SeyFana Medium Clinic/SeyFaana Mereerima Kilinike

  • Home
  • SeyFana Medium Clinic/SeyFaana Mereerima Kilinike

SeyFana Medium Clinic/SeyFaana Mereerima Kilinike We Treat God heals!!

ስለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ምን ያውቃሉ?ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት አንደ ስሙ በአጣዳፊ ሁኔታ የሚከሰት የኩላሊት ህመም ነው። ጉዳቱ በደማችን ውስጥ በሚኖር የተረፈ ምርት ክምችት ምክንያት የሚ...
26/02/2022

ስለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ምን ያውቃሉ?

ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት አንደ ስሙ በአጣዳፊ ሁኔታ የሚከሰት የኩላሊት ህመም ነው። ጉዳቱ በደማችን ውስጥ በሚኖር የተረፈ ምርት ክምችት ምክንያት የሚከሠት ሲሆን ኩላሊት ትክክለኛ የፈሳሽ ማጣራት ተግባሩን እንዳያከናውን ያደርገዋል። ይህ በሽታ እንደ ልብ፣ ሳንባ እና አእምሮ የመሳሰሉትን የሠውነት አካሎች ይጎዳል። ተግቢውን ሕክምና ካገኘ አና ምክንያቶቹ ከተስተካከሉ አጣዳፊ /ድንገተኛ የ ኩላሊት ህመም ብዙ ጊዜ የመዳን አድል አለው ።
#በየዓመቱ በአለም ደረጃ ከ13.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በድንገተኛ ኩላሊት ጉዳት ይጠቃሉ። ከእነዚህ ውስጥ 85% የሚሆኑቱ ባላደጉ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ናቸው።
በድንገተኛ ኩላሊት ጉዳት ብቻ በየዓመቱ ወደ 1.7 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ለህልፈተ ህይወት ይዳረጋሉ።
እ.እ.አ ከ2013-2017 በሀረር ክልል፤በሁለተኛው ስኳር ዓይነት ህመምተኞች ላይ የተደረገው ጥናትና ምርምር ውጤት 14.5%ቱ በድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት የተጠቁ መሆናቸውን ያሳያል።

#የድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• የሽንት መጠን መቀነስ
• የሠውነት እብጠት በተለይ አግር አና አይናችን አከባቢ
• ከፍተኛ የሆነ የመዛል እና የድካም ስሜት
• የማዞር ስሜት
• የትንፋሽ ማጠር
• አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛ የኩላሊት ህመም ምንም አይነት ምልክቶችን በህመምተኛው ላይ ሳያሳይ በሆስፒታል ውስጥ በሚደረግለት ምርመራ ሊታወቅ ይችላል።
#ለበሽታው መከሠት ዋና መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
1. ወደ ኩላሊት የሚሄደው ደም ማነስ
አንዳንድ በሽታዎች እና ሁኔታዎች ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም መጠን ሊቀንሡት ይችላሉ። ለምሳሌ:-
•በጣም ዝቅ ያለ የደም ግፊት
• በተለያየ ምክንያት የሚከሠት በሠውነታችን ውስጥ ያለ ደም ወይም ፈሳሽ ማነስ (በደም መፍሠስ ወይም አንደ ተቅማጥ ያሉ በሽታዎች …)
• አንዳንድ የሠውነት ክፍሎች በአግባቡ አለመስራት (ልብ፣ ጉበት)
• የልብ ህመም
• የተላያዩ መድሃኒቶችን ከመጠን በላይ መጠቀም ( ለምሳሌ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች NSAIDs-ዲክሎፈናክ አይቡፕሮፌን , Antibiotics..vancomycin Gentamycin.... )
2. ኩላለት ላይ የሚኖር ቀጥተኛ ጉዳት
አንዳንድ መድኃኒቶች ፣ ከተለያዩ የ ካንሰር ህመሞች ጋር ተያይዞ ፣ ከፍተኛ ኢንፌክሽን …
3. የሽንት ቧንቧ መዘጋት
• ለወንዶች የፕሮስቴት እና ሴቶች ማህፀን በር ካንሰር
• የፕሮስቴት እጢ ማደግ በተለይ በ አዋቂ ወንዶች ላይ
• የኩላሊት ጠጠር
4.ተላላፊ ያልሆኑ ውሎ ያደሩ በሽታዎች[የስኳር ህመም፤ ከፍ ያለ የደም ግፊት ...
#ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት እንዳለ ለማወቅ የሚረዱ ምርመራዎች ምንድን ናቸው?
በተቻለ መጠን ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ቶሎ ቢታወቅ መልካም ነው። ምክንያቱም በአግባቡ ካልታከመ ለረጅም ጊዜ የኩላሊት ጉዳት ብሎም ለልብ ህመም እና ሞት ሊያጋልጥ ይችላል። አንድ ታካሚ የኩላሊቱን ጤንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉት ምርመራዎች ይታዘዙለታል።
1. የሽንት ምርመራ: በሽንት ውስጥ ደም ወይም ፕሮቲን እንዳለ ለማረጋገጥ ይረዳል። ይህም የድንገተኛ የኩላሊት ህመም ካለ
ለማወቅ ይረዳል።
2. የሽንት ፍሠቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ
3. የደም ምርመራ: በደም ውስጥ የሚገኘውን የክሪአቲኒን መጠንን / ጂ.ኤፍ.አር (ኩላሊት በደቂቃ ምን ያህል ቆሻሻ ማጣራት እንደሚችል) ለማወቅ ይረዳል።
4.የድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት መንስኤዎቹ ምንድናቸው የምለውን ለማወቅ ሶኖግራፊ ማሰራት ይጠበቅብናል፤በተለይም ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት የተከሰተው በሽንት ቱቦ መዘጋት ነው[የሽንት ቧንቧ መዘጋት ......ለወንዶች የፕሮስቴት እና ሴቶች ማህፀን በር ካንሰር
የፕሮስቴት እጢ ማደግ ፤የኩላሊት ጠጠር] ነው ወይንስ ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ቀድሞ ከነበረው ጉዳት ተባብሶ ነው የሚለውን ያጣራል።
5. ከኩላሊትዎ ላይ በተለየ መርፌ ከሚወሰድ እና በማይክሮስኮፕ በሚመረመር ናሙና (Kidney Biopsy )
6.CBC, electrolyte, ABG,CXR,ECG ECHO,.....የመሳሰሉት ምርመራዎች ይሠራሉ።

ለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚደረገው ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ህመምተኛውን በህክምና ስፍራ ላይ እንዲቆይ ያስገድዳል። በሆስፒታል ውስጥ ምን ያህል ይቆያል የሚለው ነገር ህመሙን ካመጣው መንስኤ እና ኩላሊቱስ በምን ያህል ፍጥነት ወደ ስራው ይመለሳል የሚሉት ነገሮች ላይ ይወሠናል። ህመምተኛው አስጊ ደረጃ ላይ ከሆነ በህክምና ባለሙያዎች ድያሊሲስ እንዲያደርግ ሊታዘዝለት ይችላል። ዲያሊሲስ በማሽን የሚደረግ የሠውነት ቆሻሻን የማጥራት ስራ ነው።
በድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ከተጠቁ በኋላ በሌሎች ተያያዥ ህመሞችን የመጠቃት እድል በጣም ከፍተኛ ነው።
ራሳችንን ከዚህ ጉዳት ለመከላከል የሐኪምን ምክር መከተል ፣ የኩላሊት ተግባርን ለመላካት የሚጠቅሙ ምርመራዎችን ማድረግ እና በተቻለ መጠን ራስን ለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ከሚዳርጉ ነገሮች ማራቅ ይገባል ።

Seyfaana Owaantete anguwa!!!
Seyfaana Caring Hands!!!
ሠይፋና የእንክብካቤ እጆች!!!

ስለእንቅርት እጥ እብጠትና ተያያጅ ህመም ምን ያውቃሉ?በመሠረቱ የእንቅርት እጥ ለሰውነታችን ጠቃም የሆኑ ሆርሞኖችን ያመነጫል።እነዚህም thyroid hormones ተብሎ የምጠሩ ስሆኑ በዝርዝር...
25/02/2022

ስለእንቅርት እጥ እብጠትና ተያያጅ ህመም ምን ያውቃሉ?

በመሠረቱ የእንቅርት እጥ ለሰውነታችን ጠቃም የሆኑ ሆርሞኖችን ያመነጫል።
እነዚህም thyroid hormones ተብሎ የምጠሩ ስሆኑ በዝርዝር ስታዩ triiodothyronine[T3] and thyroxine[T4] ናቸው።
እነዚህ ሆርሞኖች በሰውነታችን ውስጥ ሁሉንም በሚባል ደረጃ፣ጤናማ Metabolism እንድካሄድ ያደርጋል።
ይህ ጤናማ ሜታቦሊዚም ልካሄድ የሚችለው የእንቅርት እጥያችን ጤናማ የሆነና በመጠኑ የሚያመርት ከሆነ ነው።
የእንቅርት እጥ ከልክ ያለፈ ወይንም ዝቅተኛ የሆነ ሆርሞን ስያመርት በሰውነታችን ውስጥ የተለያዩ የጤንነት እክሎች ያጋጥሙናል።
አንዳንደም እንቅርት እጥ በእንፌክሽን አልያም በእጥው መቆጣት[glandular infilamation] ምክንያት ልያብጥ ይችላል።
በሌላ በኩል የእንቅርት እጥው ያብጥና ወደ ካንሰር ልቀየርም ይችላል።

ለዚህም ክሊንካችን ሠይፋና እንድህ አይነት ችግሮችን መርምረው የሚያክሙ ስፔሳሊስት ሀኪሞች ይዜው በዘመናዊ መመርመሪያ ማሽኖች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

👉Thyroid function test[free T3, free T4,TSH]
👉Fine needle aspiration cytology[FNAC]

Seyfaana Owaantete anguwa!!!
Seyfaana Caring Hands!!!
ሠይፋና የእንክብካቤ እጆች!!!

የጉበትና የኩላሊት ህመም ያስቸግሮታል?በዘመናዊ ተክኖሎጂ የታገዘ የኮለስትሎል፤የኤሌክትሮላይት፣የጉበትና የኩላሊት   ኬሚስትር መመርመሪያ ማሽን አስገብተን በክሊንካችን በስፔሻሊስት ሀኪም  የህ...
24/02/2022

የጉበትና የኩላሊት ህመም ያስቸግሮታል?

በዘመናዊ ተክኖሎጂ የታገዘ የኮለስትሎል፤የኤሌክትሮላይት፣የጉበትና የኩላሊት ኬሚስትር መመርመሪያ ማሽን አስገብተን በክሊንካችን በስፔሻሊስት ሀኪም የህክምና አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን!

Seyifaana Owaantete anguwa!!!
Seyfana Caring Hands!!!
ሠይፋና የእንክብካቤ እጆች!!!

TEAM SEYFAANA

Oduu gammachiisaa!Naannoo Sidaamaa, magaalaa Hawaasaatti Kiliniikni Giddu-galeessaa SeyFaanaa haakimota ispeeshaalistoot...
22/02/2022

Oduu gammachiisaa!

Naannoo Sidaamaa, magaalaa Hawaasaatti Kiliniikni Giddu-galeessaa SeyFaanaa haakimota ispeeshaalistootaa muuxannoo olaanaa gonfataniin hundaa'ee hojii eegaluu isaa yoo ibsinu gammachuu guddaatu nutti dhaga'ama.

Bu'aa teknooloojii jabaanaa kan ta'an meeshaalee yaalaa ammayyaawaan gargaaramuun yaaliiwwan fayyaa armaan gadiitti heeraman haakiimota ispeeshaalistootaan sa'a 24 guutuu ni kennina.

1) Yaalii dhibeewwan keessoo
2) Yaalii dhibeewwan daa'immanii
3) Yaalii dhiibeewwan gadameessaa fi hordoffii yeroo ulfaa
4) Yaalii baqaqsanii yaaluu giddu-galeessa
5) Yaalii dhibeewwan gogaa fi wantoota gogaa waliin wal qabatan
6) Qorannoo xannachaa fi kaansarii
7) Tajaajila altiraasaawundii fi raajii
8) Yaalii dhibeewwan mormaa olii
9) Qorannoo akkasumas yaalii dhibeewwan onnee fi kalee
10) Qorannoo hucubaa fi wantoota isa waliin wal qabatan
11) Yaalii dhibeewwan hormoonii waliin wal qabatan
12) Qorannoo walii galaa seelota dhiigaa
13) Qorannoo keemistirii dhiigaa
14) Qorannoo kolestiroolii
15) Qorannoo tubboo fincaanii, pirosteetii fi afuuffee fincaanii; akkasumas yaalii isaanii
16) Qorannoo buusaa lafee fi yuriik asiidii yaalii isaanii waliin, akkasuma tajaajiloota biroos ni kennina.

Teessoon :- Magaalaa Hawaasaa, daandii mana barumsa Nigist Furraa gara mana barumsa Aliitoo geessurratti argamna.

Lakk. Bilbilaa
- 0994167019
- 0924579335
- 0468978348

Kunuunsa gahaa waliin!

Galatoomaa!

Seyfaana Kilinike hala'ladunni looso hanaffinota egensiinseemmo!!!Seyfana clinic officially started working!!!We are ope...
13/02/2022

Seyfaana Kilinike hala'ladunni looso hanaffinota egensiinseemmo!!!

Seyfana clinic officially started working!!!

We are open for the whole 24 hour!

hands!!!
anguwa!!!

08/02/2022
የምስራች =====================በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ  ብዙ ልምድ ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀክሞች የተመሠረተው ሰይፋና መካከለኛ ክሊኒክ ስራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ። ...
08/02/2022

የምስራች
=====================

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ብዙ ልምድ ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀክሞች የተመሠረተው ሰይፋና መካከለኛ ክሊኒክ ስራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ።

ከዚህ በታች ያሉ አገልግሎቶችን ለ24 ሰዓት በእስፔሻሊስት ዶክተሮች እንደሚሰጥ አስታውቋል።

1) የውስጥ ደዌ ህክምና

2) የህፃናት ህክምና

3) የማህፀንና የፅንስ ክትትል ህክምና

4) መካከለኛ የቀዶ ጥገናና የልጆችና የአዋቂዎች ግርዛት

5) የቆዳና ተያያዥ ህክምና

6) የዕጥና የካንሰር ምርመራ

7) የሲኖግራፍና የራጅ ምርመራ

8) ከአንገት በላይ ህክምና

9) የልብና የኩላልት ምርመራና ህክምና

10) የእንቅርትና ተያያዥ ምርመራና ህክምና

11) ከሆርሞን ጋር የተያያዘ በሽታ ምርመራ

12) አጠቃላይ የደም ሴል ምርመራ

13) የደም ኬሚስትሪ ምርመራ

14) የኮሌስትሮል ምርመራ

15) የጉበት፣ የአንጀትና የሀሞት ህመም ምርመራ

16) የሽንት ቱቦ፣ የፕሮስቴትና የፍኛ ህመም ምርመራና ህክምና

17) የመገጣጠሚያና የሪህ ህመም ምርመራና ህክምና እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ገልጿል።

አድራሻ:- ሀዋሳ ከንግስቴ ፉራ ት/ቤት ወደ አሊቶ ት/ቤት በሚወስደው መንገድ ላይ።

ስልክ +251 994 1670 19
+251 924 5793 35

07/02/2022
07/02/2022
የምስራች =====================በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ  ብዙ ልምድ ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀክሞች የተመሠረተው ሰይፋና መካከለኛ ክሊኒክ ስራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ። ...
07/02/2022

የምስራች
=====================

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ብዙ ልምድ ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀክሞች የተመሠረተው ሰይፋና መካከለኛ ክሊኒክ ስራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ።

ከዚህ በታች ያሉ አገልግሎቶችን ለ24 ሰዓት በእስፔሻሊስት ዶክተሮች እንደሚሰጥ አስታውቋል።

1) የውስጥ ደዌ ህክምና

2) የህፃናት ህክምና

3) የማህፀንና የፅንስ ክትትል ህክምና

4) መካከለኛ የቀዶ ጥገናና የልጆችና የአዋቂዎች ግርዛት

5) የቆዳና ተያያዥ ህክምና

6) የዕጥና የካንሰር ምርመራ

7) የሲኖግራፍና የራጅ ምርመራ

8) ከአንገት በላይ ህክምና

9) የልብና የኩላልት ምርመራና ህክምና

10) የእንቅርትና ተያያዥ ምርመራና ህክምና

11) ከሆርሞን ጋር የተያያዘ በሽታ ምርመራ

12) አጠቃላይ የደም ሴል ምርመራ

13) የደም ኬሚስትሪ ምርመራ

14) የኮሌስትሮል ምርመራ

15) የጉበት፣ የአንጀትና የሀሞት ህመም ምርመራ

16) የሽንት ቱቦ፣ የፕሮስቴትና የፍኛ ህመም ምርመራና ህክምና

17) የመገጣጠሚያና የሪህ ህመም ምርመራና ህክምና እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ገልጿል።

አድራሻ:- ሀዋሳ ከንግስቴ ፉራ ት/ቤት ወደ አሊቶ ት/ቤት በሚወስደው መንገድ ላይ።

ስልክ +251 994 1670 19
+251 924 5793 35

07/02/2022

Address


Telephone

+251924661342

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SeyFana Medium Clinic/SeyFaana Mereerima Kilinike posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram