እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic

እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic አላማችን ህሙማን መርዳት ነው!!

25/10/2025

Watch, follow, and discover more trending content.

የጡት ካንሰር ምልክቶች!
25/10/2025

የጡት ካንሰር ምልክቶች!

🧬የቅድመ-ወር አበባ ቅምረ ህመም - Premenstrual syndrome (PMS) በዶ/ር በእምነት አየነውከወር አበባ በፊት እና ከኦቭሌሽን በኋላ (ከ5-7 ቀን) የሚከሰቱ ምልክቶች ሲሆኑ አብ...
22/10/2025

🧬የቅድመ-ወር አበባ ቅምረ ህመም - Premenstrual syndrome (PMS) በዶ/ር በእምነት አየነው
ከወር አበባ በፊት እና ከኦቭሌሽን በኋላ (ከ5-7 ቀን) የሚከሰቱ ምልክቶች ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የግለሰባዊ ግንኙነቶች እና መደበኛ እንቅስቃሴን ሲያስተጓጉል ይስተዋላል። የቅድመ-ወር አበባ (Premenstrual syndrome) ዓለም አቀፍ ስርጭት 47.8% ሲሆን 90% የሚሆኑት የመራቢያ ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ በሆነ ጊዜ ይጠቃሉ።
ይህ ሲንድሮም ትክክለኛ መንስኤ በትክክል ባይታወቅም እንቁላል ከወጣ በኋላ በሆርሞን ለውጦች ምክንያት እንደሚነሳሳ ይታመናል። ፕሮጄስትሮን ከ PMS ምልክቶች በስተጀርባ ያለው ዋና ምክንያት ነው።
🚦ምልክቶቹ
• ውጥረት ወይም ጭንቀት
• ድብርት
• ማልቀስ
• የስሜት መለዋወጥ እና ንዴት ወይም ቁጣ
• የምግብ ፍላጎት ለውጦች
• እንቅልፍ የመተኛት ችግር (እንቅልፍ ማጣት)
• ማህበራዊ ግንኙነትን ማቋረጥ
• ደካማ ትኩረት
• አጠቃላይ ህመም
• ማቅለሽለሽ
• ብጉር እና የአለርጂ ምላሾች
🎯መፍትሄ
• በቫይታሚን B6 ፣ ካልሲየም እና ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች ሊመከሩ ይችላሉ።
• ትራይፕቶፋን የያዙ ምግቦችን መመገብም ሊረዳ ይችላል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ የወተት ተዋጽኦዎች፣ አኩሪ አተር፣ ቱና እና ሼልፊሽ ናቸው።
• በወሩ ውስጥ ብዙ እንቅልፍ ለመተኛት ይሞክሩ።
• እንደ ውሃ ወይም ጭማቂ ያሉ ብዙ ፈሳሽ ይጠጡ። ለስላሳ መጠጦችን፣ አልኮልን ወይም በውስጡ ካፌይን ያለበትን (ቡና፣ ኮካ) ያስወግዱ።
• ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ የሚበላ ነገር ይኑርዎት። ነገር ግን ከመጠን በላይ አይብሉ።
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጡንቻን ማዝናናት እና የማያቋርጥ ማነቃቂያ መደጋገም ፣ ለምሳሌ በእያንዳንዱ እስትንፋስ ጊዜ “አንድ” የሚለው ቃል እየደጋገምን; ለ 10-20 ደቂቃዎች ልምምድ ማድረግ
• የግንዛቤ ባህሪ ሕክምና (Cognitive behavioral therapy) እና በሀኪም የሚታዘዙ መድሀኒቶችም ስለሚኖሩ አስጊ ደረጃ የሚደርስ (PMDD) ከሆነ ሀኪም ያማክሩ።
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!! በደስታ እናስተናግዶታለን!!
👇 መገኛችን
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት) እና ሌሎች
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

Thanks for being a top engager and making it on to my weekly engagement list! 🎉 Azeb Adane Azti, Selame Mesfin, Abinet A...
21/10/2025

Thanks for being a top engager and making it on to my weekly engagement list! 🎉 Azeb Adane Azti, Selame Mesfin, Abinet Adane, Temesgen Alemu

20/10/2025

.search.insight abinet kebede

🚫የጥንቃቄ መልእክት (Precautionary Message)🚫በእርግዝና ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩ ሃኪም ዘንድ በፍጥነት ቀርቦ መታየት ይገባዎታል፡፡🔺ደም መፍሰስ (Blooding)🔺ከባድ ማ...
20/10/2025

🚫የጥንቃቄ መልእክት (Precautionary Message)🚫
በእርግዝና ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩ ሃኪም ዘንድ በፍጥነት ቀርቦ መታየት ይገባዎታል፡፡
🔺ደም መፍሰስ (Blooding)
🔺ከባድ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ (Severe nausea and vomiting)
🔺የጽንሱ እንቅስቃሴ በጣም ከቀነሰ (If the fetal movement is very low)
🔺ዘጠኝ ወር ሳይሞላ የምጥ አይነት ህመም መሰማት (Feeling labor-like pain before the ninth month)
🔺የእንሽርት ውሃ መፈሰስ (Breaking of the amniotic fluid)
🔺ከባድ ወይም ድንገተኛ የሰውነት ማበጥ እንዲሁም ራስ ምታ (Severe or sudden swelling of the body and headache)
🔺ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል (pain when urinating)
ቸር እንሰምብት!!
#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡
ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
👇 መገኛችን
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
📞 0913295363
📞0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/@ #

በስቅታ( Hiccup) ይቸገራሉ ?ስቅታ የድምጽ ሳጥን ወይም ማንቁርት እና ዲያፍረም ድንገተኛ እና ፍቃደኛ ባልሆነ ሁኔታ በመጨማደድ የድምጽ አውታሮችን በድንገት በመዝጋት የሚፈጠር ክስተት ነው...
16/10/2025

በስቅታ( Hiccup) ይቸገራሉ ?

ስቅታ የድምጽ ሳጥን ወይም ማንቁርት እና ዲያፍረም ድንገተኛ እና ፍቃደኛ ባልሆነ ሁኔታ በመጨማደድ የድምጽ አውታሮችን በድንገት በመዝጋት የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡

በድንገት አየር ወደ ሳንባ መግባትና መዘጋት ‹‹ሂክ›› የሚል ድምጽ የሚፈጥረው ስቅታ መጠነኛ ከሆነ እምብዛም ችግር የማያስከትል ሲሆን የተራዘመ ስቅታ ግን የጤና ችግር ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ስቅታ ብታውን ጊዜ የሚመጣው በጨጓራ መታወክ ምክንያት ነው፡፡ አብዛኛው ጊዜ የሚነሳው ብዙ ምግብ በደንብ ሳያኝኩ በጥድፊያ ሲመገቡ ነው፡፡ በዚህም የጨጓራ መነፋት ያጋጥማል፡፡
ብዙን ጊዜ ስቅታ ያለምንም ሕክምና በጥቂት ደቂቃ ይጠፋል፡፡ ነገር ግን ከ2 ወራት በላይ የዘለቀ እንደሆነ ግን ከስትሮክ፣ ከጨጓራ ስግነት፣ ከሚጥል በሽታ፣ ከነርቭ መታወክና ከሌሎች በሽታዎች ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ እንዲሁም ስቅታ ሲበዛ ለእንቅልፍ እጦትና ለድባቴ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
ስቅታን ለመከላከል ወይም ለማቆም ቀጥሎ ያሉትን ጠቃሚ ምክሮች ከሚከተሎት ውስጥ አንዱን ይተግብሩ
1. በፍጥነት አይመገቡ፤ሲመገቡ ምግብ በደንብ አኝከው ይዋጡ፡፡
2. አልኮል አይጠጡ፡፡
3. ውጥረትና ኃይለኛ ስሜታዊነትን ይቀንሱ፡፡
4. ስቅታ ሲጀምሮ ቀዝቃዛ ውሃ ፉት ይበሉበት፡፡
5. አንኳር ስኳር ይዋጡ ወይም አንድ ማንኪያ ስኳር ይቃሙ፡፡
6. ሎሚ ይብሉበት፡፡
7. ስቅታው ሲጀምር የተወሰነ ሳይተነፍሱ ይቆዩ ፡፡
8. በውሃ ይጉመጥመጡ፤ ትንሽ ቆምጣጢ ቢጤ ካገኙ ይውሰዱ፡፡
9. ጨቀላ ሕፃን ስቅታ ከያዘው በጀርባው አስተኝተው በቀስታ ሆዱን ይጫኑ ወይም ይሹት፡፡
10. በወረቀት ከረጢት ውስጥ አፍንጫዎን እስከ አፎ ድረስ አስገብተው ለተወሰነ ደቂቃ በውስጡ ይተንፍሱ፡፡

ሁሌም አብሮን ስለሆኑ እናመሠግናለን!!Thank you being with us!ወድ የFacebook ወዳጆቻችን ገፃችንን follow, share!በማድረግ አገልግሎቶቻችን ለሁሉም እንድደርስ እንድት...
15/10/2025

ሁሌም አብሮን ስለሆኑ እናመሠግናለን!!
Thank you being with us!

ወድ የFacebook ወዳጆቻችን ገፃችንን follow, share!በማድረግ አገልግሎቶቻችን ለሁሉም እንድደርስ እንድትተሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃለን!!
አድራሻ፡ ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0913295363 / 0926268855 በመደወል ወይም
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/ በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

Big shout out to my newest top fans! Selame Mesfin, Temesgen Alemu
15/10/2025

Big shout out to my newest top fans! Selame Mesfin, Temesgen Alemu

Infantile colic (የጨቅላ ህፃን ቁርጠት) የእናት ጭንቀትስለ ጨቅላ ህፃን ቁርጠት ምን ያውቃሉ ??ቁርጠት (የህፃናት ኮሊክ) በተወሰነ ደረጃ ሚስጥራዊ የሆነ የስቃይ አይነት ነው፡፡ ቃ...
28/06/2025

Infantile colic (የጨቅላ ህፃን ቁርጠት) የእናት ጭንቀት
ስለ ጨቅላ ህፃን ቁርጠት ምን ያውቃሉ ??
ቁርጠት (የህፃናት ኮሊክ) በተወሰነ ደረጃ ሚስጥራዊ የሆነ የስቃይ አይነት ነው፡፡ ቃሉ ለማንኛውም ጤናማ ፣ ባግባቡ አየተመገበ ከ3 ሳምንታት ለሚበልጥ ግዜ በሳምንት ከ3ቀናት ለሚበልጥ ግዜ ለሚያለቅስ ህፃንን የሚመለከት ነው፡፡
ቁርጠት ቢያንስ ለ 3 ሳምንታት ያክል በሳምንት በላይ ለሆኑ ቀናት ከ3 ሰዓታት ለበለጡ ጊዜያት የጨቅላ ህፃን ማልቀስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ፡፡
ቁርጠት ህፃኑ በግዜው የተወለደ ከሆነ የ2 ሳምንታት እድሜ ሲሞላው የሚጀምር ሲሆን ግዜው ሳይደርስ የተወለደ ከሆነ ደግሞ ከ2 ሳምንታት በኋላ ሊከሰት ይችላል ፡፡
ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ከ3 ወይም ከ4 ወራት በኋላ በራሱ ግዜ ይተወዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ አራስ ልጆች ለሰዓታት ያለቅሱ እና ብስጩ ይሆናሉ ፡፡ አንድ ጨቅላ ህፃን ጤነኛ ሆኖ እያለ ለበርካታ ጊዜያት ብስጩ በጣም እየጮኸ የሚያለቅስ ከሆነ የምቾት ስሜት ሳይሰማው ሳምንቱን ሙሉ የሚያሳልፍ ከሆነ ፣ ቁርጠት የሚባለው ሁኔታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
የቁርጠት ምክንያት
የቁርጠት ትክክለኛው ምክንያት አይታወቅም ለዚህም ነው እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል ግልፅ መንገድ የሌለው፡፡
- ብዙውን ጊዜ እየዳበሩ በሚሄዱ ጡንቻዎች አያደገ የሚሄድ የምግብ መፈጨት ስርዐት
- በተዋሲያን መጠቃት
- ጋዝ - ወተት ሲጠባ አብሮት ወደ ሆዱ የሚገባ አየር (ጋዝ)
- የጨጓራ ህመምን የሚያስከትሉ ወይም ደስ የማይል ስሜት የሚያስከትሉ ሆርሞኖች
- ስሜታዊ የሆነ ህፃን
- አሁንም በማደግ ላይ ያለ የነርቭ ስርዓት
መፍትሄ
ምግብ በሚመገብበት ወቅት በተቻለ መጠን ቶሎ ቶሎ እንዲያገሳ ሙከራ ማድረግ
ልጁን በሆዱ በታፋዎ ላይ አስተኝተውት ጀርባውን ማሸት
ልጅዎትን በዥዋዥዌ መቀመጫ ላይ / በህጻናት መኪና መቀመጫ ላይ ያስቀምጡት ፡፡ እንቅስቃሴው እንዲሻለው ያደርገዋል፡፡
- የልጅዎ የሙቀት መጠን ከፍ ማለት ፣ በደምብ ምግብ አለመውሰድ ፣ ተቅማጥ ፣ ትውከት ፣ እንቅልፍ አለመተኛት ካለው ወዲያውኑ የጤና ባለሙያ ጋር መውሰድ አስፈላጊ ነው፡
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!! በደስታ እናስተናግዶታለን!!
👇 መገኛችን
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram