12/09/2023
እናመሰግናለን Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) :: ፅሁፉ የተወሰኑ ስህተቶች አሉት:: እንደሚከተለው ቢነበብ እንላለን::
አንጋፋዉ የ ኬሚስትሪ ምሁር ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኜ በ"በጎ ሰዉ" ሽልማት እዉቅና ተሰጣቸዉ
በመኮንን ተሾመ
(የሳይንስ ጋዜጠኛ)
| በየዓመቱ "በጎ ሰዎችን በመሸለምና እውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ" በሚል ሽልማት የሚሰጠዉ በጎ ሰው ሽልማት በዚህ አመት ትላንት ጳጉሜ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለ11ኛ ጊዜ ባካሄደዉ የእዉቅና መርሃግብር ከተሸለሙ እዉቅ ኢትዮዽያዉያን መካከል ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኜ አንዱ ናቸዉ።
ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ ሰኔ 1 ቀን 1936 ዓ.ም በሀረርጌ ክፋለሀገር ተወለዱ። ፕሮፌሰር ኤርሚያስ በ1960 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ1966 ዓ.ም ደግሞ አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (ሳንፍራንሲስኮ) የፒ ኤች ዲ ዲግሪ አግኝተዋል።
የተለያዩ የትምህርትና ምርምር _ ሽልማቶችን ከታዋቂ ተቋማት አግኝተዋል። ከነዚህም ከቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሽልማት ድርጅት ለኣራት ዓመት እስኮላርሺፕ፣ ከካሊፎርኒያ ዮኒቨርሲቲ የፒኤች ዲ ትምህርት ድጋፍ ፣ ከጀርመን አገር የሁለት ዓመት የሁምቦልት የምርምር ፌሎሺፕ፤ _ ከአሜሪካን አገር የፉልብራይት የምርምር ፌሎሺፕ ተጠቃሽ ናቸው። እንዲሁም በተፈጥሮ ውጤቶች ላይ ምርምር ለማካሄድ ከስዊድን የሲዳ ሳሬክ እና ከሌሎች ድርጅቶች የምርምር ድጋፍ ለማግኘት ችለዋል።
ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ የሚከተሉትን ስራዎችም አከናውነዋል፣ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ (Masters and PhD) የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተማሪዎችን በማስተማርና በማማከር ፣ SINET በመባል የሚታወቀውን የኢትዮጵያ የሳይንስ ጆርናል የመጀመሪያ አዘጋጅ በመሆን፣ Natural Products Research Network for Eastern and Central Africa NAPRECA) በምስራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ በተፈጥሮ ውጤቶች ጥናትና ምርቶች ላይ ያተኮረ የእውቀት ትስስር ተቋም በዋና ፀሀፊነት ለ12 ዐመት በመምራት ፣ Science and tchnology tems translation project ( የሳይንሳዊ ቃላት ስያሜና ትርጉም መርሀ ግብር) ለ6 ዓመት በመሳተፍ፣ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ፍላጉት እና አቅም ቅኝት ፕሮጀክት (University Industry Needs and Capabilities Survey Project) - ለሁለት ዐመት በመሳተፍ ፣ የጌታቸው ቦሎዲያ ተቋም (foundation) ለ12 ዐመት መምራት ፣ African Laboratory for Natural Products (ALNAP) የተባለውን ኔትወርክ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ መመስረትና መምራት ፣ www.alnapnetwork.com የተባለውን ከ5000 በላይ አገር በቀልና የአፍሪካ እፅዋትን ዝርዝር እና ጥቅም የያዘ ዳታቤዝ በመፍጠር ፣ በዘርፉ የሚሰማሩ ተመራማሪዎች እንዲሁም ማንኛውም ሰው የእፅዋቶችን ሣይንሳዊ ስምና ሌላ መረጃ በቀላሉ እንዲያገኝ አድርገዋል። ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ከ15 በላይ የዓለም አቀፍ የውይይት የልምድ እና የመማማሪያ መድረኮች ላይ ተሳትፈዋል፤ ልምዳቸውንም አካፍለዋል ። አራት የሚሆኑ የሙያ ማህበራት አባል ሲሆኑ ማህበራቶቹን በማቋቋምም እረድተዋል። ከ100 በላይ ሳይንሳዊ የምርምር ጽሁፎችን በአለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል።
ፕሮፌሰር ኤርሚያስ የምርምር ጥናቶችና ውጤቶችን ወደተግባር ቀይረው፣ ሀገር በቀል ተክሎችን ግብአቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ እና ከኢትዬጵያ ውጭ የማህበረሰብ ጤና እና ደህንነት እንዲሻሻል፣ ሰፊ አበርክቶ አላቸው። ለዚህም ዋነኛ ተጠቃሽ የሆነው በ1992 ዓ.ም በእርሳቸውና በቤተሰባቸው የተቋቋመው አሪቲ የመዓዛማ ዕፅዋት ምርቶች ተብሎ የሚታወቀው ድርጅት ነው፡፡ አሪቲ ለውበት እና ለጤንነት መጠበቂያ የሚሆኑትንና እና ጥሩ መአዛ ያላቸውን ውጤቶችን ከሀገር በቀል እና መጤ እፅዋት ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም በማምረት እና ለገበያ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
ምርቶቹም በዲስቲሌሽን ከተለያዩ እፅዋት መዐዛማ ዘይትን በማውጣት፤ እንደባህሪያቸው በመቀመም ለጤና እና ውበት መጠበቂያ፤ ለጥሩ የቤት ውስጥ ጠረን እንዲሆን ተደርጎ እየተዘጋጁ በሀገር ውስጥ እና ውጭ ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። እነዚህ ምርቶች በሀገር ውስጥ ለግል ተጠቃሚዎች፤ ሆቴሎች፤ ሎጆች እና የተለያዩ የጤና እና የውበት መንከባከቢያ ቦታዎች (SPA) በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ፣ ለውጭ ገበያ ሲቀርቡ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት እየጠቀሙ ይገኛሉ።
ከላይ ለተጠቀሱት ምርቶች ግብአት የሚሆኑት እፅዋት ከግል እርሻ እና ከተለያየ የአገሪቱ አካባቢ ገበሬዎች ይወሰዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አሪቲ ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር የአርክቦት ውል (Agreement on Access to, and Benefit Sharing) ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኜ ባለትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባትና የአራት ልጅ ልጆች አያት ናቸው።
አንጋፋዉ የ ኬሚስትሪ ምሁር ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ በ"በጎ ሰዉ" ሽልማት እዉቅና ተሰጣቸዉ
በመኮንን ተሾመ
(የሳይንስ ጋዜጠኛ)
| በየዓመቱ "በጎ ሰዎችን በመሸለምና እውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ" በሚል ሽልማት የሚሰጠዉ በጎ ሰው ሽልማት በዚህ አመት ትላንት ጳጉሜ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለ11ኛ ጊዜ ባካሄደዉ የእዉቅና መርሃግብር ከተሸለሙ እዉቅ ኢትዮዽያዉያን መካከል ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ አንዱ ናቸዉ።
ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ ሰኔ 1 ቀን 1936 ዓ.ም በሀረርጌ ክፋለሀገር ተወለዱ። ፕሮፌሰር ኤርሚያስ በ1960 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ1966 ዓ.ም ደግሞ አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (ሳንፍራንሲስኮ) የፒ ኤች ዲ ዲግሪ አግኝተዋል።
የተለያዩ የትምህርትና ምርምር _ ሽልማቶችን ከታዋቂ ተቋማት አግኝተዋል። ከነዚህም ከቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሽልማት ድርጅት ለኣራት ዓመት እስኮላርሺፕ ከካሊፎርኒያ ዮኒቨርሲቲ የፒኤች ዲ ትምህርት ድጋፍ ፡ ከጀርመን አገር የሁለት ዓመት የሁምቦልት የምርምር ፌሎሺፕ፤ _ ከአሜሪካን አገር የፉልብራይት የምርምር ፌሎሺፕ ተጠቃሽ ናቸው። እንዲሁም በተፈጥሮ ውጤቶች ላይ ምርምር ለማካሄድ ከስዊድን የሲዳ ሳሬክ እና ከሌሎች ድርጅቶች የምርምር ድጋፍ ለማግኘት ችለዋል።
ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ የሚከተሉትን ስራዎችም አከናውነዋል፣ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ (Masters and PhD) የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተማሪዎችን በማስተማርና በማማከር ፣SNEI በመባል የሚታወቀውን የኢትዮጵያ የሳይንስ ጆርናል የመጀመሪያ አዘጋጅ በመሆን፣ Natural Products Research Network for Eastern and Central Africa NAPPECA) በምስራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ በተፈጥሮ ውጤቶች ጥናትና ምርቶች ላይ ያተኮረ የእውቀት ትስስር ተቋም በዋና ፀሀፊነት ለ12 ዐመት በመምራት ፣ Science and tchnology toms translation project ( የሳይንሳዊ ቃላት ስያሜና ትርጉም መርሀ ግብር) ለ6 ዓመት በመሳተፍ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ፍላጉት እና አቅም ቅኝት ፕሮጀክት (University Industry Needs and Capabilities Survey Project) - ለሁለት ዐመት በመሳተፍ " የጌታቸው ቦሎዲያ ተቋም (foundation) ለ12 ዐመት መምራት ፣ African Laboratory for Natural Products (ALNAP) የተባለውን ኔትወርክ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ መመስረትና መምራት ፣ .com የተባለውን ከ5000 በላይ አገር በቀልና የአፍሪካ እፅዋትን ዝርዝር እና ጥቅም የያዘ ዳታቤዝ በመፍጠር ፣ በዘርፉ የሚሰማሩ ተመራማሪዎች እንዲሁም ማንኛውም ሰው የእፅዋቶችን ሣይንሳዊ ስምና ሌላ መረጃ- ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ከ15 በላይ _ የዓለም - አቀፍ : የውይይትና የልምድ : እና በቀላሉ እንዲያገኝ አድርገዋል፣ የመማማሪያ መድረኮች ላይ ተሳትፈዋል፤ ልምዳቸውንም አካፍለዋል ፤ አራት የሚሆኑ የሙያ ማህበራት አባል ሲሆኑ ናቸው፤ ማህበራቶቹን በማቋቋምም እረድተዋል እና ከ100 በላይ ላይ አሳትመዋል።ሳይንሳዊ የምርምር ጽሁፎችን በአለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ጆርናሎች
ፕሮፌሰር ኤርሚያስ የምርምር ጥናቶችና ውጤቶችን ወደተግባር ቀይረው፣ ሀገር በቀል ተክሎችን ግብአቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ እና ከኢትዬጵያ ውጭ የማህበረሰብ ጤና እና ደህንነት እንዲሻሻል፣ ሰፊ አበርክቶ አላቸው። ለዚህም ዋነኛ ተጠቃሽ የሆነው በ1992 ዓ.ም በእርሳቸውና በቤተሰባቸው የተቋቋመው አሪቲ የመዓዛማ ዕፅዋት ምርቶች ተብሎ የሚታወቀው ድርጅት ነው፡፡ አሪቲ ለውበት እና ለጤንነት መጠበቂያ የሚሆኑትንና እና ጥሩ መአዛ ያላቸውን ውጤቶችን ከሀገር በቀል እና መጤ እፅዋት ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም በማምረት እና ለገበያ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
ምርቶቹም በዲስቲሌሽን ከተለያዩ እፅዋት መዐዛማ ዘይትን በማውጣት፤ እንደባህሪያቸው በመቀመም ለጤና እና ውበት መጠበቂያ፤ ለጥሩ የቤት ውስጥ ጠረን እንዲሆን ተደርጎ እየተዘጋጁ : በሀገር ውስጥ እና ውጭ ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። እነዚህ ምርቶች በሀገር ውስጥ ለግል ተጠቃሚዎች፤ ሆቴሎች፤ ሎጆች እና የተለያዩ የጤና እና የውበት መንከባከቢያ ቦታዎች (SPA) በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ፣ ለውጭ ገበያ ሲቀርቡ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት እየጠቀሙ ይገኛሉ።
ከላይ ለተጠቀሱት ምርቶች ግብአት የሚሆኑት እፅዋት ከግል እርሻ እና ከተለያየ አካባቢ ገበሬዎች ይወሰዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አሪቲ ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር የአርክቦት _ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ (Agreement on Access to, and Benefit Sharing)። ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኜ ባለትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባትና የአራት ልጅ ልጆች አያት ናቸው።