03/09/2025
ተጠየቁ እስኪ
ጥያቄ ልጅቷ ላይ አዋጅ አስነግራችሁ ለዘመታችሁባት እና ላዘመታችሁባት
1ኛ ምን ያክል ትዉልዱ ባእድ ለምትሉት እዉቀት እንዳይጋልጥ ትክክለኛ በምትሉት እዉቀት እንዲገነባ አድርጋችሆል?
2ኛ የሰዉልጅ ሀሳብንስ በማወገዝ ሀሳቡን ማስቆም ይቻላላ ብላችሁ ታስባላችሁ?
3ኛ ሀይማኖታችን እና ባህላችን እንደዚህ ያለ ግብዝነትንስ ያበረታታል?
4ኛ ለሀገር ለዉጥ የወጣቱ መንቃትንስ አያስፈልግም ነዉ የምትሉት?
5ኛ ትዉልዱ የራሱን ህይወት ራሱ ለመስራት መሞከሩ ክፋቱ የቱ ጋር ነዉ?
6ኛ ………….
ራስን ማወቅ/self awrenness : ራስን ማሳደግ/self development : ጥያቄ መጠየቅ ወደ ዉስጥ መመልከት/introspection እንዲሁም ከዉጭ አለም ይልቅ ራስ ሀላፊነት መዉሰድ/ የሀይማኖት ጉዳይ አይደለም ለአንድ ማህበረሰብ ፤ ቤተሰብ ፤ ሀገር ፤ ግለሰብ የህልዉና ጉዳይ ነዉ።
ራሱን ያላወቀ ትዉልድማ በአንድ ቴክስት ወደ ጎዳና ግር ብሎ ሲወጣ እና ሀገር ሲያፈርስ አየነዉ እኮ
ራሱን የማያዉቅ ትዉልድማ በዘር ተቦዳድኖ 24 ስአት ሲሰዳደብ መዋል ማደር የእለትተእልት ሰረዉ ከሆነ ቆየ
ራሱን ያላወቀ ትዉልድ እኮ ድግሪ የሚባል ወረቀት ይዞ ህይወቱን እንዴት መቀየር እንደሚችል ሳይገባዉ አንድ ማስታወቂያ ሲወጣ 30ሺህ አመልካች እያያን ነዉ
ራሱን ያላወቀ ትዉልድማ ፈጣሪ የሰጠዉን አእምሮ ተሸክሞ በሊቢያ በረሀ ሲሳይ ሲሆን እያየን ነዉ
ራሱን የማያዉቅ ትዉልድማ ራሳቸዉን አንቅተዉ ሌላዉን ለማንቃት ሲሞክሩ እንደ ግሪሳ ግር ብሎ ከምድር ገፅ እያጠፋቸዉ እያየን ነዉ ።
እዉነት ሀይማኖታችን ነዉ እንደዚህ ልጅቷ ላይ እንደንዘምትባት ያደረገን ወይስ ድንቁርናችን ለምን ተነካ ነዉ?
እዉነት ሰነፎች ሀይማኖት ላይ አፋቸዉን ቢከፍቱ በዚህ ደረጃ ለመዝመት ዝግጁ ነን?
ለማንኛዉም ትዉልዱ ከእኛ የትናንት የድንቁርና አስተሳሰብ ራሱን ካላቀቀ ቆየ ተስፋ እንቁረጥ ብንችል እንረዳቸዉ እና መልካም የሆነዉን የእነሱን እዉነት ወደሂወታችን እናምጣዉ ካልቻልን ግን ድድብናችንን ለራሳችን ብቻ ይዘነዉ በጨለምተኝነት አለም ዉስጥ እንኑር።