22/10/2025
ዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?
በእያያው አዲሱ
ሲኒየር ፊዚዮቴራፒስት
አብዛኛውን ግዜ ታካሚዎቻችን ወደ ሆስፒታላችን በሚመጡበት ሰዓት አብዝተው ከሚጠይቁን ጥያቄዎች መካከል አንዱ ዲስክ መንሸራተት አለብህ ተባልኩ ለመሆኑ ዲስክ (disc) ማለት ምን ማለት ነው?
ዲስኮች(disc) የምንላቸው በጀርባ አጥንቶቻችን መካከል እንደ እስፕሪንግ (Shock Absorption) ተግባር ይሰራሉ፤ ይህም ሰውነታችን በምናቀሳቀስበት ጊዜ የሚያጋጥሙንን ግፊቶች ይቀንሳሉ። ይህም ሰውነት ሲንቀሳቀስ እንደፈለገ እንዲተጣጠፍ ያግዛል፤ ሌላው የዲስኮች ተግባር በጀርባ አጥንቶች መካከል ያለውን ንክኪ ይጠብቃሉ (cushion)፤ ይህም አጥንቶቹ እርስበርስ እንዳይገናኙ ያደርጋል፡፡
ዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?
ዲስክ በውስጣቸው ለስላሳ ጄሊ (nucleus pulposus) እና ጠንካራ ውጫዊ ክብደት (annulus fibrosus) ያላቸው ሲሆን፣ ዲስክ መንሸራተት የሚከሰተው ይህ ውጫዊ ክፍል በሚጎዳበትና/ጫና በሚበዛበት ጊዜ ውስጣዊው ጄሊ ወደ ውጭ ስለሚፈስ የዲስክ ቅረፁ ይቀየራል/ይበላሻል። ይህም በአቅራቢያው ያሉ ነርቮችን (nerves) በመጫን ህመም፣ የእግር መደንዘዝ (numbness) ወይም የጡንቻ መስነፍን (weakness) ያስከትላል።
ዋና ምልክቶች (Symptoms) ምንድን ናቸው?
1ኛ፡ ከፍተኛ የጀርባ ህመም (በተለይ በታችኛው ወገብ Lumbar region)
2ኛ፡ የእግር መደንዘዝ ወይም የማቃጠል ስሜት (ብዙውን ጊዜ በአንድ እግር ላይ)
3ኛ፡ የእግር ጡንቻ መስነፍ
መፍትሔ
አብዛኛው የወገብ ህመም እንደ ፊዚዮቴራፒ ባሉ የህክምና ዘዴዎች ሊታከም ወይም ህመሙ እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል።
ለመመርመር እና ህክምና ለማግኘት በአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል መከታተል ይችላሉ።
እያያው አዲሱ
ሲኒየር ፊዚዪቴርፒስት