሕክምናው ኦስቲዮፖሮሲስ(Osteoporosis) ይባላል👉የአጥንት የሚነራል ክምችት (Bone mineral density) በእጅጉ በመቀንሱ ምክንያት የሰውነታችን ...
01/08/2025

የአጥንት መሳሳት ምንድን ነው?

👉በሕክምናው ኦስቲዮፖሮሲስ(Osteoporosis) ይባላል

👉የአጥንት የሚነራል ክምችት (Bone mineral density) በእጅጉ በመቀንሱ ምክንያት የሰውነታችን የአጥንት በመሳሳቱ ምክንያት ይከሰታል።

👉አጥንቶቻችን በየጊዜው ራሳቸውን የሚገነቡ ሲሆን ነገር ግን አዲስ አጥንት መተካት ሳይችል ሲቀር የአጥንት መሳሳት ይከሰታል ።

✅️ማንን ያጠቃል?

👉የአጥንት መሳሳት ሴቶችም ወንዶችም ላይ ሊከሰት ይችላል

👉በተለይም እድሜያቸው ገፋ ያሉ ሴቶች ላይ እና ከማረጥ በዃላ (post menopause) ፣ የኢስትሮጅን ሆርሞን (Estrogen hormone) እየቀነሰ ስለሚሄድ ለዚህ ችግር ይጋለጣሉ

👉ወንዶች ላይ ደግሞ የቴስቴስትሮን ሆርሞን (testesretone hormone) ማነስ መንስኤ ሊሆኑ።

👉ለአጥንት መሳሳት የሚያጋልጡን ተጨማሪ ነገሮችስ?

-የተመጣጠነ ምግብ እጥረት (Malnutrition)

-መድሀኒቶች ለምሳሌ Corticosteroid የምንላቸው በተለይ አሁን አሁን ሴቶች ክብደት ለመጨመር እያሉ እየተጠቀሟቸው በመሆኑ አደጋ እንዳላቸው ሊታወቅ ይገባል

-ለቀላሉም ለከባዱም ህመም በተደጋጋሚ የምንወስዳቸው ማስታገሻዎች ፣ ለአስም የሚወሰዱ, በተጨማሪ የሚጥል በሽታ መድሀኒቶች:የካንሰር ሕክምና መድኃኒቶች :PPI የሚባሉ የጨጓራ መድሃኒት ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ ወዘተ

-ሲጋራ ማጨስ ፣ አልኮል መጠጥ

-የኩላሊት ፣ የጉበት ችግር ፣ የአንጀት መቆጣት እንዲሁም ሌሎች Autoimmune diseases ችግሮች

✅️ምልክቶቹስ?

👉በብዛት የአጥንት መሳሳት ስበራት እስኪኖር ድረስ ምልክት ላያሳይ ይችላል።

👉ምልክት የሚያሳይ ከሆነ አጥንት አካባቢ የህመም ስሜት ፣ የቁመት መቀነስ

👉በመውደቅ ወይም በግጭት አንዳንዴ ጎንበስ ስንል እንኳን የአጥንት መሰበር በተለይም የጀርባ አከርካሪት እና የዳሌ አጥንት ስብራት ሊያጋጥም ይችላል

👉የሰውነት መጉበጥ

✅️እንዴት መከላከል እንችላለን?

-በቂ የሆነ የፀሀይ ብርሀን ማግኘት ለአጥንት ጥንካሬ በጣም ወሳኝ የሆነውን ቪታሚን D እንድናገኝ ይረዳል

-በካልሽየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ ወተት እና የወተት ተዋፅኦ ፣ የአሳ ምርቶች እንዲሁም

-በቂ የአካል በቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

-ተመጣጣኝ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ማድረግ

-ቡና እና ጨው አለማብዛት ምክንያቱም ካልሽየም በብዛት በሽንት እንዲወጣ ስለሚያደርጉ

✅️የአጥንት መሳሳት መኖሩ እንዴት ይረጋገጣል?

-የአጥንት ሚንራል ክምችት በcentral dual-energy x-ray absorbitometry (DXA) ታይቶ መረጋገጥ ይችላል።

✅️ህክምናውስ?

-ከሁሉም በላይ ይሄ ችግር ያለባቸው ሰዎች ስብራት እንዳይከሰት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው

-አጥንት እንዲጠነክር እና የስብራት ተጋላጭነት አንዲቀንስ የሚያደርጉ መድሀኒቶች መስጠት

- የአጥንትን የሚነራል ክምችት ሙሉ በሙሉ መመለስ ባይቻልም በተወሰነ መለኩ መመለስ ይችላል።

-ያረጡ ሴቶች ላይኤስትሮጅን ሆርሞን (Estrogen) የመተካት ህክምና

-ስብራት ካለ ስብራቱን መጠገን ነገር ግን በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ስብራት ከተከሰተ በዃላ መጠገን እና ወደነበረበት መመለስ ጊዜ የሚወስድ እና ትንሽ ከበድ ስለሚል መጠንቀቅ ይገባል።

  | እርግዝና ሊፈጠር የሚችልባቸውን ቀናት ታውቂያለሽ?🚻ሰላም ውድ የገፃችን ተከታታዮች በዛሬዉ ፅሁፌ ይዤላችሁ የቀረብኩት የወር አበባን መሠረት ያደረገ እርግዝና ሊፈጠርና ላይፈጠር የሚችሉባ...
30/07/2025

| እርግዝና ሊፈጠር የሚችልባቸውን ቀናት ታውቂያለሽ?

🚻ሰላም ውድ የገፃችን ተከታታዮች በዛሬዉ ፅሁፌ ይዤላችሁ የቀረብኩት የወር አበባን መሠረት ያደረገ እርግዝና ሊፈጠርና ላይፈጠር የሚችሉባቸውን ቀናት ለይተን ለማወቅ የሚረዳ ግንዛቤ ለመፍጠር ነዉ::

ይህ መረጃ ሁለት ጥቅሞች አሉት አሉት:: እነርሱም እርግዝናን ለመከላከል ወይንም እርግዝናን ለመፍጠር ይጠቅማል::

🚫 እርግዝናን ለመከላከያነት እንድትጠቀሙበት አንመክርም:: በማወቅ ደረጃ ብቻ ቢሆንና ወደ ተግባሩ ለመሄድ አደጋ እንዳለው ከወዲሁ እንድትገነዘቡ ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ ምክንያቱም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህን እርግዝና መከላከያ መንገድ ከተጠቀሙ 100 ሴቶች ዉስጥ እስከ 30 የሚሆኑት ሊያረግዙ ይችላሉ::

✅ነገር ግን በተቃራኒዉ ማርገዝ ለሚፈልጉ ይህንን መንገድ ቢጠቀሙበት ጥሩ እንደሆነ እንመክራለን::

🚻በትክክል እርግዝና ሊፈጠርበት የሚችሉት ቀናት ኦቪውሌሽን (እንቁላል የምትለቀቅበት ለማለት ነዉ) ከተከሰተ በሗላ ነዉ፡፡ ኦቪውሌሽን (Ovulation) የሚከሰትበት ቀን አንዲት ሴት ልጅ የወር አበባ ካየችበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ14ኛው ቀን አካባቢ ይከሰታል፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ የማርገዝ ዕድል የሚኖርባቸው ቀኖች የወር አበባ በኋላ ባሉ ከ8-10 ቀኖች ነው (የወር አበባዎ ለመቆም ከ4-6 ቀኖች የሚፈጅበት ከሆነ)፡፡ ነገር ግን ረዘም ያለ የወር አበባ ጊዜ ካለዎት ኦቪውሌሽን የሚከሰትበትም ጊዜ ስለሚረዝም የወር አበባዎን አማካኝ እርዝመት ማወቅ አለብዎት፡፡ ይህንን ለማወቅ ቢያንስ ከ6-12 ወር ያለዉን የቀናት እርዝመት በአማካይ በመዉሰድ ነዉ::

✅የሚከተለው መረጃ ከወር አበባ በኋላ እርግዝና የሚፈጠርባቸውን ቀኖች የሚያሳይ ሲሆን መሰረት ያደረገው በየ 28 ቀን የወር አበባዋን ለምታይ ሴት ብቻ ነው፡፡

💠ከቀን 1-5 (የወር አበባ ከፈሰሰበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ቀን) = የወር አበባ መፍሰሻ ጊዜ (Menstrual Bleeding time) ነው::

💠ከቀን 6-9 = በንጽጽር እርግዝና የማይፈጠርበት ጊዜ (Relatively Infertile) ነው፡፡

💠ከቀን 10-12 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር የሚችልበት ጊዜ (Relatively Fertile) ነዉ::

💠ከቀን 13-15 = በነዚህ ቀኖች ከሌሎቹ ቀናት በተሻለ እርግዝና የሚፈጠርበት ጊዜ (Most Fertile) ነዉ::

💠ከቀን 16-19 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር የሚችልበት ጊዜ (Relatively Fertile) ነዉ::

💠ከቀን 20-28 = በነዚህ ቀኖች እርግዝና የማይፈጠርበት ጊዜ (Infertile) ነዉ:

✔ #ማስታወሻ
🌐ትክክለኛው የኦቪውሌሽን ጊዜ የሴት እንቁላል የወንድ የዘር ፍሬን ዝግጁ ሁኖ የሚጠብቅበት ጊዜ ሲሆን ይህም ጊዜ ከ 12 – 24 ሠዓት ብቻ ይረዝማል፡፡ ምክንያቱም የወንድ የዘር ፍሬ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ በሴት ሰውነት ውስጥ እስከ ሶስት (3) ቀናቶች ብቻ መቆየት ይችላል:: ነገር ግን የሴቶች ዕንቁላል ደግሞ ከ 12 ሰአት እስከ 24 ሰአት ብቻ ነዉ ሊቆይ የሚችለዉ፡፡ ስለዚህ ሊያረግዙባቸው የሚችሉ እስከ አምስት(5) የሚደርሱ ቀኖች አሉ ማለት ነው፡፡

መልካም ጤንነት!!

┄✽┄
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!

የዎባ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የአንጀት ጥገኛ ትላትል ክትባት ዘመቻ ኦሬንቴሽን ለጤና ኤክስቴንሽንና ለጤና ባለሙያዎች መስጠቱን አስታወቀ ።ሰኔ 6/2017 ዓ/ም      ቦይካበመድረኩ መክፈቻ ...
13/06/2025

የዎባ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የአንጀት ጥገኛ ትላትል ክትባት ዘመቻ ኦሬንቴሽን ለጤና ኤክስቴንሽንና ለጤና ባለሙያዎች መስጠቱን አስታወቀ ።

ሰኔ 6/2017 ዓ/ም
ቦይካ

በመድረኩ መክፈቻ ክቡር የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሕዝቅኤል ጋርታ እንደተናገሩት ከቅርብ ግዜ ወዲህ ጀምሮ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ እና እየተስፋፋ ሕዝብን እያመሰ ካለዉ የወባ በሽታ ወረርሽኝ በተጨማሪ በወቅታዊነት የአንጀት ጥገኛ ትላትል እየተስፋፋ መሆኑን ተከትሎ የክትባት ዘመቻ በሁሉም ቀበሌ ከቀን 9-15/10/2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚካሄድ ገልፀዉ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የየበኩላቸውን ሚና እንድወጡም ጥብቅ መለዕክትም አስተላልፈዋል ።

አቶ ዳንኤል ገበየዉ የጤና ጽ/ቤት አክለዉ በመንግስት በጀት ድጎማ በነፃ የሚታደሉ መድሐኒቶች ዋጋቸዉ ዉድ ከመሆኑ የተነሳ በግለሰብ ደረጃ ለመግዛት የማይቻል መሆኑን በመገንዘብ ህፃናትንና ክትባቱ የሚዳስሳቸዉ የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍልን በሙሉ በማስከተብና በመከተብ የዜግነት ግዴታቸዉን እንድወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በስተመጨረሻም ለዘርፉ ሥራ ለባለሙያዎች ስምሪት በመስጠትና ያለፉ ግዜያት ጉዴሌቶችን ለማረም አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለተግባራዊነቱ አስፈፃሚ ግብረሃይል እና ኮማንድ ፖስት በማቋቋም መድረኩን መቋጨቱን ተናግረዋል ።

የዎባ ኣሪ ወረዳ"ወባን መከላከል ከእኔ ይጀምራል "በሚል መርህ ቃል የወባ በሽታ መከለል ዘመቻ ቅድመ ዝግጅ መርሃግብር ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄዴ ።ግንቦት 26/2017 ዓ/ም   ...
03/06/2025

የዎባ ኣሪ ወረዳ"ወባን መከላከል ከእኔ ይጀምራል "በሚል መርህ ቃል የወባ በሽታ መከለል ዘመቻ ቅድመ ዝግጅ መርሃግብር ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄዴ ።

ግንቦት 26/2017 ዓ/ም
ቦይካ

በመድረኩ መክፈቻ ክቡር የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሕዝቅኤል ጋርታ እንደተናገሩት ከቅርብ ወራት ጀምሮ ሕብረተሰባችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያመሰና ለበርካቶች የሕወት መቀጠፍ እየሆነ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለዉን የወባ ወረርሽኝ ለመግታትና የአምራቹን ኃይል አቅም በማዳከም ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ቀዉስ እያስከተለ የሚገኘዉን የወባ በሽታ ለመከላከል ዘላቂዉ መፍትሔ ሕክምና ሳይሆን ከቤት ጀምሮ አካባቢያችንን ፅዱ ማድረግ እንደሆነ በማስገንዘብ የመንግስት ተቋማትንና ባለሙያን ጨምሮ ለአንድ ሳምንትየፅዳት ዘመቻ እንድያካህድና የዘርፉ ባለሙያዎችም የግንዛቤ ሥራዎችን አጠናክረው እንድሠሩ መለዕክት አስተላልፈዋል ።

አክለዉም ይኸንን የወባ በሽታ ወረርሽኝ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ነገ የእያንዳንዳችን በር ሳያንኳኳ የማይቀር እንደሆነ በመገንዘብ የሚንወዳቸዉን ከማጣትና በሕክምና ላልተፈለገ ወጪ ከመዳረግ የተሻለዉ አማራጭ ቤትንና አካባቢን ማፅዳት በእጃችን ያሉ አጎበሮች በማጠብና በመስፋት በአግባቡ በመወጠር መጠቀም መቻል የመጀመሪያ የመከላከል ሥራ በመሆኑ ልተኮርና ልዘወተር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል ።

በተጨማሪም የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ መምህሩ ጌታቸዉ እንዳሉት የሕዝብን ቁጥር በፍጥነት ከመቀነሱም በጤና መናጋት የማምረት ምጣኔ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ያለ ወቅታዊ ወረርሽኝ በመሆኑ ችላ ማለት እንደማያስፈልግና ከጤና ባለሙያዎች የሚተላለፉ ምክረ ሀሶቦችን በመተግበር የራሳችንና የቤተሰቦቻችንን ብሎም የሕብረተሰባችንን ደኅንነት ለመታደግ የበኩላችንን ሚና ለመወጣት ወባን መከላከል ከእኔ ይጀምራል ዘመቻን ተግባራዊ ልናደርግ ያስፈልጋልም ብለዋል ።

በስተመጨረሻም ክቡር አቶ ዳንኤል ገበየዉ የወረዳው የጤና ጽ/ቤት አያይዘዉ ከነገ ጀምሮ በሁሉም በኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል በሁሉም ቀበሌ የፅዳት ዘመቻዉንና የሕክምና አገልግሎት ይዘዉ እንደሚወርዱ አስረድተዉ በዚህም ዘመቻ የመፀዳጃ ቤትና የአካባቢ ንፅሕና ጉድሌት የሚስተዋልባቸዉ ምግብ ቤቶችና ድርጅቶች የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ እርምጃ እየተወሰደ እንድከድ መወሰኑንም ገልፀዋል።

በዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሁለተኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደግንቦት 22/9/2017 ዓ/ም።።።።። ቦይካ።።።።።።በዎባ  አሪ ወረዳ  ሁለተኛው ዙ...
30/05/2025

በዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሁለተኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ
ግንቦት 22/9/2017 ዓ/ም
።።።።። ቦይካ።።።።።።
በዎባ አሪ ወረዳ ሁለተኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለትካ ዘረፍ መለሰና የመንግሰት ተጠሪ አቶ ስዩም ዳረጋንሶ በተገኙበት በሻማምር ቀበሌ ጋርዲ ከተማ ላይ ተካሂዷል።

ሁለተኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ለ4 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ የዎባ አሪ ወረዳ አቶ ዳንኤልን ገበየሁ የገለፁ ሲሆን እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከግንቦት 22-25/2017 ዓ.ም ድረስ በቤት ለቤት በሚደረግ ጉብኝት ስለሚሰጥ ህፃናት ከዚህ በፊት የፖልዮ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡሞ ወላጆች በዘመቻው እንድከተቡ በማድረግ የወላጅነት ሃላፊነታቸዉን እንድወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሁለተኛዉ ዙር ዘመቻ እንደ ወረዳ 9829 ሕጻናትን መከተብ የሚያስችል ግብዓት ተረክበዉ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ተግባር መገባቱንም አንስተዋል።

ከዘመቻዉ በተጨማሪም የፖሊዮ መሰል ኬዝ ለመግታት የቅኝትና አሰሳ ሥራዎችም ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

ከአምስት አመት በታች የሆኑ በመደበኛው የክትባት መርሀ-ግብር ተደራሽ ያልሆነ ወይም ጀምረው ያቋረጡ ህፃናትን መለየት እና በጤና ተቋማት ወይም በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንድከተቡ ማድረግ አንዱ የዘመቻዉ አካል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የትንሳኤ በዓል መዳንና መለወጥ ከመስዓዋትነት በቀር እንዲሁ የማይታሰብ መሆኑን የሚያመላክት አስተምህሮት ያለውና ከመጥፎ ወደ በጎ የመለወጥ እሳቤና ተስፋን ማየት እንድንችል ታላቅ አስተምህሮት...
17/04/2025

የትንሳኤ በዓል መዳንና መለወጥ ከመስዓዋትነት በቀር እንዲሁ የማይታሰብ መሆኑን የሚያመላክት አስተምህሮት ያለውና ከመጥፎ ወደ በጎ የመለወጥ እሳቤና ተስፋን ማየት እንድንችል ታላቅ አስተምህሮትን ለሰው ልጆች የሰጠ መንፈሳዊ በዓል ነው፡፡

አቶ ዳንኤል ገበየሁ
የዎባ አሪ ወረዳ ጤ/ጽ/ቤት ኃላፊ

ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም (ዎአወጤ)፤ ቦይካ
አቶ ዳንኤል ገበየሁ የዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የስቅለትና የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለዎባ አሪ ወረዳ ህዝብና ለመላው ኢትዮጽያን የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን! መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ዳንኤል ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍጹም ፍቅር እና አክብሮት በህማማቱ፣ በስቅለቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው የገለጸበት ነው።

የትንሳኤ በዓል መዳን፣ ነፃነትና መለወጥ ከመስዓዋትነት በቀር እንዲሁ የማይታሰብ መሆኑን የሚያመላክት ሐይማኖታዊ አስተምህሮት ያለው ፤ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በዓል መሆኑን የገለፁት አቶ ዳንኤል ገበየሁ ክህደትና እምነትንም አካቶ ያስተማረ በዓል መሆኑን ተናግረዋል።

የአስቆሮቱ ይሁዳ ወዳጁን መምህሩን በዕለተ ሐሙስ የካደበት፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ምክንያት የሆነበትና ከመከራና ፈተናዎች ሁሉ ከባድ ጭካኔ የተፈፀመበት፤ ስቅለት ለትንሳኤ ምክንያት የሆነበት በዓል መሆኑን የተናገሩት አቶ ዳንኤል ገበየሁ ከመጥፎ ወደ በጎ የመለወጥ እሳቤና ተስፋን ማየት እንድንችል ታላቅ አስተምህሮትን ለሰው ልጆች የሰጠም ነው ብለዋል።

የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በመስቀል ላይ እስከሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ፅኑ ፍቅር ያሳየበት ለበደሉትም ሳይቀር ይቅርታና ምህረትን የሰጠበት፣ ሞትንም ድል ያደረገበት በዓል በመሆኑ እኛም እርስ በርሳችን በመዋደድ፣ በይቅርታና በመረዳዳት ልንኖር ይገባልም ብለዋል ።

ስለሆነም የዘንድሮውን የትንሳዔ በዓል ስናከብር እንደዞንም ሆነ፥ እንደሀገር ባላፉት የለውጥ አመታት የታዩ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን በመውሰድ፤ በቀጣይ ጊዜያት አዲስ ነገር በምንሰራበት ሁኔታ ላይ በማተኮር መሆን አለበት ያሉት አቶ ዳንኤል ገበየሁ ፤ በሚገጥሙን ፈታኝ ሁኔታዎች እጅ ሳንሰጥ ለውጤታማነት የበለጠ ተቀናጅተን በትብብር ልንሰራ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በተለይም መንግስትም የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት መላውን ህዝብ በማሳተፍ በከተማ እና በገጠር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እያካሄደ ያለው ጥረት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስገኘ ያለ ስለሆነ፣ የተጀመረው የለውጥና የብልፅግ ጉዞ ሊጠናከር ስለሚገው፣ መላው ህዝብ በየአካባቢው ያሉ ዕድሎች እና ፀጋዎች ሳይመክኑ በሙሉ አቅሙ በመጠቀም፣ የቤተሰብ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በመልዕክታቸው አስገንዝበዋል።

በዓሉ የእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን የምናስታውስበትና የምናከብርበት መስዋዕትነቱን እና ለሰው ልጆች ሁሉ ያለውን ፍፁም ፍቅር የምናሰላስልበት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን ይህንን ታላቅ በዓል ስናከብር በአመስጋኝነት ፣ በደግነት የምንችለውን ሁሉ ለተቸገሩ ወገኖች በመለገስና በማጋራት ልናከበረው ይገባል ሲሉም አቶ ዳንኤል ገበየሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በስተመጨረሻው በዓሉ ለቀበሌ ፣ ለወረዳ፣ ለዞን ፣ክልልሉና ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የብልጽግና እንዲሆን መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል።

የዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አቶ ዳንኤል ገበየሁ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፥ቦይካ ፣መጋቢት 20/2017 (ዎአወጤጽ/ቤት)፦ ለመላዉ የእስልምና  እምነት ...
30/03/2025

የዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አቶ ዳንኤል ገበየሁ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፥

ቦይካ ፣መጋቢት 20/2017 (ዎአወጤጽ/ቤት)፦

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ!

የዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ዳንኤል ገበየሁ በመልዕክታቸው፤ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፤ የመቻቻል፣ የመደጋገፍ እና የአንድነት እሴቶች በማጠናከር እና በየተሰማራንበት ዘርፍ ሀገራችንን በሀቀኝነት በማገልገል የድርሻችንን እየተወጣን እንዲሆን አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እንገልፃለሁ ።

Address

SNNPRG Jinka
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woba Ari Worda Health Office page 2012 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram