13/05/2025
የምስራች!
በቅርቡ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በአቤት ሆስፒታል የተጀመረውን የዳሌ እና የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ቀዶ ሕክምና እያገዝን መሆኑን ስናበስር በኩራት ነው።
አዲሱ አገልግሎት በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚያ ቅየራ ፍላጎት ለማሟላት የጎላ ድርሻ ያለው አስፈላጊ ጅማሮ ነው።
የተጀመረው ህክምና ከባድ የመገጣጠሚያ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ሕይወታቸውን በእጅጉ ሊያሻሽሉ የሚችሉ የቀዶ ጥገና አገልግሎቶችን የያዘ ነው።
ይህ የረጅም ጊዜ እቅድ እውን ይሆን ዘንድ አስፈላጊ የሆኑ የመገጣጠሚያ ቅየራ ቁሳቁሶችን በጥራት እና በተሟላ መልኩ ስናቀርብ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማናል።
በአዲስ ኦርቶ የጤና ስርዓቱን በአዳዲስ ፈጠራ እና በአስተማማኝ አቅርቦት ለማጠናከር ሌት ተቀን እንተጋለን። 💚💚
አዲስ ኦርቶ
ታማኝ የአጥንት ህክምና አጋርዎ!
St. Paul's Hospital Millennium Medical College-SPHMMCAaBET HOSPITALALDr Samuel Hailu ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ - አጥንት ህክምና በኢትዮጵያይSamuel HailueSamuel Hailulu