Care Land General Hospital

Care Land General Hospital 🕹️Furi Sub-city, Shagar ( on the main road from Ayertena to Alemgena, adjacent to GM furniture)

የጨጓራ ባክቴሪያ ይህ ባክቴሪያ ጨጓራ ውስጥ የሚኖር ሲሆን በአንዳንድ ምክንያቶች መኖር ካለበት በላይ ሲሆን የጨጓራ ህመም ያስከትላል፡፡ ባክቴሪያው ቁስለት በሚፈጥርበት ወቅት የበሽታው ምልክቶ...
31/12/2025

የጨጓራ ባክቴሪያ
ይህ ባክቴሪያ ጨጓራ ውስጥ የሚኖር ሲሆን በአንዳንድ ምክንያቶች መኖር ካለበት በላይ ሲሆን የጨጓራ ህመም ያስከትላል፡፡ ባክቴሪያው ቁስለት በሚፈጥርበት ወቅት የበሽታው ምልክቶች መታየት ይጀምራል፡፡በሽታው ሁል ጊዜ ያለ ባይሆንም ሄድ መጣ የሚል ምልክት ነው ያለው፡፡
የጨጓራ ባክቴሪያ መንስኤዎች
• ከምንበላው ምግብ
• ከምንጠጣው ውሃና
• ከምንጠቀማቸው በባክቴሪያው ከተበከሉ ቁሶች በተፋፈገ ቦታ(ትራንስፖርት ፣ብዙ ሰው ያለበት ወዘተ) የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች
• የሆድ መነፋት ስሜት
• ከሁል ጊዜው የበለጠ ግሳት
• የረሃብ ስሜት አለመሰማት(የምግብ ፍላጎት ማጣት)
• ማቅለሽለሽ
• ማስመለስ
• የሰውነት ክብደት መቀነስ እና
• ቃር ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
ከባድ የሚባሉት የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች
• የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ
• ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን
• ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን
• የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን
• የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ
• ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል ሀኪም ዘንድ መታየት አስፈላጊ ነዉ!!
የጨጓራ ባክቴሪያ መከላከያ መንገድ
• እጅን በሳሙና ከምግብ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ በደንብ መታጠብ
• በፅዱ ሁኔታ ያልተዘጋጀ ወይም የቀረበ ምግብና መጠጥ አለመጠቀም
• ያልበሰሉ ምግቦችን አለመጠም
• ጭንቀትና ውጥረት ማስወገድ
• ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን አለመመገብ
• በቂ ዉሃ መጠጣት
• ሲጋራ ማጨስ ማስወገድ
• በሀኪም የተሰጡ መድሀኒቶችን ባግባቡ መውሰድ ናቸው፡
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!!

የወገብ ህመምአሁን ላይ በተደጋጋሚ ወገቤን አመመኝ የሚሉ ሰዎች በስፋት ይሰማሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የወገብ ህመም ከእድሜ መግፋት እና ከወሊድ ጋር ቢያያዝም በወጣቶች ላይም የመከሰት እድሉ ሰፊ...
24/12/2025

የወገብ ህመም
አሁን ላይ በተደጋጋሚ ወገቤን አመመኝ የሚሉ ሰዎች በስፋት ይሰማሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የወገብ ህመም ከእድሜ መግፋት እና ከወሊድ ጋር ቢያያዝም በወጣቶች ላይም የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው፡፡
የወገብ ህመም ሲባል በጀርባ በኩል ያለውን የታችኛውን የአካል ክፍል ወይም ወደ መቀመጫ አከባቢ ያለውን የህመም ስሜት የሚያመለክት ነው፡፡ የወገብ ህመም ምንም አይነት ስራዎችን ስንሰራ ከሚፈጥረው ቀላል የህመም ስሜት ጀምሮ ፣ እየተባባሰ ሲሄድ በእግራችን ጉዞ ማድረግ እንዳንችል እና ፓራላይዝ የማድረግ ደረጃም ላይ ሊያደርስ ይችላል::
የወገብ ህመም ምልክቶች
• ትኩሳት
• የእግር መደንዘዝ ወይንም መስነፍ
•ሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግር
• ከዚህ በፊት የአጥንት መሳሳት
• ህመሙ በጣም እየባሰ መሄድና በእረፍት ወይንም በአቀማመጥ የማይሻል ከሆነ
• ህመሙ በሳምንት ውስጥ ለውጥ ከሌለው አና ተመሳሳይ ስሜቶች ሲኖሩ
የወገብ ህመም መንስኤዉ ምንድነዉ?
• የወገብ አጥንት መዛነፍ
• የመገጣጠሚያ አካባቢዎች መቆጣት
• የአጥንት መብቀል
• የተለያዩ ኢንፌክሽኖች (የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣ የማህፀን ኢንፌክሽን)
• አደጋ (መደብደብ፤ ምት ወዘተ)
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት
• እግርን አጣምሮ መቀመጥ፡-የዳሌ ጡንቻ እንዲወጣጠር ስለሚያደርግ ህመም ይፈጥራል
• ለብዙ ሰዓት መቆም
• ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ በውስጡ ኒኮቲን ስላለው በቂ ሆነ ደም ዝውውር እንዳይዳረስ ስለሚያደርግ
የወገብ ህመም መፍትሄ እና ህክምና
• የእንቅሳቃሴ ህክምና (ፊዚዮቴራፒ) በማድረግ ማስተካከል ይቻላል፡፡
• የመድሀኒት ህክምና
•የቀዶ ጥገና ህክምና
• በተቻለ መጠን መንቀሳቀስ ምክንያቱም እንቅስቃሴ በተደረገ ቁጥር የወገብ ህመም የመሻል እድሉ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!!

የ ተሟላ  የ Electromyography (EMG) ምርመራ ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እና አንቱታን ባተረፉ ባለሞያዎች በመጠቀም ጥራት ያለዉ አገልግሎት በመስጠት ...
20/12/2025

የ ተሟላ የ Electromyography (EMG) ምርመራ ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እና አንቱታን ባተረፉ ባለሞያዎች በመጠቀም ጥራት ያለዉ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ፡፡ እርሶም የ EMG ምርመራ ከታዘዘልዎት በ ሆስፒታላችን ሳምንቱን ሙሉ ማግኘት ይችላሉ። ለምርመራ እንዲሁም ለነርቭ ህክምና የ ነርቭ ስፔሻሊስት ሃኪሞቻችን ጋር ቀጠሮ ለማስያዝ
ቀጠሮ ለማስያዝ
📞8699
📞0977868686
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!!

ከምግብ በኋላ ማድረግ የሌለብን ነገሮች 🔴ፍራፍሬዎችን መብላት: ፍራፍሬዎች ከምግብ በኋላ ስንመገባቸው ከተመገብነው ምግብ ጋር ይደባለቃሉ እና ምግብ እንዳይመጠጥ ያደርጋሉ።  ምግብ ካልተመጠጠ ...
19/12/2025

ከምግብ በኋላ ማድረግ የሌለብን ነገሮች
🔴ፍራፍሬዎችን መብላት: ፍራፍሬዎች ከምግብ በኋላ ስንመገባቸው ከተመገብነው ምግብ ጋር ይደባለቃሉ እና ምግብ እንዳይመጠጥ ያደርጋሉ። ምግብ ካልተመጠጠ ደግሞ ከምግብ ማግኘት ያለብንን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች አናገኝም።ይህ የምግብ መፈጨት ችግርን ሊያስከትል እና እንዲሁም ከበላነዉ ምግብ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን እንድናጣ ያደርጋል።
🔴እንቅልፍ መተኛት: በመሠረቱ ምግብ ከተመገብን በኋላ በምትተኛበት ጊዜ በጨጓራ የሚመረቱ የምግብ መፍጫ ኤንዛይሞች መጠናቸው ይጨምራል። በዚህም ምክንያት ቃርን ያስከትላሉ። ይህም በአጠቃላይ የምግብ መፍጫ ሂደትን ይጎዳል።
🔴 ገላን መታጠብ: ከምግብ በኋላ ገላችንን በምንታጠብበት ጊዜ ደም ወደ ቆዳ በፍጥነት በመሄድ የሰውነትን የሙቀት መጠን ይቆጣጠረዋል። ይህም ለምግብ መፈጨት እንቅፋት ይሆናል።
🔴 እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም ስፖርት መስራት: ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የምግብ መፈጨት ሂደትን ሊረብሽ ይችላል። አልፎ ተርፎም ማስመለስ፣, የሆድ እብጠት እና የእንቅስቃሴ ችግር ሊፈጥር ይችላል።
🔴ሻይ/ቡና መጠጣት: የብረት ነክ ምግቦችን ለመምጠጥ የሚገድቡ ውህዶች በውስጣቸው ይገኛሉ። ስለዚህ, ምግብ ከተመገብን ከ አንድ ሰዓት በኋላ ብንጠጣ የተሻለ ነው።
🔴 ውሃ መጠጣት: ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ውሃ መጠጣት በጨጓራ ውስጥ የሚመረቱትን ምግብን ለመፍጨት የሚረዱትን ኤንዛይሞች እና ፈሳሾችን ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት አሲድነት እና እብጠት ሊያስከትል ይችላል, ይህም የምግብ መፈጨትን አስቸጋሪ ያደርገዋል።
🔴ማጨስ : ማጨስ ለጤና እጅግ ጎጂ ነው። ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ማጨስ ደግሞ 10 እጥፍ ያህል የከፋ ነው።.
ጤናማ እና ደስ የሚል እረፍት ተመኘንላችሁ!
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!

የቆዳ አስም (Atopic Dermatitis ) የተለመደና በተደጋጋሚ በህፃናት ላይ የሚታይ የቆዳ ህመም ነው።በዚህ ህመም የተጠቁ ህፃናት ሌሎች ተያያዥ የአለርጂ ህመሞች ሊኖርባቸው ይችላል-የም...
18/12/2025

የቆዳ አስም (Atopic Dermatitis ) የተለመደና በተደጋጋሚ በህፃናት ላይ የሚታይ የቆዳ ህመም ነው።
በዚህ ህመም የተጠቁ ህፃናት ሌሎች ተያያዥ የአለርጂ ህመሞች ሊኖርባቸው ይችላል
-የምግብ አለርጂ
-አስም ( የአየር ቧንቧ )
-ሳይነስ ( Allergic sinusitis ) አብረው ከሚታዩት ችግሮች መካከል ናቸው።
የቆዳ አስም ምልክቶች ምንድናቸው?
የቆዳ አስም (Atopic Dermatitis ) አብዛኛውን ጊዜ በመጀመሪያው አንድ አመት እድሜ ውስጥ ይጀምራል።
-ማሣከክ (በተለይ ምሽት ላይ የሚብስ)
-የቆዳ መቅላት
- መቁሰልና ውሀ መቋጠር (በሁሉም የአካል ክፍል ላይ ነገር ግን ዳይፐር የሚደረግበት ቦታ ላይ ግን ሽፍታ አይኖርም)
-የቆዳ ድርቀትና መሰነጣጠቅ
-የቆዳ መሻከር( ብርጭቆ ወረቀት መምሰል)
-በተለይ በለጋ እድሜ ላይ ያሉ ህፃናት ላይ:-በጭንቅላት ቆዳ,በፊታቸው ላይ, በአይበሉባቸው በኩል ባለ ክርናቸው ላይ የሚወጡ ሽፍታዎች ይታያሉ።
ይህ የቆዳ ህመም በቀላሉ የማይድን ሄድ መጣ የሚል ዘላቂ ህመም መሆኑን ወላጆች ሊረዱት ይገባል!
የቆዳ አስምን እንዴት ከመባባስ እንከላከል?
ይህ ህመም ያለባቸውን ልጆች አንዳንድ ምግቦችን መመገብ ሁኔታውን ያባብሳል። እንደ እንቁላል ፣ የላም ወተት ፣ ለውዝ ፣ አኩሪ አተር ፣ ስንዴ የመሳሰሉት ከሚያባብሱ ነገሮች ተጠቃሾች ናቸው። እንዲሁም አንዳንድ የሳሙና አይነቶችና ልብሶች ሁኔታውን ስለሚያባብሱ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ በአንክሮ መከታተል አለባቸው።
በአግባቡ ካልታከሙ ለባክቴሪያ ኢንፌክሽን ለሌሎች አለርጂ ህመሞች ይዳርጋል። በተለይም በማሳከኩ የተነሳ ለከፍተኛ የእንቅልፍ ችግር ይጋለጣሉ። በመሆኑም ወደሀኪም በመሄድ ህክምናን መከታተል መድሀኒት መውሰድ ያስፈልጋል።
ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 0977868686
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!

የጥርስ መቦርቦር በምን ይከሰታል?የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተ...
17/12/2025

የጥርስ መቦርቦር በምን ይከሰታል?
የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን (Cavities) እንዲፈጠሩ ያደርጋል። የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ።
ለጥርስ መቦርቦር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች፦
🔴 ጥርስን በሚገባና በመደበኛ ሁኔታ አለማፅዳት
🔴 ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር
🔴 የፍሎራይድ እጥረት መኖር
🔴 የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
🔴 በህመም ወይንም በተለያዩ መድሀኒቶች ምክንያት የአፍ ድርቀት ሲኖር
🔴 ሲጋራን ማጨስ ናቸው።
የጥርስ መቦርቦር የሚያስከትላቸው ምልክቶች
⚠️ የጥርስ ህመም ስሜት
⚠️በተጎዳው ጥርስ አካባቢ የድድ ማበጥ
⚠️ መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን መኖር
⚠️ በጥርስ ላይ ነጭ፣ ግራጫ፣ ቡኒ ወይንም ጥቁር ቀለማት የያዙ የተቦረቦሩ ቦታዎች መኖር ናቸው።
የጥርስ መቦርቦርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
🟢ጥርስዎን በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጊዜ የፍሎራይድ ኬሚካል ባለው የጥርስ ሳሙና መታጠብ።
🟢 በማንኛው ግዜ ምግብ ከተመገቡ በኃላ አፍዎን በንፁህ ውሀ በሚገባ መጉመጥመጥ
🟢 ከእንቅልፍ በፊት ጥርስዎን ከታጠቡ በኃላ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ
🟢 ጣፋጭ የበዛባቸው ምግቦችን ማስወገድ
🟢የጥርስ ሀኪምዎ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በመሄድ ጥርስዎን በባለሞያ ማሳጠብና ማስመርመር።
ማሳስቢያ፦
የጥርስ ህመም ሲሰማዎ ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሀኪም መሄድን አይዘንጉ ምክንያቱም የህመም ስሜቱ ከጥቂት ጊዜ በኃላ በራሱ ሊጠፋ ቢችልም የጥርስ መቦርቦር ግን ያለ ህመም ሊቀጥል ይችላል። በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገ ጥርስዎን እስከማጣት ሊያደርስዎ ይችላል።

ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ !!

Team Care Land at Ethiopian Shipping and Logistics Enterprise CompoundOn December 10, 2025, the Care Land General Hospit...
16/12/2025

Team Care Land at Ethiopian Shipping and Logistics Enterprise Compound

On December 10, 2025, the Care Land General Hospital team conducted a comprehensive medical campaign at the Ethiopian Shipping & Logistics Enterprise compound.
During the campaign, our medical, optical, and dental teams provided free medical services to more than 300 employees. The services delivered included general medical checkups, full ophthalmological examinations, and dental procedures such as scaling and extraction.

This outreach initiative reflects Care Land General Hospital’s ongoing commitment to expanding access to quality medical service and supporting the well-being of our community partners. It was a highly successful and fruitful campaign, and similar initiatives will continue in the future.

Care Land General Hospital
Beyond Treatment!!

20-20-20 የአይን  ህግ  በአለም አቀፍ ደረጃ ስናይ 1 ሰው በአማካኝ በ 1 ቀን ውስጥ 6 ሰዓት ከ 40 ደቂቃ ስክሪን ላይ  ያሳልፋል። ይህም በሞባይል፣ በላፕቶፕ፣ በኮምፒውተር ወይም በ...
12/12/2025

20-20-20 የአይን ህግ
በአለም አቀፍ ደረጃ ስናይ 1 ሰው በአማካኝ በ 1 ቀን ውስጥ 6 ሰዓት ከ 40 ደቂቃ ስክሪን ላይ ያሳልፋል። ይህም በሞባይል፣ በላፕቶፕ፣ በኮምፒውተር ወይም በሌላ ኤሌክትሮኒክስ ላይ ሊሆን ይችላል።
👀ጤናማ የሆነ ስክሪን ላይ የመቆየት ጊዜ ደግሞ ከ2 ሰአት በታች ነው። ስለዚህ የአይናችንን ጤና ለመጠበቅ 20-20-20 ህግ መከተል አለብን ማለት ነው።
20-20-20 የአይን ህግ ማለት ምን ማለት ነዉ?
👀20-20-20 ህግ ማለት ስክሪን እያየን ብምንቆይበት ወቅት በየ20 ደቂቃው ቢያንስ ለ 20 ሴኮንድ ቢያንስ በ 20 ጫማ (6 ሜትር) ርቀት ላይ የሚገኝን ነገር መመልከት ነው። ይህን ማድረጋችን የአይናችን ጡንቻ ዘና እንዲል ይጠቅመዋል።
ለምን 20 ሴኮንዶች ?
አይናችን በ አግባቡ ዘና እንዲል ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች ስለሚያስፈልገው ነው። ይህን በምናደርግበት ወቅት ብንችል ተነስተን ውሃ ጠጥተን ብንመለስ የተሻለ ነው። ውሃ መጠጣትም አይናችን ጤናማ እንዲሆን ይጠቅመናል።
በግምት እስከ 20 ጫማ (6 ሜትር) ርቀት ላይ የሚገኝን ለ 20 ሴኮንድ በመመልከት የአይናችንን ጤና እንጠብቅ !
እንዴት 20 ደቂቃውን አስታውሳለው?
በንባብ ወይም ኮምፒውተር በምንጠቀም ጊዜ ደቂቃውን ለማስታወስ አላርም መሙላት ይረዳል።

ጤናማ እና ደስ የሚል እረፍት ተመኘንላችሁ!!
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!!

ኬር ላንድ አጠቃላይ ሆሲፒታል / CARE LAND GENERAL HOSPITAL, [12/11/2025 8:40 AM]በልጆች ላይ የሚከሰት ሳል እና ጉንፋንሳል እና ብርድ ብርድ ማለት በልጆች ላይ በ...
11/12/2025

ኬር ላንድ አጠቃላይ ሆሲፒታል / CARE LAND GENERAL HOSPITAL, [12/11/2025 8:40 AM]
በልጆች ላይ የሚከሰት ሳል እና ጉንፋን

ሳል እና ብርድ ብርድ ማለት በልጆች ላይ በጣም የተለመዱ ኢንፌክሽኖች ሲሆኑ የመተንፈሻ አካላትን በሚጎዱ ቫይረሶች ውስጥ ስለሚተላለፉ ምንም እንኳን ጉንፋን እና ሳል በሰውነት ላይ ምንም አይነት ከባድ ተጽእኖ ባይኖራቸውም, ግን ስርዓቱን ያዳክማሉ፡፡ ነገርግን በተገቢው እንክብካቤ እና እረፍት ብቻ ህፃናት በፍጥነት መዳን ይችላሉ::

የጉንፋን እና ሳል ምልክቶች

🔴የአፍንጫ ፈሳሽ መኖር
🔴በጉንፋን የተዘጋ ጉሮሮ
🔴ራስ ምታት
🔴የሰውነት ሕመም
🔴በጆሮ ላይ ህመም
🔴ቀላል ትኩሳት እና የድካም ስሜት
🔴አይን ማሳከክ
🔴ማስነጠስ

ጉንፋን እና ሳል እንዴት እንቆጣጠር
ሳል እና ጉንፋን ለማከም ልዩ ምግቦች የሉም. ነገር ግን በእንፋሎት መታጠን፣ ጥሩ እረፍት ማድረግ እና ጤናማ ምግብ መመገብ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል። ከቅባት ፣ ቅመም ከበዛበት እና ከውጪ ምግብ ልጆችን መቆጠብ፡፡

በልጆች ላይ ለጉንፋን እና ለሳል የሕክምና እርዳታ መቼ ማግኘት አለባቸዉ?
አብዛኛውን ጊዜ የጉንፋን እና ሳል ምልክቶች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይቀንሳሉ, ነገር ግን ህጻኑ እያገገመ ካልሆነ, ትኩሳት አልቀንስ ካለ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርቦታል፡፡

ቀጠሮ ለማስያዝ
📞0977868686
📍ፉሪ ኖክ አባገዳ አደባባይ ፊት ለፊት

ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!!

የቆዳ እና የአባላዘር  ህክምና ክፍላችን ሳምንቱን ሙሉ  አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል!የተሟላ የቆዳ ህክምና በ ቆዳ ስፔሻሊስት  ሀኪሞቻችን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጥራቱን ...
09/12/2025

የቆዳ እና የአባላዘር ህክምና ክፍላችን ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል!

የተሟላ የቆዳ ህክምና በ ቆዳ ስፔሻሊስት ሀኪሞቻችን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎ በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡

ቀጠሮ ለማስያዝ / ለበለጠ መረጃ
📞8699
📞0977868686
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ !!

በስራቸዉ ተወዳጅነትን ያተረፉ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት  ሀኪም ዶ/ር ሀያት መሀመድበሆስፒታላችን ዉስጥ በማገልገል ላይ ይገኛሉ!!ቀጠሮ ለማስያዝ 📞8699📞0977868686ኬርላንድ አጠቃ...
08/12/2025

በስራቸዉ ተወዳጅነትን ያተረፉ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም
ዶ/ር ሀያት መሀመድ
በሆስፒታላችን ዉስጥ በማገልገል ላይ ይገኛሉ!!
ቀጠሮ ለማስያዝ
📞8699
📞0977868686
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!!

አመታዊ የጤና ምርመራ እድሜ እየገፋ ሲሄድ ከሚወሰዱት ብልህ ዉሳኔዎች ዉስጥ ዋነኛዉ ነዉ!!ዕድሜዎ እየገፋ ሲሄድ ጤናዎ ላይ ለውጥ ይኖራል፡፡ በተለያዩ የእድሜ  ደረጃዎች ውስጥ  የሚኖረን የበ...
05/12/2025

አመታዊ የጤና ምርመራ እድሜ እየገፋ ሲሄድ ከሚወሰዱት ብልህ ዉሳኔዎች ዉስጥ ዋነኛዉ ነዉ!!
ዕድሜዎ እየገፋ ሲሄድ ጤናዎ ላይ ለውጥ ይኖራል፡፡ በተለያዩ የእድሜ ደረጃዎች ውስጥ የሚኖረን የበሽታ ተጋላጭነትእና በሽታን የመከላከል አቅማችን ይለያያል. እድሜዎ እየገፋ ሲሄድ ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭነቶ የበለጠ ይሆናል ፡፡ ተጋላጭ ከሚሆኑባቸዉ በሽታዎች በጥቂቱ የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ፣ የደም ግፊት ፣ የስኳር በሽታ እና የደም ቧንቧ መጥበብ (arteriosclerosis) ይጠቀሳሉ።
ምን አይነት ምርመራ ማድረግ አለብዎት ( እድሜ >40)
✅ክብደት እና ቁመት
✅የደም ግፊት ልኬት
✅የዓይን ምርመራ
✅የጆሮ ምርመራ
✅አጠቃላይ የደም ህዋሶች ምርመራ
✅የኩላሊት ፣ የጉበት ምርመራዎች
✅የተለያዩ የደም ውስጥ ንጥረ ነገሮች ምርመራ
✅በሰውነት ውስጥ ያለ የስብ መጠን ምርመራ
✅የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
✅የስኳር በሽታ ምርመራ
✅የሽንት ምርመራ
✅የልብ ምርመራ
✅ኮሎኖስኮፒ
✅ለሴቶች ደግሞ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ፤የጡት ካንሰር ምርመራ እና በሰውነት ውስጥ ያለ የካልሲየም መጠን ምርመራ

⚠️ሁሉም ሰው ዓመታዊ የጤና ምርመራ የማድረግ ልማድ(Annual health checkup) ሊኖረው ይገባል በተለይ እድሜ እየገፋ ሲሄድ በቋሚነት ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ እንዲሁም የራስዎን እና የቤተሰብዎን መልካም ጤንነት ለመጠበቅ ይሄን ተግባር በህይወት ዘመንዎት በቁርጠኝነት ከሚያከናውኗቸው ተግባራት ውስጥ ማካተት አለብዎት።
ጤናማ እና ደስ የሚል እረፍት ተመኘንላችሁ!!
ኬርላንድ አጠቃላይ ሆስፒታል
ከማከምም በላይ!

Address

Oromia Region
Sebeta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Care Land General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Care Land General Hospital:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category