በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office

  • Home
  • Ethiopia
  • Mito
  • በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office

በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office, Medical and health, ሚቶ ወረዳ, Mito.

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በሀይጅን ና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ስራ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻና ሞዴል ቀበሌዎችን ለመፍጠር የንቅናቄ መድረክ አካሄደ!የካቲት 27/2018 የሚቶ ወረዳ የመንግስት ኮ...
06/03/2026

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በሀይጅን ና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ስራ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻና ሞዴል ቀበሌዎችን ለመፍጠር የንቅናቄ መድረክ አካሄደ!

የካቲት 27/2018 የሚቶ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን

በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በሀይጅን ና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ስራ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻና ሞዴል ቀበሌዎችን ለመፍጠር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

በዕለቱም ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ ና ሞዴል ቀበሌያትን ለመፍጠር የተዘጋጀውን ሰነድ የጽ/ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ዋበላ አብዶ አቅርበው በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።

በዕለቱም መድረክ የተገኙት የሚቶ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ፎሌ ሞሳ እንዳሉት፦ጤና ለሁሉም ነገር ወሳኝ እንደሆነ አንስተው ጤናማ ና አምራች ዜጋን በመፍጠር የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን እውን ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም አካል ለተግባሩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት እና ጤና ለሁሉም ልማቶች መሰረት ስለሆነ ማህበረሰቡ ጤናውን በተገቢው መጠበቅ እንዳለበት ገልጸዋል።

ሞዴል መጸዳጃ ቤቶችን በመገንባት ሞዴል ቀበሌያትን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት በቁርጠኝነት ና በትኩረት መስራት እና ማህበረሰቡ በሁሉም የልማት ስራዎች ላይ ውጤታማ እንዲሆን መጀመሪያ ጤናው እንዲጠበቅ ሚናውን በሚገባ መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤተረ ኃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን በበኩላቸው እንደገለጹት፦የማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በጤናው ዘርፍ ላይ ከባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ በመስራት ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር በልዩ መልኩ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ በማድረግ ሞዴል ቀበሌያትን መፍጠር የማህበረሰቡን ጤና በተገቢው ለመጠበቅ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

የማህበረሰቡን ጤና በተገቢው ለመጠበቅ እና አካባቢዎችን ከውጭ ከመጸዳዳት ነጻ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው በባለቤትነት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በሚቶ ወረዳ የላብራቶሪ ባለሙያዎች የክህሎት ማሻሻያ ስልጠና ተካሄደ።        የካቲት 26/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ ቁልፍ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎ...
05/03/2026

በሚቶ ወረዳ የላብራቶሪ ባለሙያዎች የክህሎት ማሻሻያ ስልጠና ተካሄደ።

የካቲት 26/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ ቁልፍ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች መካከል አንዱ ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የሆነ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ህብረተሰብ ማድረስ ነው።

ይህንን ግብ ለማሳካት የጤና ባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ እና የጤና ተቋማትን አቅም ማጠናከር በጣም አስፈላጊ ነው።በዚህ መሠረት በቀን 26/06/2018 ዓ.ም በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በሚቶ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የሚሰሩ የላብራቶሪ ባለሙያዎችን ክህሎት ለማሳደግ ያለመ የሥራ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው ከጦራ ሆስፒታል በመጡ የላብራቶሪ ባለሙያዎች በተለያዩ የላብራቶሪ ሥራ መስኮች ላይ ተግባራዊና ንድፈ ሀሳብ የተያያዙ ስልጠናዎችን በመስጠት ተካሂዷል።

በስልጠናው ውስጥ በተለይም የላብራቶሪ ምርመራ ትክክለኛ አፈፃፀም፣ የጥራት ቁጥጥር ሂደቶች፣ የምርመራ ውጤት አያያዝ እና የታካሚዎች ደህንነት ዙሪያ ጠቃሚ ትምህርቶች ተሰጥተዋል። ይህም በጤና ጣቢያው ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች አቅም እንዲጠናከር እና ትክክለኛና ጥራት ያለው የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት እንዲሰጡ በከፍተኛ ደረጃ ይረዳል።

በአጠቃላይ ይህ ዓይነቱ የክህሎት ማሻሻያ ስልጠና በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል፣ የባለሙያዎችን ብቃት ለማጠናከር እና ለህብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

የሚቶ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ከድር መሀመድ 1447ኛው ታላቁ የረመዳን ወርን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!!የካቲት 10/2018ዓ.ም የሚቶ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬ...
17/02/2026

የሚቶ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ከድር መሀመድ 1447ኛው ታላቁ የረመዳን ወርን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!!

የካቲት 10/2018ዓ.ም የሚቶ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

የሚቶ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ከድር መሀመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳቹ!! አደረሰን!! በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ ከድር ታላቁ የረመዳን ፆምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለፁት ታላቁ የረመዳን ወር የመደጋገፍ፣ የመዋደድ፣ የተቸገሩትን የመርዳት እንዲሁም የመተዛዘንና የይቅር ባይነት ዕሴቶቻችን ይበልጥ የምናጠናክርበት ወር በመሆኑ ይህንኑ በመተግበር ልናሳልፈው ይገባል ብለዋል።

የእስልምና ሀይማኖት የደጋገፍ የመተባበር የእዝነትና አንድነትን በማጠናከር ረገድ ያለው ህግጋት የሚታወቅ ስሆን መላው የወረዳው ህዝብ የጀመረውን የማዕድ ማጋራት አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብለዋል።

የዘንድሮውን የረመዳን ፆም በማስመልከት ለወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ባስተላለፊት መልዕክት ወቅት ረመዳን የምህረት ወር በመሆኑ ፀሎትን በማጠናከር፣ በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት እንዲያበዙ ና በሰው ተኮር ሀይማኖታዊ ትዛዛት በመፈፀም ማሳለፍ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚጠበቅ መሆኑን አቶ ከድር መሀመድ ገልፀዋል።

እንደሚታወቀው የረመዳን ፆም በዓመት አንድ ጊዜ በመጠበቅ የሚተገበር በመሆኑ እንኳን አደረሰን!! አደረሳችሁ በማለት የፍቅር፣ የመቻቻል፣ የመተባበርና የመልካም ፀሎት ጊዜ እንዲሆንልን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

በድጋሚ ለ1447ኛው ለታላቁ የረመዳን ወር እንኳን በሰላም አደረሳቹ!!ረመዳን ሙባረክ!!

የሚቶ  ጤና አጠባበቅ ጣቢያ  የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የEPAQ 2nd cycle Bridge Document መድረክ አካሄደ። የካቲት 6/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)...
13/02/2026

የሚቶ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የEPAQ 2nd cycle Bridge Document መድረክ አካሄደ።

የካቲት 6/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

በሚቶ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የEPAQ 2nd cycle Bridge Document መድረክ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩም የሚቶ ጤና አጠ/ጣቢያ በ6 ወሩ የተሠሩ የReform,KPI,EPHCG Implementation በጋራ መገምገም፣ እና አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን እና ዋና ዋና ተግባራትን ተገምግሟል።

በተጨማሪም የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ እና የልምድ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን በመጨረሻም የነበሩ ውስንነቶችን ለማስተካከል መግባባት ላይ ተደርሶ የቀጣይ መድረክ ቀጠሮ እና ቦታ በማምረጥ ተጠናቆዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተሻለ ደሳለኝ;የሁለቱም ጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጆች;እና የኬዝ ቲም አስተባባሪወች ተገኝተዋል።

የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ።የካቲት 05/2018 ዓ.ም(የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት) በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ጤናና ጤናነክ አገልግሎቶች እና ግ...
12/02/2026

የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ።

የካቲት 05/2018 ዓ.ም(የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ጤናና ጤናነክ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ስራ ሂደት ወረዳው ላይ በሚገኙ የጤና ነክ ተቋማት ላይ የጤና ቁጥጥር እየካሄደ ይገኛል።

የቁጥጥር ስራዉ ከወረቀት ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በቴክኖሎጂ የታገዘ ሲሆን የጤና ነክ ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ደህንነቱ እና ጥራቱ የተረጋገጠ እንዲሆን እና ከወጣላቸዉ ሀገራዊ ስታንዳርድ አንጻር ደረጃቸዉን እንዲያሻሽሉ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።

የጤና ነክ ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚያቀርቡት አገልግሎት በተጠቃሚው ማህበረሰብ ጤና ላይ አሉታዊ ጉዳት እንዳያደርሱ መስሪያ ቤቱ ከተቆጣጣሪዎች ጋር በመሆን ለተቋማት ሀገራዊ ስታንዳርዶችን የማስተዋወቅ ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በየጊዜዉ የቁጥጥር ስራዎችን በማድረግ በሚገኙ ግኝቶች መነሻ አስተማሪ የሆኑ እርምጃዎችን እየወሰደ ቆይቷል።

ተገልጋዩ ማህበረሰብ የሚያገኘዉን አገልግሎት ደህንነትና ጥራት እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ ተገቢዉን የብቃት ማረጋገጫ ስለመያዛቸዉ ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ማንኛዉም አጠራጣሪ ነገር በሚያገኝበት ወቅት በአቅራቢያዉ ለሚገኙ የጤና ተቆጣጣሪዎች ማሳወቅ ይጠበቅበታል።

የጤና ነክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወጣላቸዉን አስገዳጅ ሀገራዊ ስታንዳርድ ለማሟላት በየጊዜዉ በሚደረጉ የቁጥጥር ስራ ግብረመልሶችን ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የቁጥጥር ስራዉም ዉጤታማ እንዲሆን የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል። በየደረጃ ያለዉ የጤና ነክ ተቋም የቁጥጥር ስራዉን በባለቤትነት እንዲተባበሩ ጤና ጽ/ቤቱ ያሳሰበ ሲሆን የባለድርሻ አካላት ሚናም የጎላ መሆኑ ተገልጿል።

የተጀመረዉ የቁጥጥር ስራ ለተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የሚጠበቀዉን ዉጤት ማስመዝገብ እንዲችል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

 #የደምበዬ ተድበበሎት በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ለስልማ የደንበዬ ቻሌንጅ 1.በጽ/ቤት ባለሙያ የተሰበሰበ=7,0002.በጤና ባለሙያና በጤና ኤክስቴንሽን የተሰበሰበ=19,3003.በመካከለኛ ክሊ...
10/02/2026

#የደምበዬ ተድበበሎት በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ለስልማ የደንበዬ ቻሌንጅ
1.በጽ/ቤት ባለሙያ የተሰበሰበ=7,000
2.በጤና ባለሙያና በጤና ኤክስቴንሽን የተሰበሰበ=19,300
3.በመካከለኛ ክሊኒክ የተሰበሰበ=50,000
4.በመጀመሪያ ደረጃ ክሊኒክ የተሰበሰበ=15,000
5.በመድሃኒት መደብሮች የተሰበሰበ=9,000
ጠቅላላ ድምር=100,300 ብር ገቢ በማድረግ የስልጤ ልማት ማህበር(ስልማ) ገቢ ማሰባሰቢያ ቻሌንጅ በይፋ ተቀላቅለዋል።

❗️

👉 ሀደ በሆኒ ቀለም ቢዮኒ ሀደም ኢሎኒ ሀደ በሎኒ በላም ቢዮኒ ሀደም ኢላኒ።

#የጋራ ቤታችንን፣ የአንድነታችን መሶሶ የሆነውን የስልጤ ልማት ማህበርን ለማጠናከር ሁላችንም እንተባበር፣ እናስተባብር፣ እናቋቁም፣ የሀገርና የህዝብ ዋልታና መከታ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣ መልዕክታችን ነው።

#ቻሌንጁን እንቀላቀል፤ ለትውልድ የማይነጥፍ አሻራችንን እናኑር።
- 1000282156974 የስልጤ ባህል ማዕከል ግንባታ።

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ በሚቶ ወረዳ በመገኘት ከጽ/ቤት እስከ ማህበረሰብ ድረስ በመውረድ ድጋፍና ክትትሉን በማጠናቀቅ ግብረ መልስ መሰጠቱን ተገለፀ ።ጥር 26/2018 ዓ.ም(የሚቶ ወረዳ ጤና...
03/02/2026

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ በሚቶ ወረዳ በመገኘት ከጽ/ቤት እስከ ማህበረሰብ ድረስ በመውረድ ድጋፍና ክትትሉን በማጠናቀቅ ግብረ መልስ መሰጠቱን ተገለፀ ።

ጥር 26/2018 ዓ.ም(የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹን ስድስት ወራት የተቀናጀ ሁሉ አቀፍ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ድጋፍና ክትትሉን በማጠናቀቅ ግብረ መልስ ተሰጥቷል።

ግብረ መልሱን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ድጋፍና ክትትል የተመራው ቡድን በወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ተገኝተው ግብረ መልስ መስጠት ችለዋል።

በዚህም በድጋፍና ክትትል ወቅት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል፣ደካማ ጎኖችን በመቅረፍ፣እንድሁም ቀጣይ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና መግባባት በመቻል ተጠናቋል።

በመድረኩም የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን፣የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ዋበላ አብዶ ፣የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ የድጋፍና ክትትል ቡድን እና የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የማኔጅመንት አካላት ተገኝተዋል።

የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና የቲቢ በሽታን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ !!!ጥር /16/2018ዓ.ም(የሚቶ ኮሙኒኬሽን )በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ6 ወር ዕቅድ አፈ...
24/01/2026

የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና የቲቢ በሽታን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ !!!

ጥር /16/2018ዓ.ም(የሚቶ ኮሙኒኬሽን )

በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና የቲቢ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያለመ የንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል ።

በመድረኩ የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን፣የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ዋበላ አብዲ፣የተቋሙ ማኔጀመንትና ባለሙያዎች ፣የጤና ጣቢያ ሃለፊዎች፣የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩም የ6 ወር የእናቶችና ህፃናት ሪፖርት በወ/ሪት ለይላ ክምሰሮ ፣የ6 ወር በሽታ መከላከል ሪፖርት በአቶ ተሻለ ደሳለኝ እና የቲቢ የንቅናቄ ሰነድ በአቶ ግዛቸው ብሻዉ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል።

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የፋርማሲ አገልግሎትን ከማዘመን አንፃር፣ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና አጠባበቅ ዙሪያ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተገልጿል።

ቀልጣፋና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በመስጠት የወላድ እናቶችን ሞት መቀነስ ፣ጤና መድህን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣ የበሽታ የመከላከል ስራ፣የHIV ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ተግባር ፣የጤና ተቋማትን ፅዱ ለተገልጋይ ምቹ ከማድረግ አንፃር ፣ተላላፊ ያልሆኑ ስኳር ግፊት በመከላከል ስራዎች የተሰሩ መሆኑ ተገልፆዋል።

የTB (tuberculosis) በሽታ በቀላሉ በህክምና መዳን የሚችል በሽታ በመሆኑ የትኛውም አይነት ሳል ያለበት ሰው ወደ ጤና ጣቢያ በመሄድ ምርመራ ማድረግ እንዳለበት መልዕክት የተላለፈ ሲሆን ለሚደረገው የቲቢ ምርመራና ህክምና ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው ተጠቁሟል።

በሽታውን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር ማህበረሰቡ በወባ መከላከል እና ማስወገድ ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፣ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር፣ ህብረተሰቡ አጎበርን በአግባቡ እንዲጠቀምና ላልተገባ አላማ እንዳያዉል በማድረግ እና ህብረተሰቡ ለቲቢ በሽታ ተገላጭ እንዳይሆን የግልና የአካባቢን ንፅህናን በመጠበቅ ጤንናቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ድጋፍ መድረግ እንደለበት ተገልጿል።

ከዘመቻው ጎን ለጎን የወባ መከላከልና ህክምና፣ የህፃናት የስነ-ምግብ እጥረት ክትትል፣ የእናቶች ጤናና ሌሎች ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ የጤና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን አክለው ተነግረዋል ።

በወረዳው የቲቢ በሽታ ንቅናቄ ዘመቻው ከሰኞ ጀምሮ የሚጀመር ሲሆን ባለፉት ግዜያት ህክምና ያልጀመሩ የቲቢ በሽታ ታማሚዎችን በማከም እና የማካካሻ ስራ በመስራት ማህበረሰቡን መታደግ እንደሚያስፈልግ በንቅናቄው መድረክ መግባባት ላይ በማድረስ መድረኩ ተጠናቋል።

ታላቅ ጨዋታ በዛሬው ዐለት !ከጠዋቱ 5:00 ላይ !  _Vs_አልቾ_ዊሪሮ_ወረዳ ጨዋታው ሊጀምር ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይቀሩታል ጥሎ ለማለፍ በወራቤ እስታዲየም ይፋለማሉ !ለወረዳችን እግር ኳስ ...
19/01/2026

ታላቅ ጨዋታ በዛሬው ዐለት !

ከጠዋቱ 5:00 ላይ !

_Vs_አልቾ_ዊሪሮ_ወረዳ

ጨዋታው ሊጀምር ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይቀሩታል

ጥሎ ለማለፍ በወራቤ እስታዲየም ይፋለማሉ !

ለወረዳችን እግር ኳስ ቡድን መልካም እድል ተመኘን!

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ 05 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና ወቅታዊ የጤና የንቅናቄ ተግባራት እየገመገመ ነው፡፡መምሪያው በዛሬው እለትም ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ባለድረሻ አካላት ጋር የ2018 በ...
27/12/2025

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ 05 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና ወቅታዊ የጤና የንቅናቄ ተግባራት እየገመገመ ነው፡፡

መምሪያው በዛሬው እለትም ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ባለድረሻ አካላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት 05 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ጨምሮ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ተግባራትና ወቅታዊ የጤና የንቅናቄ አጀንዳዎች እየገመገመ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሀይራዲን እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተያዙ ቁልፍ ተግባራት ላይ የግብ ስምምነት መፈጸሙን አንስተዋል፡፡

ከዚህ መነሻ እስካሁን የተፈጸመባት አግባብና በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮች ለመገምገም ያለመ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማረጋገጥ ከልቻልን የጤና ተግባራት ማሳካት አይቻልም ያሉት ኃላፊው በተለይም የጤና ኢክስቴንሽን ፍኖታ ካርታ መሬት ከማውረድ አንጻር በልዩነት ይታያል ብለዋል፡፡

የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማስፋፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊ በተለያዩ መዋቅሮች የተጀመረው የማህበረሰብ ፋርማሲ ፣የጤና ተቋማት ግንባታና ማስፋፊያ ስራዎችን በአብነት ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለጻ ማህበረሰቡን ቀረብ ብለን አድምጠን በጤናው ዘርፍ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ የጋራ መግባባት ከፈጠርን ህዝቡ ማገዝና መደገፍ እንደሚችል በአንዳን መዋቅሮች የተጀመረው ንቅናቄ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

መንግስት የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ጤና መድህን አሰራር መዘርጋቱን የጠቆሙት ኃላፊው ተግባሩ በተቀመጠው ግዜ እንዲሳካ ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የሁለተኛው ዙር የትራኮማ በሽታ መከላከያ (ዚትሮማክስ) መድሀኒት እደላ የ4ኛ ቀን ውሎ አፈጻጸም የቀበሌ ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት ገመገመ።     ታህሳስ 13/2018...
22/12/2025

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የሁለተኛው ዙር የትራኮማ በሽታ መከላከያ (ዚትሮማክስ) መድሀኒት እደላ የ4ኛ ቀን ውሎ አፈጻጸም የቀበሌ ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት ገመገመ።

ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም -(የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

የትራኮማ መከላከያ መድሀኒት ዕደላው በወረዳው ባሉት በሁሉም ቀበሌዎች ከ6 ወር እስከ 9 ዓመት ታላሚ ያደረገ ዘመቻ እስከ አራተኛው ቀን ውሎ 16,542(93%) ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን እስከ አ4ኛው ቀን ውሎ 6 ሰዎች የአይን ቆብ ሽፋሽፍት መቀልበስ ያለባቸው ሰዎችን ልያታ የአይን ሞራ ግርዶሽ 51 ሰዎች ልያታ TB/ቲቢ ምርመራ 9 መለየት ተችሏል።
በዘመቻው የነበሩ ጠንካራና በጉድለት የተለዩ ተግባራትን በዝርዝር መገምገም ተችሏል።

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን እንደገለፁት በየደረጃው ያሉ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ጉድለቶችን ደግሞ በማስተካከል ዘመቻውን በውጤታማነት እየተከናወነ የተሰራ መሆኑ አበረታች ነው ብለዋል።

አያይዘውም በቀሪ ቀናቶች ጥራት ባለው ሁኔታ እና በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የመድሀኒት እደላ አፈፃፀሙን መሰረት በመድረግ ታላሚ ህብረተሰብ ክፍሎች መድረስ እንደሚገባ የገለፁት ሃላፊው የተሰሩ ስራዎችን መመዝገብና መደራጀት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የፅ/ቤቱ ም/ሃላፊ አቶ ዋበላ አብዶ እንዳሉት ለወረዳው ከ6 ወር እስከ 9 ዓመት ታላሚ ህፃናት የትራኮማ በሽታ መከላከያ መድሀኒት እደላ በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።



page
👇👇👇??👇👉
https://www.facebook.com

የሚ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የሁለተኛው ዙር የትራኮማ በሽታ መከላከያ (ዚትሮማክስ) መድሀኒት እደላ የ3ኛ ቀን ውሎ አፈጻጸም የቀበሌ ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት ገመገመ።     ታህሳስ 12/2018...
21/12/2025

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የሁለተኛው ዙር የትራኮማ በሽታ መከላከያ (ዚትሮማክስ) መድሀኒት እደላ የ3ኛ ቀን ውሎ አፈጻጸም የቀበሌ ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት ገመገመ።

ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም -(የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

የትራኮማ መከላከያ መድሀኒት ዕደላው በወረዳው ባሉት በሁሉም ቀበሌዎች ከ6 ወር እስከ 9 ዓመት ታላሚ ያደረገ ዘመቻ እስከ ሶስተኛው ቀን ውሎ 14,190(80%) ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን እስከ 3ተኛው ቀን ውሎ 5 ሰዎች የአይን ቆብ ሽፋሽፍት መቀልበስ ያለባቸው ሰዎችን ልያታ የአይን ሞራ ግርዶሽ 47 ሰዎች ልያታ TB/ቲቢ ምርመራ 7 መለየት ተችሏል።
በዘመቻው የነበሩ ጠንካራና በጉድለት የተለዩ ተግባራትን በዝርዝር መገምገም ተችሏል።

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን እንደገለፁት በየደረጃው ያሉ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ጉድለቶችን ደግሞ በማስተካከል ዘመቻውን በውጤታማነት እየተከናወነ የተሰራ መሆኑ አበረታች ነው ብለዋል።

አያይዘውም በቀሪ ቀናቶች ጥራት ባለው ሁኔታ እና በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የመድሀኒት እደላ አፈፃፀሙን መሰረት በመድረግ ታላሚ ህብረተሰብ ክፍሎች መድረስ እንደሚገባ የገለፁት ሃላፊው የተሰሩ ስራዎችን መመዝገብና መደራጀት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የፅ/ቤቱ ም/ሃላፊ አቶ ዋበላ አብዶ እንዳሉት ለወረዳው ከ6 ወር እስከ 9 ዓመት ታላሚ ህፃናት የትራኮማ በሽታ መከላከያ መድሀኒት እደላ በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በመጨረሻም በዘመቻው በቀሪ ቀናት በየክላስተሩ መሰራት ያለባቸው ተግባራትን በማስቀመጥ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የመረጃ ገፆችን በመከታተል ስለጤናና ጤና ነክ ተጨማሪ ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት፦

page
👇👇👇??👇👉
https://www.facebook.com

የሚ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት

Address

ሚቶ ወረዳ
Mito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share