አሌፍ የጤና ማማከር Aleph Health Consultancy

አሌፍ የጤና ማማከር Aleph Health Consultancy በአሌፍ ጤናንና ሕክምናን የተመለከቱ ርዕሶች ዙሪያ ማማከርና ስልጠና ያገኛሉ።

22/10/2025

በመጪው እሁድ (በጥቅምት 16/2018 ዓ.ም) በሚካሄደው የማህፅን እና ተያያዥ አካላት ካንሰር በሽታዎች የጤና ዘመቻ ላይ በመሳተፍ ከተለያዩ ስፔሻሊቲ የተወጣጡ የሐኪሞች ቡድን ጋር በአንድ ጊዜ በመታየት በማህፅን እና ተያያዥ አካላት ላይ ለሚከሰቱ የካንሰር በሽታዎች ;እና ተያያዥ ችግሮችን መፍትሄ ያግኙ።
ባለሙያዎቻችን
-ዶ/ር ማለደ ቢራራ (የማህፅን እና ተያያዝ አካላት የካንሰር ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት)
-ዶ/ር የምስራች መንግስቱ ( የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት)
-ብዙሃረግ ተካ (የስነምግብ እና አመጋገብ ባለሙያ)
ሁሉኑም ሕክምናዎች በአንድ ጊዜ!
ቀደም ብሎ ለመመዝገብ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉልን.
መቅረዝ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!

Reclaim Your Health & The Health of the Planet•¨ የምንመገበው ምግብ•¨ የምንተነፍሰው አየር•¨ የምንጠጣው ውሃ•¨ የምንኖርበት አካባቢ•¨ የአየር ንብረት ለውጥ ፣...
22/10/2025

Reclaim Your Health & The Health of the Planet

•¨ የምንመገበው ምግብ
•¨ የምንተነፍሰው አየር
•¨ የምንጠጣው ውሃ
•¨ የምንኖርበት አካባቢ
•¨ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ በከባቢው ውስጥ የምንጥላቸው ፕላስቲኮች ወዘተ…
•¨ ሁሉም ጤናችን ላይ አዎንታዊም አሉታዊም ተፅዕኖ ይኖራቸዋል::
• ለጤናችን መጠበቅ ተፈጥሮን እንከባከብ

•¨ The food we eat
•¨ The air we breathe
•¨ The water we drink
•¨ The environment we live in
•¨ Climate change, plastic pollution and destruction of natural habitats.
•¨ All these impact our health
•¨ Health For All: means protecting nature.

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
ማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.alephhealthconsult.com
https://t.me/alephhealthconsult
https://linktr.ee/alephhealthconsultancy

የደም ማነስን እንዴት መከላከል ይቻላል?በኢትዮጵያ ውስጥ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የደም ማነስ ተጠቂ መሆናቸውን ያውቃሉ?¨ በብረት ንጥረ ነገ...
20/10/2025

የደም ማነስን እንዴት መከላከል ይቻላል?

በኢትዮጵያ ውስጥ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የደም ማነስ ተጠቂ መሆናቸውን ያውቃሉ?
¨ በብረት ንጥረ ነገር ፤ በፎሌት ፤ ቫይታሚን ቢ12 ፤ ሲ እና ኤ የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትረው በመመገብ የደም ማነስን ይከላከሉ፡፡ ለምሳሌ:-
¨ ቀይ ስጋ ፤ አሳ ፤ የዶሮ ስጋ
¨ ባቄላ ፡ ሽንብራ ፤ ምስር ….
¨ ብርቱካንና ሌሎች ቢጫ የሆኑ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች
¨ ብሮኮሊ ፤ ቆስጣና ሌሎች አረንጓዴ አትክልቶች ...`

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
ማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.alephhealthconsult.com
https://t.me/alephhealthconsult
https://linktr.ee/alephhealthconsultancy

Reclaim Your Health & The Health of the Planetሁኔታዎች በሚፈቅዱልዎት መጠን በእግር መጓዝ ወይም ብስክሌት መጠቀምን ይምረጡይህን ማዘውተርዎ በጤናዎ ላይ ጉልህ አስተ...
19/10/2025

Reclaim Your Health & The Health of the Planet

ሁኔታዎች በሚፈቅዱልዎት መጠን በእግር መጓዝ ወይም ብስክሌት መጠቀምን ይምረጡ
ይህን ማዘውተርዎ በጤናዎ ላይ ጉልህ አስተዋፆ ይኖረዋል
የልብ ምትና ጤናዎ የተስተካከለ ይሆናል
የአእምሮ ቅልጥፍና ይጨምራል
የሚኖሩበትን አካባቢ የተሻለና ንፁህ እንዲሆን ያደርጋል

Choose to walk or cycle whenever possible.
It can improve:
Your heart
Your mind
And the Planet

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
ማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.alephhealthconsult.com
https://t.me/alephhealthconsult
https://linktr.ee/alephhealthconsultancy

Reclaim Your Health & the Health of the Planet¨ Did you know❓ Cycle lanes count for just 0.2% of the current road infras...
17/10/2025

Reclaim Your Health & the Health of the Planet

¨ Did you know❓ Cycle lanes count for just 0.2% of the current road infrastructure.
¨ It’s time to demand safer streets that put the health & safety of pedestrians and cyclists first.

¨ በአለማችን ከአጠቃላይ የመንገድ መሠረተልማት ውስጥ ለብስክሌት የዋለውከ0.2% ያነሰ መሆኑንያውቃሉ፡፡
¨ በሀገራችን ደግሞ ጥሩጅማሮ ቢኖርምከዚህም ያነሰ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
¨ ለእግረኞችና ለብስክሌት ተጠቃሚዎችየተሰተካከሉና ደኅንነታቸውየተጠበቁ መንገዶች በብዛት ያስፈልጉናል፡፡

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
ማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.alephhealthconsult.com
https://t.me/alephhealthconsult
https://linktr.ee/alephhealthconsultancy

May Your Soul Rest In Eternal Peace!
15/10/2025

May Your Soul Rest In Eternal Peace!

Message of Condolence

The Ethiopian Medical Association (EMA) is deeply saddened by the passing of Professor Amezene Tadesse, former Vice President of the Ethiopian Medical Association and a distinguished Pediatric Surgeon, educator, and leader.

Prof. Amezene was born in Addis Ababa and completed his medical degree with distinction from the Gondar College of Medical Sciences in 1995. His professional journey was marked by excellence, dedication, and an unwavering commitment to advancing surgical education and patient care in Ethiopia.

He served at the University of Gondar and later at Addis Ababa University, College of Health Sciences, where he rose to the rank of full Professor of Surgery. Prof. Amezene’s leadership extended beyond academia—he contributed immensely to professional associations, including his service as Vice President of the Ethiopian Medical Association.

A respected researcher and mentor, Prof. Amezene authored numerous scientific publications, presented in international forums, and actively participated in collaborative projects aimed at strengthening health systems across Africa. His impact on medical education and surgical practice will be remembered by colleagues, students, and the broader medical community.

EMA extends its heartfelt condolences to his beloved wife, Dr. Rahel Demissew, his children, family, colleagues, and friends. His legacy of professionalism, humility, and service will continue to inspire generations of Ethiopian physicians.

May his soul rest in eternal peace.
Ethiopian Medical Association (EMA)

የቅርብ እይታ / ከርቀት  ማየት መቸገር /MYOPIA /Nearsightedness/ለልጅዎ ዓይኖች ይጠንቀቁ ከርቀት ማየት መቸገርን ይከላከሉ።በቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየት እና ከቅርብ እይታ ጋ...
15/10/2025

የቅርብ እይታ / ከርቀት ማየት መቸገር /
MYOPIA /Nearsightedness/

ለልጅዎ ዓይኖች ይጠንቀቁ ከርቀት ማየት መቸገርን ይከላከሉ።
በቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየት እና ከቅርብ እይታ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን /ሥራዎች በብዛት መከወን ብዙ ልጆች ለቅርብ እይታ ችግር እንዲጋለጡ / ተጠቂ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል፡፡
በቅርብ እይታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች / ሥራዎች (እንደ ንባብ ፤ ስልክ ፤ ታብሌት ፤ ኮምፒውተር...) መካከል እረፍት እንዲወስዱ ያድርጓቸው።
በየቀኑ ቢያንስ 90 ደቂቃ ከቤት ውጭ እንዲያሳልፉ /የተፈጥሮ ብርሃን እንዲያገኙ/ ያድርጉ።

Too much time spent indoors & intensive near vision activity lead to more children suffering from nearsightedness or myopia.
Protect your child’s eyes & prevent myopia
Take regular breaks during near activities
Spend at least 90 minutes outdoors daily
Get regular eye checks!
Take care of your eye today!

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
ማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.alephhealthconsult.com
https://linktr.ee/alephhealthconsultancy

Safe Lifting Technique / ደኅንነትን ጠብቆ እቃ ማንሳትPractice safe and proper lifting techniques, especially when lifting heavy ob...
13/10/2025

Safe Lifting Technique / ደኅንነትን ጠብቆ እቃ ማንሳት

Practice safe and proper lifting techniques, especially when lifting heavy objects or performing physical tasks. Use your legs to lift, keep the load close to your body, and avoid twisting or jerking motion.
1. Lean the sack onto your kneeling leg
2. Slide the sack up onto your kneeling leg
3. Slide the sack onto the other leg while keeping the sack close to your body
4. As you fully stand up keep the sack close to your body.

ከባድ እቃዎችን በሚያንሱበት ጊዜ ወይም አካላዊ እንቅስቃሲዎችን በሚሰሩብት ጊዜ አስትማማኝ እና ትክክለኛ የማንሳት ቴክኒኮችን መጠቀም ይለማመዱ።
ከባድ እቃዎችን ለማንሳት እግሮችዎን ይጠቀሙ ፤ ጭነቱን ወደ ሰውነትዎ ያቅርቡ እና ከመጠምዘዝ ወይም ከመንቀጥቀጥ ይጠብቁ።

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
ማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://linktr.ee/alephhealthconsultancy

https://www.alephhealthconsult.com

ጉልበተኝነት/Bullying/ጉልበተኝነት ምንድን ነው? • ጉልበተኝነት ማለት ሆን ብሎ ጠብ አጫሪ መሆንና የሀይል ወይም የጉልብትኝንት ስሜተ በገሃድ ማንፀባረቅና የራስን ስሜት በሌሎች ላይ ለመ...
11/10/2025

ጉልበተኝነት/Bullying/
ጉልበተኝነት ምንድን ነው?
• ጉልበተኝነት ማለት ሆን ብሎ ጠብ አጫሪ መሆንና የሀይል ወይም የጉልብትኝንት ስሜተ በገሃድ ማንፀባረቅና የራስን ስሜት በሌሎች ላይ ለመጫን መሞከርና የሃይል አለመመጣጠንንም ያጠቃልላል፡፡ ጉልበተኝነት“ በአካልም ሆነ በሚዲያ (በሚኒ ሚዲያ ፤ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎች) የሚተላለፉ የቃል ተግባራት ሊሆኑም ይችላሉ ፡፡
• የጉልበተኝነት ጠባይ በየጊዜው የሚደጋገምና በአደገኛ ሁኔታ ስሜትን ለማዛባት መንስኤ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ጉልበተኝነትበሌላው ላይ መቀለድን ወይም ማፌዝን ይጨምራል ፣ ሆኖም ግን ቀላል ማብሸቅን ረብሻና ጫጫታ የበዛበትን ቀላል ክርክርን ፣ ቀላል የቡድን ብጥብጥን ወይም የተናጠል ማንቋሸሽ ተግባራትን ፣ ቀላል ጠብ አጫሪ ጠባይንና ማሳፈራራትን ባይጨምርም ወደ ጉልበተኝነትሊመሩ የሚችሉ ድርጊቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በተለይ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተከለከሉ ተግባራት መሆነ አለባቸው፡፡
• “ ተማሪ በግልም ሆነ በቡድን ሌሎችን መሳደብ ፣ ማናደድ ወይም ማፌዝ አይገባም፡፡ የተከለከሉ ስነምግባር የሚይዘው በአካል ማስፈራራት ፣ ማሾፍ ፣ ስም ጠርቶ መሳደብና ሌለሎች የተከለከሉ ተግባራትን ይጨምራል፡፡ሆኖም ግን እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡”
ልጅዎን ሌሎች እየረበሹት ወይም እያስፈራሩት ከሆነ ምን ያደርጋሉ?
• ያነጋግሩዋቸው ፣ ያድምጡዋቸው እናም ልጅዎ የሆነውን ወይም የሆነችውን ይወቁ፡፡
• መረበሽ ወይም መሳደብ ስህተት እንደሆነ ለልጅዎችዎ በመግባባት ያሳውቁዋቸው፡፡
• መሰደብ ወይም መረበሽ የልጅዎ ስህተት እንዳልሆነ ማወቃቸውን ያረጋግጡ፡፡
• ያጋጠማቸውን ስድብ ወይም የጉልበተኝነትወይም ማስፈራራት የተቋቋሙበትን መንገድ አይተቹ፡፡ምክንያቱም ልጆች በተሳካ ሁኔታ ለመመለስ ዘወትር ይቸገራሉ፡፡
• መሳደብን ማስፈራራትን ወይም ረብሻን ለማቆም በአንድ ላይ እንደምትሰሩ ያሳውቁዋቸው፡፡
• ልጅችዎን ሌሎች እያስፈራሩዋቸው ወይም እየሰደቡዋቸው ወይም እየረበሹዋቸው ከሆነ ለልጅዎችዎ ትምህርት ቤት አስተዳደር ያሳውቁ፡፡
• የልጅችዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዳ እቅድ ለመንደፍ የልጅችዎን የትምህርት ቤት ሰራተኞች ያግኙና ይወያዩ፡፡
• እርስዎንም ሆነ ልጅዎን የሚያግዙ የትምህርት ቤትም ሆነ የማህበረሰብ ክፍሎች ያስሱ፡፡
• የርስዎን ልጅ ያስፈራራውን ወይም የሰደበውን ልጅ ወይም የልጅ ቤተሰቦች ለማግኘት አይሞክሩ፡፡
• እርስዎም ሆነ ልጅዎ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልግ ከሆነ ከልጅዎ ትምህርት ቤት አማካሪ፣ማህበራዊ ሰራተኛ፣ የስነልቡና ባለሙያ ወይም የአዕምሮ ጤና ባለሙያን ድጋፍ መሻት ያስፈልጋል፡፡
• አዎንታዊ የትምህርት ከባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር ከትምሀርት ቤት ሃላፊዎች ጋር ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ በዚህም የቀለም ትምህርት ብቃት ፣ ማህበራዊ ፤ ስሜታዊና አካላዊ ደህንነት በሁሉም ተማሪዎች ዘንድ እንዲጠበቅ ማድረግ፡፡
ወላጆች ፓሊስን ወይም የትምህርት ቤት የፀጥታ ሰራተኞችን / ሃላፊዎችን ማግኘት ያለባቸው መቼ ነው?
• ማስፈራራቱ ወይም ረብሻው የወንጀል ድርጊት ያካተተ ከሆነ ይህም ሲባል አካላዊ ጥቃት ፣ ስም ማጥፋት ፣ ስድብ ፣ ስርቆትና ከፍተኛ የሆነ ማስፈራራትና የጥፋት ድርጊት ሲፈጽም
• ልጅዎ በጦር መሳሪያ ማስፈራራት ሲደርስበት ወይም ሲደርስባት
ወላጆች ልጆቻቸውን ከጉልበተኝነት፣ ከማስፈራራት ወይም ከስድብ ለመጠበቅ ምን ማድረግ አለባቸው?
• ለልጅዎችዎ ቤት ውስጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በዚህም ምቾትና የመፈቀር ስሜት እንዳላቸው በህሊናቸው እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል
• ልጅዎችዎን መሰረታዊ የስድብ ፣ ማስፈራራት ወይም ጉልበተኝነትማስወገጃ መንገዶች ማስገንዘብ ፦ አዝማሚያውን አይተው ከመጋፈጥ ይልቅ ከአካባቢው ራቅ እንዲሉ
• ለልጆች በረባሾች ማስፈራራት ቢደርስ ፤መሸሽ ወይም ለጎልማሳ ሰዎች ሁኔታውን በመንገር እርዳታ በመጠየቅ ሀፍረት መሰማት እንደማይገባ መግለጽ፡፡
• ለልጅዎችዎ የጉልበተኝነትወይም የማስፈራራት ድርጊቶች እንደሚጨምሩና እናም ህይወትን ማዳን ገጽታን ከማዳን የበለጠ ጠቃሚ እንደሆነ ማስተማር፡፡
• ማስፈራራትን ወይም መረበሽን እንዴት መከላከል እንዳለባቸው በትዕይንት ለልጆች መግለጽ ማለትም ቀጥ ብሉ መቆም ፣ጮክ ያለ ድምጽ መጠቀም ፣ለምሳሌ “ስማ፣አቁም” ወይም “እጅህን ከሰውነቴ ላይ አንሳ”
• ልጅዎችዎ ወደ ጥል ሳይጋበዙ ፀጥ ብለው እንዲቆዩ ማበረታታት፡፡ ካልሆነ ግን ልጅዎችዎ ሊጎዱ ወይም ከትምህርት ቤት ሊታገዱ ይችላሉ፡፡
• ልጅዎችዎ ማስፈራራት ወይም ጉልበተኝነትካዩ ወይም እራሳቸው የችግሩ ሰለባ ከሆኑ ሁኔታውን በአፋጣኝ ለትምህርት ቤት ሰራተኞች ወይም ሌሎች ለሚታመኑ ጎልማሶች (ለምሳሌ፦ ለወላጅ አስተማሪና ተማሪዎች ማህበር) መንገር፡፡
• ልጅችዎ ሌሎች ማስፈራራት ወይም ጉልበተኝነትሲደርስባቸው ካዩ በጉዳዩ ላይ እንዲገቡ ያበረታቱዋቸው፡፡ ይህም ሌሎች የክፍል ተማሪዎች የክፍል ጓደኞቻቸውን ለመከላከል ከተባበሩ የጉልበተኝነትወይም የማስፈራራት ሁኔታ በግማሽ ይቀንሳል፡፡

ለተጨማሪ ሙያዊ ምክር የሚከተሉትን ይጠቀሙ
 +251 941 171819 ይደወሉ
 ዌበሳይት ላይ ቀጠሮ ማሰያዝም ይችላሉ፡ https://alephhealthconsult.com/en/appointment/
 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/AlephHealthConsult

የአቻ እድሜ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅእኖዎችየነገ ማንነታችን የዛሬ ሕይወታችን ውጤት መሆኑ እሙን ነው፡፡መልካም መልካሙን እያየና እየሠማ፤ የራስ ማንነትን ከሚበርዙ ድርጊቶች ተቆጥቦ ፤ የሚረባው...
10/10/2025

የአቻ እድሜ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅእኖዎች

የነገ ማንነታችን የዛሬ ሕይወታችን ውጤት መሆኑ እሙን ነው፡፡መልካም መልካሙን እያየና እየሠማ፤ የራስ ማንነትን ከሚበርዙ ድርጊቶች ተቆጥቦ ፤ የሚረባውንና የሚያጠፋውን መለየት የሚያስችለውን ንቃት እያጎለበተ ያደገ ልጅ ነገ በመልካም ስፍራ ላይ መገኘቱ አያጠራጥርም፡፡አሁን ባለንበት ዘመን ግን የልጅን ፀባይ አርቆ በመልካም ጎዳና የመምራት ኃላፊነት ከባድ ያደርገዋል፡፡ በተለይም የሚበጀውንም የማይበጀውንም ዘርገፈው የሚያቀርቡ ማኅበራዊ ድረገጾችና አሉታዊ የሆነ አቻ ግፊት ልጆቻችን ራሳቸውን ሆነው ለፍሬ እንዲበቁ የምናደርገውን ጥረት ውሃ ያስበሉታል፡፡
ግፊት ከወላጆች ከሃይማኖት አባቶች ከጎረቤቶችና ከመምህራን ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ከአቻዎች የሚመጣው ግን የተለየ ተጽዕኖ ያደርሳል፡፡
የአቻ ግፊት ማለት የዕድሜ እኩዮች ሌሎች ጓደኞቻቸው እነርሱ የሚፈልጉትን ሥራ እንዲሠሩ የሚያደርጉት ተጽዕኖ ነው፡፡
የአቻ ግፊት በሁሉም የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በወጣትነት ጊዜ ያለው ከፍተኛ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡ የአቻ ግፊት አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ሊሆን ይችላል፡፡
ሰዎች አቻዎቻቸው በጠባያቸው ምስጉን በሥራቸው ታታሪ በኑሯቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ሲገፋፏቸው አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊባል ይችላል፡፡
ሰዎች በተለይም ወጣቶች በአቻዎች ላለመገለል ላለመለየት እና አንሶ ላለመታየት ሲሉ የማይፈልጉትንና የሚጐዳቸውን ተግባር ለመፈጸም ሲገፋፉ አሉታዊ ተጽዕኖ ይሆናል፡፡
የአቻ ግፊትን በበጎ ጎኑ ካየነው አጠገባችን ያሉ እኩዮቻችንን ነገ ለፍሬ በሚያበቃ ተልዕኮ ማሰለፍ ፤ እኛ በምንጓዝበት ቀና ጎዳና አብረውን እንዲጓዙ ተጽዕኖን መፍጠር ነው ብለን መውሰድ እንችላለን፡፡ ይህ አዎንታዊ የአቻ ግፊት የራስን ዓላማ ከግብ ከማድረስ ፣ የሌሎችንም መንገድ እንዲቀና በማድረግ ረገድ ላቅ ያለ ዋጋ ያለው ቢሆንም ፣ ብዙ ታዳጊዎችና ወጣቶች ግን ካነገቡት ዓላማ ጎን ጓደኞቻቸውን ከማሰለፍ፣ ከመንጋው ተለይተው ከመውጣት ይልቅ በአሉታዊ የአቻ ግፊት ይዋጣሉ፡፡ በአሉታዊ የአቻ ግፊት ተጽዕኖ ሥር የወድቁ ታዳጊዎችና ወጣቶች በመጀመሪያ የተነሱበትን ዓላማና ወላጅ የሰነቀባቸውን ተስፋ ሁሉ ችላ ይላሉ፤ ነገ ምን ያመጣብኛል የሚለውን ሳያገናዝቡ የእድሜ እኩዮቻቸው ስላደረጉት ብቻ ጤናቸውንና ትምህርታቸውን የሚጎዱ የተለያዩ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፡፡ የአቻዎቼ ድርጊት የሚያዋጣ ነው ወይስ የሚያከስር? ብለው ለማጤን የሚያስችላቸውን ጊዜ እንኳ ለራሳቸው አይሰጡም፡፡ ቁም ነገር አድርገው የሚወስዱት ቢጠቅምም ቢጎዳ ከእድሜ እኩዮቻቸው አለመለየታቸውን ነው፡፡
ሌላው ያደረገውን አለማድረግ ፤ መንጋው ከሚሄድበት መንገድ በተለየ መጓዝ ፋራ በሚያስብልበት ፤ ከበጎ ነገሮች ይልቅ የማይበጁ ልማዶች ፈጥነው በሚዛመቱበት በዚህ ዘመን በተለይም ለታዳጊዎችና ለወጣቶች አሉታዊ የአቻ ግፊትን ተቋቁሞ ማለፍ ቆራጥነትን የዓላማ ጽናትን ይጠይቃል፡፡
አዎንታዊ የአቻ ግፊት ምሳሌዎች
• ጥናት በማጥናት በትምህርት ጐበዝ እንድንሆን መገፋፋት፡፡
• የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ለመጐብኝት የሚደረግ ግብዣ፡፡
• የተጣሉ/ የተጋጩ ጓደኞችን ለማስታረቅ የሚደረግ ግፊት፡፡
• ትምህርት ሲያበቃ የልምድ ልውውጥ ውይይት መርኃግብር ማዘጋጀት፡፡
• አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት የሚደረግ ግፊት፡፡
• በዓመታዊ በዓሎች እና በሌሎችም ላይ የስነጽሑፍ እና የግጥም ውድድሮች ላይ ለመቅረብ መገፋፋት፡፡
• የታመሙ ሰዎችን ለመጠየቅ ፣ አዛውንቶችን ለመደገፍና ችግረኞችን ለመርዳት የሚደረግ ግፊት፡፡
አሉታዊ የአቻ ግፊት ምሳሌዎቸ
• በተለምዶ አነቃቂ የሚሏቸውን አደንዛዥ ዕፆች ፤ ሺሻ ፤ አሽሽ ፤ ጫትና ሲጋራን እንድንሞክር መገፋፋት
• ለመዝናናት በሚል ሰበብ አልኮል እንድንጎነጭ መጋበዝ
• ሕጋዊ ከሆኑት መንገዶች ይልቅ አጫጭር /አቋራጨ የሆኑትንና ሕጋዊ ያልሆኑ መንገዶች እንድንከተል መምከር
አሉታዊ የአቻ ግፊትን እንዴት መከላከል / መቋቋም ይቻላል?
• ወጣቶች በህይወታቸው ዋጋ የሚሰጡበት ነገር ከሌሎች ጋር ሊደራደሩበት የማይችሉት ስብዕናና ማንነት ከሌላቸው በቀላሉ በሌሎች ተጽእኖ ስር ሊወድቁ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ ወጣቶች በአሉታዊ የአቻ ግፊት ውስጥ ላለመውደቅ ለእራሳቸውና ለፍሎጎታቸው ክብር መስጠት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም፡-
o ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለእራስ ህይወት ውሳኔ መስጠት
o ለማይመች የሌሎች ፍላጎት እንቢ ማለት
o ለሚተቹዋቸውና ለሚያሳንሷቸው ወጣቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት
o ከሌላው ልዩ መሆን አልያም ሌሎችን ለመምሰል አለመጣር
o በአቻ ተጽእኖ ስር መውደቅ የሚያስከትለውን ጉዳት አስቀድሞ መመልከት ወጣቶች ህይወታቸውን በኃላፊነት እንዲመሩ ከማስቻሉም ባሻገር ገብተው ከማይወጡበትና ዋጋ ከሚያስከፍል የህይወት ዘይቤ እንዲታቀቡ ይረዳቸዋል፡፡
• አብሮ የሚውል ጓደኛንም በብስለት መምረጥ ሌላው መሠረታዊ ጉዳይነው ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ደግሞ ጤናማ የቤተሰብ አስተዳደግን ይሻሉ፡፡
• አንድ ወጣት ራስን በመሆንና ሌላውን በመምሰል መካከል ያለውን ትግል በድል መወጣት የሚችለው አስተዳደጉ ጤናማ መሆን ሲችል ነው፡፡ ቤተሰብ ልጆቹን ሲያሳድግ በራስ መተማመን እንዲኖራቸው፣ ራሳቸውን ብቻ ሆነው እንዲወጡ አድርጎ የሚያሳድግ ከሆነ እነዚህ ልጆች አሉታዊ የአቻ ግፊትን ከመቋቋማቸውም ባሻገር ሌሎች ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን የሚያሳርፉ መሆን ይችላሉ፡፡
• ከላይ ከተጠቀሰው በሚጻረር ሁኔታ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌላው ጋር እያወዳደሩ ራሳቸውን ሳይሆን ሌላውን እንዲመስሉ እየገፋፉ የእነርሱን ሐሳብ ወደጎን ትተው እነርሱ ያሉትን ብቻ እየጫኑ ሁሌም ድጋፋቸውን የሚሹ አድርገው ካሳደጓቸው ነገ አሉታዊ ለሆነ የአቻ ግፊት መጋለጣቸው የማይቀር ይሆናል ፤ እንዲህ ያሉ ልጆች ምንጊዜም ራሳቸውን ሳይሆን ሌላውን የሚፈልጉ በመሆናቸውና ራሳቸውን ሆነው ይወጡ ዘንድ እድል በመነፈጋቸው ለመውጣት ከሚቸገሩበት የሌሎች የኪሳራ ሕይወት ውስጥ ይዘፈቃሉ፡፡
• የጓደኛ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም ትልቁ ቁም ነገር ያለው ዓላማዬ ምንድነው? ከእኔ ዓላማ ጋር መሄድ የሚችለውስ ምን ዓይነት ጓዳኛ ነው? የሚለውን አጢኖ ትክክለኛ ጓደኛ ከመምረጥ ላይ ነው፡፡
• የአቻ ግፊትን ለመቋቋም በሕይወታቸው ዓርዓያ መሆን የሚችሉ ሰዎችን፣ የሥነልቡና ባለሙያዎችን ከእኛ የተሻለ የሕይወት ልምድ ያላቸው ሰዎችን ማማከርና ከእነርሱም ጋር ጊዜ ማሳለፍ ፤ ጊዜን በንባብ ማሳለፍ ከራስም አልፎ ለሌላው የሚበቃ ግንዛቤና ንቃትን ለማትረፍ ይረዳል ፡፡ ከንባብ የምናገኘው እውቀት የሚበጀንን እንድንመርጥ ብሎም አካባቢያችንንና በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎችን ማንነት እንድንረዳ ያስችለናል፡፡
• ታዳጊዎችና ወጣቶች ከቤት ሲወጡ ጤናማ አእምሮና ዓላማ ይዘው በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሌሎች ጎጂ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የሚገኙበት ዋነኛ ምክንያት አሉታዊ የአቻግፊት በሚፈጥረው ተጽዕኖ ነው ፣ለዚህ ችግር መፍትሔ በመሻት ረገድ ከቤተሰብና ከራሳቸው ከታዳጊዎችና ከወጣቶች ባልተናነሰ መምህራንም የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ መምህራንም አንድ ተማሪ አዲስ ጠባይ ሲታይበት፤ ከክፍል መቅረት ሲደጋግምና ውጤቱ ሲቀንስ ልክ እንደ ልጆቻቸው ለምን ብለው ሊጠይቁ ፤ ከተማሪው ጋር ቀርበው የሚመክሩ ችግሩንም የሚያደምጡ ፤ ራሳቸውን ለተማሪው ክፍት በማድረግ አሉታዊ የአቻ ግፊትን ተቋቁሞ የሚያልፍበትን አቅም በመገንባት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡
• በአጠቃላይ ወጣቶች በሌሎች ተጽእኖ ስር ወድቀው ጉዳት የሚያስከትሉ ድርጊቶችን ከመተግበራቸው በፊት ሁኔታዎችን መቆጣጠር አለባቸው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች ማንነታችንን የመቅረጽ ትልቅ ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ ‘’ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር … እንደሚባለው ወጣቶች አዋዋላቸው ከማን ጋር መሆን እንዳለበት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በማይመች አኳሃን ተጉዘው በኋላ ከመጸጸት ማንነታቸውን ማነጽ ከማይችሉ ጓደኞች በመራቅ በመልካም ስብዕናና ጎዳና ላይ ሊመሯቸው ከሚችሉ አዳዲስ ወዳጆች ጋር ህብረት መፍጠር ብልህነት ነው፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ ሁልጊዜ ለሌሎች ፍላጎት ምርኮኛ ከመሆን እንቢተኝነትን መማር ያስፈልጋል፡፡

Address

Https://maps. App. Goo. Gl/47shbTuZ6vnkcr6i8 ሲኤምሲ አደባባይ መዛብር ሪልስቴት ህንፃ ምድር ላይ CMC Squrae Mezaber Realstate Building Ground Floor
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 19:00
Tuesday 09:00 - 19:00
Wednesday 09:00 - 19:00
Thursday 09:00 - 19:00
Friday 09:00 - 19:00
Saturday 09:00 - 19:00
Sunday 10:00 - 15:00

Telephone

+251941171819

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሌፍ የጤና ማማከር Aleph Health Consultancy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to አሌፍ የጤና ማማከር Aleph Health Consultancy:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram