19/03/2026
ዒድ ሙባረክ! ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!
በዓልን ለየት እና ደመቅ ከሚያደርጉት ዋነኛ ጉዳዮች መካከል ከቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ ጋር ተሰብስበን ማሳለፋችን ነው። በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን በአብሮነት ማሳለፍ መብላት እና መጠጣታችን ከምንም በላይ የምንወደው ነገር ነው።
ታዲያ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለይም ከሃገር ውጪ ስንሆን ይህ ድባብ አይኖርም አብዛኛውን የበዓል ጊዜያት ብቻችንን ነው የምናሳልፈው፣ ይህ በዓልን ለብቻ ማሳለፍ በተለይም ለረጅም ጊዜ ሲሆን የሚያመጣው የራሱ የሆነ የስነልቦና ጫና አለ። ድባቴ በዋነኛነት የሚጠቀሰው ችግር ነው።
የበዓልን ሰሞን እንደድሮ አብሮ ማሳለፍ ባንችል እንኳን በተቻለ አቅም የምንወደውን እና የሚያስደስተንን ነገር እያደረግን እራሳችንን ከበዓል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ home seeking እና የድባቴ ስሜት መከላከል እንችላለን።
እፎይ የስነ-አዕምሮ ስፔሻሊቲ ክሊኒከ!
ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤናዎ!
https://t.me/efoypsycenter
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-94olT6oorVX