EthioPharma

EthioPharma Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from EthioPharma, Medical and health, .

ግንቦት 10፣2012በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ከእስከ ዛሬው ከፍተኛ የሆነ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ተገኘ፡፡1 775 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 35 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ...
18/05/2020

ግንቦት 10፣2012

በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ከእስከ ዛሬው ከፍተኛ የሆነ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ተገኘ፡፡

1 775 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 35 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 352 አድርሶታል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 17 ወንድምና 18 ሴት ናቸው ተብሏል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜአቸው ከ15 እስከ 80 መሆኑን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡

ከ35ቱ 29ኙ ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ እንዲሁም 1 ሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ የተገኙ ናቸው ተብሏል፡፡

ከ35ቱ 24ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 6ቱ የውጪ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ ቀሪዎቹ 5ቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 3 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል፡፡

05/03/2020

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወደ ተከሰተባቸው አገሮች ተጉዘው ከሆነና ትኩሳትና ሳል ካለዎ በ8335 በመደወል ያሳዉቁ!

የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ስቴፈን ፎርማን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመድሃኒት ግብአቶች ላይ ያጋጠመው እጥረት በዋጋ ላይ ጭማሪን እያስከተለ ነው። "ህንድ ውስጥ የመድሃኒቶች አቅርቦት መቀነስ ምልክ...
04/03/2020

የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ስቴፈን ፎርማን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመድሃኒት ግብአቶች ላይ ያጋጠመው እጥረት በዋጋ ላይ ጭማሪን እያስከተለ ነው። "ህንድ ውስጥ የመድሃኒቶች አቅርቦት መቀነስ ምልክቶች በመታየቱ በዋጋ ላይ ጭማሪ እየተስተዋለ ነው።" ይህንን ተከትሎ የተፈጠረውን ስጋት ለማረጋጋት የህንድ መንግሥት በሰጠው መግለጫ፤ እስከ ሦስት ወር ድረስ ሊቆይ የሚችል የመድሃኒት ክምችት እንዳለው ገልጿል።
ከፍተኛ መጠን ያለው መሰረታዊ መድሃኒቶችን ከህንድ የምታስገባው አሜሪካ ህንድ በመድሃኒቶችና በመድሃኒት ማምረቻ ግብአቶች ላይ ከጣለችው ክልከላ አንጻር ሊያስከትል የሚችለውን ተጽእኖ ለመለየት እየሰሩ መሆናቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

01/03/2020
ዶክርተር ሊያ ታደሰ ኮሮና ቫይረስ     : ዛሬ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠረ ግለሰብ በለይቶ ማቆያ መግባቱን የኢትዮጵያ  ጤና ሚንስትር ዴታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፃለች።  ይህ ግለሰብ ከ...
28/02/2020

ዶክርተር ሊያ ታደሰ ኮሮና ቫይረስ

: ዛሬ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠረ ግለሰብ በለይቶ ማቆያ መግባቱን የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ዴታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፃለች። ይህ ግለሰብ ከቤንጂንግ በFeb 22 የመጣ ሲሆን እራሱን በቤት ውስጥ ለይቶ ቆይቶ ነበር ዛሬ ግን የራስ ምታቱ መጠን መጨመሩን ተከትሎ የጤና ሚንስትር ማቆያ ውስጥ መግባቱን ሚንስተሯ በቲዊተር ገጷ ላይ አስፍራለች። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያ ውጤቱ ማታ እንደሚገለፅ ሚንስተሯ ጨምራ ተናግራለች ።

አፍሪካዊቷ አገር አልጄሪያ  የኮሮናቫይረስ ወደ ሃገሯ እንደገባ አሳወቀች ቫይረሱ ከጣሊያን ሳይዛመት እንዳልቀረም ነው የተነገረውኦስትሪያ፣ ክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን...
26/02/2020

አፍሪካዊቷ አገር አልጄሪያ የኮሮናቫይረስ ወደ ሃገሯ እንደገባ አሳወቀች
ቫይረሱ ከጣሊያን ሳይዛመት እንዳልቀረም ነው የተነገረው
ኦስትሪያ፣ ክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ኮሮናቫይረስን ሪፖርት ያደረጉ አገራትየአውሮጳ ሃገራት ሲሆኑ፤ 'ወደ አገራችን የገባው ከጣሊያን በመጡ ሰዎች ነው' ብለዋል
ኑሮውን በብራዚል ያደረገው ግለሰብም ቫይረሱን ከጣሊያን ወደ መኖሪያ አገሩ በመውሰድ በላቲን አሜሪካ የመጀመሪያው ኮሮናቫይረስ ሊመዘገብ ችሏል
በጣሊያን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 300 የደረሰ ሲሆን 11 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል
የጣሊያን ጎረቤት አገራት ከጣሊያን ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበር ሊዘጉ ይችላሉ የሚል መላ ምት በስፋት ቢነገርም፤ የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ድንበርን ክፍት በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
በቁጥር ከፍ ያሉ የአውሮፓ አገራት ወደ ጣሊያን ሲጓዙ መውሰድ ስላለባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች ዜጎቻቸውን እያስጠነቀቁ ይገኛሉ
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሊካሄዱ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ የጣሊያን እግር ኳስ ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም እንዲካሄዱ ተወስኗል።
እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 80 ሺህ የሚጠጋ ሲሆን በቻይና ብቻ 2 ሺህ 715 ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸውን ቢቢሲ አስታውሷል

(Tenofovir+Lamivudine+Efavirenz) የተባለው የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒት የ Efavirenz ጥንካሬ (strength) ከ600mg ወደ 400mg መቀነሱ ተገለጸ፡፡=========...
20/02/2020

(Tenofovir+Lamivudine+Efavirenz) የተባለው የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒት የ Efavirenz ጥንካሬ (strength) ከ600mg ወደ 400mg መቀነሱ ተገለጸ፡፡
================================
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የአለም ጤና ድርጅትን የጥናት ምክረ-ሐሳብ መሠረት ተደርጎ የፀረ ኤች አይቪ መድኃኒቱ ግራም መቀነሱን እና መድኃኒቱን ማቅረብ መጀመሩን በኤጀንሲው የኤች አይ ቪ፣ ቲቢ እና ወባ ምጠና ቡድን መሪ ወ/ሪት ጽዮን ፀያጸጋየ የካቲት 5/2012 ዓ.ም ገልጸዋል፡፡

የፀረ-ኤች አይቪ መድኃኒቱ ከአሁን በፊት Tenofouir300mg+Lamivudine300mg+Efavirenz 600mg እንደነበረ ገልጸው በአሁኑ ወቅት Tenofouir300mg+Lamivudine300mg+Efavirenz 400mg እንድቀየር ተደርጓል በማለት ተናግረዋል፡፡

የ Efavirenz መጠኑ ከ 600 mg ወደ 400 mg ዝቅ ያለበት ምክንያት የመድኃኒቱን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስ ሲባል መኾኑን ገልጸው ለነፍሰ-ጡር እና የቲቢ መድኃኒት እየወሰዱ ላሉ ታካሚዎችም ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር አብሮ መወሰድ የሚችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በጤና ሚንስቴር የኤች ኤይ ቪ ሕክምና መመሪያ /HIV Treatment guideline/ ላይ Efavirenz ባለ 400 በዝርዝሩ መካተቱን ገልጸው የዓለም ጤና ድርጅትን (WHO) ምክረ ሃሳብ እና የሚኒስቴር መስሪያቤቱን አቅጣጫ በመከተል በግሎባል ፈንድ በጀት መድኃኒቱ እየተሠራጨ እንዳለ እና የኤች እይ ቪ ምርመራ ለሚሰጡ ጤና ተቋማትም ግንዛቤ እንዲኖራቸው መደረጉን ቡድን መሪዋ አክለው ገልጸዋል፡፡

በቻይና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሃኪሞች በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ተጠቁበቻይና በመቶዎች የሚቆጠሩ የህክምና ዶክተሮች በኖቭል ኮሮናቫይረስ መጠቃታቸው ተነገረ፡፡እስካሁን ድረስ በቫይረሱ 1 ሺህ 114 ሰ...
12/02/2020

በቻይና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሃኪሞች በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ተጠቁ

በቻይና በመቶዎች የሚቆጠሩ የህክምና ዶክተሮች በኖቭል ኮሮናቫይረስ መጠቃታቸው ተነገረ፡፡

እስካሁን ድረስ በቫይረሱ 1 ሺህ 114 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን እየተገለፀ ነው፡፡

በተያያዘም የአለም ጤና ድርጅት በሽታው ከኢቦላ ወይም ከሳርስ በበለጠ በጣም በፍጥነት የመሰራጨት አቅም እንዳለው አስጠንቅቋል፡፡

ምንጭ፦ ኔዜርላንድ

ኮሮና ቫይረስ መላ ቻይናን ማዳረሱ እና የሟቾች ቁጥርም 170 መድረሱ ተነገረ********************በቻይና አንድ ግዛት ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ መላ ቻይናን ማዳረሱና በበሽ...
30/01/2020

ኮሮና ቫይረስ መላ ቻይናን ማዳረሱ እና የሟቾች ቁጥርም 170 መድረሱ ተነገረ

********************

በቻይና አንድ ግዛት ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ መላ ቻይናን ማዳረሱና በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም 170 መድረሱ ተነግሯል።

የቻይና የጤና ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በአገሪቱ እስከ ትናንት ድረስ 7711 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

በሽታው ከቻይና ባሻገር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ቢያንስ 16 አገራት መዛመቱም ተገልጿል።

የዓለም የጤና ድርጅትም ዛሬ ተሰብስቦ በወረርሽኙ ላይ ከመከረ በኋላ በሽታው ያለበት ደረጃ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆን አለመሆኑን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።

በሽታውን አስመልክተው ትናንት በሰጡት አስተያየት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም "ባለፉት አምስት ቀናት በተለይም በአንዳንድ አገራት በዋናነት ከሰው ወደ ሰው የታየው የበሽታው ስርጭት አሳስቦናል" ብለዋል፡፡ በአብነትም ጀርመንን፣ ቬትናምንና ጃፓንን ጠቅሰዋል።

ዳይሬክተሩ ጨምረውም "ከቻይና ውጪ ያለው የበሽታው ስርጭት በአንጻራዊነት ትንሽ ቢሆንም ከፍተኛ ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችልበት ዕድል አለ" ብለዋል።

እስካሁን በሽታውን የሚፈውስ መድሃኒትም ሆነ የሚከላከል ክትባት አልተዘጋጀም።

ኮሮና ቫይረስ የከፋ የመተንፈሻ አካላት ህመምን በማስከተል እስከ ሞት የሚያደርስ ሲሆን በተለይም በሽታው ቀደም ሲል ህመም በነበረባቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ እንደሚጸና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

እስካሁን ድረስ ቻይና ውስጥ በበሽታው መያዛቸውና መሞታቸው የተረጋገጠው አብዛኞቹ ሰዎች ሁቤይ የምትባለው ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው እና ወረርሽኙ በተቀሰቀሰባት የዉሃን ከተማ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ ያሉ ሰዎች እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን ቻይና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በግዛቶቿ ውስጥ በርካታ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን ጥላለች።

በሁቤይ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ከቤታቸው መውጣታቸው ምንም ስጋት እንደሌለው እኪረጋገጥ ድረስ የዕለት ተለት ሥራቸውን ከቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ በአሰሪዎቻቸው ተነግሯቸዋል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወደ አገራችን እንዳይገባ ዝግጅቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ  ___________እስከጥር 18, 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለው የኖቨል ኮሮና ቫይረስ ወቅ...
29/01/2020

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወደ አገራችን እንዳይገባ ዝግጅቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
___________

እስከጥር 18, 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለው የኖቨል ኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ

በዓለም የጤና ድርጅት ዕለታዊ ሪፖርት መሰረት በሽታው በወረርሽኝ መልክ ሪፖርት መደረግ የጀመረው ከታህሳስ 24፡ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን እስከ ዛሬ ጥር 18፡ 2012 ድረስ በጠቅላላው 2700 ሰዎች በበሽታው የታመሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የሰማኒያ (80) ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ታውቋል፡፡ በሽታው ወደ ሀገራቸው መግባቱን ሪፖርት ያደረጉ ሀገራት ቁጥር 11 ደረሶዋል።

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን እንዳይገባ ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት፡

◾️በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከ ቻይና እና አጎራባች አገሮች ለሚመጡ መንገደኞች የሙቀት ልየታ (thermal screening) እና ፎርም የማስሞላት ስራ ተጀምሯል፡፡ የልየታ ስራውን ለማጠናከር በቂ የሰው ኃይል ተመድቧል፡፡

◾️እስከ ዛሬ (18/05/2012) ድረስ ጠቅላላ ለሃያ ሺ ስምንት መቶ ሁለት (20,802) መንገደኞች ልየታ የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አምስት መቶ ሃምሳ ሁለቱ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ካለባቸው ሀገራት የመጡና ለዚህ ስራየ ተዘጋጀውን ቅፅ ሞልተው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ እና ክትትል የሚደረግባቸው መንገደኞች ናቸው፡፡

◾️እስካሁንም በአጠቃላይ ከ ቻይና የመጡ 4 የተጠረጠሩ ሰዎች በለይቶ ማከሚያ ማእከል ተለይተዉ ክትትል እየተደረገላቸዉ ነው። ከተለዩት ተጠርጣሪዎች ሁለቱ የሳል እና የሙቀት ምልክት ያሳዩ ቢሆኑም በአሁኑ ሰአት ግን አልፎ አልፎ ሳል ከማሳየታቸዉ ዉጭ ሌላ የበሽታ ምልክት የላቸውም። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ምንም አይነት የህመም ምልክት ባያሳዩም ከ ቻይና ወረርሽኙ ካለበት ቦታ የመጡ መሆናቸዉ እና ከ ምልክቱን ካሳየዉ ተጠርጣሪ ጋር ቅርብ ግንኙነትያላቸዉ መሆኑ ተለይተዉ ክትትል እየተደረገላቸዉ ነው፡፡

◾️ከአራቱ ተጠርጣሪዎች የላብራቶሪ ናሙና ተወስዶ ለምርመራ በዛሬው ዕለት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኳል። ከተወሰደው ናሙና በአገራችን በተደገላቸው ምርመራ ከ 5 አይነት ኮሮና ቫይረሶች ነጻ መሆናቸውን ማወቅ ተችሎዋል።

◾️በተለይም ከቻይና ለመጡ 280 መንገደኞች በየዕለተቱ ባረፉበት ቦታ ክትትል እየተደረገላቸው ነው፡፡ ዪሄም ክትትል ለ አስራ አራት ቀናት የሚቆይ ነው።

◾️በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጊዜያዊ የለይቶ መከታተያ ክፍል ና የሰዉሃይልን ጨምሮ አስፈላጊዉ ግብአት ተዘጋጅቶዋል።

◾️በበሽታው ለተጠረጠሩ መንገደኞች የጊዚያዊ ማቆያ ማዕከል በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ተዘጋጅቷል፡፡

◾️የከፋ ሁኔታ ላለታየባቸው 30 ለሚሆኑ በበሽታዉ የሚጠረጠሩ ታካሚዎችን የሚይዝ የለይቶ ማከሚያ የህክምና መእከል በቦሌ ጨፋ ተዘጋጅቶ አስፈላጊዉ የህክምና እና ልዩ ልዩ ግብአቶች እየተሟሉ ይገኛሉ። በዚህ ማእከል በሽታዉ የተረጋገጠባቸዉ፣ የተጠረጠሩ እና ተለይቶ ክትትል ለሚደረግላቸዉ ክፍሎች ተለይተው ተዘጋጅቶዋል፡፡

◾️በጽኑ ለታመሙና ከፍተኛ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸዉ ታካሚዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የተለየ ክፍል ተዘጋጅቶዋል፡፡

◾️በጤና ሚኒሰቴር የሚመራ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ የወረርሽ ቅድመ ዝግጅት ብሄራዊ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ የመጀመሪያ ውይይቱን ያደረገ ሲሆን ውይይቱ ሌሎችን በማካተት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡በዚህ ግብረ ሃይል የተካተቱት ፤ አዲስ አበባ መስተዳድር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ቀይ መስቀል፣ ባህል እና ቱሪዝም ፣ ኢሚግሬሽን እና ሌሎች አግ ባብነት ያለቸው ይገኙበታል ።

◾️በኢትዮያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚመራ የቴክኒካል ቡድን ተቋቁሞ ስራዉን ጀምራል፡፡

◾️በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን ለኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ቅድመ ዝግጅት የአደጋ ማስተባበሪያ ማእከል (Emergency Operation Center ) ወደ ተግባር በማስገባት ጭምጭምታዎችን የማረጋገጥ እና ለተጠርጣሪዎች ጥልቅ ምርመራ እየተሰራ ነው፡፡

◾️በመደበኛነት የዓለማችንን ወቅታዊ ሁኔታ ክትትል በማድረግ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ወቅታዊ መረጃ እና ምክረ ሃሳብ እየተሰጠ ነው፡፡

◾️የክልል እና የከተማ ጤና ቢሮዎችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ በኢሜልና በደብዳቤ የአለም የጤና ድርጅት ምክረ ሐሳቦችን መሰረት ያደረገ የማንቂያ ምልዕክት አስተላለፈናል፡፡

◾️የዝግጁነትና ምላሽ ለመስጠት የሚረዳ የትግበራ እቅድ ተዘጋጅቷል

◾️ለባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና መስጠት ተጀምሮዋል፡፡

◾️የሕብረተሰቡን ስለ ቫይረሱ ወረርሽኝ ለማንቃት ና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ወቅታዊ መረጃዎችን ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ክትትልም ይደረጋል፡፡

◾️የጋዜጣዊ መግለጫ የመስጠት እና ሕብረተሰቡን፣መንገደኞችን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን የማንቃት፣አስፈላጊ የኮሚኒኬሽን ማቴሪያሎችን የማዘጋጀት እና የማሰራጨት ተግባራት ከመከናወናቸውም በላይ ከአፍሪካ ሲዲሲ እና የዓለም የጤና ድርጅት ጋር በምክር እና ሪኤጀንትን በመተለከተ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0112765340 ወይም በኢሜል አድራሻችን
phemdatacenter@gmail.com ወይም ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ዒንስቲትዩት

28/01/2020

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሰው ተገኘ!
Ethiopia confirms first case of coronavirus

23/12/2019

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

ከግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለተመረቁ ጠቅላላ ሐኪሞች ለኦሮሚያ ክልል ብዛት 300 ፤ ለአማራ ክልል ብዛት 100 ፤ ለደቡብ ክልል ብዛት 50 ፤ ለአፋር ክልል ብዛት 9 ፤ ለሱማሌ ክልል ብዛት 11 ጠቅላላ ሐኪሞች ማስታወቂው ከተነገረበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት በየክልሎች የትምህርት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የየክልሎቹ ጤና ቢሮዎች

Address


22242

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioPharma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram