Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C

Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C Fit Corner Sport & ConsultancyPLC sport training , consultancy company based in Ethiopia Addis Ababa.

ኢሬቻ ለአብሮነት ፤ ለወንድማማችነት!Irreechi Obbolummaaf! 'ኢሬቻ ለወንድማማችነት' በሚል መሪ ሀሳብ ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር ተካሄደ!  sport ...
28/09/2025

ኢሬቻ ለአብሮነት ፤ ለወንድማማችነት!
Irreechi Obbolummaaf!

'ኢሬቻ ለወንድማማችነት' በሚል መሪ ሀሳብ ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር ተካሄደ!
sport

sport

The gym isn’t just a place to build muscles, it’s where we build discipline, consistency, and support systems. Training ...
21/09/2025

The gym isn’t just a place to build muscles, it’s where we build discipline, consistency, and support systems. Training with friends reminds us that the journey is easier and way more fun when you’ve got people beside you who motivate, inspire, and celebrate every milestone along the way. Together we grow stronger—physically and mentally.
sport
# Fit corner sport
# Adewa Gym

204 likes, 23 comments. “የከተማችን ምርጥ አሰልጣኞች በ አድዋ ጂም fitness eyoba”

https://youtu.be/TEUuLN_1u78?si=xTtWpZw8uQ1l76Ga
19/09/2025

https://youtu.be/TEUuLN_1u78?si=xTtWpZw8uQ1l76Ga

ኢትዮጵያ በመላ አለም በታሪክ ከምትታወቅባቸው ስፖርት ዘርፎች አትሌትክስ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ለዚህ ውጤት ጉልህ ድርሻ ሚወስዱት አትሌቶቹ ቢሆኑን ከጀርባ ደግሞ በርከት ያሉ አካላ.....

የሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ደማቅ የማስ ስፖርት አዘጋጀ። መስከረም 5/2018 ዓ.ም፤ ፊት ኮርነር ስፖርት===//====የህዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የኦሮ...
15/09/2025

የሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ደማቅ የማስ ስፖርት አዘጋጀ።
መስከረም 5/2018 ዓ.ም፤ ፊት ኮርነር ስፖርት
===//====
የህዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል አመራሮችና ሠራተኞች የተሳተፋበት የብዙሃ-የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት ማለዳ ተከናውኗል።

ይህ የብዝሃ-የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተስፋ ሜዳ የተከናወነ ሲሆን ኢንስትራክተር ነፃነት ካሳና ሌሎች ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች መርተውታል።
==//==

በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።መስከረም 02 ቀን 2018ዓ.ም፤ አዲስ አበባ***//***የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድ...
12/09/2025

በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።
መስከረም 02 ቀን 2018ዓ.ም፤ አዲስ አበባ
***//***

የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ‘በህብረት ችለናል’ በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ በተከናወነው የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው የተሳትፈውበታል፡፡
በዚህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፤ የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ መስራችና ባለቤት ኢንስትራክተር ነጻነት ካሣ፣ የተለያዩ የመንግስትና የግል ሰራተኞችና ከ300ሺ በላይ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።
የአባይ ግድብ ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በህብረት፤ በራስ ሃብት፣ በራስ እውቀትና በራስ አቅም ተረባርበው ያከናወኑት መሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል፡፡
የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ኢንስትራክተር ነጻነት በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያን በአድዋ ተራሮችና በአትሌቲክስ ስፖርት ለአለም ያሳየነውን አይበገሬነታችንን በአባይ ግድብም ደግመነዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ ልዩ ልዩ የመንግስት ኃላፊወችም የእንኳን ደስያላችሁ መልዕክትና የአባይ ግድብ መጠናቀቅ ያለውን ሃገራዊ ፋይዳ አብራርተዋል፡፡
===//===

እንኳን ለዚህ ታላቅ ታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ! ከደስታችን ጎን... ቤታችን፣ ፋብሪካዎቻችንና ኑሯችን በተሟላ የኤሌክትሪክ ሃይል መደገፍ ከመቻሉም በላይ...ይህ በአፍሪካ አህጉር ፍፁም ተገዳዳሪ...
10/09/2025

እንኳን ለዚህ ታላቅ ታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ!
ከደስታችን ጎን... ቤታችን፣ ፋብሪካዎቻችንና ኑሯችን በተሟላ የኤሌክትሪክ ሃይል መደገፍ ከመቻሉም በላይ...
ይህ በአፍሪካ አህጉር ፍፁም ተገዳዳሪ የሌለው ግድብ እንደ ቻይናው ስሪ-ጎርጅስ /Three Gorges/ ግድብ ታላቁን የአለም-የጀልባ ቀዘፋ ስፖርት ስናዘጋጅበት... ልክ እንደ ካሪባ ሃይቅ /Lake Kariba/ የአለም የአሳ ማጥመድ /fishing/ ውድድር ስናዘጋጅበት....
ልክ የግብፁ አስዋን ግድብ በፈጠረው የናስር ሃይቅ ላይ እንደሚካሄደው የስፖርት ቱሪዝምና የአሳ ማጥመድ ማዕከል ሲሆን....

በዓለም ላይ ያለው ተሞክሮ እንደሚያሳየው ሰው ሰራሽ ግድቦችና የውሃ መጠባበቂያዎች ለተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችና የስፖርት ቱሪዝም ልማት ቁልፍ ሚና ይጫዎታሉ። ይህ ዛሬ የተመረቀው ታሪካዊው ግድብም ለኢትዮጵያ ተመሳሳይ አስተዋጽዖ ከማበርከት የሚያግደው የለም።

በመሆኑም ለመላው ኢትዮጵያዊያንና ለስፖርት ቤተሰብ በሙሉ እንኳን ለዚህ ብሩህ የስፖርት ቱሪዝም ቀን የማበቢያ ቀን፣ ለታላቁ ግድባችን የምረቃ ቀን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለው።

ኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ
የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ መስራችና ባለቤት

እውቁ ሙህርና ተመራማሪ፤ የስፖርት ሳይንስ ሊቁ! ዶክተር በዛብህን ስራዎችና አበርክቶት የሚዳስሰው ዘጋቢ ፊልም በዚህ ማስፈንጠሪያ (link) ያገኙታል።👇
07/09/2025

እውቁ ሙህርና ተመራማሪ፤ የስፖርት ሳይንስ ሊቁ! ዶክተር በዛብህን ስራዎችና አበርክቶት የሚዳስሰው ዘጋቢ ፊልም በዚህ ማስፈንጠሪያ (link) ያገኙታል።
👇

ይህንን ሊንክ 👉👉 http://bit.ly/subscribe_netsisport በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ

07/09/2025

የእውቁ ሙህርና ተመራማሪ ዶ/ር በዛብህ ወልዴ የመታሰቢያ ሃውልት ምርቃት ተካሄደ።
ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም
***=***
በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዮችና ኮሌጆች በተለይም በኮተቤ ዩኒቨሮሲቲ ለረጅም አመታት በስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል በአስተማሪነት ያገለገሉትና በርካታ ጥናታዊ ምርምሮችን ሰርተው ለህትመት ያበቁት ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወልዴ ሃውልት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

በዚህ የሃውልት ምርቃት ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ የቀድሞ ተማሪዎቹ፣ የስራ ባልደረቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ተከናውኗል።

ዶ/ር በዛብህ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩና ለኢትዮጵያ የስፖርት እድገት ቁልፍ ሚና የተጫወቱ፣ በተለያዩ የስፖርት ልማት ተቋማት ላይ ያገለገሉ የማይተኩ ታላቅ ሙህር መሆናቸውን በመታሰቢያ ሃውልት ምርቃቱ ላይ በቀረበው ዘጋዚ ፊልም በስፋት ተዳሷል።
==//===

 # ዶ/ር አያሌው  ጥላሁንበኢ/ያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ሀኪምበ15 እና በ5 ቀን ስልጠና ብዙ ለምታወሩ አሰልጣኞች የተሰጠ ምክር::
04/09/2025

# ዶ/ር አያሌው ጥላሁን
በኢ/ያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ሀኪም

በ15 እና በ5 ቀን ስልጠና ብዙ ለምታወሩ አሰልጣኞች የተሰጠ ምክር::

234 likes, 32 comments. “ዶ.ር አያሌው ጥላሁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሃኪም ይህንን በለዋል እስቲ ስሟቸው። ቆይታ ከኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ ጋር ስለ ስፖርት ሳይንስ ብዙ ተዳስሷል። ሙሉውን .....

Weekends are for dreamers, but also for doers. Saturday grind mode 💪Thanks Hugre!!!
30/08/2025

Weekends are for dreamers, but also for doers. Saturday grind mode 💪
Thanks Hugre!!!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram