13/04/2026
የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የትንሳኤ በዓልን ከታማሚዎች እና ከሰራተኞች ጋር በደማቅ ሁኔታ አከበረ!
አዲስ አበባ:-ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።
በበዓሉ ዕለት የሆስፒታሉ የሲኒየር ማኔጅመንት አባላት በየክፍሉ በመዘዋወር በሕክምና ላይ የሚገኙ ታማሚዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ ለታማሚዎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትና የፈውስ ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። ይህ ጉብኝት ታማሚዎች የበዓል ስሜት እንዳይለያቸውና የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው ለማድረግ ነው።
በተጨማሪም በበዓል ቀን ቤተሰቦቻቸውን ትተው በስራ ተረኝነት ላይ በመገኘት ለታማሚዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የህክምና አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ማኔጅመንቱ አመስግኗል።
በመርሃ ግብሩ ለታካሚዎች ለአስታማሚ እንዲሁም ለስታፍ የምሳ ግብዣ በማድረግ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
ይህ ባህል የታካሚና የባለሙያዎችን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር የተለመደ መልካም እሴት ነው።
"የአገልግሎት ጥራት አርማችን"