Ethio Doctors

  • Home
  • Ethio Doctors

Ethio Doctors This is a site created by Ethiopian Doctors to provide the best lifestyle and health tips. Like and follow us to be updated with recent medical advices.

Meqrez Hospital @ Addis Ababa!Where you will find every speciality and subspecialties!!!
17/11/2023

Meqrez Hospital @ Addis Ababa!
Where you will find every speciality and subspecialties!!!

10 Athletes who brought the medals!!!
31/07/2022

10 Athletes who brought the medals!!!

This is the list of athletes who brought these medals for Ethiopia.

World Kidney Day
10/03/2022

World Kidney Day

03/02/2022

Hello guys,
What do you think about our page? We would like to get your reviews on our page and please write the things you want to be improved in the review.

ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች 8 ምርጥ ምግቦች 1. ገብስ:- ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸ...
03/12/2021

ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች 8 ምርጥ ምግቦች

1. ገብስ:- ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

2. ባቄላ እና ዘሮቹ:- ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

3. እንቁላል(በመጠኑ):- እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

4. አሳ:- የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

5. የአበሻ አይብ:- የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

6. የወይራ ዘይት:- በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ ዘይት ከፍተኛ anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

7. ስኳር ድንች:- ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው። ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን insulin resistance ይዋጋሉ።

8. ቀይ ስጋ በመጠኑ:- ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?1) የፀጉር መነቃቀል ያስከትላል አልፎም መመለጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡2) በአንጎል ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ለእንቅልፍ እጦት፤ራስምታት፤መነጫነ...
29/11/2021

ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?

1) የፀጉር መነቃቀል ያስከትላል አልፎም መመለጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡

2) በአንጎል ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ለእንቅልፍ እጦት፤ራስምታት፤መነጫነጭ፤መደበትና እና የባህርይ ለዉጥን ያስከትላል፡፡

3) በከንፈር ላይ የሚወጡ አንዳንድ ቁስለቶች ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

4) ለደም ግፊት መጨመር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡ ለልብ ሕመምም ይዳርጋል፡፡

5) በሳንባ ላይ የሚያስከትለው ችግር የአስም ሕመምተኞች ላይ የአዕምሮ ጭንቀት ሕመማቸው እንዲነሳባቸው ያደርጋል፡፡

6) በጡንቻዎች ላይ ሕመም ስሜት እንዲኖር ያደርጋል ለወገብ ሕመም ያጋላጣል፡፡

7) ጭንቀት የጨጓራ ሕመምን ከማስከተል ባለፈ ለአንጀት ቁስለትም ሊዳረግ ይችላል፡፡

8) ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት የወር አበባ ዑደትን ያዛባል፡፡ ወንዶችን ለስንፈተ ወሲብ ስለሚዳርግ የትዳር እና የፍቅር ግንኙነት እንዲሻክር ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ጭንቀትን በማስወገድ ጤንነትዎን ይጠብቁ የዛሬዉ መልዕክቴ ነዉ፡፡

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ

ጤና ይስጥልኝ

ነስር (የአፍንጫ መድማት)እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ነስር በሁ...
26/11/2021

ነስር (የአፍንጫ መድማት)
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!

በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡
ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል፡፡

1) ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)
• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡ ከፍተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይንም ማቆም ይቻላል፡፡

2) ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)
• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይንት በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከሌላኛው የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡

✔ ነስርን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

• የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነስር ነው፡፡
• በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት
• በተለያዩ የሕመም ወይንም መድኃኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል

✔ ነስርን እንዴት ማቆም ይቻላል?

• ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም)
• ቀጥ ብለው መቀመጥ
• ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣትዎ እና በጠቋሚ ታትም ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት
• በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት
• ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት ናቸው፡፡

✔ ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ የሚያቆም ካልሆነ
• በአጭር ጊዜ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነስርዎ ከሆነ
• ራስ ማዞር ወይንም ራስዎን የሚስቱ ከመሰለዎት
• የልብ ምትዎ የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ ከተቸገሩ
• ደም የሚያስመልስዎ ከሆነ
• በሰውነትዎ ላይ ሽፍታ ከኖረ
• ትኩሳት ካለዎት
• ከነስር ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች መድማት የሚኖር ከሆነ
• በቀላሉ የመበለዝ ምልክቶች በሰውነትዎ ላይ ከተገኙ
• ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወሰዱ ከሆነ
• የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለዎት
• የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ ነው፡፡

✔ነስርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

• በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ጊዜ ነው፡፡ ለነስር ተጋላጭ የሆኑ ከሆነ አፍንጫዎ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) በመጠቀም ማለስለስ ይችላል፡፡
• አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት
• የነስርዎ መነስዔ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪምዎን ማማከር የሚሰጥዎን የጤና ምክር መተግበር
• ሲጋራ ማጤስ አፍንጫን በማድረቅ ለነስር ስለሚዳርግ ማስወገድ ናቸዉ፡፡

ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።

ኩላሊትዎን ሊጎዱ የሚችሉ 7 ሁኔታዎች1. በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ - በቂ ውሃን አለመጠጣት የኩላሊት ሥራ የሆነውን አላስፈላጊ ቆሻሻን ከሰውነታችን ማስወገድ በሚገባ እንዳያከናውን ስለሚያደርግ ቆ...
22/11/2021

ኩላሊትዎን ሊጎዱ የሚችሉ 7 ሁኔታዎች

1. በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ - በቂ ውሃን አለመጠጣት የኩላሊት ሥራ የሆነውን አላስፈላጊ ቆሻሻን ከሰውነታችን ማስወገድ በሚገባ እንዳያከናውን ስለሚያደርግ ቆሻሻው በኩላሊታችን ውስጥ ተከማችቶ ጉዳት እንዲያስከትል ያደርጋል፡፡

2. የውሃ ሽንትን መቋጠር - የውሃ ሽንትን ማስወገድ በሚገባን ጊዜ ሳናስወግድ የምንይዘው ከሆነ እና ይህን ተግባር የምናዘወትር ከሆነ የሽንት ፊኛችንም ሆነ ኩላሊታችንን አደጋ ላይ የምንጥል መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

3. ጨው የበዛበትን ምግብ መውሰድ - ጨዋማ ምግቦችን መመገብ የኩላሉትን ጨውን (sodium) ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራ ጫና እንዲበዛበትና ሲቆይም ለችግር እንዲጋለጥ ያደርጋል፡፡

4. ካፊን በብዛት መውሰድ - በሚጠማን ጊዜ ውኃ ከመጠጣት ይልቅ ለስላሳ መጠጦችን እንደ ጥም ቆራጭነት እንጠቀማለን፡፡ ካፌን የደም ግፊት መጠናችንን በመጨመር ኩላሊትን ይጎዳል፡፡

5. ሕመም ማስታገሻ አለአግባብ መውሰድ - ቀላል ለሚባል የሕመም ስሜት ሕመም ማስታገሻዎችን መውሰድ አላስፈላጊ እና አልፎ ተርፎም ከባድ የሆነ የኩላሊት ጉዳትን ሊያደርስ ይችላል፡፡

6. የአልኮል መጠጥን በብዛት መጠጣት - ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥን ማዘውተር የኩላሊት ችግር ያስከትላል፡፡

7. ሲጋራ ማጤስ - ለኩላሊት መድረስ የሚገባውን የደም መጠን ስለሚቀንስ ሲጋራ ማጤስ እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

ሼርርርር

🚹 ጤናማ የደም ግፊት መጠን ― 120/80 🚹 ጤናማ የደም ሥኳር መጠን ― ከ 70 እስከ 120🚹 ጤናማ የልብ ምት በደቂቃ ― ከ 60 እስከ 100🚹 ጤናማ የኮሌስትሮል መጠን በሚሊ-ግራም ― 2...
19/11/2021

🚹 ጤናማ የደም ግፊት መጠን ― 120/80
🚹 ጤናማ የደም ሥኳር መጠን ― ከ 70 እስከ 120
🚹 ጤናማ የልብ ምት በደቂቃ ― ከ 60 እስከ 100
🚹 ጤናማ የኮሌስትሮል መጠን በሚሊ-ግራም ― 200
🚹 ጤናማ የሰውነት ክብደት ከቁመት ጋር ያለው ንጽጽር (BMI) ― ከ 20 እስከ 25
🚹 ሰውነታችን በሳምንት ውስጥ የሚያስፈልገው የእንቅስቃሴ መጠን በደቂቃ ― 150 ደቂቃ
🚹 በቀን ውስጥ የሚያስፈልገን የመጠጥ ውሃ መጠን በሊትር ― ከ 2 እስከ 3 ሊትር
🚹 በቀን ውስጥ ማግኘት ያለብን የእንቅልፍ ሠዓት ― ከ 7 እስከ 9 ሠዓት

“ጤና ይብዛልዎት”
ሼርርርር

✅🌀 በኩላሊት ጠጠር ለሚሰቃዩ ሰዎች የጤና መረጃ ✅🌀 የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ-----------••••••••••••••••••------------------በአሁኑ ሰዓት የ...
15/11/2021

✅🌀 በኩላሊት ጠጠር ለሚሰቃዩ ሰዎች የጤና መረጃ
✅🌀 የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ
-----------••••••••••••••••••------------------
በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ጠጠር በጣም በብዙዎች ዘንድ የሚከሰት ችግር ሆኗል፡፡ ጠጠሩ የሚፈጠረው በሚኒራሎች እና በአሲዳማ ጨው በኩላሊት ውስጥ ሲሆን የሚከማቸው በኩላሊት ውስጥ ወይም በላይኛው የሺንት ቧንቧ አልያም በሽንት ፊኛ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡
የሚፈጠሩት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ግን እዚያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ እዚያው የሚቆዩ ጠጠሮች ካልተወገዱ፣ አንድ ላይ ትልቅ ጠጠር መፍጠራቸው አይቀርም፡፡

ምናልባት የጎልፍ ኳስ ያክል መጠን ሊደርስም ይችላል፡፡ ይህም የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ፣ በምንሸናበት ሰዓት ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል፣ ማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም ማስታዎክ ያስከትላል እነዚህ ችግሮች ጠጠሩ አስካልተወገደ ድረስ ቀጣይነት ይኖራቸዋል እንጂ አይተውንም፡፡

🚺🚹 የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች

የኩላሊት ጠጠር ከሰውነታችን በተለያዩ መንገዶች ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም በጠጠሩ መጠን እና አይነት ይወሰናል፡፡ የኩላሊት ጠጠር በውስጣችን እንዳለ ካወቅን ስለሁኔታው የጤና ባለሙያ ማማከር የመጀመርያ ስራችን መሆን አለበት!!!
ዋናው ነገር ግን አስቀድሞ መከላከል ነው፡፡ ይሄም በቀላሉ ከቤት በምናዘጋጃቸው ነገሮች (home remedies) የኩላሊት ጠጠርን መጠን መቀነስ እና በሽንት አማካኝነት እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡

🚺🚹 ከነዚህ home remedies መካከል በጣም የሚታወቀው የሚከተሉትን ነገሮች በመቀላቀል የሚገኝ ነው።

🟢 #እነርሱም፦
👉 1 ብርጭቆ ንጽህ ሙቅ “ውሃ”
👉 2 የሾርባ ማንኪያ “የአፕል ጭማቂ”
👉 1 ወይም 2 የሾርባ ማንኪያ “ማር”
👉 ግማሽ የሻይ ማንኪያ “ቀረፋ” ናቸው፡፡

🟢 #አወሳሰድ
👉 “ለሁለት ሳምንታት” “ማታ” ከመተኛታችን በፊት መጠጣት፡፡
👉 እንደ ጠጠሩ መጠን በአስር ቀን ውስጥ ጥሩ ውጤት ማግኘት እንችላለን፡፡

ሌሎችም ያንብቡት ሼርርርር አርጉት
ጤናዎ ይብዛለዎት!!!

የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ...
12/11/2021

የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡

► የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል፧

የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡
እነዚህም፤

✔ የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)
✔ ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር
✔ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
✔ የዲስክ መንሸራተት
✔ የመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽን
✔ የአጥንት መሳሳት

► የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡

✔ ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተት
✔ ከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳት
✔ ለብዙ ሰዓት በመቆም
✔ ለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥ
✔ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር

► የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል፧

✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡፡ ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡

✔ ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመም ተጋላጭ ናቸው፡፡

✔ የሰውንት ክብደት መቀነስ፡፡ የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡

✔ የተስተካከለ አቀማመጥ፡፡ በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡

✔ የተስተካከለ አቋቋም፡፡ በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡

✔ ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡፡ ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን፨ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡

✔ ጫማ፡፡ የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡

✔ መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

✔ የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡፡ የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡

የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤

✔ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔ ከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔ በሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመም
✔ ከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜት
✔ ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር
✔ ከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ

Eat healthy
27/10/2021

Eat healthy

Address

St. Nigeria

1000

Telephone

+251920256344

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Doctors posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram