Nigist Eleni Hospital-WCU

Nigist Eleni Hospital-WCU Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nigist Eleni Hospital-WCU, Hospital, Hossana.

Nigist Eleni Mohammed Memorial Comprehensive Specialized Hospital is Wachemo University's Medicine and Health Science College Hospital with almost all the specialities

29/11/2025
28/11/2025
ማርበርግ ቫይረስን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠህዳር 17/2018 ዓ.ም********//********በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕ...
26/11/2025

ማርበርግ ቫይረስን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ህዳር 17/2018 ዓ.ም
********//********

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማርበርግ ቫይረስን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ከሆስፒታሉ ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለተወጣጡ የጤና ባለሞያዎች ተሰጥቷል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ን/እ/መ/መ/ኮ/ስ/ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር እንዳለ ፍቅሬ እንደተናገሩት ቫይረሱን ለመከላከል የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው በተቋም ደረጃም የዝግጅት እና የቅድመ-ጥንቃቄ ስራዎችን መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

አክለውም ዶ/ር እንዳለ እንደገለጹት ህብረተሰቡን የሚያሰጋ የጤና ችግር ሲከሰት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር የሚሰራ ቢሆንም በተቋም ደረጃ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መስራት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የወሰዱ ባለሞያዎች የግንዛቤና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ህዳር 17/2018 ዓ.ም
ዘገባው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ ሆስፒታል ህዝብ ግንኙነት ነው።
Let Your light shine in the Society!!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የምሽት ገጽታ!!ሕዳር 16/2018 ዓ.ም*********//*******//***
25/11/2025

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የምሽት ገጽታ!!
ሕዳር 16/2018 ዓ.ም
*********//*******//***

24/11/2025

#ማስታወቂያ

21/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus ) ምንድነው?ህዳር 9/2018 ዓ.ም******//******በህዳር 5/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተወሰኑ ሰዎችን ያጠቃው የትኩሳት ደም መፍሰስ (Hem...
18/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus ) ምንድነው?
ህዳር 9/2018 ዓ.ም
******//******

በህዳር 5/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተወሰኑ ሰዎችን ያጠቃው የትኩሳት ደም መፍሰስ (Hemorrhagic Fever) ወረርሽኝ መንስኤው የማርበርግ ቫይረስ ሲሆን ስለቫይረሱ የተወሰኑ ሀሳቦችን እናነሳለን ።
የማርበርግ ቫይረስ እንዴት ይተላለፋል?

የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት የሚጀምረው በቫይረሱ ከተያዙ የሌሊት ወፎች እና አካባቢያቸው ወደ ሰው ሲተላለፍ ነው።
በሌሊት ወፍ ሽንት፣ ኩስ እና ምራቅ የተበከሉ ነገሮችም ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።
ቫይረሱ አንዴ ሰው ጋር ከደረሰ በኋላ ከሰው ወደ ሰው በቀጥታ ንክኪ ይተላለፋል።

ቫይረሱ የሚዛመተው ከታመመ ሰው ደም እና የሰውነት ፈሳሽ (ትውከት፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ ምራቅ፣ ላብ፣ የጡት ወተት፣ የብልት ፈሳሽ ወዘተ) ጋር በቀጥታ ንክኪ ነው።

በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተጠቀመባቸውን መርፌ፣ ቁሳቁሶች፣ የተነካኩ ልብሶች ወዘተ ቫይረሱን ያስተላልፋሉ። በግብረ ስጋ ግንኙነትም ይተላለፋል። አስከሬንም መንካት ቫይረሱን ያስተላልፋል።

የማርበርግ ቫይረስ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የማርበርግ ቫይረስ ህመም የመጀመሪያ ምልክቶች እንደሌሎች ቫይረሶች ሁሉ ጉንፋን መሰል እንደ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮ መቁሰል፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም እና ድካም ናቸው።

እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጠንከር ያለ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ እና የሆድ ህመም የመሳሰሉ የጨጓራና አንጀት ህመም ምልክቶች ያሳያሉ።
በመቀጠል በሽታው እየገፋ ከባድ ምልክቶች ይመጣሉ። በቆዳ ላይ፣ አፍና አፍንጫ ወይም የውስጥ የአካል ክፍል ላይ ደም መፍሰስ ያመጣል።
ህመሙ እየጸና ሲሄድ የደም ግፊት ከልክ በታች መቀነስ፣ የጉበት፣ ኩላሊት እና ሌሎችም የሰውነት ክፍሎቻችን ይጎዳሉ።
ሲብስም የብዝሃ-አካል መድካም ያመጣል።
በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ እስኪያገግሙ ድረስ ድካም፣ ቁርጥማት እና የስነ ልቦና ጫና ሊሰማቸው ይችላሉ።

የማርበርግ ቫይረስ ምርመራዎች

የቫይረስ ህመሙን ለማረጋገጥ የማረጋገጫ ምርመራ ያስፈልጋል - የቫይረሱን ዘረመል የሚለዩ ፕ ሲ አር ሞለኩዩላር ምርመራዎች ናቸው።

ማርበርግ ህክምና አለው?
ህክምናው በአብዛኛው የሚያካትተው የሰውነት ፈሳሽ በግሉኮስ መተካት፣ በባለሙያ ክትትል ማድረግ እና ተጓዳኝ ችግሮችን ማከም ላይ ያተኩራል። እንዳስፈላጊነቱ የትኩሳት ማብረጃ እና የህመም ማስታገሻ መስጠት ይገባል።
በጣም ደም መፍሰስ ላጋጠማቸው የደም ልገሳ ሊፈልጉ ይችላሉ።

የማርበርግ ቫይረስ መከላከል መንገዶች

በሽታው እንዳይዛመት ዋና መከላከያ መንገዱ በቫይረሱ የተጠረጠረን ሰው መለየት ነው።
በበሽታው ከተያዙ ግለሰብ የሰውነት ፈሳሾች ጋር ንክኪን ማስወገድ ይገባል።
የታመመን ሰው በቤት ለማከም ከመሞከር ይልቅ ወዲያዉኑ ወደጤና ተቋም ሄዶ እንዲታከም ማድረግ የተሻለ ነው።

እያንዳንዱ ሰው እጁን በአልኮል ወይም በሳሙና በደንብ በመታጠብ ንጽህና መጠበቅ አለበት።
ከታማሚ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን አልባሳት፣ እቃዎችና እና ምንጣፎችን በክሎሪን በረኪና ዘፍዝፎ ማጽዳት ይገባል።
ከጓንት እና ማስክ በተጨማሪ አይን እና ፊት መከላከያ ማድረግ ያስፈልጋል።
የተለያዩ ኤሮሶል ብናኞችን የሚፈጥሩ የህክምና ፕሮሲጀሮች ሲሰሩ የአየር ወለድ ጥንቃቄዎች (ለአብነትም N95 ማስክ) መተግበር አለባቸው። የመርፌ እና ሌሎች ቆሻሻ አወጋገድም ጥንቃቄ ይፈልጋል።

በቫይረሱ ምክኒያት የሞተ ሰው ቢያጋጥም በማህበረሰቡ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የቀብር ሥነ ሥርዓቶች መተግበር ይኖርበታል።

የማርበርግ ቫይረስ ምን ያህል አሳሳቢ ነው?

ማርበርግ ቫይረስ ታማሚው ላይ የሚያስከትለው የጤና ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም በጠንካራ የመከላከል እርምጃዎች መቆጣጠር እና መከላከል የሚቻል ህመም ነው።

የሚተላለፈው ከሰውነት ፈሳሾች ጋር በቅርበት በመነካካት እንጂ በገበያ፣ በአውቶብስ ወይም በመንገድ ላይ በቅጽበታዊ የሚተላለፍ አይደለም።

አሁናዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ማርበርግ እንደኮሮና ወይም ጉንፋን በቀጥታ አየር ወለድ ተላላፊ አይደለም።

የማርበርግ ተዛማችነቱ (transmission rate) መጠነኛ ነው።
ለምሳሌ ያክል አንድ በማርበርግ የተያዘ ሰው ቶሎ አስተላላፊ አለመሆኑ ሲሆን ይህ ባህሪው ተዛማችነቱን ይገታዋል።
ስለዚህ በጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርአት ስርጭቱን በቶሎ ማስቆም ይቻላል።

ዶ/ር ወርቁ አባገዳ
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የድንገተኛና ጽኑ-ህሙማን እስፔሻሊስት

ህዳር 9/2018 ዓ.ም
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ ሆስፒታል!!
Let Your light shine in the Society!!

Address

Hossana
42528

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nigist Eleni Hospital-WCU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category