13/08/2025
የኩላሊት እጥበት /Dialysis/
Dialysis ማለት የሰው ኩላሊት ስራ በማቆሙ ወይም ስራ በመቀነሱ ምክንያት ሰውነት ውስጥ የሚከማቹትን ተረፈምርት እንዲሁም toxins ደማችንን ከሰውነታችን በማውጣት በ ማሽን ታጥቦ እንዲገባ ማድረግ ማለት ነው።
በዲያሊሲስ ወቅት ደም ከሰውነት ውስጥ በቀይ ቱቦ ተወግዶ በዳያሊስስ ማሽኑ ውስጥ አልፎ ከተጣራ በኋላ በሰማያዊው ቱቦ ወደ ሰውነታችን ተመልሶ ይገባል።
በሽተኛው በአልጋ ላይ የማይንቀሳቀስ ሆኖ ሲቆይ ይህ ሂደት አራት ሰዓታት ይወስዳል።
የአሰራር ሂደቱ በሳምንት እስከ ሶስት ጊዜ የሚከናወን ሲሆን ይህም በወር አስራ ሁለት ጊዜ ወይም አርባ ስምንት ሰአት ማለት ነው።
👉 Dialysis የ ኩላሊት ህመም ምክንያቱ እስከሚታከም ወይም ኩላሊቱ እስከሚቀየር ድረስ ይቀጥላል ።
⛔️ ይህም ከ ዋጋ ውድነቱ በተጨማሪ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል።
🫵🫵🫵 ይህን የምታነቡ ሲጋራ ና አልኮልን ያቁሙ፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን ይቀንሱ፣ አላስፈላጊ የስኳር አጠቃቀምን ይተዉ፣ በአስፈላጊ ሁኔታ ጂም/ስፖርት/ያዘውትሩ፣በቂ ውሃ ይጠጡ።
👉 ህመም ሲሰማዎ በፍጥነት ህክምና ያድርጉ ።
👊እነዚህን ካደረጉ ኩላሊቶችዎ እና ጉበትዎ ጤነኛ እንዲሆኑ ለማድረግ ቀላል እና ርካሽ አማራጮች ናቸው።
🙏🙏🙏 ከሁሉ በላይ ሙሉ ጤንነትን የሰጠንን ፈጣሪ ሁል ጊዜ አመስጋኝ እንሁን።
🔉🔉🔉 ጤናችንን ልክ እንደ አደራ እንጠብቅ🏨
ደዋ የህክምና ና ቀዶ ጥገና ማዕከል(DMSC) !!!