Dr Robel ዶ/ር ሮቤል

Dr Robel ዶ/ር ሮቤል ዶ/ር ሮቤል አሳምነው፤
የህፃናት እስፔሻሊስት ሀኪምና በህፃናት ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር

 # #መቼም ቢሆን  # #ልጆችን  # #ለማሳደግ ማስታወስ ያለባችሁ ነጥብ.....🙅🙅
21/11/2025

# #መቼም ቢሆን # #ልጆችን # #ለማሳደግ ማስታወስ ያለባችሁ ነጥብ.....🙅🙅

We have to appreciate and acknowledge such incredible works!! Abebech Gobena Hospital በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም ተለግሶት የእናትን ጭ...
20/11/2025

We have to appreciate and acknowledge such incredible works!! Abebech Gobena Hospital በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም ተለግሶት የእናትን ጭንቀት ወደ ደስታ የቀየረው የተሳካ ሕክምና
********

በአፍሪካ ለመጀመሪያ በዓለም ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ግሩም የሕክምና ጥበብ የተስተዋለበት ሥራ የተከናወነው በኢትዮጵያ ነው።

በእናቱ ሆድ ውስጥ ብዙ ጊዜ ደም እየተለገሰው የነበረው ሕጻን በትናትናው እለት ወደዚህች ምድር በጤንነት ተቀላቅሏል፡፡

ወይዘሮ ሰናይት ታምራት ቀደም ሲል በነበረው እርግዝናዋ በተፈጠረባት የሾተላይ ችግር ምክንያት ልጇን አጥታለች፡፡

በጤና ጣቢያ ክትትሏን ታደርግ የነበረችው የ28 ዓመቷ ታካሚ፣ ቀደም ሲል በተፈጠረባት ችግር ምክንያት 'ዳግም ልጄን አጣው ይሆን' የሚል ከፍተኛ ጭንቀት ገብቷታል፡፡

ይህች እናት 21 ሳምንት ሲሆናት ክትትል ከምታደርግበት ጤና ጣቢያ በተፃፈላት ሪፈር መሰረት ወደ አበበች ጎበና እናቶች እና ህፃናት ማዕከል ታመራለች፡፡

የአበበች ጎበና የእናቶች እና የህፃናት ሕክምና ማዕከል ባደረገው ምርመራ ፅንሱ በሾተላይ ምክንያት የደም ማነስ እንዳጋጠመው ደረሰበት፡፡

ቀደም ሲል በሾተላይ ምክንያት ልጇን ላጣች እና አሁን በሆድዋ ለተሸከመችው ልጅ በጭንቀት ውስጥ ላለች እናት መፍትሔ ፍለጋ የተቋሙ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ማድረግ ስለሚችሉት ነገር ምክክር ጀመሩ፡፡

ፅንሱ ገና የ21 ሳምንት መሆኑ የታሰበውን ሕክምና ከባድ አድርጎታል፡፡

በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ የደም ማነስ ችግር ላጋጠመው የ21 ሳምንት ብቻ ዕድሜ ላለው ፅንስ የደም ስሮቹ ደም ለመስጠት የሚያስቸግሩ ቀጫጭን ቢሆኑም፣ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም የመስጠት ሕክምና ማድረግ ለፅንሱ ህልውና አማራጭ የሌለው መፍትሔ እንደሆነ ለታካሚዋ ተነገራት፡፡

የመጀመሪያው ደም የመለገስ ሕክምናም እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ተከናወነ። ታካሚዋ የመጀመሪያዎቹን ወራቶች በሳምት ሁለት ቀን ለክትትል ወደ ሕክምና ተቋሙ በማምራት አስፈላጊውን ክትትል ስታደርግ ቆየች፡፡

ፅንሱ ሕክምናውን እያገኘ መፋፋት እና እድገት ማሳየት ሲጀምር በሳምት አንዴ በመምጣት ክትትሉ ቀጠለ፡፡

ለእናት እና ለልጅ ጥብቅ የሆነ ክትትል በማድረግ ደም የመለገስ ሂደቱ እስከ 10 ጊዜ ቀጥሎ ፅንሱ የመወለጃው ጊዜ ሲደርስ በቀዶ ሕክምና 3.5 ኪ.ግ የሚመዝን ልጅ በሰላም ተገላግላ እናት ልጇን ማቀፍ ችላለች፡፡

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና እናቶች እና ህፃናት ሕክምና ማዕከል የተፈጠረው ይህ ታሪክ፣ በሕክምናው ታሪክ በዓለም በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም ተለግሶ ስኬታማ የሕክምና ክትትል በማድረግ ወደዚህ ዓለም የተቀላቀለ ሁለተኛው ልጅ ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ፅንስ በእናቱ ሆድ እያለ 10 ጊዜ ደም ተሰጥቶት የተሳካ የሕክምና ሂደት አልፎ የተወለደው በብራዚል ሲሆን፣ በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ ደግሞ የመጀመሪያው የ21 ሳምንት ፅንስ በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም በመሰጠት ስኬታማ የሕክምና ሒደት አልፎ በስኬት የተወለደ መሆኑ ልዩ አድርጎታል፡፡

ሕክምናው በኢትዮጵያ ውስጥ በጳውሎስ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በየካቲት 12 የአበበች ጎበና የእናቶች እና ህፃናት ሕክምና ማዕከል የሚሰጥ ሲሆን 30 ሳምንት እና ከዛ በላይ የሆነ እድሜ ያለው ፅንስ የእናት ሆድ ውስጥ እንዳለ የመወለጃው ቀን እስኪቃረብ ድረስ ደም የመስጠት ሒደት የተለመደ ነው፡፡

በአሁን ሰዓት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና እናቶች እና ህፃናት ህክምና ማዕከል እናት እና ልጅ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

20/11/2025

አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን ከተለያዩ መፀሃፍት አና መደብር ሳይቆራረጥ ለማድረስ የተከፈተ ድኅረ ገፅ ቢሆንም የተለያዩ ወቅታዊ አና ስሜትን የሚጎዱ ሃገራዊ ሁኔታዎች ሙያዊ ስራን በነፃነት ለመስራት አንቅፋት መሆናቸው ግልፅ ነው:: የተለያዩ ወንድም አህቶችን ስሜት መጠበቅም አስፈላጊ በመሆኑ ለአመታት በሚፈለገው መልኩ ሞያዊ አገዛ አላደረገም:: ይሁን አንጂ አልፎ አልፎም ቢሆን አንዳንድ ሙያው ምክረ ሃሳቦችን አስተላልፌያለሁ አሁንም ማካፈል አወዳለሁ:: መልካም ቀን ይሁንላቺሁ!!

# # ቅርበት
:::::::::::::::

ልጆች ከመብላት እና መጠጣት ባለፈ ከወላጆቻቸው(ከአሳዳጊያቸው) መቀራረብን ይሻሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የወላጅ ልጅ ትስስር በተጠናከረ ቁጥር የልጆች የአእምሮ፣ የጤና፣ የስሜት፣ እና የመስተጋብር ክህሎታቸው ያድጋል፤ይበለፅጋል፡፡

በ Duke's University ለ30 አመታት የዘለቀ ተከታታይ ጥናት በልጅነታቸው በወላጅና ልጅ መካከል ጥብቅ የስሜት ትስስር ኖሯቸው ያደጉ ልጆች ከሌሎች ልጆች የተሻለ በራስ መተማመን ፣ ደስተኛ፣ በት/ቤት የተሻለ ውጤት ማግኘትና ችግር ቢገጥማቸው የመፍትሄ ሰዎች ሆነው ተገኝተዋል።

ምንም እንኳን ሁላችንም በተፈጥሮ የመቀራረብ አቅም (Potential intimacy) የተሰጠን ቢሆንም እንደ ችግኝ በመኮትኮት ማሳደግ የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው፡፡

✅ በወላጅ እና በልጅ መካከል ያለውን ቅርርብ ለማሳደግ

1. አብሮ መጫወት
2. በጋራ መብላት
3. ልጆችን መስማት
4. ፍቅርን ማሳየት
5. ጤናማ እና ሚዛኑንን የጠበቀ ገደብ ማድረግ
6. በቤተሰብ የጋራ ጊዜ የማሳለፍ ልማድ ማዳበር!

Be careful!! ይህንን መረጃ ተረጋግታችሁ አንብቡት:: Ministry of Health
18/11/2025

Be careful!! ይህንን መረጃ ተረጋግታችሁ አንብቡት::
Ministry of Health

We are waiting for you!!
31/03/2025

We are waiting for you!!

የዘመቻ ሕክምና ሰላም አንደምን አላችሁ? ጥብቅ መልአክት ይዤ መጥቻለሁ: ላልሰማ አሰሙ በጣም ጠቃሚ ነው:: የብዙዎችን ችግር ይፈታል::ከየካቲት 25 አስከ የካቲት 29/2017 ዓ. ም በደሴ ...
23/02/2025

የዘመቻ ሕክምና
ሰላም አንደምን አላችሁ? ጥብቅ መልአክት ይዤ መጥቻለሁ: ላልሰማ አሰሙ በጣም ጠቃሚ ነው:: የብዙዎችን ችግር ይፈታል::
ከየካቲት 25 አስከ የካቲት 29/2017 ዓ. ም በደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል እግራቸው የተቆለመመ (የዞረ ) ልጆች ና አዋቂዎች በዘመቻ ስለሚካሄድ በተባለው ጊዜ በመገኘት ሕክምናዉን አንድያገኙ ሲል የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል:: ደብዳቤዉን ከስር አያይዜዋለሁ::

Dear CMHS Team,  and leadersI would like to take a moment to express my deepest gratitude to CMHS, Wollo University for ...
22/02/2025

Dear CMHS Team, and leaders

I would like to take a moment to express my deepest gratitude to CMHS, Wollo University for the invaluable support, guidance, and opportunities you have provided. As a cornerstone of growth and development, your institution has played a pivotal role in shaping not only my career but also my personal growth.

The foundation and values instilled by CMHS, Wollo University continue to inspire and guide me in all my endeavors. Your commitment to excellence, innovation, and community has left an indelible mark, and I am truly honored to be associated with such a prestigious institution.

Thank you for being a beacon of knowledge and a source of unwavering support. I look forward to continuing this meaningful relationship and contributing to the legacy of Wollo university, CMHS in any way I can.

With sincere appreciation,

Thank you very much Wollo university PCH energetic, responsible and dedicated staff, WU and DCSH admin and staff, my mom...
21/02/2025

Thank you very much Wollo university PCH energetic, responsible and dedicated staff, WU and DCSH admin and staff, my mom and wife, EMA board members, and those who are with me at large!! 🙏🙏

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Elias Manaye, Arega Hussien, Wondu Habesha, Brhanu Belay,...
25/01/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Elias Manaye, Arega Hussien, Wondu Habesha, Brhanu Belay, Osman Tilahun, Tiyobi Ye Sari

15/01/2025

አስደሳች ዜና
በደሴ አና አካባቢው ላለው የደሴ አጠቃላይ: ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል የሕፃናት ሕክምና ክፍል የሄሞፊሊያ ( ደም መድማትን የሚቆጣጠሩትን ፋክተር VIII አና IX, factor 8 and 9 አጥረት: መስጠት መጀመራችንን ስንገልፅ በደስታ ነው:: ይህ በሽታ በዘር የሚተላለፍ ሆኖ በወንድ ልጆች ላይ( በአብዛኛው )የሚከሰት የደም መፍሰስ ችግር ሲሆን
በሆስፕታላችን ብዙ ታካሚዎች አንደመኖራቸው አገልግሎቱን ሲያገኙ የነበሩት ወደ ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ረፈር በመባል ነበር::

በደሴ አጠቃላይ አና ስፔሻልዝድ ሆስፒታል የሕፃናት የካንሰር ሕክምና (የሕፃናት ካንሰር ሳተላይት ክሊኒክ) መጀመሩን ያዉቃሉ? ህዳር 17/2017 ዓ.ም የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ (ዶክተር መንግ...
07/01/2025

በደሴ አጠቃላይ አና ስፔሻልዝድ ሆስፒታል የሕፃናት የካንሰር ሕክምና (የሕፃናት ካንሰር ሳተላይት ክሊኒክ) መጀመሩን ያዉቃሉ?
ህዳር 17/2017 ዓ.ም የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ (ዶክተር መንግስቱ ወርቁ), ከጥቁር አንበሣ ሆስፒታል የሕፃናት ካንሰር ሕክምና ማአከል የሕፃናት ሀኪም አና የሕፃናት ደም አና ካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ጋሻው አረጋ, የደሴ አጠቃላይ አና ስፔሻልዝድ ሆስፒታል
ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሃይማኖት አየለ አና ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር እንድርስ መሐመድ አንዲሁም ሌሎች ለስራው አስተዋፅኦ ያላቸው አስተባባሪዎች አና ኃላፊዎች በተገኙበት ተከፍቶ ሥራ መጀመራችንን በድጋሜ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው::
PHOSC( Pediatric Hematooncology satellite clinic) ምንድነው? አንዴትስ በደሴ አጠቃላይ አና ስፔሻልዝድ ሆስፒታል ይሰጣል?
1. የተመረጡ የሕፃናት ካንሰር በሽታዎችንና ሕክምናቸዉን በጥቁር አንበሣ ስፔሻልዝድ ሆስፒታል, በፓዉሎስ ሆስፒታል አና በጎንደር ሆስፒታል የተጀመሩ:
2. በደሴ አጠቃላይ አና ስፔሻልዝድ ሆስፒታል አዲስ
ካንሰር ያለባቸው አና የተጠረጠሩ, ለሪፈር ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚላኩ: በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካል ጋር በማገናኘት እንግልት አና መጉላላትን ለመቀነስ
3. ከፍ ሲልም የሚያስፈልጉ በቂ ሐኪሞችን በማምጣት በሙሉ አቅም አገልግሎት አንዲሰጥ ማድረግ ነው::
ለዚህም ሥራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጉትን
* ዶክተር ድሪባ ፉፋ , በጅማ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል የሕፃናት ካንሰር ሕክምና ማአከል የሕፃናት ሀኪም አና የሕፃናት ደም አና ካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት
*ዶክተር ሙሉጌታ አያሌው በጎንደር ዩንቨርስቲ ሆስፒታል የሕፃናት ካንሰር ሕክምና ማአከል የሕፃናት ሀኪም አና የሕፃናት ደም አና ካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት
* ዶክተር ታደለ ኃይሉ በፓዉሎስ ሆስፒታል የሕፃናት ካንሰር ሕክምና ማአከል የሕፃናት ሀኪም አና የሕፃናት ደም አና ካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት
* በወሎ ዩኒቨርሲቲ Chief Exceutive Director ዶክተር መታደል አዳነ
* የጥቁር አንበሳ ሕፃናት ትምህርት ክፍል አና የሕፃናት ካሰር ሕክምና ንዑስ ክፍል አንዲሁም
* በደሴ አጠቃላይ አና ስፔሻልዝድ ሆስፒታል ክልኒካል/ adult oncologist ዶክተር ያሲን, አና የሆስፒታሉ ማኔጂንግ ቲም ምስጋና አናቀርባለን::

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913252415

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Robel ዶ/ር ሮቤል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Robel ዶ/ር ሮቤል:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram