Bisirat Health Service Medium Clinic

Bisirat Health Service Medium Clinic keep in touch

07/11/2024
25/10/2024
23/10/2024
17/07/2024
03/06/2024

የሞሪንጋ/ሽፈራው ዛፍ ምንነትና ጠቀሜታው
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)


🍃የሞሪንጋ ዛፍ በኢትዮጵያ በተለምዶ ሽፈራው በሚል የሚታወቅ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ13 በላይ ዝርያዎች ያሉትና በሁለገብ ጠቀሜታቸው ከሚታወቁት ዛፎች መካከል አንዱ ነው።

🍃ይህ ዛፍ ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች መካከል ለምግብነት፣ ለመድሃኒትነት፣ ለውሃ ማጣሪያነት፣ ለእንስሳት መኖነትና ለንብ ቀሰምነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

🍃የሞሪንጋ ቅጠሎች በጣም ገንቢ እና በሚከተሉት የበለፀጉ ናቸው

• ቫይታሚን፡ ኤ፣ ሲ እና ኢ

• ማዕድናት፡ ካልሲየም፣ ፖታሲየም፣
ብረት እና ማግኒዚየም

• ፕሮቲኖች፡ ሁሉም ዘጠኙ አስፈላጊ አሚኖ አሲዶች

• አንቲኦክሲደንትስ፡- እንደ ኮሊነርጂክ አሲድ

🍃የሞሪንጋ የጤና ጥቅሞች

🍃በአንቲኦክሲደንትስ የበለጸጉ:

የሞሪንጋ ቅጠሎች በሰውነት ውስጥ የሚካሄዱትን ኢንፍላሜሽን ለመቋቋም የሚረዱ በርካታ ንጥረ-ምግቦችን ይይዛሉ።

🍃ፀረ-ብግነት(ኢንፍላሜሽን) ባህሪያት:
በሞሪንጋ ውስጥ ያሉ ውህዶች ፀረ-ብግነት(ኢንፍላሜሽን) ባህሪያት ስላላቸው እንደ አርትራይተስ እና የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎችን ለመከላከል ጠቃሚ ነው።

🍃የደም ስኳር መጠን መቀነስ:

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሞሪንጋ የደም ስኳር መጠንን ለመቀነስ ይረዳል ይህም የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ነው

🍃የኮሌስትሮል መጠንን መቀነስ:

ሞሪንጋ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ይረዳል ይህም የልብ በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል

🍃የልብ ጤናን ማሻሻል:

ሞሪንጋ የኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ የደም ግፊትን በመቆጣጠር ለአጠቃላይ የልብ ጤና አስተዋጽኦ ያደርጋል።

🍃የአዕምሮ ጤናን መደገፍ:

የሞሪንጋ አንቲኦክሲደንትስ እና ፀረ-ብግነት ባህሪያቶች የአንጎልን ጤና ለመጠበቅ እና የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባርን ለማሻሻል ይረዳሉ

🍃የበሽታ መከላከያዎችን ማጠናከር:

በሞሪንጋ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያጠናክራል።

🍃ምግብ እንዲፈጭ ይረዳል፡

ሞሪንጋ በአንጀት ውስጥ ያሉ ኢንፌክሽኖችን ለመቋቋም የሚያግዙ ፀረ-ባክቴሪያ እና ፀረ-ተህዋሲያን ባህሪያት ያለው ሲሆን በውስጡ ያለው ከፍተኛ የፋይበር ይዘት የምግብ መፈጨትን ይረዳል።

🍃የቆዳ ጤናን ማሻሻል:

በሞሪንጋ ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚን ኤ እና ኢ ለቆዳ ጤንነት አስተዋፅዖ ያደርጋሉ፣ ይህም የእርጅና ምልክቶችን በመቀነስ ጤናማ የቆዳ ቀለም እንዲኖር ያስችላል።

🍃ለአጥንት ጤና ይረዳል:

በካልሲየም፣ ፎስፈረስ እና እንደ ኤ፣ ሲ እና ኬ ያሉ አስፈላጊ ቪታሚኖች የበለጸገው ሞሪንጋ የአጥንት ጥንካሬን ይደግፋል።

የጤና ምክሮችን በሚከተሉት ማህበራዊ ገጾች ይከታተሉ

📌Facebook https://www.facebook.com/honeliat

📌Telegram https://t.me/drhoneliat

📌Instagram https://instagram.com/drhoneliat

ጤና ይስጥልኝ!

26/03/2024

ክፍቱን ያደረ ውሃ መጠጣት ጉዳት አለው?

በእንቅልፍ ሰአት ሰውነት ፈሳሽ ስለሚጠቀም ተጠምቶ መነሳት ይተለመደ ነው። ስንተኛ አጠገባችን አስቀምጠነው ክፍቱን ያደረ ውሃ ጧት መጠጣት የሚያስከትለው ችግር አለ?

ክፍቱን የቆየ ውሃ መጠታት አይመከርም። ውሃ ክፍቱን ሲያደር አቧራ፣ ቆሻሻ እና ተባዮች ሊገቡበት ይችላሉ። የጠጣንበትን የፕላስቲክ ውሃ ዘግተን ብናሳድር እንኳ ችግር ሊፈጠር ይችላል። ከፕላስቲክ ውሃ ስንጠጣ በቆዳችን የሚገኝ ላብ፣ አቧራ እና የቆዳ ሴሎች ከውሃው ጋር በመቀላቀል ውሃውን ያቆሽሻሉ። ምራቅ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎችም ወደ ውሃው ይገባሉ።

ማሳቹሴትስ የሚገኘው መርሲ ሜዲካል ሴንተር የሚሰራው ዶክተር ማርክ ሊቪ የሚከተለውን ይላል፦

“ውሃ ውስጥ የቆየ ባክቴሪያ ውሃውን ሊበክለው ይችላል። ደግመን ከዛው ፕላስቲክ ስንጠጣ ባክቴሪያውን መልሰን እንወስዳለን። ውሃን ከብርጭቆ ከጠጣን በኋላ እስኪታጠብ ደግመን ከዛው ብርጭቆ አለመጠጣት ይመከራል።”

ብዙ ግዜ የራሳችንን ባክቴሪያ መልሰን መውሰዳችን የጤና ችግር አይፈጥርብንም። ብዙ ሰዎች መልሰው መላልሰው ከአንድ ፕላስቲክ ወይም ብርጭቆ ይጠጣሉ። ንገር ግን የብርጭቆ ወይም የፕላስቲክ ውሃን ከሌላ ሰው ጋር መጋራት በፍጹም አይመከርም። በበሽታ ወይም በህክምና ምክንያት የሰውነት በሽታ መከላከል አቅማቸው የወረደ ሰዎች ውሃን ሁሌም በንጹህ ብርጭቆ መጠጣት አለባቸው።

መኪና ውስጥ የቆየ ውሃስ መጠጣት ችግር ያመጣል? ጸሃይ ላይ የቆየ ውሃ ሲሞቅ የባክቴሪያ መፈልፈያ ይሆናል። በተለይ አንዴ የጠጡበት ፕላስቲክ ከሆነ። ውሃውን ከወንበር ስር ማድረግ የጸሃይ ተጋላጭነቱን ቢቀንስም ባክቴሪያ ከመፍጠር አያድነውም።

አንዳንድ የፕላስቲክ አይነቶች ጸሃይ ሲነካቸው በትንሹም ቢሆን ፕላስቲኩ ወደ ውሃው መቀላቀል ይጀምራል። የአሜሪካ ምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር ወደ ውሃው የሚገባው የፕላስቲክ መጠን ለጤና እንደማያሰጋ ቢናገርም ጸሃይ ከመታው ፕላስቲክ ወሃ መጠጣት አይመከርም።

በማንኛውም ግዜ ውሃን ከጠርሙስ ወይም ከፕላስቲክ ቀጥታ ከመጠጣት ይልቅ ወደ ንጹህ ብርጭቆ ቀድቶ መጠጣት ይመከራል።

23/03/2024

ነስር
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡
ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል፡፡

1) ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)

• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡ ከፍተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይንም ማቆም ይቻላል፡፡

2) ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)

• ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይንት በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከሌላኛው የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡
ነስር በአብዛኛው በቅዝቃዜ ወቅት የሚከሰት ሲሆን ከ2 - 10 ዓመትና ከ50 - 80 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትንም ያጠቃል፡፡

✔️ ነስርን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

• በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት

• በተለያዩ የሕመም ወይንም
መድኃኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል

• የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነስር ነው፡፡

✔️ የነስር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• በአብዛኛው ደም የሚፈሰው በአንደኛው የአፍንጫ ቀዳዳ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ ካለ በሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች ደም ሊፈስ ይችላል፡፡ እጅግ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ደግሞ በጉሮሮ አድርጎ በአፍ በኩል ሊመጣ ይችላል፡፡

• ከፍተኛ የሆነ ድም መፍሰስ ሲኖር ራስ ማዞር፣ግራ የመጋባት እና ራስ መሳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

✔️ ነስርን እንዴት ማቆም ይቻላል?

• በመጀመሪያ ራስዎን ማረጋጋት

• ቀጥ ብለው መቀመጥ

• ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም)

• ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣትዎ እና በጠቋሚ ታትም ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት

• በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት

• ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት ናቸው፡፡

✔️ ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ የሚያቆም ካልሆነ

• በአጭር ጊዜ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነስርዎ ከሆነ

• ራስ ማዞር ወይንም ራስዎን የሚስቱ ከመሰለዎት

• የልብ ምትዎ የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ ከተቸገሩ

• ደም የሚያስመልስዎ ከሆነ

• በሰውነትዎ ላይ ሽፍታ ከኖረ

• ትኩሳት ካለዎት ናቸው፡፡

✔️ ሐኪምዎን ማማከር የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• በተደጋጋሚ ነስር የሚያስቸግርዎ ከሆነ

• ከነስር ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች መድማት የሚኖር ከሆነ

• በቀላሉ የመበለዝ ምልክቶች በሰውነትዎ ላይ ከተገኙ

• ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወሰዱ ከሆነ

• የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለዎት

• የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ ነው፡፡

✔️ነስርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

• በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ጊዜ ነው፡፡ ለነስር ተጋላጭ የሆኑ ከሆነ አፍንጫዎ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) በመጠቀም ማለስለስ ይችላል፡፡

• አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት

• የነስርዎ መነስዔ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪምዎን ማማከር የሚሰጥዎን የጤና ምክር መተግበር

• ሲጋራ ማጤስ አፍንጫን በማድረቅ ለነስር ስለሚዳርግ ማስወገድ ናቸዉ፡፡
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!

የጤና ምክሮችን በሚከተሉት ማህበራዊ ገጾች ይከታተሉ

📌Facebook https://www.facebook.com/honeliat

📌Telegram https://t.me/drhoneliat

📌Instagram https://instagram.com/drhoneliat

ጤና ይስጥልኝ!

Address

Addis Abeba
Bole
BULBULA

Telephone

251987271717

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bisirat Health Service Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Bisirat Health Service Medium Clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram