Environmental Health professional Services

Environmental Health professional Services Provision of professional services and technical advice for health and safety Professional services
1. Counseling service for pre-and updating license
4.

Health and safety institutional assessment in Hotels, schools, industries and other public facilities to recommend feasible solutions
2. Health and safety training for food handlers, workers, managers, and owners
3. Technical advices on solid and liquid waste management
5. Facilitate food and water physical, chemical, bacteriological examination and
6. Others services

ሰምና ወርቅ አውጡ።።።የጳጉሜ ንዝንዝ እንደ አምና ታች'ምና መብረቅ ነጎድጓዱ የክረምቱ ጭፍና  የነ ሞፈር ማግዳ የነ እኝኝ ብላየሁለት ወር ዝናብ ሐምሌና ነሐሴመስከረም አበራ ተመለሰች ነፍሴ።
06/01/2023

ሰምና ወርቅ አውጡ
።።።
የጳጉሜ ንዝንዝ እንደ አምና ታች'ምና
መብረቅ ነጎድጓዱ የክረምቱ ጭፍና
የነ ሞፈር ማግዳ የነ እኝኝ ብላ
የሁለት ወር ዝናብ ሐምሌና ነሐሴ
መስከረም አበራ ተመለሰች ነፍሴ።

የጎዳና ላይ ምንግብ እና ንፅህና አጠባበቅምግብ ለሕይወት እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው፡፡ የምግብ ሙያተኞች እንደሚሉት ምግብ ከሰውነት መገንባት፣ በሽታን ከመከላከል ...
22/02/2016

የጎዳና ላይ ምንግብ እና ንፅህና አጠባበቅ
ምግብ ለሕይወት እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው፡፡ የምግብ ሙያተኞች እንደሚሉት ምግብ ከሰውነት መገንባት፣ በሽታን ከመከላከል እና ሃይል ና ጉልበት ከመስጠት ባሻገር ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ፋይዳዎች አሉት፡፡ እነዚህን ፋይዳዎች ከምግብ ለማግኔት ደግሞ ምግብ በንፅህና በመያዝ ከበሽታ ጠንቆች ተጋላጭነቱን መጠበቅ አለብን፡፡
ምግብ ከሚመረትበት ቦታ እስከ ጥቅም ላይ እስከሚውል ድረስ በአይን በማይታዩ ተሕዋስያን እና ለጤና ጠንቅ በሆኑ ኬሚካሎች የመበከል እድሉ በጣም የሰፋ ነው፡፡ የምግብ ወለድ በሽታ ደግሞ በህብረተሰቡና በሀገር እድገት ሊያስከትል የሚችለው ጫና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በስዕሉ ላይ እንደምታዩት በመንገድ ላይ የሚሽጡ ምግቦች ለዚህ ችግር ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው፡፡ ምክንያቱም
1. ምግብ ለማዘጋጅት የሚጠቀሙባቸው የምግብ ጥሬ እቃዎች የሚመረቱበት ቦታ በንፅህና መዘጋጅት አለመዘጋጀት ምንም አይነት መረጃ አለመኖር እና ዋጋ እንዲቀንስ ተብሎ ምናልባት የሚዘጋጁበት ስንዴ ዱቄት ወይም የሚጠበሱብት ዘይት ንፅሕናውን የጠበቀ መሆን አለመሆኑ ስለማይታወቅ፡፡
2. በማዘጋጀት ውቅት ያለው ሁኔታ ለምሳሌ በንፁህ ውሃ የተዘጋጁ ስለመሆናቸው እና የሚያዘጋጁት ግለሰቦች የንፅህና አጠባበቅ ግንዛቤ እና ጥንቃቄ ምን እንዲሚመስል የሚያመለክት ነገር ባለመኖሩ
3. ምግቦች ተዘጋጅተው ወደ ገበያ ከወጡ በኋላ በደንብ ስለማይሸፈኑ እና ስለማይያዙ
- ለምሳሌ ዳቦ በስተት ቢወድቅ የወደቀውን ዳቦ እስከ አቧራው ውደ ጤነኛው ምግብ የመቀላቀል እድሉ የሰፋ በመሆኑ
- የተዘጋጀው ምግብ በደንብ ስለማይከደን ለአቧራ እና ለዝንብ የመጋለጥ እድሉ በጣም ሰፊ በመሆኑ
4. ለተጠቃሚ በሚሰትበት ወቅት ያለምንም መቆንጠጫ ወይም መሳሪያ በመሆኑ የመነካካት እድሉ በጣም ሰፊ ነው፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን ምክሮች ለጓድኞቼ እመክራለው በሁኔታው ካመናችሁ ደግሞ ለሌሎች ጓደኞቻችሁ በማጋራት ሃላፊነታችን እንወጣ፡፡
ለተጠቃሚዎች፡-
- መንገድ ላይ የተዘጋጀን ምግብ ያለመመገብ ባህልን ማደበር አስገዳጅ ሁኔታ ከተፈጠረ ደግሞ ሁኔታዎችን በማመዛዘን በንፅህና የተዘጋጁ ምግቦችን መጠቀም
ምግብ ለሚሸጡ ግለሰቦች ፡ - የምግብን ንፅህና በመጠበቅ ከማዘጋጅት እስከ ተጠቃሚ እስከማቅረብ ድረስ ያሉትን ሰንሰለቶች በንፅህና መርህ ማዘጋጅት እና በአካባው በሚገኝ የጤና ድርጅት ስለ ምግብ ንፅህና ማብራሪያ በመጠየቅ በተገኜው ምክርና እውቀት መሰረት መስራት፡፡
ለመንግስት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች
1. መንገድ ላይ ምግብ የሚሸጡ ግልሰቦችን ስለ ምግብ ንፅህና እና ተያያዥ ጉዳዮች ስልጠና በመስጠት ወይም ዚጎች ሌሎች የስራ አማራጮችን እንዲሰሩ ማድረግ፡፡
2. በቀላሉ ሊበስሉ እና ሊደርሱ የሚችሉ ምግቦችን እሰከ መመሪያቸው ድረስ ለምግብ አዘጋጆችና ሻጮች መጠቆም ከነዚህም ውጭ ዚሰሩ ከተገኙ የማስተካከያ ርምጃ መውሰድ
3. በምግብ ንፅህና ላይ ጠለቅ ያለ እውቀትና ትግበራ እንዲኖር ህብረተሰቡን በተለያዬ መንገድ ለምሳሌ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጣ እና በመሰብሰቢያ ቦታዎች ማስተማር

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችከ50 በላይ የሚሆኑ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በአግቡ የተሰራ መፀዳጃ ቤት ሰርቶ በትክክል መጠቀም አማራጭ የለውም፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሰው ልጅ ክብሩን ማንነቱን ...
17/12/2015

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች
ከ50 በላይ የሚሆኑ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በአግቡ የተሰራ መፀዳጃ ቤት ሰርቶ በትክክል መጠቀም አማራጭ የለውም፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሰው ልጅ ክብሩን ማንነቱን እና የአካባቢውን ውበት ለመጠበቅ መፀዳጃ ቤት ቁልፍ ሚና ይጫዎታል፡፡ ስለሆነም ሕዝብ በበዛበት አካባቢ በተለይም በከተማ አካባቢ ለምሳሌ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች ከአገልግሎት መስጫ እና ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ በየ ሜዳው መፀዳዳት የተለመደ ስለመሆኑ በየ አጥሩ የተለጠፉ ማስጠንቀቂያዎች ምስክርነታቸው የጎላ ነው ፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የመፀዳጃ ቤት ተደራሽነት ሽፋን ደሕና በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል ነገር ግን የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር ከ10% አይበልጥም ይሕ ደግ አዲስ አበባን አበባ አስብሎ እና የአፍሪካ መዲና ተብላ እንድትጠራ አያስችላትም ታሪኳ እና የደረሰችበት ደረጀ አይመጥንም፡፡ አጠቃላይ የአካባቢን ንፅሕና በተመለከተ እያንዳንዱ ግለሰብ ለሚፈጥረው ቆሻሻ ሓላፊነቱን እንዲወስድ መንግሥትም ዜጎች በንፁሕ አካባቢ እንዲኖሩ ከሕገ መንግስቱ አንስቶ እስከ ተለያዩ ሕጎች ከግለሰብ እስከ ድርችት ድረስ አቅም በመገንባት የአገልግሎት ተደራሽነት እንዲረጋገጥ ማድረግ እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ በመሆኑም ከዚሕ በታች በሥዕሉ እንደምትመለከቱት በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች ቀጣይነታቸውን ያረጋግጣል በተባለ መንገድ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው ፡፡ ይሕ በራሱ ስኬት ባይሆንም የተጀመረው ጅማሮ እጅግ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ነገር ግን በሐገራችን እንዳንድ ተሞክረው የከሸፉ ተግባራት መኖራቸውን እንገነዘባለን ለምሳሌ የጋሼ አበራ ሞላ ፕሬጀክትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ያ ፕሮጀክት ጅማሮው ያማረ ሕዝብ የወደደው አብዛኛው ወጣት የተሳተፈበት ነበር ፡፡ ነገር ግን ለኛም ምናልባት ለራሱም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ወደ ሗላ ተቀልብሷል ይህ የሚመር የምንቀበለው እውነታ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚሕ መፀዳጃ ቤቶች ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ከተፈለገ ክትትል ና ንቁ ተሳትፎ ከሁላችንም የሚጠበቅ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ክትትል በማድረግ ዘላቂነቱን ከማረጋገጥ በተጨማሪ
1ኛ፡ የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች መፀዳጃ ለተጠቃሚዎች ክፍት እንዲያደርጉ መምከር ወይም ጥፋተኛችን ለሕዝብ ጤና ሲባል ማስተካካያ ርምጃ መውሰድ ፡፡
2ኛ፡ ድርጅቶችንና መገናኛ ብዙሃኑን በዚሕ ዙሪያ ላይ እንዲሰሩ ማድረግ
3ኛ፡ የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ
4ኛ፡ የፖሊሲ አቅጣጫን ማስተካከል እና ሌሎችንም መተግበር ያስፈልጋል፡፡ ከረጅም ባጭሩ ከብዙ በጥቂቱ ይሕ ሲሆን የዜጎችን ጤና በመጠበቅ የከተማዋንም ደረጃ መጠበቅ የሚቻለው፡፡ ከዚሕ በተጨማሪ ሌሎች ከተሞችም ልምድ በመቅሰም በዚሕ ዙሪያ ያለውን ችግር መቅረፍ ይቻላል፡፡

ለምንድን ነው በመፀዳጃ ቤት ውስጥ እባክዎ ከተጠቀሙ በኋላ ውሃ ያፍሱበት ተብሎ የሚፃፍ፡፡ ስለ እውነት በውሃ የሚሰራ መፀዳጃ ቤት መሆኑን  ባለማዎቅ ነው? ስለ እውነት እንዱ ያንዱን ቆሻሻ መ...
13/10/2015

ለምንድን ነው በመፀዳጃ ቤት ውስጥ እባክዎ ከተጠቀሙ በኋላ ውሃ ያፍሱበት ተብሎ የሚፃፍ፡፡ ስለ እውነት በውሃ የሚሰራ መፀዳጃ ቤት መሆኑን ባለማዎቅ ነው? ስለ እውነት እንዱ ያንዱን ቆሻሻ መመልከት የማያሳፍርና የሰው ልጆችን ክብር የሚፃረር መሆኑን አለማዎቅ ነው? ወይስ የስራ ብዛት ውሃ ማፍሰስ እንኳን የማንችልበት ጊዜ ጥበት አጋጥሞን ነው? ወይስ እያንዳንዳች ለራሳችን ቆሻሻ ሃላፊነትን ለመውሰድ ፈቃደኞች ሳንሆን ቀርተን?
ወይስ በሰውልጅ ዓይነ ምድር አማካኝነት የሚተላለፉ ከ50 በላይ ተላላፊ በሽታዎች መኖራቸውን ያለማወቅ ?
ወይስ ፅዳት ሰራተኞች የራሳቸው ጉዳይ ወይም የራሳቸው ስራ ብለን ትተነው?
ከትልቅ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ እስከ ትንሽ ሕንፃ ያለ ችግርና ምሬት ስለሆነ በተለይ ከተሜው እና ሙህር ነኝ የሚል ሁሉ ጥያቄው ስለሚያነጣጥር መልሱን እኔም፣ አንተም፣ አንችም እያንዳንዳችን እንመልሰው እና ከተጠቀምን በኋላ ውሃ ማፍሰስ እንጀምር፡፡ የተማረሩትን ፀዳት ሰራተኞችና የህንፃ እስተዳደሮች፣ የስራ አለቆችንም ይጨምራል

ስንቶቻችን ነን የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ አጠቃቀሙን የምንችል? እንዲያው አጋነንክ ባትሉኝ የእሳት ማጥፊያ በተለያዩ ድርጅቶች ተንጠልጥሎ ስናየው በትክክል የምናውቀው? እሳትን ያክል አደጋ አስፈ...
03/10/2015

ስንቶቻችን ነን የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ አጠቃቀሙን የምንችል? እንዲያው አጋነንክ ባትሉኝ የእሳት ማጥፊያ በተለያዩ ድርጅቶች ተንጠልጥሎ ስናየው በትክክል የምናውቀው? እሳትን ያክል አደጋ አስፈሪና አውዳሚ የእሳት ማጥፊያ ማጥፊያ ገዝተን በተጠንቀቅ መቆም ባንችልም፡፡ እችላለው የሚል እሰየው ነው፡፡ ከአጠገባችን ያለውን ለመጠቀም በሙሉ ልብ እንዴትስ እንደምንጠቀም በሙሉ ልብ የምንናገር እና የምናስረዳ ስንቶቻችን ነን ? ለማንኛውም የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ እንዴት የእሳት አደጋን ማጥፋት እንደሚቻል ይህንን ተንቀሳቃሽ ምስል በማየት ግንዛቤ እና ችሎታ ታገኛላችሁ በማለትና ተስፋ በማድረግ ለክቡራን ጓደኞቼ እንደሚከተለው ለጥፌአለው ፡፡

Training video for using a fire extinguisher

Do you have enough knowledge about indoor Air Pollution?
25/09/2015

Do you have enough knowledge about indoor Air Pollution?

22/09/2015

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Environmental Health professional Services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Environmental Health professional Services:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram