Hakim

Hakim Ethiopian blend of medicine, history & humor.
(217)

የፍቅረኛሽ የፆታዊ ግንኙነት ታሪኮች የአንቺን በማህፀን ጫፍ ካንሰር የመያዝ ዕድል ሊያሰፋ እንደሚችል ታውቂያለሽ? ዛሬ ስለ ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ እንማማራለን።አንድ ቫይረስ፤ አንድ ካንሰር።...
15/04/2026

የፍቅረኛሽ የፆታዊ ግንኙነት ታሪኮች የአንቺን በማህፀን ጫፍ ካንሰር የመያዝ ዕድል ሊያሰፋ እንደሚችል ታውቂያለሽ?

ዛሬ ስለ ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ እንማማራለን።

አንድ ቫይረስ፤ አንድ ካንሰር። ነገር ግን ብዙ የተቀጠፉ የሴት ልጅ ህይወቶች!

ወጣት እና ልጅ አገረድ ልጆች ሊያውቋቸው የሚገባ እውነቶች፦

I) አብዛኛው የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚከሰተው በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ መሆኑን።

II) ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ በፆታዊ ግንኙነት/ወሲብ ወቅት መተላለፉን።

III) የፍቅር ወይም የወሲብ አጋርሽ በበዛ ቁጥር በማህፀን ጫፍ ካንሰር የመያዝ ዕድልሽም ይጨምራል።

ማህበረሰባችን ውስጥ የሚታየው የግንዛቤ አናሳ መሆን፤ ለቫይረሱ የሚደረገውን ጥንቃቄ አስተጓግሎት ይገኛል። ይህ ቫይረስ በጣም በሰፊው የሚገኝ እና ብዙ ወጣት ወንዶች እና ሴቶችን የሚያጠቃም ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህ ቫይረስ የተጠቃች እንስት ሰውነቷ በአግባቡ ካልተቆጣጠረው እና ካላጠፋው ወደ ካንሰር የማደግ ዕድሉ ይበልጡን ያይላል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ችግሩን አሳሳቢ ከሚያደርጉት ነገሮች መኃከል፤ አብዛኛው ሴቶች ወደ ህክምና ተቋም ሲመጡ በመጨረሻው የበሽታ ደረጃዎች ላይ መገኘታቸው ነው። ይህም የህክምናውን ሂደት የሚገታ እና የመዳንን ዕድልንም በጣም የሚቀንስ ሆኖ እናገኘዋለን።

ታድያ እዚህ አስከፊ የበሸታ ደረጃ ላይ ላለመገኘት የሚረዱ ምርጦቹን ዘዴዎች እነሆ።

ሀ) የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባትን መውሰድ፤ በተለይ ልጅ አገረድ እንስቶች ከ 9 አመት ጀምሮ ቢወስዱት ይመከራል።

ለ) በተወሰኑ ግዜያት ልዩነት የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ

ሐ) አንድ ለአንድ መወሰን ወይም መታቀብ

መ) በወጣት ሴቶች መኃል የእርስ በእርስ ንግግሮች እና ምክክሮችን መከወን። ይሄ ሴት ልጅን ለተሻለ ግንዛቤ የማብቃት ዕድል አለው!!!

ከምንም በላይ እርስ በራስ ከመወነጃጀል ወይም ከመተማማት፤ ቀላል ውይይቶች ማድረግ ያለንን የዕውቀት ምህዳር ያሰፋል።
ዛሬውኑ እራስሽን እወቂ፤ በካንሰር የህክምና ማዕከሎችም በመገኘት በቂ ምርመራዎችንም አድርጊ።

ስለ ቅድመ ምርመራ፣ ስለ ፆታዊ ግንኙነት ያለመተፋፈር መወያየት ስልጡንነት ነው!!! እስኪ ለዛሬ እቺን ተወያዩባት?

References
1. https://share.google/F8tmk9Tjm2MUS0sEM

Source: National Institutes of Health (.gov) https://share.google/cANosqARveL3XLRUG

ዶ/ር ሚካኤል ሻውል ለማ
በካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር እና ቺፍ ክሊኒካል ኦንኮሎጂስት
ሐረማያ እና ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ

Telegram: t.me/HakimEthio

𝐀𝐝𝐯𝐚𝐧𝐜𝐞𝐝 𝐈𝐧𝐭𝐞𝐫𝐯𝐞𝐧𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐑𝐚𝐝𝐢𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲 𝐒𝐞𝐫𝐯𝐢𝐜𝐞𝐬𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐓𝐄𝐁𝐈𝐁 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥 is proud to provide cutting-edge 𝐈𝐧𝐭𝐞𝐫𝐯𝐞𝐧𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐑𝐚𝐝𝐢𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲...
15/04/2026

𝐀𝐝𝐯𝐚𝐧𝐜𝐞𝐝 𝐈𝐧𝐭𝐞𝐫𝐯𝐞𝐧𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐑𝐚𝐝𝐢𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲 𝐒𝐞𝐫𝐯𝐢𝐜𝐞𝐬

𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐓𝐄𝐁𝐈𝐁 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥 is proud to provide cutting-edge 𝐈𝐧𝐭𝐞𝐫𝐯𝐞𝐧𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐑𝐚𝐝𝐢𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲 services, offering minimally invasive, image-guided treatments for a wide range of conditions.

Using advanced technologies, our skilled team delivers precise, safe, and effective care with faster recovery and reduced hospital stays.

✳️ 𝐎𝐮𝐫 𝐈𝐧𝐭𝐞𝐫𝐯𝐞𝐧𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐑𝐚𝐝𝐢𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲 𝐒𝐞𝐫𝐯𝐢𝐜𝐞𝐬
♦️ Percutaneous Transhepatic Biliary Drainage (PTBD)
♦️ Trans-Arterial Chemoembolization (TACE)
♦️ Trans-Arterial Chemoinfusion (TACI)
♦️ CT / Ultrasound-Guided Biopsy, FNA & Drainage
♦️ Transrectal Ultrasound & Biopsy (TRUS)
♦️ T-Tube Cholangiography
♦️ MRI-Guided Procedures
♦️ Pigtail Catheter Placement & Exchange
♦️ Bronchial Artery Embolization (BAE)

🔆 𝐖𝐡𝐲 𝐂𝐡𝐨𝐨𝐬𝐞 𝐮𝐬?

➡️ Minimally invasive procedures with less pain and quicker recovery

➡️ High precision using advanced imaging guidance

➡️ Shorter hospital stays and faster return to daily life

➡️ Care delivered by experienced specialists with a patient-centered approach

Our Interventional Radiology unit is dedicated to innovation, accuracy, and compassionate care, helping patients achieve better outcomes with modern, less invasive techniques.

📞 For more information or to schedule an appointment:
Call 0935402078 or 9000

📍 Visit us: Road to Kolfe, Masalemiya Sefereselam

📱Telegram 📱Tiktok 📱Facebook 📱Instagram 📱Youtube

🩺 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨-𝐓𝐞𝐛𝐢𝐛 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥
We always strive for your health!

Mattu University's Medical Laboratory science graduates, 2026.
15/04/2026

Mattu University's Medical Laboratory science graduates, 2026.

Mattu University's Pharmacy graduates, 2026.
15/04/2026

Mattu University's Pharmacy graduates, 2026.

የጡት ሞኛሞኝ እጢ (Fibroadenoma) እድገት ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ  ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?አጋላጭ ምክንያቶች ብዙ ሲሆኑ፣  በዋነኛነት ከሆርሞን ለውጥ እና ከዘረመል ምክንያቶች ጋ...
15/04/2026

የጡት ሞኛሞኝ እጢ (Fibroadenoma) እድገት ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?

አጋላጭ ምክንያቶች ብዙ ሲሆኑ፣ በዋነኛነት ከሆርሞን ለውጥ እና ከዘረመል ምክንያቶች ጋር የተገናኙ ናቸው።

፩ የሆርሞን ተጽእኖ እና ለውጦች፦ ይህ በጣም ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ነው።

ከፍተኛ የኢስትሮጅን መጠን፦ እጢው የሚነሳው ጡት ለሴት ሆርሞን (estrogen) ከፍተኛ ስሜት በማሳየቱ እና በሆርሞኑ ተነሳስቶ በማደጉ ነው ።

· እርግዝና፦ በእርግዝና ወቅት የሆርሞን መጠን ከፍ ስለሚል እጢው በፍጥነት ሊያድግ ይችላል ።

· የወር አበባ ዑደት፦ በወር አበባ ወቅት በሚኖረው የሆርሞን መለዋወጥ ምክንያት የእጢው መጠን ሊለዋወጥ ይችላል ።

· ማረጥ፦ ከማረጥ በኋላ የሆርሞን መጠን ስለሚቀንስ እጢው እየጠበበ ሊጠፋ ይችላል።

· የሆርሞን ሕክምና ወይም ክኒን መጠቀም፦ ከ20 ዓመት በታች የወሊድ መከላከያ ክኒን መጠቀም እና ሌሎች የሆርሞን ሕክምናዎች ለእጢ መፈጠር እና እድገት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ።

፪ የዘረመል ምክንያቶች፦

· የጄኔቲክ ሚውቴሽን፦ እንደ MED12 እና PIK3CA ባሉ ጂኖች ላይ የሚከሰቱ ለውጦች (ሚውቴሽን) ለእጢ እድገት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። በተለይም PIK3CA ሚውቴሽን ከተደጋጋሚ እና ከፍተኛ እድገት ጋር ተያይዞ ሊገኝ እንደሚችል ይታመናል ።

የቤተሰብ ታሪክ፦ በቤተሰብ ውስጥ ሞኛሞኝ እጢ መኖሩ በዘር የሚተላለፍ ተጋላጭነት እንዳለ ያመላክታል ። በተለይም በርካታ እጢዎች (multiple fibroadenomas) ሲኖሩ የቤተሰብ ታሪክ በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ።

፫ ሌሎች አጋላጭ ሁኔታዎች፦

· ዕድሜ፦ በአብዛኛው ከ15 እስከ 35 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣት ሴቶች ላይ በብዛት ይታያል ።

· ከመጠን ያለፈ ውፍረት (obesity)፦ ከመጠን ያለፈ ውፍረት አጋላጭ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

· አመጋገብ፦ ከፍተኛ ስብ እና ስኳር ያለው ምግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የሆርሞን መጠን ሊጨምር ስለሚችል እንደ አንድ አጋላጭ ሁኔታ ይጠቀሳል።

· ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም፦ ጥቁር ቆዳ ያላቸው ሴቶች ላይ በብዛት እንደሚገኝ ጥናቶች ያመለክታሉ።

· ከፍተኛ የፕሮላክቲን ሆርሞን፦ አንዳንድ ጥናቶች ከፍተኛ የፕሮላክቲን መጠን ከከፍተኛ እድገት ጋር ተያይዞ ሊገኝ እንደሚችል ያሳያሉ።

ዶ/ር ካሳሁን ምትኩ: ጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት : ዓለም ሆስፒታል

‎telegram - https://t.me/Behaset
‎tik tok- https://www.tiktok.com/.kassahun?_t=ZM-8xXq1Uxnq2H&_r=1
‎face book
https://www.facebook.com/share/1Mpmhj7Uem/
‎linkedin -https://www.linkedin.com/in/kassahun-mitiku-b92373270

3 publication alert1. The burden of surgical site infection and associated factors among patients admitted to the surgic...
15/04/2026

3 publication alert

1. The burden of surgical site infection and associated factors among patients admitted to the surgical ward in resource-limited countries: an institutional-based cross-sectional study

Simachew Zewdu, Abel Daniel, Amene Abebe, Zinabu Abraham, Hailu Elias, Adamu Belete

2. Food insecurity and associated factors among adult cancer patients in south Ethiopia: a cross-sectional study

Samson Kastro Dake, Debritu Nane, Dibora Teferi Haile, Abiyu Legesse Munea & Abel Daniel Kuche

3. Testicular pain as an unusual presenting symptom of Aortic coarctation: a case report and review of the literature

Ephrem Basazinew, Temesgen Alemayehu, Azeb Werede, Maranata Teferi, Bereket Alemayehu, Getahun Derso & Merahi Kefyalew

PDF's uploaded on t.me/HakimEthio

14/04/2026

Best of luck to PC2 students of Hawassa University who will start their qualification exam tomorrow.

Meet Dr. Abebayehu Sahle, Psychiatrist and Dr. Kidist Hailemariam, Dermatovenereologist; graduating couples from the Uni...
14/04/2026

Meet Dr. Abebayehu Sahle, Psychiatrist and Dr. Kidist Hailemariam, Dermatovenereologist; graduating couples from the University of Gondar class of 2026.

"The path wasn’t a ladder; it was a mountain range. Some days we climbed, some days we stumbled, but today we stand at the peak together"

Telegram: t.me/HakimEthio

First batch Anesthesiology, critical care and pain medicine graduates of Yekatit 12 Hospital Medical College, 2026Pictur...
14/04/2026

First batch Anesthesiology, critical care and pain medicine graduates of Yekatit 12 Hospital Medical College, 2026

Pictured: Dr. Abel, Dr. Abiy, Dr. Bereket and Dr. Bisrat

ሚያዝያ ከአንገት በላይ የካንሰር ህመሞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር'በደንብ እናውራበት ፣ በጊዜ ቅድመ ምርመራዎችን እናድርግ ፣ ሂወትን እንታደግ''ይህ የያዝነው ሚያዝያ (April) ወር በተለያዩ...
14/04/2026

ሚያዝያ ከአንገት በላይ የካንሰር ህመሞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር

'በደንብ እናውራበት ፣ በጊዜ ቅድመ ምርመራዎችን እናድርግ ፣ ሂወትን እንታደግ''

ይህ የያዝነው ሚያዝያ (April) ወር በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በጤናው ማህበረሰብ ዘንድ የ'አንገት በላይ ካንሰር ህመሞች' ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ፤ ወሩ ስለ አንገት በላይ ካንሰር ህመሞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች ፡ ነፃ ምርመራዎች እና ህክምናዎች እየተሰጡበት የሚያልፍ ይሆናል።

እኔም ይህን በማስመልከት ስለአንገት በላይ ካንሰር ህመሞች ከሀገራችን ተጨባጭ ጋር በማያያዝ የተወሰኑ የግንዛቤ ነጥቦችን ለማንሳት ወደድኩ።

የአንገት በላይ ካንሰር ህመም ምንድነው?

በተለምዶ በአማርኛ ተቀራራቢ ፍቺው ' ከአንገት በላይ ካንሰር' እያልን ምንጠራው ህመም በእንግሊዝኛው 'Head and Neck Cancer' ተብሎ ሲጠራ ፤ የሰውነት ካንሰር ህመም አይነት ሲሆን በዋነኝነት የሚያካትተውም፦

1. የአፍ ውስጥ ካንሰር ህመሞች፥
ከንፈር : ምላስ : ላንቃ : ድድ:ጉንጭ...ያሉ የአፍ ውስጥ ክፉሎች ላይ ሚከሰቱ የካንስር ህመሞች

2. የጉሮሮ ካንሰር፥
የላይኛው : የመሀከላኛው እና የታችኛው ጉሮሮ ክፉል ካንሰር ህመሞች (Naso pharynx, Oropharynx, Hypopharynx & larynx Ca)

3. የአፍንጫ ውስጥ እና በአፍንጫ ዙሪያ የሚገኙ የ'ሳይነሰ'ክፍሎች ካንሰር ህመሞች

4. የምራቅ አመንጪ አካላት/'ዕጢዎች' የካንሰር ህመሞች (Salivary gland Ca): በአፋችን ውስጥ: ፊታችን ላይ እና አንገት ስር የሚገኙ የምራቅ አመንጪ አካላት ላይ የሚከሰቱ የካንሰር ህመሞችን ያካትታል።

የትኞቹ አይነቶች የካንሰር ህመሞች ከአንገት በላይ ሊከሰቱ ይችላሉ?

የተለያዩ የካንሰር ህመም አይነቶች ከላይ በዘረዘርናቸው የአንገት በላይ ክፍሎች ላይ ሊከሰቱ ቢችሉም፤በዋኝነት ግን ከአፍ ውስጥ ወይም ጉሮሮ ሽፋን ስጋዎች ላይ የሚነሳው ካንሰር ; በሳይንሳዊ ስያሜው Squamous cell carcinoma (SCC) ተብሎ ሚጠራው ዋነኛ/ቁጥር አንድ ተጠቃሽ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ከአጥንት (osteosarcoma): ከጡንቻዎች (Rhabdomyosarcoma): ከደም ቧንቧዎች (Angiosarcoma) : ከምራቅ አመንጪ አካላት (Mucoepidermoid Ca, ACC, AdCC...): ከንፍፊቶች (lymphomas): ከቆዳ ክፍሎች (Melanoma, BCC) ... የሚነሱ የካንሰር ህመሞች ከአንገት በላይ ባሉ ክፍሎች ላይ ሊከሰቱ ሚችሉ ተጠቃሽ የካንሰር አይነቶች ናቸው::

ስርጭቱ

እንደ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ከአንገት በላይ ካንሰር ህመሞች ከሌሎች የሰውነት ክፍል የካንሰር ህመሞች አንፃር በመከሰት በ7ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ። የሳንባ ካንሰር:የሴቶች የጡት ካንስር እና የትልቁ አንጀት ካንሰር ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

እንዲሁም ከአንገት በላይ ካንሰር ህመሞች በአብዛኛው(ወደ 50% ሚጠጉት) ሚከሰቱት አፍ ውስጥ ባሉ አካላት ላይ እንደሆነ ጥናቶች ያመላክታሉ።

አጋላጭ ምክንያቶች/መንስኤዎቹ

የተለያዩ ምክንያቶች ለአንገት በላይ ካንሰር እንደ አጋላጭ መንስኤዎች ቢቀመጡም፤በዋነኝነት ግን ሲጋራ መጠቀም: አልኮል መጠጣት እና የ'HPV '(ቫይረስ) ኢንፌክሽን ተጠቃሾች ናቸው።

በተጨማሪም መጥፎ የአፍ ውስጥ ንፅህና : የፀሀይ ጨረር : የህክምና ጨረር : ሌሎች የቫይረስ ኢንፌክሽኖች (EBV, CMV..): የስራ ቦታ ተጋላጭነት(የካንሰር አመንጪ ኬሚካሎች/carcinogenic chemicals) : እድሜ : በዘር (genetics )... ሌሎች ተጠቃሽ አጋላጭ ምክንያቶች ሆነው ይቀርባሉ።

በአጠቃላይ አጋላጭ ምክንያቶቹ (risk factors) እንደ ካንሰሩ አይነት እና የተከሰተበት የሰውነት ክፍል የተለያየ ሊሆን ይችላል። ማለትም; ለአፍ ውስጥ ካንሰር ሲጋራ እና አልኮል እንደ ዋነኛ አጋላጭ ምክንያቶች ሲጠቀሱ ፤ ለጉሮሮው የመሀከለኛው ክፍል ካንሰር (OPCa) ደግሞ HPV (ቫይረስ) ኢንፌክሽ ቁጥር አንድ ተጠቃሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ለከንፈር ላይ ካንሰር የፀሀይ ጨረር ተጋላጭነት በዋነኝነት ይጠቀሳል።

ምልክቶቹ

የአንገት በላይ ካንሰር ህመም ምልክቶች ;ካንሰሩ እንደተከሰተበት ቦታ : የካንሰሩ አይነት እና ደረጃ የተለያዩ ሲሆኑ ፤ በቀጣይ በዝርዝር በሌሎች ፅሁፎች የምመለስበት ይሆናል።

የሀገራችን ነባራዊ ሁኔት እና የአንገት በላይ ካንሰር ህመሞች

ከአንገት በላይ የሚከሰቱ የካንሰር ህመሞች በሀገራችን ስላላቸው ስርጭት እና በህብረተሰባችን ላይ እያሳደሩ ስላለው ህመም : ስቃይ : ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫና እንዲሁም የሞት ቁጥር በሰፊው እና በዝርዝር የተሰሩ ብዙ ጥናቶች ባይኖሩንም ፤ እኔም ሆንኩ ሌሎች በዚህ አካባቢ/ዙሪያ ላይ የምንሰራ ባለሞያዎች ላለፉት አመታት እያየነው/እያስተናገድነው ካለው የህመሙ ተጠቂዎች ሁኔታ አንፃር ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ለመናገር አያዳግትም።

በተለይም በአብዛኛው የማህበረሰባችን ክፍል ውስጥ ስለእነዚህ የካንሰር ህመም አይነቶች ያለው ግንዛቤ ደካማ በመሆኑ(በስራ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ካየነው አንፃር)፤ብዙሀኑ የህመሙ ተጠቂዎች ተገቢው ህክምና ቦታ ሲደርሱ ደረጃው በጣም ከፍ ብሎ እንዲሁም በአካባቢው በጣም ተስፋፍቶ አልፎም ወደ ሌሎች ራቅ ያሉ የሰውነት አካባቢዎች ተሰራጭቶ /distal metastasis (ወደ ሳንባ : ጉበት : ኩላሊት...) እና በህክምና የመዳን ውጤታማነቱም ካነሰ ቡሀላ ነው።

ለዚህም እንደምሳሌ ባለፈው አንድ ወር ብቻ አራት የአንገት በላይ ካንሰር ታማሚዎችን ያየሁ (ያከምኩ ሲሆን) ካየዋቸው (ካከምኳቸው) አራቱ የአንገት በላይ ካንሰር ታማሚዎች (የከንፈር : የምላስ : የድድ/ጉንጭ እና የፊት ላይ ምራቅ አመንጪ አካል ካንሰር ታማሚዎች ሲሆኑ) ሶስቱ እኔ ሳያቸው የካንሰር ህመማቸው ደረጃ 4 ከፋተኛው ላይ የደረሰ እና ወደ ሳንባ ሳይቀር ስርጭት ያለው አካባቢያዊ ስርጭቱም ቢሆን ከፍተኛ ሆኖ ለቀዶ ህክምና አመቺ ስላልሆኑ (non Operable) ወደ ሌሎች ህክምና አማራጮች (chemo-radio theraphy) የላንክናቸው ሲሆን አንደኛው ግን ደረጃ 3 ሆኖ ስርጭቱም አነስተኛ ስለነበር የቀዶ ህክምና ሰርቼለታለሁ።

የሚያስከትለው ጉዳት

ከአንገት በላይ የካንሰር ህመሞች በጊዜ ተደርሶባቸው ተገቢውን ህክምና እና ክትትል ካልተደረገላቸው ፤ ከፍተኛ ህመም ስቃይ እንዲሁም በቀን ተቀን ኑሮው ላይ ከፍተኛ ጫና ከማሳደር አልፈው ለሞት ይዳርጋሉ።

ማስታወሻ

ስለ አንገት በላይ የካንሰር ህመሞች አጋላጭ ምክንያቶች/መንስኤዎች ፣ ምልክቶች ፣ ደረጃዎች ፣ ቅደመ ጥንቃቄዎች ፣ ተያያዥ ጉዳዮች እና የህክም አማራጮች በዝርዝር በተከታታይ በሚቀጥሉት ቀናት መረጃዎችን ለማድረስ እሞክራለሁ።

*ማጣቀሻ መፀሀፍት መረጃዎች/References

1. Oral and Maxillofacial Surgery Fonseca ... Volume 2, third edition

2. Jatin Shah's Head and Neck Surgery and Oncology: Expert Consult: Online and Print
5th Edition

3. Neelima-Anil-Malik, Textbook of Oral and Maxillofacial Surgery ,5th Edition

''በደንብ እናውራበት ፣ በጊዜ ቅድመ ምርመራዎችን እናድርግ ፣ ሂወትን እንታደግ''

ዶ/ር ፉአድ ሙሀመድ (DMD, OMFS)
የአፍ ውስጥ የመንጋጋ እና ፊት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት

Telegram: t.me/HakimEthio

𝗔𝘀 𝗮 𝗦𝗼𝘂𝘁𝗵 𝗦𝘂𝗱𝗮𝗻𝗲𝘀𝗲 𝗱𝗼𝗰𝘁𝗼𝗿 𝘁𝗿𝗮𝗶𝗻𝗲𝗱 𝗮𝗻𝗱 𝗻𝗼𝘄 𝘀𝗲𝗿𝘃𝗶𝗻𝗴 𝗮𝘀 𝗮𝗻 𝗶𝗻𝘁𝗲𝗿𝗻 𝗶𝗻 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮, 𝗜 𝗵𝗮𝘃𝗲 𝗯𝗼𝘁𝗵 𝗼𝗯𝘀𝗲𝗿𝘃𝗲𝗱 𝗮𝗻𝗱 𝗲𝘅𝗽𝗲𝗿𝗶𝗲𝗻𝗰𝗲𝗱 𝘁𝗵𝗲 𝗰𝗵...
14/04/2026

𝗔𝘀 𝗮 𝗦𝗼𝘂𝘁𝗵 𝗦𝘂𝗱𝗮𝗻𝗲𝘀𝗲 𝗱𝗼𝗰𝘁𝗼𝗿 𝘁𝗿𝗮𝗶𝗻𝗲𝗱 𝗮𝗻𝗱 𝗻𝗼𝘄 𝘀𝗲𝗿𝘃𝗶𝗻𝗴 𝗮𝘀 𝗮𝗻 𝗶𝗻𝘁𝗲𝗿𝗻 𝗶𝗻 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮, 𝗜 𝗵𝗮𝘃𝗲 𝗯𝗼𝘁𝗵 𝗼𝗯𝘀𝗲𝗿𝘃𝗲𝗱 𝗮𝗻𝗱 𝗲𝘅𝗽𝗲𝗿𝗶𝗲𝗻𝗰𝗲𝗱 𝘁𝗵𝗲 𝗰𝗵𝗮𝗹𝗹𝗲𝗻𝗴𝗲𝘀 𝗱𝗼𝗰𝘁𝗼𝗿𝘀 𝗳𝗮𝗰𝗲—𝗮𝗻𝗱 𝘁𝗵𝗲 𝘀𝘂𝗳𝗳𝗲𝗿𝗶𝗻𝗴 𝘁𝗵𝗲𝘆 𝗲𝗻𝗱𝘂𝗿𝗲—𝗶𝗻 𝗯𝗼𝘁𝗵 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 𝗮𝗻𝗱 𝗦𝗼𝘂𝘁𝗵 𝗦𝘂𝗱𝗮𝗻.

Medical doctors across sub-Saharan Africa, including Ethiopia and South Sudan, confront multiple overlapping challenges that undermine their working conditions and the quality of care they provide.

𝗕𝗲𝗹𝗼𝘄 𝗮𝗿𝗲 𝗳𝗼𝘂𝗿 𝗺𝗮𝗷𝗼𝗿 𝗰𝗵𝗮𝗹𝗹𝗲𝗻𝗴𝗲𝘀:

1. 𝗦𝗲𝘃𝗲𝗿𝗲 𝘀𝗵𝗼𝗿𝘁𝗮𝗴𝗲 𝗮𝗻𝗱 𝘂𝗻𝗲𝘃𝗲𝗻 𝗱𝗶𝘀𝘁𝗿𝗶𝗯𝘂𝘁𝗶𝗼𝗻 𝗼𝗳 𝗱𝗼𝗰𝘁𝗼𝗿𝘀.

Sub‑Saharan Africa has far fewer doctors per capita than WHO recommends, and most physicians are concentrated in urban centers, leaving rural areas critically underserved.
In Ethiopia and South Sudan, the doctor‑to‑population ratios are extremely low, which means each doctor carries an enormous clinical load, especially in rural and conflict‑affected regions.

2. 𝗪𝗲𝗮𝗸 𝗶𝗻𝗳𝗿𝗮𝘀𝘁𝗿𝘂𝗰𝘁𝘂𝗿𝗲 𝗮𝗻𝗱 𝗹𝗮𝗰𝗸 𝗼𝗳 𝗯𝗮𝘀𝗶𝗰 𝘀𝘂𝗽𝗽𝗹𝗶𝗲𝘀.

Many health facilities lack reliable electricity, clean water, laboratory capacity, and essential medicines, forcing doctors to work with limited diagnostic and therapeutic tools. In South Sudan, for example, repeated conflict and under‑funding have left many clinics non‑functional or operating without adequate drugs, so doctors often cannot treat conditions that would be straightforward in better‑resourced settings. The best example happened a few months ago, when Juba Teaching Hospital stayed without electricity for 3 days.

3. 𝗟𝗼𝘄 𝗽𝗮𝘆, 𝗽𝗼𝗼𝗿 𝘄𝗼𝗿𝗸𝗶𝗻𝗴 𝗰𝗼𝗻𝗱𝗶𝘁𝗶𝗼𝗻𝘀, 𝗮𝗻𝗱 𝗷𝗼𝗯 𝗱𝗶𝘀𝘀𝗮𝘁𝗶𝘀𝗳𝗮𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻.

Public‑sector doctors in Ethiopia and similar countries are among the lowest‑paid in the region, leading to high dissatisfaction and morale problems. Long hours, overcrowded wards, and frequent strikes or political crackdowns on health‑worker protests further demotivate the workforce and drive some to seek opportunities abroad.

4. 𝗣𝗼𝗹𝗶𝘁𝗶𝗰𝗮𝗹 𝗶𝗻𝘀𝘁𝗮𝗯𝗶𝗹𝗶𝘁𝘆, 𝗰𝗼𝗻𝗳𝗹𝗶𝗰𝘁, 𝗮𝗻𝗱 𝘄𝗲𝗮𝗸 𝗵𝗲𝗮𝗹𝘁𝗵‑𝘀𝘆𝘀𝘁𝗲𝗺 𝗴𝗼𝘃𝗲𝗿𝗻𝗮𝗻𝗰𝗲.

In Ethiopia and South Sudan, armed conflict, displacement, and volatile governance directly disrupt healthcare delivery and threaten the safety of doctors.

Heavy political interference, inadequate health‑system leadership, and under‑funding mean that doctors often work in environments where health policy is unpredictable and resources are rationed according to priorities other than patient need.

𝗜𝗻 𝗰𝗼𝗻𝗰𝗹𝘂𝘀𝗶𝗼𝗻, I know someone may ask, "What are the possible solutions to these challenges?"

Well, the answer is complex, far and wide. The solution requires regional political stability, clear states priorities, and redirection of the countries' resources to where concerns are most severe and cannot wait.

𝗔𝘁 𝘁𝗵𝗲 𝗲𝗻𝗱 𝗼𝗳 𝘁𝗵𝗲 𝗱𝗮𝘆, I must recognize and applaud the dedication, commitment, and stamina of Ethiopian doctors, who serve their people and country despite low pay and job dissatisfaction.

𝗠𝗼𝗿𝗲𝗼𝘃𝗲𝗿, Ethiopia's healthcare system is trying its best to solve many challenges. All it needs to do is pay a little more attention to the challenges faced by doctors and all health professionals—because, as the Uganda Medical Association (UMA) posted in the context of doctors' grievances over salaries and working conditions, “A hungry and angry doctor is a dangerous doctor.”

In the case of South Sudan's dead healthcare system, which has failed both health professionals and its people, all it needs is the power of the resurrected Jesus Christ to restore it to life.

𝗟𝗮𝘀𝘁 𝗯𝘂𝘁 𝗻𝗼𝘁 𝗹𝗲𝗮𝘀𝘁, I must applaud the resilience of health professionals in South Sudan, who are giving their best to serve their people despite all the challenges.

𝗕𝘆 𝗗𝗿. 𝗖𝗵𝗼𝗹 𝗣𝗲𝘁𝗲𝗿 𝗞𝗲𝗹𝗲𝗶. 𝗠𝗲𝗱𝗶𝗰𝗮𝗹 𝗜𝗻𝘁𝗲𝗿𝗻 𝗮𝘁 𝗝𝗶𝗺𝗺𝗮 𝗠𝗲𝗱𝗶𝗰𝗮𝗹 𝗖𝗲𝗻𝘁𝗿𝗲, 𝗝𝗶𝗺𝗺𝗮 𝗭𝗼𝗻𝗲, 𝗢𝗿𝗼𝗺𝗶𝗮 𝗥𝗲𝗴𝗶𝗼𝗻, 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮.



Telegram: t.me/HakimEthio

የከሰል ጭስ: እንደ ቀልድ ነፍስ ነጣቂው መርዝ! #ወቅታዊ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ካለው የአየር ፀባይ ጋር ተያይዞ ቅዝቃዜን ለመከላከል ወይም ምግብ ለማብሰል በርካቶች ከሰልን ይጠቀማሉ። ይሁን...
13/04/2026

የከሰል ጭስ: እንደ ቀልድ ነፍስ ነጣቂው መርዝ!
#ወቅታዊ

ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ካለው የአየር ፀባይ ጋር ተያይዞ ቅዝቃዜን ለመከላከል ወይም ምግብ ለማብሰል በርካቶች ከሰልን ይጠቀማሉ።

ይሁንና ከሰል በአግባቡ ካልተያዘ ወደ መርዝነት በመቀየር ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡

የከሰል ጭስ በውስጡ ካርበን ሞኖክሳይድ (CO) የሚባል በአይን የማይታይ ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ ይይዛል።

ይህ መርዛማ አየር (CO) በሳንባችን በኩል ወደ ወደ ደም ዝውውር ብሎም ወደ መላው ሰውነት ውስጥ ይገባል። CO ቀይ የደም ህዋሳት (Red blood cells) ኦክስጂንን (O2) የሚሸከሙበትን ቦታ በመሻማት ይጣበቅና የኦከስጂን እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል። በዚህም የተነሳ አንጎል፣ የነርቭ ክፍሎች እና ልብ ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።

በከሰል ጭስ ወይም በካርበን ሞኖክሳይድ (CO) መመረዝ/መታፈን ቀላል የሆነ ጉዳት የደረሰበት ሰው ማዞር፣ ግራ መጋባት ፣ ሚዛን ለመጠበቅ መቸገር ፣ የሆድ ህመም እና ማቅለሽለሽ ፣ ለመተንፈስ መቸገር እና የመሳሰሉት ምልክቶችን ያሳያል።

በካርቦንሞኖክሳይድ በከፍተኛ ሁኔታ የተመረዘ ሰው ደግሞ መንቀጥቀጥ ፣ የልብ ምት መዛባት ፣ ደረት አካባቢ የሚሰማ ከፍተኛ የልብ ምት ፣ እራስን መሳት ፣ ፓራላይዝ መሆን እንዲሁም እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት ሊያጋጥመው እንደሚችል ባለሙያው አስረድተዋል።

በከሰል ጭስ ጉዳት የደረሰበት ሰው ወደ ሕክምና ተቋም ከመወሰዱ በፊት የሚደረግለት የሕክምና እርዳታ ምን መምሰል አለበት?

የመጀመሪያው በከሰል ጭስ ጉዳት የደረሰበትን ሰው ክፍት የሆነ እና አየር የሚያገኝበት ቦታ ላይ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው። እራሱን ያልሳተ ሰው ከሆነ ወደ ጤና ተቋም እስኪወሰድ በፍጥነት ከቤት ውጭ በመውጣት አየር የምያገኝበት ቦታ ላይ አድርጎ ማናፈስ ተገቢ ነው።

በተለይ እያስመለሰው ያለ ሰው ከሆነ ከጭንቅላቱ ደገፍ ተደርጎና እግሮቹ በከፍል ታጥፎ በጎኑ በማስተኛት ወደ ሕክምና ተቋም በፍጥነት መውሰድ እንደሚገባ ባለሙያው ገልፀዋል፡፡

እራሱን የሳተ ሰው ከሆነ ወደ አፉ ውስጥ ምንም አይነት ነገር አለመጨመር ይመከራል ፤ እንዲሁም አፉ ውስጥ ምግብ ፣ ትውከት ወይም ሌላ ባዕድ ነገር ካለ በጥንቃቄ ወደ ጎን አስተኝቶ ከአፉ ውስጥ ጠርጎ ማስወጣት ይገባል።

ለመተንፈስ በመቸገር ላይ ያለ ሰው ከሆነ በተቻለ ፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ማድረስ ተጎጂውን ሰው ከሞትና ከቋሚ የጤና ጉዳት ለመታደግ ወሳኝ ነው። በመንገድ ላይም አፍና አፍንጫው ክፍት መሆኑን ማረጋገጥ፣ አንገቱን ቀና ማድረግ እንዲሁም ደረቱን በማይጎዳ ሁኔታ በየሰከንዱ ልዩነት ጫን ጫን በማድረግ (CPR) እርዳታ ማድረግ የነፍስ ማዳን እንቅስቃሴውን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል።

ከሰል በምንጠቀምበት ወቅት ቤት ውስጥ በቂ አየር እንዲገባ በር እና መስኮቶች ክፍት መሆን እንደሚገባቸው አንስተው ፤ ከሰልን ከተጠቀሙ በኋላም በማጥፋት ቤት ውስጥ በቂ አየር እንዲገባ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በተለይ በዚህ የክረምት ወቅት እና በበዓል ሰሞን ማህበረሰቡ ለእራሱም ሆነ ለጎረቤቶቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ አደጋዎችን በንቃት እንከላከል።

References

1. Carbon Monoxide Poisoning Basics. CDC.gov. Jan., 2026.

2. CO Poisoning. First Aid & Emergencies. Nov, 2024.

3. CO Poisoning causes & symptims. Mayo Clinic First-Aid Guide for the Outdoor Adventurer. March, 2025

4. Carbon Monoxide Poisoning.
Medically Reviewed. Cleveland Clinic. July, 2023.

Dr. Girma Diltata: Neurologist

Telegram: t.me/HakimEthio

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hakim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share