Arbaminch General Hospital

Arbaminch General Hospital ይህ የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው!

በሆስፒታላችን መደበኛ የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ሰርቪስ ማኔጅመንት ውይይት ተካሄደ።                 ቀን: 13/08/2018 ዓም በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል መደበኛ የነርሲንግ ...
22/04/2026

በሆስፒታላችን መደበኛ የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ሰርቪስ ማኔጅመንት ውይይት ተካሄደ።
ቀን: 13/08/2018 ዓም
በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል መደበኛ የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ሰርቪስ ማኔጅመንት ውይይት አካሄደ።
በውይይቱም ሁለት አንኳር አጀንዳዎች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን
በአንደኛነት ደረጃ የተቋሙን ጠቅላላ ወራዊ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን በሁለተኛነት ደረጃ የተቋሙ ዋነኛ ግብ የሆነውን የተገልጋይ ዕርካታና ዕሴቶች ዙሪያ በጋራ መክረዋል።

በወራዊ አፈጻጸሙ ዙሪያ እንደ ጠንካራ ጎን ተብለው የተወሰዱና ሊቀጥሉ ይገባል የተባሉትን በማስቀጠል መሻሻል በሚገባቸው ዙሪያም በአጽኖት መክረዋል።

በተጨማሪም የተገልጋይን እርካታና ዕሴቶችን በሚጨምሩ የአሰራር ለውጦች በመዘርጋት ለተሻለ ውጤት በጋራ ወደ ተግባር የሚገባበት አግባብ እንደሚኖር አሳስበዋል።

በመጨረሻም በጋራ በመሆን የተሻሉ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በጋራ መግባባት ተጠናቋል።

በውይይቱም የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ሰርቪስ ማኔጅመንት ኃላፊዎች እና የሁሉም የሥራ ክፍል አስተባባሪዎች በውይይቱ ታድመዋል።


@አርባምንጭ

የድንገተኛ አደጋዎች ክስተት አስተዳደር ግብረኃይል የዜጎች ጤና በዘላቂነት ለመጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።‎  ‎በናዳ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሰጠው ሁሉ...
20/04/2026

የድንገተኛ አደጋዎች ክስተት አስተዳደር ግብረኃይል የዜጎች ጤና በዘላቂነት ለመጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

‎በናዳ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሰጠው ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በጊዚያዊ መጠለያ ለተጠለሉ ወገኖች በተቋቋመው ጊዚያዊ ክሊኒክ የሚሰጠው አገልግሎት መጠናከሩን የድንገተኛ አደጋዎች ክስተት አስተዳደር ዕለታዊ ሪፖርት አትቷል።

የቲቢ በሽታ ምልክት ባሳዩ 10 ሰዎች የአክታ ምርመራ ተደርጎላቸው በ 5 ሰዎች በሽታው ተገኝቶባቸው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል።

በጊዜያዊ የህክምና ማዕከሉ 1 ሺህ 309 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል።

‎ከሪፈራል አገልግሎት ጋር በተያያዘ 24 ሰዎች ለተሻለ ህክምና ወደ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ከተደረጉት መካከል 20 ሰዎች ህክምና አጠናቀው ወደ ቀያቸው የተመለሱ ሲሆን የተቀሩት 4 ሰዎች ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆናቸው 2 ሺህ 148 ህፃናት ‎ከስርዓተ-ምግብ ልየታ ተደርጎላቸው 64 ህፃናት ከፍተኛ የምግብ አለመመጣጠን ችግር ተግኝቶ ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

በወባማ ወረዳዎች የበሽታው ስርጭት ከመጨመሩ ጋር በተገናኘ በዜጎች ላይ የከፋ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ማህበረሰቡን የማሳተፍ ሂደት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል።

ለተጎጂ ወገኖች የህክምና አገልግሎት ለማሳለጥ የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች አቅርቦትና ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎‎
#ምንጭ
ክልል ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን
ጂንካ

የክትባት አገልግሎት በ20 ፋርማሲዎች መሰጠት ተጀመረ**********የጤና ሚኒስቴር ከፒ.ኤስ.አይ (PSI) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፋርማሲዎች ውስጥ የክትባት አገልግሎት ...
19/04/2026

የክትባት አገልግሎት በ20 ፋርማሲዎች መሰጠት ተጀመረ
**********

የጤና ሚኒስቴር ከፒ.ኤስ.አይ (PSI) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፋርማሲዎች ውስጥ የክትባት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የፓይለት ፕሮጀክት አስጀምሯል።

በተመረጡ 20 ፋርማሲዎች የተጀመረው የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ የክትባት ተደራሽነትን ማሳደግ ሲሆን፣ ከጤና አገልግሎት መስፋፋት ባለፈ የሚታለፉ የክትባት ዕድሎችን በመቀነስ ፍትሃዊ የክትባት ስርጭትን ማረጋገጥ ነው።

መደበኛ የሕፃናት ክትባቶች፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት (HPV) እና የመንጋጋ ቆልፍ እና የጉሮሮ በሽታ ክትባቶችን በፋርማሲዎቹ ውስጥ የሚሰጡት ክትባቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የክትባት አገልግሎቱ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን አስፈላጊው ሥልጠና እና ድጋፍ ለባለሙያዎቹ ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የእያንዳንዱ ፋርማሲ የአገልግሎት ጥራትና ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን ከጤና ተቋማት ጋር ትስስር ተፈጥሯል።

በቀጣይም አገልግሎቱን በሁሉም ፋርማሲዎች ለማዳረስ በትኩረት የሚሠራ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ላደረጉት ለጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል ማህበር፣ ለተሳታፊ ፋርማሲዎች እና ለሁሉም አጋር አካላት ምስጋና ቀርቧል።

የአገሪቱን የጤና አጠባበቅ ስርዓት ለማጠናከር በኢትዮጵያ የመድኃኒቶችን እና የጤና ግብአቶችን ምዝገባ ስርአትን እና የተፋጠነ የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር...
18/04/2026

የአገሪቱን የጤና አጠባበቅ ስርዓት ለማጠናከር በኢትዮጵያ የመድኃኒቶችን እና የጤና ግብአቶችን ምዝገባ ስርአትን እና የተፋጠነ የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ።
__________

በዚህ የበይነ መረብ ውይይት ላይ አለም አቀፍ አምራቾች፤ አስመጪዎች እና አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

በኢትዮጵያ የጤና ግብአቶችን የምዝገባ እና የገበያ ፈቃድ ስርዓትን ለማዘመን እና ወደተሻለ ውጤት ለማድረስ በኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለስልጣን (EFDA) የቁጥጥር ቅልጥፍናን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እና የዝግጅት ሁኔታዎች እና አስቻይ ተግባራትን ለተሳታፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ትልቅ የጤና አቅርቦት ፍላጎት ካላቸው ሃገራት አንዷ መሆኗን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለስልጣን በመድኃኒት ዘርፍ የጥራት፣ የደህንነት እና ውጤታማነት አረጋጋጭ በመሆን ማዕከላዊ ሚና እንዳለው አፅንዖት ሰጥተዋል።

ሚኒስትሯ በቁጥጥር ሂደቱ ውስጥ ቅልጥፍናን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማሻሻል ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ከመሆኑ አኳያ የኤሌክትሮኒክስ የቁጥጥር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ የቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የዲጂታል የቁጥጥር ዘዴዎች መጀመራቸው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን ለማፋጠን እና ወደ ገበያ የሚገቡ የጤና ምርቶችን የበለጠ ቁጥጥር ለማረጋገጥ እንደሚረዳ የተናገሩት የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ሄራን ገርባ፤ የመድኃኒት ኩባንያዎች እና ባለሀብቶች ኢትዮጵያን ለኢንቨስትመንት ስትራቴጂካዊ መዳረሻ አድርገው እንዲያስቡ አበረታተዋል።

Email: arbaminchgeneralhospital1@gmail.com
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61566261579966

በሆስፒታላችን የተፈጥሮ አደጋ ደርሶባቸው ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ተገልጋዮች ሽኝት ተደረገላቸው።                        ቀን: 08/08/2018 ዓም                ...
17/04/2026

በሆስፒታላችን የተፈጥሮ አደጋ ደርሶባቸው ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ተገልጋዮች ሽኝት ተደረገላቸው።
ቀን: 08/08/2018 ዓም
አርባምንጭ
በጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ ልብ ሰባሪና በርካታ ነብስ የነጠቀ አስከፊ የተፈጥሮ አደጋ የተረፉ ተገልጋዮች የሆስፒታሉ ሥራአስኪያጅ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

በአከባቢው የደረሰውን አደጋ እጅግ አሳዛኝ እንደነበር ያስታወሱት የሆስፒታሉ ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ የተረፉ በመሆናቸው በማጽናናት በአደጋው ተጎጂ የነበሩና የጤና ዕክል የገጠማቸው በርካታ ሰዎች በሆስፒታላችን ልዩ ልዩ የሕክምናና የእንክብካቤ አገልግሎት ሲያገኙ መቆየታቸውን ተናግረዋል።አክለውም ይህ ሽኝት የመጀመሪያ እንዳልሆነና በዚህ ልክ የጤና ሁኔታቸው በሕክምና ተረጋግጦላቸው የተሸኙ በርካታ ሰዎች እንደነበሩም አንስተዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ ተስፋዬ አክለውም ይህ እንክብካቤ ቀጣይነት ባለው መልኩ እዚሁ በሆስፒታልና እዚያው ደግሞ የጤና ባለሙያን በመላክ በቦታው የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን በማስታወስ እንዲበረቱና ጤናቸውን ባሉበት እንዲጠብቁም አሳስበዋል።

በመጨረሻም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የነበሩት የአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦችና ግለሰቦችን በጎ ሀሳባቸውንም ተቀብለናል።
ሀሳባቸውን ከሰጡን ተገልጋዮቻችን መካከል አንዱ የሆነው አቶ ሳጌ ሳሌ እዚያው አደጋው ከደረሰበት ቦታ መምጣተታቸውን በመናገር የደረሰባቸውን የአደጋ ሁኔታ እንደተናገሩት የሞቱ ሬሳዎችን ለማውጣት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ነበር ዳግም ናዳው በእኛ ላይ የወረደው እንግዲህ ትረፍ ያላት ነብስ ሆና ነበር መላ አካላቴ ተውጦ የቀኝ እጄ ብቻ ወደላይ ቀርታ በእጄ ምልክት ሰው ደርሶልኝ የተረፍኩት ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚያ ባሻገር አደጋው ከደረሰበት ዕለት አንስቶ እስከዛሬው ዕለት ድረስ ይህ ሆስፒታል እንክብካቤና ፍቅር ሲሰጠን አቆይቷል። የአልባሳት,የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናዎች የሕክምና ምርመራ አገልግሎቶች ወዘት በልዩ ሁኔታ ሲሰጡን ቆይተዋል ለዚህ ደግሞ ልዩ ምስጋና ይገባቸዋልና ከልብ እናመሠግናለን ብለዋል።

ሌላኛዋ ተገልጋያችን የነበረችው እህታችን ወ/ሮ ደመቀች ደበበ እንደተናገረችው በቀኑ አራት ሰዓት ላይ የመጣው ናዳ እኔና አምስት ቤተሰቦቼን ጎድቶ መንግስት አፋጣኝ ድጋፍ ባያደርግልን እኔና ልጄ እንዲሁም ባለቤቴ በጠፋን ነበር ነገርግን በተደረገልኝ ድጋፍ ይሄው እኔና ቤተሰቤ ተርፈን በሆስፒታሉ እንክብካቤን ለልጄና ለቤተሰቤ ሲደረግ ቆይተን ይሄው ዛሬ ደህና ሆነን ልንሄድ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

በተመሳሳይ ሀሳባቸውን የሰጡት አቶ አዲሱ አባይነ እና ካዝና ጨነቀ በተመሳሳይ የደረሰባቸውን አደጋ በመናገር ለተደረገላቸው እንክብካቤና ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ለግሰዋል።


ሊንኩን በመጫን ተከታያችን ይሁኑ !!
የፌስቡክ ገጽ- https://www.facebook.com/profile.php?id=61566261579966

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ስታርሊንክን በመጠቀም በገጠር የጤና ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስፋት የሚያስችል ውይይት ከስፔስኤክስ ልዑካን ቡድን ጋር አካሂደዋል።በስብሰባው የስ...
15/04/2026

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ስታርሊንክን በመጠቀም በገጠር የጤና ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስፋት የሚያስችል ውይይት ከስፔስኤክስ ልዑካን ቡድን ጋር አካሂደዋል።

በስብሰባው የስፔስኤክስ ልዑካን ቡድን ስታርሊንክ በአሁኑ ጊዜ በ169 አገሮች ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎት ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል።

አገልግሎቱ በተለይም በሩቅ እና በቂ የኔትወርክ አገልግሎት በማያገኙ አካባቢዎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነት ለማቅረብ ያለመ ነው።

ስፔስኤክስ በተለይ ለገጠር የጤና ተቋማት የኢንተኔት አገልግሎትን በማቅረብ ረገድ መልካም አማራጭ ማቅረቡን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ብዙ የጤና ተቋማት አሁንም አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እያገኙ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአገሪቱን የዲጂታል የጤና ስርዓት ለማጠናከር ከስፔስኤክስ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልፀዋል።

ሚያዚያ 7/2018
የፌስቡክ ገጽ- https://www.facebook.com/profile.php?id=61566261579966
ሊንኩንን በመጫን ተከታያችን በመሆን አጋርነቶን ያሳዩን !!

አርባምንጭ

15/04/2026

Big shout out to my newest top fans! Tsegaye Bk, Ayenat Desta, Redi John, Mistir Girma, እንደ ንስር የሺ, Abdi Nebro Nebro, Hailu Halke, Tadu Zegeye, Mimi Kebo, Haileselasse Gk, Lijalem Minale, Shasho G**o Chulda, Mihire Desalegn

15/04/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Zelalem Paulos, Tsegaw Girma, Bersu Dem Dignalew, Eshetu Gestie Ze-Lalibela, Yohannes Ayele, Mesfin Melaku, Getish Bekele, Misgana Muntasha, Desalegn Zekarias, Azazhu Desalegn, Girma Gobeze, Tesfalegn Teferi Abire, Eyasu Guja, Anteneh Dabare Anteneh Dabare, Tarekegn Aganso Andisew, Paulos Markos, Danka Ye Kalkaassa Lij, Aman Aman Aman, Legese Lemma, Mekonnen Borago, Kura Man Man, Alemseged Sisay, Abiyot Wegayehu Mengistu, Tizita Assefa, Dawit Tolcha, Gashaw Gofere Gura B***a, ጋሻው ከበደ ባሼ, Ethiopian Ethiopian, Tewoflos Torcha, Tesfaye Tsegaye, Lukas Bore, Alemayehu Bulga, Wondefero Wetera Man, Gashu Dosegna, JD Mitaye, Mayza Mekuria, አህመድ ቃፍሬ, Tamiru Wade, Anu Ye Adi Liji, Yesihak Endashaw Watte, Markos Jesus, Aba Abate, Merried Mengistu, Samson Bassa, Milash Mika, Singer Mahi, Dagi D Yihun, Jafar Mohammed, Endrish Mu, Habitish Hode Matalo

👉የሆስፒታላችን ሥራአስኪያጅ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ በመሆን በዓሉን የተፈጥሮ አደጋ ተጎጅዎች ጋር በጋራ በመሆን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።               @ቀን 05/08/201...
14/04/2026

👉የሆስፒታላችን ሥራአስኪያጅ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ በመሆን በዓሉን የተፈጥሮ አደጋ ተጎጅዎች ጋር በጋራ በመሆን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።
@ቀን 05/08/2018 (አርባምንጭ)
የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በጋሞ ዞን በጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ የተፈጥሮ አደጋ መከሰቱንና ሆስፒታሉ የገንዘብና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረጉ ባሻገር በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውንና የጤና ዕክል የገጠማቸውን በሆስፒታላችን የሕክምና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

ዛሬ ላይ ደግሞ በልዩ ሁኔታ የሆስፒታላችን ሥራአስኪያጅ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ በመሆን በዓሉን ከተጎጂዎች ጋር በጋራ በመሆን በዓሉን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።

የፕሮግራሙም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አንባቸው ዱማ በተፈጠረው አደጋ ውስጣዊ ሀዘናቸውን ዳግም በመግለጽ በግልና በተቋሙ ስም መጽናናትን በመመኘት ሲደረግ የነበረው የሕክምና የአልባሳትና የተለያዩ እንክብካቤዎች እንደሚቀጥሉ በመናገር በዓሉን በሠላም በደስታ በነፃነት እንዲያከብሩም አሳስበዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር አክለውም ቀድሞውንም ሲደረግ የነበረው የሕክምና እንክብካቤ እንደሚቀጥል በማሳሰብ በዓሉ የሠላም የጤና እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል።

በተጨማሪም የፕሮግራሙ ታደሚና የአደጋው ተጎጂ የነበሩ በሆስፒታላችን የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ከነበሩ ተገልጋዮቻችን ሀሳብ አስተያየት በመቀበልና ተገልጋዮች እየተደረገላቸው ሥላለው, ሊደረግ ስላለው ሁለንተናዊና ሰብዓዊ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሆስፒታሉን ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በጋራ

#የቡናና በጋራ የጨዋታ ጊዜን በማሳለፍ በደማቅ ሁኔታ እንዳማረበት ተጠናቋል።

ከከታች ያለውን ሊንኩን በመጫን አጋራችን የሁኑ ይከተሉ

https://www.facebook.com/profile.php?id=61566261579966

👉የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ የጋሞ ጨንቻ እግርኳስ ቡድን ጠንካራ ፉክክር በማድረግ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ በማደጉ የእንኳን ደስ አላችሁ እንኳ...
13/04/2026

👉የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ የጋሞ ጨንቻ እግርኳስ ቡድን ጠንካራ ፉክክር በማድረግ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ በማደጉ የእንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በድጋሚ

💪

👉የሆስፒታላችን ሥራአስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር አምባቸው ዱማ እና የማኔጅመንት አካላት በጋራ በመሆን በዓሉን በማስመልከት ከታካሚዎች ጋር የእንኳን አደረሳችሁ ፕሮግራም አካሄዱ።            ...
11/04/2026

👉የሆስፒታላችን ሥራአስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር አምባቸው ዱማ እና የማኔጅመንት አካላት በጋራ በመሆን በዓሉን በማስመልከት ከታካሚዎች ጋር የእንኳን አደረሳችሁ ፕሮግራም አካሄዱ።
ቀን 03/08/2018 ዓም
አርባምንጭ
የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራአስኪያጅ እና የማኔጅመንት አካላት በጋራ በመሆን በዓሉን በማስመልከት በተለያዩ ክፍሎች ላይ በተለያዩ የጤና ዕክል ገጥሟቸው በሆስፒታላችን ሕክምና አገልግሎት ከሚሰጣቸው ታካሚዎች ጋር በጋራ በመሆን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።

የሆስፒታሉ ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ እንደተናገሩት ይህን በዓል ሁሉም ታካሚ ቤቱ ያሳለፈ ያክል እንዲሰማውና በነፃነት ሕክምናቸውን በአግባቡ በመከታተል ለቤታቸው እስኪበቁ ድረስ የነፃነት ስሜት እንዲሰማቸውና እግዚአብሔር ለቤታቸው እንዲያበቃቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

#በድጋሚ
🙏

  ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።                                   ቀን 02/08/2018 ዓም                    ...
10/04/2026

ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ቀን 02/08/2018 ዓም
አርባምንጭ

የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ በበዓላት ወቅት ሕብረተሰቡ ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን በአመጋገብ ሥርዓት መዛባት ምክንያት ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች ራሳቸውን በመጠበቅ በዓሉን በሰላምና በጤና እንዲያከብር ሲሉ በጥብቅ አሳስበዋል።

የስቅለት በዓል መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅሩን ለመግለጽ ብዙ ስቃይና መከራን የተቀበለበት በመሆኑ ሁላችንም የእውነተኛውን የክርስቶስ መንገድ በመከተል

!
!
!
የሰለጠነበት ዕለት በመሆኑ ይህ የተቀደሰ ሀሳብ በተግባራችን ላይ እዲንፀባረቅ አሳስበዋል።

Address

Gamo Zone
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share