አዲስ ጠቢባን የጤና ማማከር አገልግሎት

አዲስ ጠቢባን የጤና ማማከር አገልግሎት We provide consultancy services on all medical conditions. Contact us, we will treat you with utmost care.

አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሀና ሊሻን ( በ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ ህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር).✍✍✍ስለ ትርፍ አንጀት መቆጣት ያዉቁ ኖሯል?🤔🤔✅የትርፍ አንጀት የሚባ...
20/05/2022

አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሀና ሊሻን ( በ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ ህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር).

✍✍✍ስለ ትርፍ አንጀት መቆጣት ያዉቁ ኖሯል?🤔🤔

✅የትርፍ አንጀት የሚባለው የአንጀት ክፍል (appendix) በኢንፌክሽን ምክንያት ሲቆጣ እና ሲያብጥ የ ትርፍ አንጀት መቆጣት (appendicitis) እንለዋለን፤ በተመሳሳይ ሳይታከም ወይም ሳይታወቅ ሲቆይ ደግሞ የትርፍ አንጀት መፈንዳትን (appendiceal rupture ) ሊያስከትል ይችላል።

🤔🤔🤔የበሽታዉ ምልክቶች⁉️⁉️

✅ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✅ ከእምብርት አካባቢ ተነስቶ ከጊዜ በዋላ - ከእምብርት በታችና በስተቀኝ ባለዉ የሆድ ክፍል የሚዘዋወር የሆድ ህመም።
✅ማቅለሽለሽና ማስመለስ /ማስታ
✅መለስተኛ ትኩሳት
✅ሲራመድ በቀኝ በኩል ማስነከስ እና ማስጎንበስ
✅ አልፎ አልፎ የሰገራ መለስለስ እና ሽንት ሲሸኑ ህመም መፍጠር ሊኖር ይችላል

🤔🤔🤔 የትኛውን የእድሜ ክልል ይጎዳል⁉️⁉️

🔺ከ 5 አመት በላይ ያሉ ልጆች ላይ ይከሰታል በተለየ መልኩ ደግሞ ከ 10-19 አመት ያሉ ልጆች ላይ በ ብዛት ይከሰታል።
🔺 ይህ ማለት ግን ከ 5 አመት በታች በጭራሽ አይከሰትም ማለት አይደለም። ባጠቃላይ በህፃናት የእድሜ ክልል ላይ ከሚከሰቱ የ ትርፍ አንጀት ውስጥ 5 ከ 100 (5%) በዚህ የ እድሜ ክልል ውስጥ እንደሆነ ይገለፃል።

🤔🤔🤔በሽታዉን ለይቶ ለማወቅ ሀኪሙ ምን ምን ሊያዝ ይችላል⁉️⁉️

✅ አጋዥ የሆኑ የ ደም እና ሽንት ላቦራቶሪ ምርመራዎች
✅እና የ ሆድ (ከ 10 ውስጥ 9 ይለይልናል= 90%) አልትራሳውንድ እንደአስፈላጊነታችዉና እንደየ ሁኔታው ሊያዝ ይችላል

🤔🤔🤔 ህክምናውስ⁉️⁉️

✅ ቀለል ባለ ቀዶ ጥገና የተቆጣውን የትርፍ አንጀት ማስወገድ ነው።

🔺🔺🔺 ማሳሰብያ🔺🔺🔺

🚫የህጻናት ቤተሰብ ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች ህጻናት ላይ ስታዩ ቶሎ ለህክምና መዉሰድ ያስፈልጋል🚫

🚫ህጻናት ላይ የትርፍ አንጀት በሽታ የመፈንዳት እድሉ ከአዋቂ በተለይ ከፍ ያለ ነው። ‼️ ህመሙ ከጀመረ ከ 48 ሰአት ቡሃላ 65 ከ 100(65%) ትርፍ አንጀት የመፈንዳት እድል ይኖረዋል‼️

🚫በመሆኑም የትርፍ አንጀት እንዳለ ከታወቀ ቡሃላ ቆይ እንወስን በሚል ቀዶ ጥገናን ማዘግየት ተገቢ አይደለም🚫

መልካም ጊዜ✍✍✍

📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

ለተጨማሪ የልጆች መረጃዎች ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን እና Facebook- like....telegram- join....በማድረግ ይከታተሉን‼️‼️
ለወዳጅ ዘመዶም share በማድረግ ያድርሱ 🔊🔊🔈

Facebook=

fb.me/DrHannaLishanPediatrician

Telegram=

t.me/Drhannalishanpediatrician

✅ ለ ነፃ የምክር አገልግሎትም ሆነ በ አካል ቀርበው ልጆትን ለማስመርመር በዚህ ስልክ ደዉለው ያነጋግሩ‼️

0902500239
ICMC General Hospital
Addis Tebiban Health-Care consultancy

✍✍✍ስለ ትርፍ አንጀት መቆጣት ያዉቁ ኖሯል?🤔🤔

✅በትልቁ አንጀት ጅማሮ ላይ ያለው የትርፍ አንጀት የሚባለው የአንጀት ክፍል (appendix) በኢንፌክሽን ምክንያት ሲቆጣ እና ሲያብጥ የ ትርፍ አንጀት መቆጣት (appendicitis) እንለዋለን፤ በተመሳሳይ ሳይታከም ወይም ሳይታወቅ ሲቆይ ደግሞ የትርፍ አንጀት መፈንዳትን (appendiceal rupture ) ሊያስከትል ይችላል።

🤔🤔🤔የበሽታዉ ምልክቶች⁉️⁉️

✅ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✅ ከእምብርት አካባቢ ተነስቶ ከጊዜ በዋላ - ከእምብርት በታችና በስተቀኝ ባለዉ የሆድ ክፍል የሚዘዋወር የሆድ ህመም።
✅ማቅለሽለሽና ማስመለስ /ማስታ
✅መለስተኛ ትኩሳት
✅ሲራመድ በቀኝ በኩል ማስነከስ እና ማስጎንበስ
✅ አልፎ አልፎ የሰገራ መለስለስ እና ሽንት ሲሸኑ ህመም መፍጠር ሊኖር ይችላል

🤔🤔🤔 የትኛውን የእድሜ ክልል ይጎዳል⁉️⁉️

🔺ከ 5 አመት በላይ ያሉ ልጆች ላይ ይከሰታል በተለየ መልኩ ደግሞ ከ 10-19 አመት ያሉ ልጆች ላይ በ ብዛት ይከሰታል።
🔺 ይህ ማለት ግን ከ 5 አመት በታች በጭራሽ አይከሰትም ማለት አይደለም። ባጠቃላይ በህፃናት የእድሜ ክልል ላይ ከሚከሰቱ የ ትርፍ አንጀት ውስጥ 5 ከ 100 (5%) በዚህ የ እድሜ ክልል ውስጥ እንደሆነ ይገለፃል።

🤔🤔🤔በሽታዉን ለይቶ ለማወቅ ሀኪሙ ምን ምን ሊያዝ ይችላል⁉️⁉️

✅ አጋዥ የሆኑ የ ደም እና ሽንት ላቦራቶሪ ምርመራዎች
✅እና የ ሆድ አልትራሳውንድ (ከ 10 ውስጥ 9 ይለይልናል= 90%) እንደአስፈላጊነታችዉና እንደየ ሁኔታው ሊያዝ ይችላል

🤔🤔🤔 ህክምናውስ⁉️⁉️

✅ ቀለል ባለ ቀዶ ጥገና የተቆጣውን የትርፍ አንጀት ማስወገድ ነው።

🔺🔺🔺 ማሳሰብያ🔺🔺🔺

🚫የህጻናት ቤተሰብ ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች ህጻናት ላይ ስታዩ ቶሎ ለህክምና መዉሰድ ያስፈልጋል🚫

🚫ህጻናት ላይ የትርፍ አንጀት በሽታ የመፈንዳት እድሉ ከአዋቂ በተለይ ከፍ ያለ ነው። ‼️ ህመሙ ከጀመረ ከ 48 ሰአት ቡሃላ 65 ከ 100(65%) ትርፍ አንጀት የመፈንዳት እድል ይኖረዋል‼️

🚫በመሆኑም የትርፍ አንጀት እንዳለ ከታወቀ ቡሃላ ቆይ እንወስን በሚል ቀዶ ጥገናን ማዘግየት ተገቢ አይደለም🚫

መልካም ጊዜ✍✍✍

አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሀና ሊሻን ( በ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ ህፃናት ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር)

📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

ለተጨማሪ የልጆች መረጃዎች ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን እና Facebook- like....telegram- join....በማድረግ ይከታተሉን‼️‼️
ለወዳጅ ዘመዶም share በማድረግ ያድርሱ 🔊🔊🔈

Facebook=

fb.me/DrHannaLishanPediatrician

Telegram=

t.me/Drhannalishanpediatrician

✅ ለ ነፃ የምክር አገልግሎትም ሆነ በ አካል ቀርበው ልጆትን ለማስመርመር በዚህ ስልክ ደዉለው ያነጋግሩ‼️

0902500239
ICMC General Hospital

24/04/2022

ውድ ቤተሰቦች👨‍👩‍👧‍👦👨‍👩‍👧‍👦👨‍👩‍👧‍👦

እንኳን ለ ብርሃነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳቹ‼️

በ ረመዳን ጾም ላይ ላላችሁም ፣ መልካም የጾም ጊዜ እየተመኘን

🔔🔔🔔በመቀጠል ከረዥም ጾም ቡሃላ የምንመገበው ምግብ ሆዳችንን እንዳያሳምመን ምን ብናደርግ ይመከራል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ እናስቀምጥላቹሃለን ( ለ ህጻናትም ሆነ ለ አዋቂ የሚሆን)🔔🔔🔔

✅እንደራበን በፍጥነት ስንበላ ዐእምሮዋችን ዉስጥ ያለው የ ጥጋብ ስሜት መቀስቀሻ ክፍል ቶሎ ምላሽ ስለማይሰጥ ሳይታወቀን ከልክ በላይ እንበላለን። ብዙ ቅባት ወይም ፕሮቲን ያለው ምግብ ሲሆን ደግሞ ከፍተኛ ጫና ጨጓራ ላይ ሊያሳድር ይችላል
🚫ስለዚህ ከመመገባችን በፊት በባዶ ሆዳችን ፍራ ፍሬ ብንወስድ ከሚከተሉት አንዱን ፤ ፓፓያ ፣ ሃባብ ፣ ዘቢብ ፣ ትንሽ ለዉዝ ፣ ማር በ ዉሃ(የፈላ ዉሃ ዉስት መጨመር አይመከርም) ፣ የተፈጨ ኩከምበር/ኪያር የተሻለ ይሆናል
⏩ከዚያም ወደ 45 ደቂቃ ክፍተት ሰጥቶ ወደተዘጋጅው ምግብ መግባት።
✅የምንመገበዉን ምግብ በልክ ማቅረብ ያስፈልጋል።
✅ስንበላ ከበተሰብ ጋር እየተጫወትን ቀስ ቀስ እያልን መመገብም ይመከራል።
✅ጾም እየፈታን ቢሆንም፣ የምግብ አይነታችን ዉስጥ ‘fresh’ አትክልት ቢቀልቀልበት ይመከራል።
✅ከበላን ቡሃላ በቂ ዉሃ መጠጣት (በትንሹ ሞቅ ያለ ቢሆን ይመረጣል)⏩ ይህም የምግብ ንጥረ ነገሮች በ ቀላሉ መፈጨት በሚችሉበት መልክ እንዲቀመጡ ያደርጋል።
❌በተቻለ መጠን ቀዝቃዛ መጠጦችን ምግብ እንደተበላ ባይጠቀሙ ይመከራል።
❌ከተመገቡ ቡሃል በጭራሽ አይተኙ፣ በተቃራኒው✅ የ 20 ደቂቃ እርምጃ ቢያደርጉበት ይመከራል።
❌የታሸጉ መጠጦች አብሮ ወይንም ከምግብ ቡሃል መዉሰድ አይመከርም⏩ አላስፈላጊ አየር ሆዳችን ዉስጥ ሞልቶ ለጨጓራ ትርፍ ስራ ይፈጥርበታል።

🤔🤔🤔አይበለውና ጨጓራዬን ከታመምኩኝ ምን ላድርግ❓
✅በትንሽ ትንሹ የሚከተሉትን መመገብ
➡️ሙዝ መብላት፟ _ ለመፈጨት ቀላል እና በ ፖታሲየም የበለጸገ ሲለሆነ ማስመለስ ወይም ተቅማጥ ላለው ሰው ጥሩ ነው
➡️ነጭ ሩዝ፟ ፟መብላት_ ሃይል ሰጪና ትንሽ ፋይበር ያለው ምግብ ስለሆነ፣ በጨጓራ ሚክኒያት ተቅማጥ ለጀመረው ሰው ካካዉን ደረቅ ሊያረግለት ይችላል
➡️የተፈጨ ፖም(applesauce)- በቀላሉ የሚፈጭና ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገር ያለው ነው
✅ተቅማጥ ወይንም ማስመለስ ካለን ደግሞ ተጨማሪ ORS( Oral Rehydration Solution) ከ ፋርማሲ በመግዛት ከሰዉነታችን ሚወጣዉን ፈሳሽ መተካት ያስፈልጋል
✅ለ አጭር ጊዜ እስኪሻለን የሚከተሉትን ማቆም
🚫ጨጓራዎን ያሳመሞትን ምግብ ለጊዜዉ ሙሉ በሙሉ ማቆም
🚫ወተት እና የወተት ተዋጾችን
🚫በ ዘይት የተጠበሱ ሚግቦችን
🚫የታመቀ አየር ያላቸዉን እሽግ መጠጦች
🚫ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች
🚫ጥሬ ቅጠላ ቅጠሎችን

🤔🤔🤔መች ነዉ ታዲያ ወደ ሆስፒታል መሄድ ያለብን❓

ከላይ የተጠቀሱትንም አድርገንም
♨️ የ ጨጓራ አካባቢ ህመም እና
♨️ ማስመለስ ወይንም ተቅማጥ በ 2 ቀን ዉስጥ አልቆም ካለ,
♨️ ደም የቀላቀለ ቱከት ከጀመረ

አዘጋጅ፦ ዶ/ር ሀና ሊሻን ( በ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ ህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

ውድ ቤተሰቦች ይህ መልእክት ይጠቅማል ብለው ካሰቡ የ ፌስቡክ ፔጃችንን እና ቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች 'follow' የሚለውን በመጫን ይቀላቀሉን👍👍 ለወዳጅ ዘመዶም ሼር በማድረግ ያድርሱ🙏🙏

Facebook=
fb.me/DrHannaLisha

Address

Haile Gebre Silasie
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:29 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 13:00

Telephone

+251984650912

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ ጠቢባን የጤና ማማከር አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to አዲስ ጠቢባን የጤና ማማከር አገልግሎት:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram