Womberma woreda Health office

Womberma woreda Health office "Health for All"

የልጅነት ልምሻ (ፓሊዮ) መከላከያ ክትባት ለሁሉም ከ5ዓመት በታች ህፃናትከ18/07/18ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት ይሰጣል።_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-ልጅዎን ያስ...
24/03/2026

የልጅነት ልምሻ (ፓሊዮ) መከላከያ
ክትባት ለሁሉም ከ5ዓመት በታች ህፃናት
ከ18/07/18ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ
4 ቀናት ይሰጣል።
_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-
ልጅዎን ያስከትቡ በፓሊዮ የሚከሰት የልጅነት ልምሻን ይከላከላሉ!
__________-
👉ፓሊዮን ለማስወገድ ሃላፊነትዎን ይወጡ!

07/03/2026

‎እንኳን ደስ አላችሁ!
‎*****
‎በአገር አቀፍ ውድድር በወርቅ ደረጃ ዕውቅና ካገኙ አስር ሆስፒታሎች ውስጥ 7ቱ በአማራ ክልል የሚገኙ ሆስፒታሎች ናቸው።

‎በአገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ( EHAQ) የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ የአማራ ክልል ሆስፒታሎች ቀዳሚ በመሆን ዕውቅና ሽልማት አግኝተዋል።

‎በአገር አቀፍ ደረጃ ለአሸናፊዎች ከተመደበው 100 ሚሊዪን ብር 35 ሚሊዮን ብሩን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የአማራ ክልል ሆስፒታሎች ወስደውታል።

‎1) ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣
‎2) ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣
‎3) ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣
‎4) መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል፣
‎5) ደብረ ብርሐን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣
6) ፍኖተ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል እና
7) እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ናቸው።


‎ #አብክመጤናቢሮ

19/12/2022
📖ማሳሰቢያ📖*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣ #በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ  #የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ከ6 እስከ 59 ወር ለሆናቸው ህፃናት ከታህሳስ 13-22...
19/12/2022

📖ማሳሰቢያ📖
*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣
#በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ #የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ከ6 እስከ 59 ወር ለሆናቸው ህፃናት ከታህሳስ 13-22/2015 ዓ.ም ይሰጣል።
*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣
በወረዳችንም በጤና ተቋማት እና በሚንቀሳቀሱ የክትባት ጣቢያዎች በተቀናጀ መልኩ የሚከተሉትን ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጥ ስለሆነ በተለይም
*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣
*️⃣1 =>የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት
*️⃣2 =>የቫይታሚን ኤ መድሃኒት
#️⃣3=>ለህፃናት አጣዳፊ የምግብ ዕጥረት ልየታ እና *️⃣ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ
*️⃣4 =>የማህፀን መውጣት ችግር የሚያጋጥማቸው እናቶች ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ
*️⃣5=ከወሊድ ጋር በተገናኘ የተከሰተ ፌስቱላ መለየት እና ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ
*️⃣6=ለህፃናትየአንጀት ጥገኛ ትላትል ማጥፊያ መድሃኒት
*️⃣7=የላንቃ እና የከንፈር መሠንጠቅ ያለባቸውን ህክምና እንዲሰጣቸው መለየት
*️⃣8=ሲወለዱ ቆልማማ እግር የተከሰተባቸውን ህክምና እንዲያገኙ መለየት
*️⃣9=ሁለት ሳምንት እና ከዚያ በላይ ሳል ያለባቸውን የቲቢ ምርመራ እንዲያደርጉ መለየት
*️⃣10=ከ18ዓመት በላይ ለሆኑ የኮቪድ 19 ክትባት መስጠት
*️⃣11=መደበኛ ክትባት ያቋረጡ እና ያልጀመሩ ታላሚዎች ክትባት መስጠት አገልግሎት የሚሰጥ ስለሆነ

*️⃣ሁሉም ሰው መረጃውን አይቶ በማሳወቅ አገልግሎቱን ሳያገኝ የሚቀር የወረዳችን ነዋሪ እንዳይኖር ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ለማሳሰብ እንወዳለን።
*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣*️⃣
↔️ኩፍኝ ህፃናትን ለከፋ ዘላቂ የሆነ የጤና ችግር እና ለሞት የሚዳርግ ቫይረሰ ስለሆነ ሁሉም ህፃናት በመደበኛ እና በዘመቻ የሚሰጠውን የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እንድታስከትቡ በድጋሚ እናሳስባለን።
°°ሁሌም ጤና°°
➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️
#️⃣የወም/ወ/ጤ/ጥ /ጽ/ቤት #️⃣

#ሼር እያደርግን ለሁሉም እናድርስ!!

14/07/2022

በወምበርማ ወረዳ ከሐምሌ 04/2014 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 10/2014 ዓ/ም የሚቆይ የአንጀት ጥገኛ ትላትል መድሐኒት እየተሰጠ ነው👇
~~~~~
በወረዳችን የአንጀት ጥገኛ ትላትል ማጥፊያ መድኃኒት ከፍተኛ ጉዳት በሚያስከትልባቸው ህፃናት እና አዋቂ ሴቶች እየተሰጠ ስለሆነ እንዲወስዱ በማድረግ በአንጀት ጥገኛ ትላትል አማካኝነት የሚመጣን

✍️ የዕድገት መገታት/መቀንጨር/
✍️ አምዕሮ ዘገምተኝነት/በትምህርት ጎበዝ አለመሆን/
✍️ በእርግዝና ጊዜ የፅንስን ዕድገት መገታት እና የመሣሠሉትን ሊታዩ እና ሊታዩ የማይችሉ ጉዳቶችን መከላከል ስለሚያስችሉ ሁሉም ሰው ቢወስድ አስፈላጊ በመሆኑ ቤትለቤት ከሚመጡ ባለሙያዎች ወይም በአቅራቢያ በሚገኙ የመንግሥት ጤና ተቋማት እንድትወስዱ/እንድታስወስዱ ለማሳሰብ እንወዳለን።

መድሐኒቱ የሚያጠፋቸው በሽታዎች : -
✍️ የወስፋት በሽታ
✍️ የመንጠቆ ትል በሽታ
✍️ የህፃናትን ፊንጢጣ የሚገለብጥና ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጥ ጥገኛ ትል (በማህበረሰቡ ዘንድ የቤት ህመም እየተባለ የሚጠራው) የሚያጠፋ መድሐኒት መሆኑን እናሳስባለን።

እነዚህ በሽታዎች የመተላለፊያ መንገዶች
✍️ በባዶ እግር መንቀሳቀስ
✍️ በአይነ ምድር ንክኪ እና
✍️ በተበከለ ምግብና ውሃ የሚተላለፉ ናቸው!!

የአንጀት ጥገኛ ትላትልን ጉዳት እንዲሁም መተላለፉን ለመከላከል
✍️ ጫማ መልበስ
✍️ ንፅህናውን የጠበቀ ምግብ እና ውሀ መጠቀም
✍️ በወሳኝ ጊዜያት ሁሌም በተገቢው መንገድ እጅን መታጠብ
ማለትም
👉 ከምግብ ማብሰል በፊት እና በኋላ
👉 ከመመገብ በፊት
👉 ከተመገቡ በኋላ
👉 ከመፀዳጃ ቤት መልስ
👉 ህፃናትን ከማጥባት በፊት እና ከማጥባት በኋላ
👉 በእርግዝና ጊዜ የትላትል ማጥፊያ መድሀኒት መውሰድ
👉 ከ2-5ዓመት ለሆኑ ህፃናት መደበኛ በየ6ወሩ መድሀኒት ተከታትሎ ማሰጠት
👉 መፀዳጃ ቤት በተገቢው መልኩ በመገንባት መጠቀም እና ለመዋኛ የሚያገለግልን ውሀ ደህንነት ማረጋገጥ!
አስፈላጊ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መንገዶች ናቸው።

⭕️ለጤናማ ልጅነት የአንጀት ጥገኛ ትላትል ማጥፊያ መድሃኒት ወሳኝ ነው!!⭕️

የወምበርማ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት

በወምበርማ ወረዳ ከሐምሌ 04/2014 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 10/2014 ዓ/ም የሚቆይ  የአንጀት ጥገኛ ትላትል መድሐኒት እየተሰጠ ነው። ➖➖➖🧬🧬🧬🧬➖➖➖➖➖➖➖በወረዳችን የአንጀት ጥገኛ ትላትል...
13/07/2022

በወምበርማ ወረዳ ከሐምሌ 04/2014 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 10/2014 ዓ/ም የሚቆይ የአንጀት ጥገኛ ትላትል መድሐኒት እየተሰጠ ነው።
➖➖➖🧬🧬🧬🧬➖➖➖➖➖➖➖
በወረዳችን የአንጀት ጥገኛ ትላትል ማጥፊያ መድኃኒት ከፍተኛ ጉዳት በሚያስከትልባቸው ህፃናት እና አዋቂ ሴቶች እየተሰጠ ስለሆነ እንዲወስዱ በማድረግ በአንጀት ጥገኛ ትላትል አማካኝነት የሚመጣን
➡️የዕድገት መገታት/መቀንጨር/
➡️አምዕሮ ዘገምተኝነት/በትምህርት ጎበዝ አለመሆን/
➡️በእርግዝና ጊዜ የፅንስን ዕድገት መገታት እና የመሣሠሉትን ሊታዩ እና ሊታዩ የማይችሉ ጉዳቶችን መከላከል ስለሚያስችሉ ሁሉም ሰው ቢወስድ አስፈላጊ በመሆኑ ቤትለቤት ከሚመጡ ባለሙያዎች ወይም በአቅራቢያ በሚገኙ የመንግሥት ጤና ተቋማት እንድትወስዱ/እንድታስወስዱ ለማሳሰብ እንወዳለን።
መድሐኒቱ የሚያጠፋቸው በሽታዎች : -
➡️የወስፋት በሽታ
➡️የመንጠቆ ትል በሽታ
➡️ የህፃናትን ፊንጢጣ የሚገለብጥና ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጥ ጥገኛ ትል (በማህበረሰቡ ዘንድ የቤት ህመም እየተባለ የሚጠራው) የሚያጠፋ መድሐኒት መሆኑን እናሳስባለን።
እነዚህ በሽታዎች የመተላለፊያ መንገዶች
➡️በባዶ እግር መንቀሳቀስ
➡️በአይነ ምድር ንክኪ እና
➡️በተበከለ ምግብና ውሃ የሚተላለፉ ናቸው!!

የአንጀት ጥገኛ ትላትልን ጉዳት እንዲሁም መተላለፉን ለመከላከል
➡️ጫማ መልበስ
➡️ንፅህናውን የጠበቀ ምግብ እና ውሀ መጠቀም
➡️በወሳኝ ጊዜያት ሁሌም በተገቢው መንገድ እጅን መታጠብ
ማለትም
➡️ከምግብ ማብሰል በፊት እና በኋላ
➡️ከመመገብ በፊት
➡️ከተመገቡ በኋላ
➡️ከመፀዳጃ ቤት መልስ
➡️ህፃናትን ከማጥባት በፊት እና ከማጥባት በኋላ
➡️በእርግዝና ጊዜ የትላትል ማጥፊያ መድሀኒት መውሰድ
➡️ከ2-5ዓመት ለሆኑ ህፃናት መደበኛ በየ6ወሩ መድሀኒት ተከታትሎ ማሰጠት
➡️መፀዳጃ ቤት በተገቢው መልኩ በመገንባት መጠቀም እና
ለመዋኛ የሚያገለግልን ውሀ ደህንነት ማረጋገጥ!
አስፈላጊ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መንገዶች ናቸው

⭕️ለጤናማ ልጅነት የአንጀት ጥገኛ ትላትል ማጥፊያ መድሃኒት ወሳኝ ነው!!⭕️
⩩ሁሌም ጤና⩩
⩩የወምበርማ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት⩩

🛑ማሳሰቢያ🛑 🛑ለወረዳችን ነዋሪዎች በሙሉ🛑✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅በወምበርማ ወረዳ የትራኮማ መከላከያ መድሀኒት ዕደላ  ዘመቻ ከግንቦት 9-19/2014ዓ.ም ይካሄዳል ። ✅መድሀኒቱ የሚሰጠው ለሁሉም ሰ...
16/05/2022

🛑ማሳሰቢያ🛑

🛑ለወረዳችን ነዋሪዎች በሙሉ🛑
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
በወምበርማ ወረዳ የትራኮማ መከላከያ መድሀኒት ዕደላ ዘመቻ ከግንቦት 9-19/2014ዓ.ም ይካሄዳል ።

✅መድሀኒቱ የሚሰጠው ለሁሉም ሰው ሲሆን
ለዚህም
✳️ ቤትለቤት ለሚመጡ የጤና ባለሙያዎች ትብብር እንዲደረግላቸው እና
ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ መድሀኒቱን በመውሰድ የትራኮማ በሽታ ስርጭትን እና ብሎም የሚያስከትለውን አይነስውርነት እንድንከላከል ጥሪ እናቀርባለን‼️

15/04/2022

ጥብቅ ማሳሰቢያ 👇
~~~~~~~~
ከሚያዝያ 7-10 የፖሊዮ ወይም የልጅነት ልምሻ ክትባት ቤት ለቤት የሚሰጥ ይሆናል። ስለሆነም ዕድሜያቸው ከአምስት (5) ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በማስከተብ ኃላፊነታችንን እንወጣ!

የወምበርማ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት

05/11/2021

በወምበርማ ወረዳ እና በሽንዲ ከተማ አስተዳድር ለምትገኙ ነዋሪዎች በሙሉ!

አሸባሪውን ህውሓት ለመመከትና ለመደምሰስ እየተዋደቀ ለሚገኘው የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ እንዲሁም ለሃገር መከላከያ ሠራዊት በህልውና ዘመቻው ለተጎዱት ደም ለመለገስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በሙሉ ወምበርማ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም በጤናው ዘርፍ ማለትም በነርስ፣ በጤና መኮንንነት ተመርቃችሁ ወደ ስራ ያልገባችሁ የጤና ባለሙያዎች የህልውና ዘመቻውን እንድትቀላቀሉና በሙያችሁ እንድታገለግሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡-
0584490208
0584490213
0584490210 በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን!

፨፨በወምበርማ ወረዳ ሀገር አቀፍ የፓሊዮ ዘመቻ እየተካሄደ ነው፨፨፨--------------------------------------------------------------------ከዛሬ ጥቅምት 1...
22/10/2021

፨፨በወምበርማ ወረዳ ሀገር አቀፍ የፓሊዮ ዘመቻ እየተካሄደ ነው፨፨፨
--------------------------------------------------------------------
ከዛሬ ጥቅምት 12 እስከ 15 የሚቆይ የፓሊዮ (የልጅነት ልምሻ) በሽታ መከላከያ ክትባት
በዘመቻ ዕድሜያቸው ከ5ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ቤትለቤት እየተሰጠ መሆኑን የወረዳው የህፃናትእና ስነ ምግብ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ደረጀ ዘውዴ ተናግረዋል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ ደረጀ እንደገለፁት ፓሊዮ #በቫይረስ የሚመጣ አስከፊ በሽታ መሆኑን እና በሽታው ፓሊዮ ቫይረስ 1,2,3 ዘር አማካኝነት የሚመጣ መሆኑን በመግለፅ ዋና መተላለፊያ መንገዱም ከታመመ ህፃን ከአይነ-ምድር ጋር በሚኖር ወደ አፍ ንክኪ መሆኑን ፤
በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ በመሆኑ እና ህፃናት ላይም የልጅነት ልምሻን የሚፈጥር አስከፊ ቫይረስ በመሆኑ ዘመቻውን ለሁሉም ህፃናት ቤትለቤት እና በተመረጡ ቦታዎች እንዲሰጥ እና ዘመቻውም ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን የቅድመ ዘመቻ ስራዎችን ተሰርተዋል ። ከተሰሩ ተግባራት መካከል
፨ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ፤
፨፨ ለጤና ባለሙያዎች ፤
፨፨፨ ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ፤
፨፨፨፨ ለማህበረሰብ የቤትለቤት ቀስቃሾች፤
፨፨፨፨ ለክትባት ማስቀመጫ ፍሪጆች እና ቅዝቃዜ መጠበቂያ እና ማንቀሳቀሻ ቁሳቁስ በማሰራጨት ጥሩ የቅድመዝግጅት ሰራ መሰራቱን ጠቅሰው
ማህበረሰቡም ታላሚ ከ5ዓመት በታች ህፃናትን በመደበኛ እና በዘመቻ የሚሰጡ የፓሊዮ መከላከያ ክትባት በማስከተብ በፓሊዮ አማካኝነት የሚከሰት የልጅነት ልምሻነትን(ሽባነትን) እንዲሁም ሞትን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል ::
የወምበርማ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

22/10/2021

Send a message to learn more

Address

Shindi Gojjam
Shindi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Womberma woreda Health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Womberma woreda Health office:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram