New life home based health care

New life home based health care This page work on home based health care. Our address located in Hawassa po.n 0941050991 contact as

01/11/2022

ነርሲንግ ማለት ምን ማለት ነው?

“ነርሲንግ ማለት በህክምና ውስጥ ያለ ሙያ ነው፡፡ በጤና ውስጥ ህክምና መስጠት የሚያስችሉና ህክምናውን ደግሞ የሚደግፉ ብዙ ዓይነት ተቀራራቢና ተደጋጋፊ የሆኑ የሙያ ዘርፎች አሉ፡፡ ነርሲንግ ሙያ ደግሞ በሽታ/ችግር እንዳይከሰት ከማድረግ ጀምሮ ከተከሰተ ደግሞ የባሰ ጉዳት ሳያደርስ ሰውም ለሞትና ለስቃይ እንዳይዳረግ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ እንዲቻል ትልቅ አቅም የሚገኝበት የህክምና ዘርፍ ነው፡፡

አንድ በነርሲንግ ሙያ የተመረቀ ነርስ ብዙ ሃላፊነት አለው፡፡ በሽታ እንዳይከሰት ማህበረሰቡን ማስተማር፣ አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ፣ ቶሎ ቶሎ የቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ መምከርና፣ በሽታ ከተከሰተ ደግሞ ህሙማንን እንደ አባት፣ እንደ እናት፣ እንደ እህትና እንደ ወንድም በማየት ሙሉ ህክምና በመስጠት በቶሎ ከበሽታቸው እንዲድኑና ወደ ቀድሞው ጤንነታቸው እንዲመለሱ ማድረግ፣ አስፈላጊው ሁሉ ተደርጎ መሻሻል ከሌለና መድከሙ እየበረታ ከሄደ ደግሞ ሞት የሁሉም ነውና ትክክለኛ ሞት እንዲሞቱ ማድረግ የዚህ ሙያ አካል ነውና ባለሞያው ትልቅ አደራ አለበት፡፡

ነርስ የሚለውን ቃሉን እና ትርጉሙን ብንመለከት የተሻለ አረዳድ ሊኖረን ይችላል፡፡ እንደሚታወቀው “ነርስ” የሚለው ቃል እንግሊዘኛ ሲሆን መዝገበ ቃላችንን ከፍተን ፍችውን ብንመለከት የሚያስደንቅ ትርጉም ሊሰጠን ይችላል፡፡ ወደ አማረኛ ስንቀይረው ከሚሰጠን የተለያዬ ፍቺ መካከል አስታማሚ፣ ተንከባካቢ፣ በጥንቃቄና በፍቅር የሚይዝ፣ የሚያስብ የሚጨነቅ፣ ወዘተ የሚሉ ትርጉሞችን እናገኛለን፡፡ እነዚህ ትርጉሞች በደንብ ላጤናቸውና ላስተዋላቸው እጅግ የረቀቁ እንዲሁም የሚደነቁ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ለምን ካላችሁን ደግሞ የሰውን ልጅ ያህል ትልቅ ፍጡር በሚቸገርበት ወቅት ማገዝና መረዳት የህሊናም የመንፈስም እርካታ የሚሰጥ ትልቅ ተግባር በመሆናቸው ነው፡፡

ነርስነት ማንም ሰው የሚመኘው ሙያ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ነርስ መሆን እድለኝነት ስለሆነ፡፡ ያዘነውን ማረጋጋት፣ የታመመውን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ከህመሙ እንዲድን ማድረግ፣ የተቸገረውን ከችግሩ እንዲላቀቅ ካልተቻለ ደግሞ የችግሩን መጠን እንዲቀንስ ማድረግ፣ ጭንቀቱን ውጥረቱን ማቃለል፣…..ወዘተ ማድረግ የሚችሉት የተመረጡና የታደሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ነርስ የሆኑ ሰዎች ለዚህ ተግባር ብቁ ናቸው፡፡

የነርስ ሙያ ታማሚውን በማከምና በመንከባከብ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ከላይ እንዳየነው ከመጀመሪያው ህመም እንዳይከሰት ተግቶ የሚሰራ ውድ የሆነ የሙያ ዘርፍ ነው፡፡ እንደገናም ህመም ከተከሰተ በኋላ ታማሚው ከህመሙ ዳነም አልዳነም አስከመጨረሻው ድረስ የሚታገል በውስጡ ትልቅ የሰብአዊ ስሜት የሚፀባረቅበት ነው፡፡

Bamlaku Abebaw, Jimma
Telegram: t.me/HakimEthio

29/10/2022
በእርግዝና ጊዜ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ ምን ያህል ያውቃሉ? | Exercise in pregnancyበዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስትበእርግዝና ጊዜ የሚደረግ እንቅስቃሴ ጥቅሞች...
16/10/2022

በእርግዝና ጊዜ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ ምን ያህል ያውቃሉ? | Exercise in pregnancy
በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

በእርግዝና ጊዜ የሚደረግ እንቅስቃሴ ጥቅሞች

⁃ 👉በእርግዝና ጊዜ ያለ የጀርባ ህመም ይቀንሳል
⁃ 👉የሆድ ድርቀትን ይቀንሳል
⁃ 👉በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ሰኳር ፣ ግፊት እና በኦኘራሲዎን የመውለድ እድልን ይቀንሳል
⁃ 👉የልብንና የደም ቧንቧን ጥንካሬ ይጨምራል

እንቅስቃሴ ስናደርግ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

⁃ 👉ውሀ በደንብ እንቅስቃሴ ከመጀመራችን በፊት እንቅስቃሴ እያደረግን እና ከጨረስን በውሀላ መጠጣት አለብን።
⁃ 👉በተቻለ አቅም ቀለል ያለ ሙቀትን የማይስብ ልብስ አድርገን እንቅስቃሴ እናድርግ
⁃ 👉ሞቃት በሆነ አየር ወይም ክፍል እንቅስቃሴ አናድርግ
⁃ 👉ለብዙ ሰዐት መቆም እና ለብዙ ሰዐት ለጥ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ አይመከርም ምክንያቱም ደም ወደ ልባችን እንዳይመለስ ሰለሚከለክል

ነፍሰጡር እናት በሳምንት ምን ያህል ጊዜ መንቀሳቀስ አለባት?

⁃ 👉150 ደቂቃ መጠነኛ የሆነ ኤሮቢክስ(aerobics) መስራት ትችላለች ይህ ማለት 30 ደቂቃ በቀን እንደማለት ነው። ( መጠነኛ ሲባል ያለምንም ችግር ማውራት የምትችል ከሆነ ነገር ግን መዝፈን የሚከብዳት ከሆነ እንደማለት ነው)

እንቅስቃሴ ማድረግ የሌለባቸው ነፍሰ ጡሮች!

⁃ 👉ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ውርጃ ካጋጠመሽ
⁃ 👉በበፊት እርግዝናሽ ከ9 ወር በፊት ምጥ መቶብሽ የሚያውቅ ከሆነ
⁃ 👉የደም ምልክት በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት ከማህፀን ደም አይተሽ ከሆነ
⁃ 👉የእንግዴ ልጁ ከልጁ ቀድሞ የመጣ ከሆነ
⁃ 👉የማህፀን ጫፍ መሳሳት ወይም መቅጠን አለ ከተባልሽ
⁃ 👉የአስም በሽታ ፣ የስኳር በሽታ እና የልብ በሽታ አለብሽ ከተባልሽ
⁃ 👉መንታ እና ከዛ በላይ ያረገዝሽ ከሆንሽ

በእርግዝና ጊዜ የሚመከሩ የእንቅስቃሴ አይነቶች!

⁃ 👉ዋና
⁃ 👉ፈጠን ያለ እርምጃ
⁃ 👉የቤት ውስጥ ወይም በጂም ቤት ያለ ሳይክል መንዳት
⁃ 👉ከባድ ያልሆኑ የaerobics እንቅስቃሴዎች
⁃ 👉የጠረቤዛ ቴኒስ
⁃ 👉ዮጋ

የተከለከሉ እንቅስቃሴዎች!

⁃ 👉የፈረስ ግልቢያ
⁃ 👉እግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ እና የመረብ ኳስ
⁃ 👉ፈጣን ሩጫ፣ ዝላይ
⁃ 👉ከከፍታ ቦታ ላይ ዘሎ ዋና መግባት
⁃ 👉Gymnastic እንቅስቃሴዎች
⁃ 👉የሜዳ ቴኒስ

እንቅስቃሴ እያደረኩ ማቆም የሚገባኝ መቼ ነው?

⁃ 👉ደም ከማህፀን ከወጣ
⁃ 👉የማዞር ወይም እራስን መሳት ካለ
⁃ 👉አየር ማጠር
⁃ 👉የደረት ህመም
⁃ 👉እራስ ምታት
⁃ 👉የጡንቻ መዛል
⁃ 👉የምጥ ስሜት (ከእምብርት በታች ወደታች ጫን የሚል ስሜት ካለ)
⁃ 👉ውሀ የመሰለ ፈሳሽ ከማህፀን ከወጣ

New life home based health care
0941050991 0928733047
hawassa

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis) ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ ...
10/10/2022

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis)

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ የብግነት በሽታ ሲሆን መገለጫውም በአንድ ጎን የሚከሰት የእጅና የእግር አንጓ ብግነት ነው ቀስ በቀስም አንጓዎችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው።

ከመገጣጠሚያ በተጨማሪ ሳንባን ፣ደምን፣ ቆዳንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ነው። በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚፈጠር ነው።

የሚያሳየው ምልክቶች
☘ ከአምስት በላይ በአንድ ጎን ያሉ አንጓዎች ህመም
👉 የአንጓ እብጠት
👉 ጠዋት ሲነሱ ሰውነትን ማጠፍ አለመቻል
👉 የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴ መቀነስ
☘ የድካም ስሜት
☘ አጠቃላይ የጡንቻ ህመም
☘ የክብደት መቀነስ

🍏 ከመገጣጠሚያ ውጪ ሲከሰት

👉 ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም
👉 የአይን እንባ መድረቅ፣ የዓይን ህመምና መቅላት
👉 ቆዳ ላይ እብጠት፣ መጥቆርና መቅላት
👉 የእግርና እጅ መደንዘዝ

🍏🍏🍎 የሚታዩ ምልክቶች🍏🍎🍏

👉 እብጠት
👉 ሲነካ ምንም
👉 የመገጣጠሚያ ጉዳት

🍏🍎🍏የሚሰጡ ምርመራዎች🍎🍏🍎

✍ ምርመራው በአብዛኛው ከታካሚው በሚወሰደው ተረክ እና ሀኪሙ በሚያየው ምልክቶች ይለያል በተለይ ከሌሎች የአንጓ ብግነት የሚለየው የጣቶቻችን የመጨረሻውን አንጓ ባለማጥቃቱ ነው።
✍ የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ (rheumatoid factor, anti -CCP , ESR/CRP, CBC)
✍ ራጅ ምርመራ

🍏🍎🍏 የሚሰጡ መድኃኒቶች 🍎🍏🍎

✍ የህመም ማስታገሻ
✍ የሪማቶይድ መድኃኒቶች (methotrexate, chloroquine phosphate, steroid) ፈጽሞ ያለሀኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለባቸሁም ምክንያቱም የጎንዮሽ ጉዳታቸው የከፋ ስለሆነ ከዛም ባሻገር ክትትል በየጊዜው መደረግ አለበት።

🍏🍎 ሪማቶይድ አንጓ ብግነት ያለበት ሰው ምን መመገብ የለበትም 🍎🍏
👉 አልኮል መጠጣት የለበትም
👉 ቀይ ስጋ
👉 ቅባት የበዛበት ምግብ
👉 ለስላሳ
👉 የእንስሳት ተዋጽኦ ( ወተት ፣ እርጎ ፣አይብ)
👉 ጨው የበዛበት ምግብ
👉 ስንዴ ገብስ እና
👉 በፋብሪካ የተቀናበረ ምግብ መውሰድ የለበትም።
New life home based
Call 0941050991
0928733047

10/10/2022

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis)

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ የብግነት በሽታ ሲሆን መገለጫውም በአንድ ጎን የሚከሰት የእጅና የእግር አንጓ ብግነት ነው ቀስ በቀስም አንጓዎችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው።

ከመገጣጠሚያ በተጨማሪ ሳንባን ፣ደምን፣ ቆዳንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ነው። በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚፈጠር ነው።

የሚያሳየው ምልክቶች
☘ ከአምስት በላይ በአንድ ጎን ያሉ አንጓዎች ህመም
👉 የአንጓ እብጠት
👉 ጠዋት ሲነሱ ሰውነትን ማጠፍ አለመቻል
👉 የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴ መቀነስ
☘ የድካም ስሜት
☘ አጠቃላይ የጡንቻ ህመም
☘ የክብደት መቀነስ

🍏 ከመገጣጠሚያ ውጪ ሲከሰት

👉 ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም
👉 የአይን እንባ መድረቅ፣ የዓይን ህመምና መቅላት
👉 ቆዳ ላይ እብጠት፣ መጥቆርና መቅላት
👉 የእግርና እጅ መደንዘዝ

🍏🍏🍎 የሚታዩ ምልክቶች🍏🍎🍏

👉 እብጠት
👉 ሲነካ ምንም
👉 የመገጣጠሚያ ጉዳት

🍏🍎🍏የሚሰጡ ምርመራዎች🍎🍏🍎

✍ ምርመራው በአብዛኛው ከታካሚው በሚወሰደው ተረክ እና ሀኪሙ በሚያየው ምልክቶች ይለያል በተለይ ከሌሎች የአንጓ ብግነት የሚለየው የጣቶቻችን የመጨረሻውን አንጓ ባለማጥቃቱ ነው።
✍ የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ (rheumatoid factor, anti -CCP , ESR/CRP, CBC)
✍ ራጅ ምርመራ

🍏🍎🍏 የሚሰጡ መድኃኒቶች 🍎🍏🍎

✍ የህመም ማስታገሻ
✍ የሪማቶይድ መድኃኒቶች (methotrexate, chloroquine phosphate, steroid) ፈጽሞ ያለሀኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለባቸሁም ምክንያቱም የጎንዮሽ ጉዳታቸው የከፋ ስለሆነ ከዛም ባሻገር ክትትል በየጊዜው መደረግ አለበት።

🍏🍎 ሪማቶይድ አንጓ ብግነት ያለበት ሰው ምን መመገብ የለበትም 🍎🍏
👉 አልኮል መጠጣት የለበትም
👉 ቀይ ስጋ
👉 ቅባት የበዛበት ምግብ
👉 ለስላሳ
👉 የእንስሳት ተዋጽኦ ( ወተት ፣ እርጎ ፣አይብ)
👉 ጨው የበዛበት ምግብ
👉 ስንዴ ገብስ እና
👉 በፋብሪካ የተቀናበረ ምግብ መውሰድ የለበትም።

New life home based health care
+251941050991 +251928733047

💥💥በኦፕሬሽን ስለመውለድ (Caesarean section) ማወቅ ያለብሽ ጠቃሚ ነጥቦች።💥💥📎 በኦፕሬሽን መውለድ (Caesarean section) - ማለት ከ28 ሳምንት በውሀላ ማደንዘዣ ተሰጥቶ...
08/10/2022

💥💥በኦፕሬሽን ስለመውለድ (Caesarean section) ማወቅ ያለብሽ ጠቃሚ ነጥቦች።💥💥

📎 በኦፕሬሽን መውለድ (Caesarean section) - ማለት ከ28 ሳምንት በውሀላ ማደንዘዣ ተሰጥቶ ልጅሽ እና ከልጅሽ ጋር አብሮት የነበረው የእንግዴ ልጅ በሆድሽ በታችኛው ክፍል ላይ በሚደረግ ትንሽ መቅደድ ልጅሽን ከማህፀን የማውጣት ወይንም የማስወለድ መንገድ ነው።

📎 በኦፕሬሽን መውለድ (Caesarean section) - በድንገተኛ ሁኔታ(Emergency CS) ወይም ደግሞ ለእናቲቱ ቀን ተቆርጦላት (Elective CS) ሊሰራላት ይችላል።

📎 አንዲት እናት በC/S እንድትወልድ ሊያረጓት የሚችሉ ነገሮች ብዙ ቢሆንም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው:-

📌📌 በእናቲቱ ምክንያት📌📌

👉በፊት ኦፕሬሽን መኖር
👉የማህፀን ጥበት
👉የእንግዴ ልጅ መድማት
👉የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት
👉የምጥ መድሀኒት ተሞክሮ አለመሳካት
👉የልብ, የአተነፋፈስ እና የመሳሰሉት ችግር ካለባት
👉ፅንሱን የሚከለክል እጢ ካለ ወይም የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወዘተ…

📌📌 በፅንሱ ምክንያት📌📌

👉ፅንሱ ከታፈነ
👉መንታ ሆኖ የመጀመሪያው ልጅ በጭንቅላቱ ካልመጣ (በጎን ወይም በቂጡ ከሆነ)
👉ከሁለት በላይ ፅንስ ካለ
👉እትብት በድንገት ከወጣ
👉የፅንሱ ኪሎ ከ4.5kg ለስኳር በሽተኞች እና 5 kg ለጤናማ እናት በላይ ሲሆን( በኛ ሀገር ፅንሱ ከ4 kg በላይ ከሆነ ትልቅ ይባላል፤ ለዛም በምጥ ማምጫ በማህፀን እንድትወልድ አይመከርም
👉ፅንሱ አመጣጡ ላይ ችግር ካለ (በጎን ከመጣ፣ በእግሩ ከመጣ፣ ጭንቅላቱ በሚፈለገው መንገድ ሆኖ ካልመጣ) ወዘተ…

📌 📌 የኦፕሬሽን የጎንዮሽ ችግር📌📌

📎 በኦፕሬሽን ጊዜ

👉 የማህፀን ቅድ ልጅ ሲወጣ መለጠጥ እና ቅዱ በመጨመር ያልተፈለገ አደጋ ማምጣት፣ የማህፀን ቧንቧ እና ወደ ፊኛ የሚወስድ የሽንት ቧንቧ መጎዳት፣

👉ልጅ ከወጣ በውሀላ ማህፀን ጠንክራ ደም ማቆም ሲገባት በጣም ስስ መሆን እና ደም አልቆም ማለት

👉ከሚሰጣት የማደንዘዣ መድሀኒት ጋር ተያይዞ የሚመጡ አደጋዎች።(ከወገብ በታችም ይሁን ሙሉ ማደንዘዣ)

📎 ከኦፕሬሽን በውሀላ

👉 ኢንፌክሽን መኖር ( የማህፀን ኢንፌክሽን፣ የቁስሉ መመርቀዝ እና መግል ማውጣት)

👉 የደም መርጋት

👉 ሆስፒታል ለተወሰነ ቀን መቆየት

👉 ኦፕሬሽን አንድ ጊዜ ከተደረገ በውሀላ ለቀጣይ የእንግዴ ልጅ ከፅንሱ ቀድሞ መምጣት፣ የእንግዴ ልጅ ኦፕሬሽን በተደረገበት ላይ መጣበቅ እና ወደ ማህፀን ግድግዳ ላይ ማደግ ይህም የሚቀጥለው ወሊድ ከባድ እና ደም መፍሰስ እንዲኖር እና እስከ ማህፀን መውጣት ማድረስ

👉 ቀጣይ እርግዝና ላይ ማህፀንና የሆዳችን ሽፋ መጣበቅ እና የአሁኑን ኦፕሬሽን ከባድ ማድረግ …

📌 📌በኦፕሬሽን በድጋሚ ልወልድ የምችለው ወይም የምገደደው ምን ነገር ከገጠመኝ ነው? 🤔🤔 📌📌

1. 👉ከአንድ በላይ በኦፕሬሽን ወልደሽ ከሆነ

2. 👉ፅንሱ ከ4 ኪ.ግ በላይ ከሆነ

3. 👉በፊት የተደረገልሽ ኦፕሬሽን ምክንያት የአሁኑ ሊሰራልሽ የተባለበት ምክንያት ከሆነ

4. 👉በፊት የተሰራልሽ በተረጋገጠ የማህፀን ጥበት ምክንያት ከሆነ

5. 👉ከዚህ በፊት በነበረሽ እርግዝና በምጥ ጊዜ የማህፀን መተርተር የገጠመሽ ከነበረ

6. 👉ሀኪምሽ በኦፕሬሽን መውለድ ያለውን ተጓዳኝ ጉዳት ከነገረሽ እና ከተረዳሽ በውሀላ ….አይ ቢሆንም በኦፕሬሽን ነው ምፈልገው የምትይ ከሆነ

7. 👉በፊት የተሰራልሽ ኦፕሬሽን classical cs ወይንም ልጁ የወጣው በላይኛውና በፊተኛው የማህፀን ግድግዳ ሆኖ በቋሚ ቅድ አይነት ሲሆን

8. 👉በፊት myoma ለተባለ የማህፀን እጢ(እባጭ) ኦፕሬሽን ከተሰራልሽ ፤ ይህም እጢው የማህፀንሽን ሙሉ ግድግዳ ይዞ የነበረ ከነበረ እናም ሀኪም ወደፊት በኦፕሬሽን ነው የምትወልጂው የሚል የተፃፈ ወረቀት ወይም በቃል ከተነገረሽ።

📌📌 በማህፀን አምጦ የመውለድ ጥቅሞች ከኦፕሬሽን አንፃር📌📌

👉 በማህፀን መውለድ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
👉 ለከፋ የደም መፍሰስ እድልን ይቀንሳል (ከcs አንፃር)
👉 የእናቲቱን ሆስፒታል ለህክምና የመቆየት ጊዜዋ ይቀንስላታል።
👉 እናቲቱ በወለደች ጊዜ በ30 ደቂቃ ውስጥ ያለምንም ችግር ልጇን ማጥባት መቻል
👉 ለተለያዩ የማደንዘዣ መድሀኒቶች የመጋለጥ እድልን መቀነስ እና ከወሊድ በውሀላ ሊመጣ የሚችል የማደንዘዣ መድሀኒት የጎንዮሽ ችግር አለመኖር
👉 በቀጣይ እርግዝና ላይ አሉታዊ ተፅዓኖ አለመኖር…

new life home base

"የህፃናት ጆሮ ኢንፌክሽን" - በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲማክዳ የተባለች እናት ልጄ በተደጋጋሚ ጆሮውን ይጎትታል ፣ ምክንያቱ ም...
14/09/2022

"የህፃናት ጆሮ ኢንፌክሽን" - በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ

ማክዳ የተባለች እናት ልጄ በተደጋጋሚ ጆሮውን ይጎትታል ፣ ምክንያቱ ምንይሆን? መፍትሄውስ የሚል ጥያቅ አድርሳናለች ።

በለጋ እድሜ ላይ ያሉ ህፃናት ጆሮዋቸውን መጎተት ከውስጥ ጆሮ ኢንፌክሽን (Otitis Media) አንዱ ምልክት ነው። የጆሮ ኢንፌክሽን በአብዛኛው በባክቴሪያዎችና በቫይረሶች አማካኝነት ይከሰታል።

እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት የ3ኛ አመት ልደታቸውን ከማክበራቸው በፊት ቢያንስ አንድ ጊዜ በዚህ ችግር እንደሚጠቁ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

እነዚህ ለጋ ህፃናት ያልዳበረ የበሽታ መከላከያ ስርአት ስለሚኖራቸውና እንዲሁም ኢስታችያን ቲዩባቸው (ጆሮን አአፍና አፍንጫ ጋር የሚያገናኝ ቱቦ) አግድም የሆነ በመሆኑ በተደጋጋሚ ለዚህ ችግር ይጋለጣሉ።

ሌሎች አጋላጭ የሆኑ ነገሮች
-አስተኝቶ ልጅን ማጥባት
-የእንጀራ እናት ጡጦን አብዝቶ መጠቀም
-የጣሳ (formula milk) ወተት መጠቀም
-በደይኬር ውስጥ መዋል
-ለሲጋራ ጢስ መጋለጥ
-በጉንፋን ህመም መያዝ እና የመሣሠሉት ናቸው።

የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክቶች
-ጆሮን መጎተት
-የጆሮ ህመም
-መነጫነጭ
-ትኩሳት
-ከጆሮ መግል ወይም ፈሳሽ መውጣት
- ትውከትና ተቅማጥ
-ማልቀስ ሊሆኑ ይችላሉ።
-በኦቶስኮፕ (ጆሮን በሚያሳይ መሣሪያ) የታምቡር ማበጥ መቅላት እንዲሁም ፈሳሽ መውጣት ሊታይ ይችላል።

ወላጆች እነዚህን ምልክቶች ካስተዋሉ በቶሎ ወደ ሀኪም ቤት በመውሰድ ልጃቸውን ማሣከም አለባቸው። ህፃናትን የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት ጡት ብቻ ማጥባት፣ ማስከተብ ፣ እንዲሁም ንፅህናን መጠበቅ የጆሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል ይጠቅማሉ።

በጊዜ ያልታከመ የጆሮ ኢንፌክሽን ለታምቡር መቀደድና ለማጅራት ገትር ለመስማት ችግር ሊዳርግ ስለሚችል ህክምናን በተገቢው ሰአት ማግኘት አለባቸው።
new life home based health care
0941050991 0928733047
hawassa

በዓልን በስራ (ድሁት) ላይ ሆናችሁ ከቤተሰብ ተለይታችሁ ህበረተሰባችሁን በማገልገል የምታሳልፉት ጤና ባለሙያዎች እንኳን አደረሳችሁ Happy new year ❤❤❤❤ጀግኖች ናችሁ
11/09/2022

በዓልን በስራ (ድሁት) ላይ ሆናችሁ ከቤተሰብ ተለይታችሁ ህበረተሰባችሁን በማገልገል የምታሳልፉት ጤና ባለሙያዎች እንኳን አደረሳችሁ Happy new year ❤❤❤❤ጀግኖች ናችሁ

Happy new year መልካም አድስ ዓመት 2015አድሱ ዓመት የስኬት የደስታና የጤንነት እዲሆንላቹሁ እንመኛለን ሰላም ለሀገራችን ።New life home based health care
10/09/2022

Happy new year
መልካም አድስ ዓመት 2015

አድሱ ዓመት የስኬት የደስታና የጤንነት እዲሆንላቹሁ እንመኛለን
ሰላም ለሀገራችን ።
New life home based health care

08/09/2022

ለአዲስ አመት የምስራች አለን ❤❤❤
በአሉን ምክንያት በማድረግ ነጻ የህክምና ክትትል
ከኒው ላይፍ የደም ግፍት ' የስኳር በሙሉ መሣሪያ በመታገዝ
እንሰጣለን ይደውሉልን ከጳጉሜ 3 እሰከ መስከረም 05/1/15

መልካም ዜና *ሀዋሳ ላይ ለምትገኙ ነዋሪዎች ኒዉ ላይፍ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ስራ ጀመረ ;;;;የትኛውም አይነት የህክምና ክትትል ያለባቸው ታካሚዎች ቤትዎ ድረስ መተን ለማከም ዝግጁ...
08/09/2022

መልካም ዜና *

ሀዋሳ ላይ ለምትገኙ ነዋሪዎች ኒዉ ላይፍ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ስራ ጀመረ ;;;;
የትኛውም አይነት የህክምና ክትትል ያለባቸው ታካሚዎች ቤትዎ ድረስ መተን ለማከም ዝግጁ ሆነን እጠብቃለን ይደውሉልን ።ኒዉ ላይፍ
ስልክ :0941050991 $0928733047
አድራሻ ታቦር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ አሮጌ ገበያ መሄጃ ላይ

Address

Around Tabor Primary School
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New life home based health care posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram