1. አመሠራረት
በ1954 ዓ.ም የሀዋሳ ክሊንክ በመባል በከተማ ፣ በክልሉ እና በሌሎች አስተዳደር አካላት እርዳታ የተገነባው የመጀመሪያ የጤና ተቋም ሲሆን በወቅቱ 2,695 የነበረውን የሀዋሳ ከተማ ማህበረሰብ እና ከአጎራባች ወረዳዎች የሚመጡ ተገልጋዮችን እንዲያገለግል በወቅቱ በነበረ ጠቅላይ ግዛት እንደተቋቋመ የታሪክ ድርሳናት ያስረደሉ፡፡
ጤና ተቋሙ ሲቋቋም ዋነኛ ዓላማ የወባ ስርጭት ለመቆጣጠር ሲሆን በወቅቱ ጤና ተቋሙ ስራ ባለመጀመሩ ከከተማ ውጪ ወደ ከተማ እየመጡ በባህላዊ ህክምና ህብረተሰቡን ሲያክሙ የነበሩ አቶ ማሞ የሚባሉ የአካባቢው ሀኪም(ጤና ረዳት) “Village doctor” ነበሩ ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ክልኒኩ በ4 ባለሙያዎች (በ1 ጤና መኮንን (HO) ፣ 1 ነርስ ፣1 የሕሳብ ሠራተኛ (Accountant) እና 1 ሹፌር) መደበኛ ተግባሩን ማካሔድ ሲጀምር የሀዋሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የሚለውን ሲያሜ በማግኘት ለከተማዋና አጎራባች ወረዳዎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ለዘመናት ከረመ ፡፡
2. አዳሬ በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህደት ውስጥ ምን ይመስል ነበር?
ይህ ጤና ተቋም ከክሊኒክ ደረጃ ወደ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ማደግ የራሱ የሆነ ሂደት እንዳለው ሁሉ የአዳሬ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሆኖ ሲያድግም የራሱ የሆነ ታሪክ ነበረዉ ፡፡ ይሄዉም በሰሜን አሜሪካን የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎች ማህበር (Ethiopian North American Health Professionals Association (ENAHPA)) በደቡብ ክልል የእናቶችና ሕፃናት ማዕከል (MCH) ለመገንባት ፍላጎት እንዳላቸው ለክልሉ ጤና ቢሮ ባሳወቁት መሰረት የክልሉ ጤና ቢሮም በዚህ ተቋም የነበረው የተሸለ አፈጻጸም ስለሆነ የሀዋሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያን በመጠቆሙ የ ENAHPA ልዑካንም ቡድን የጤና አጠባበቅ ጣቢያዉን የእናቶችንና ሕፃናት ማዕክል (Maternal child Health care service (MCH) center መሆን እንዳለበት በመወሰን የማዕከሉ የመሠረት ድንጋይ ጥቅምት 8/1999 ተጣለ፡፡
ከዚያም ይህ ተቋም የእናቶችና የሕፃናት ማዕከል ብቻ ከሚሆን በከተማ ውስጥ በቂ ሆስፒታል ባለመኖሩ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መሆን እንዳለበት በመወሰኑ ሙሉ ግንባታው ተጠናቆ 124 ሠራተኞችን በማቀፍ የካቲት 11/ቀን 2003ዓ/ም በክልሉ ርዕስ መስተዳደር ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
3. አዳሬ በአጠቃላይ ሆስፒታል ደረጃ ህደት ውስጥ ምን ይመስላል?
ታዲያ ይህ ተቋም ለ5 ተከታታይ ዓመታት በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሆኖ ለከተማዋንና ለአጎራባች ወረዳዎች ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቶ የሚሰጠው አገልግሎት ከደረጃው በላይ በመሆኑ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ በጤናና ጤና ነክ ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጠን ተመዝኖ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት በቂ ውጤት አምጥቶ በማሟላቱ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል እንዲሸጋገር በመወሰኑ ሆስፒታሉ በወቅቱ የነበረውን 305 ሁሉም አይነት ሠራተኞች በመያዝ ጥር 25/2008 ዓ.ም ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልነት ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል ተሸጋገረ ፡፡