Fmoh WYA Directorate Page

  • Home
  • Fmoh WYA Directorate Page

Fmoh WYA Directorate Page FMoH WYAD established to mainstream gender and disability in health sector to create equity, quality & accessible health services for all

ዋው…. በጣም ደስ ይላል....................ወ/ሮ ያምሮት አንዱዓለም ያላት የአመራርነት ብቃትና ክህሎት የትም ቦታ ሄዳ ብትሰራ ተጫባጭ ለውጥ ማምጣት የምትችልና ስራዎችን ጠንቅቃ ...
16/11/2018

ዋው…. በጣም ደስ ይላል....................
ወ/ሮ ያምሮት አንዱዓለም ያላት የአመራርነት ብቃትና ክህሎት የትም ቦታ ሄዳ ብትሰራ ተጫባጭ ለውጥ ማምጣት የምትችልና ስራዎችን ጠንቅቃ የምታውቅ፣ ስርታ የምታሰራ ብርቱና ታታሪ ሴት ናት፡፡ በእርግጠኝነትም ከዚህ ብኃላ የምትመራው ማዕከልን ለተሻለ ደረጃ እንደምታደርሰው እርግጠኞች ነን፡፡ መልካም የስራ ዘመን ያኛ ውድ የስራ ባልደረባ፡፡ ካንቺ ጋር የሰራንባቸው እነዛ ዓመታት ብዙ የተማርንበት፣ ችሎታና እውቀትሽን ሳትሰስቺ ያካፈልሽን ድንቅ ጊዜያት ነበሩ፡፡ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

18/09/2018
13/09/2018

ሴቶች በአእምሮ ህመም እንዳይያዙ ለመከላከል በባህል፤ በአኗኗራቸዉና በማህበረሰባዊ ተጽዕኖዎች ሳቢያ የሚከሰቱባቸዉን ጫናዎችን በተለያየ መልኩ መቀነስ ያሻል፡፡

በርካታ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በአጠቃላይ ሲታይ የአእምሮ ህመም ሁለቱንም ጾታዎች በእኩል የሚያጠቃ የጤና ችግር ነው። ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች በተለያዩ አይነት የአእምሮ ጤና ችግሮች ይጠቃሉ፣ የህመም ስሜቶቹም በወንዶችና በሴቶች ላይ በተለያየ ሁኔታ ይገለጻል። ሴቶች በአብዛኛው በድባቴ ህመም የመጠቃት እድላቸው ከወንዶች ይልቅ በእጥፍ የጨመረ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ከአንድ በላይ በሆኑ የአእምሮ ጤና ችግሮች በአንድ ጊዜ የመያዝ ሁኔታ ያላቸው ሲሆን፣ ራሳቸውን ለማጥፋት ከወንዶች የበለጠ ሙከራ ያደርጋሉ።

በተጨማሪም ጥናቶቹ ከድባቴ በተጨማሪ ሴቶች በተለያዩ የጭንቀት ህመሞች በአንድ ጊዜ ይያዛሉ። ሆኖም ሳይኮሲስ እና ባይፖላር የተባሉ ከባድ የአእምሮ ህመም አይነቶች ወንዶችንም ሆነ ሴቶች በእኩል ያጠቃሉ። ሴቶች በአእምሮ ጤና ችግሮች የመጠቃት ተጋላጭነታቸውን የሚጨምሩ በርካታ ሁኔታዎች አሉ። እነዚህ አጋላጭ ሁኔታዎች በአንድ ላይ ሲያጋጥሙ ከአንድ በላይ የሆኑ የአእምሮ ጤና ችግሮች በአንድ ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ። ሴቶች ከሌላው የህብረተሰብ ክፍሎች በበለጠ የድህነት ሸክም የሚሸከሙ በመሆኑ፣ በድባቴ ህመም የመጠቃት እድላቸውን ያሰፋዋል።
ከአማኑኤል የዓእምሮ ህክምና እስፔሻላዝድ ሆስፒታል በተገኘ መረጃ መሰረት ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው። በልጅነታቸው የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች፣ በአዋቂነት የዕድሜ ዘመናቸው በድብርት ህመም የመያዛቸው ዕድል በሦስትና በአራት እጥፍ ይጨምራል። በተመሳሳይ በፍቅር ወይም በትዳር አጋራቸው ጥቃት የተፈጸመባቸው ሴቶች በድብርት ህመም የመያዛቸው ዕድል በሦስትና በአራት እጥፍ ከፍ ያለ ነው።

ከዚህም ሌላ ሴቶች አስተማማኝ ባልሆነ የስራ ሁኔታ፣ እንዲሁም በዝቅተኛ ደረጃ ባለ ስራ ላይ የመሰማራት ሁኔታ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ክፍያ በማይከፈልባቸው ሌሎችን የመንከባከብ ስራ ላይ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙ መሆኑ የበለጠ ለአዕምሮ ህመም ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።
ሴቶች በማህበረሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና ውጥረት ለተሞላ ህይወት የሚዳርጋቸው ሲሆን፣ ይህንንም ውጥረት የተሞላ ህይወት ለመቀየር የሚያስችል ሚና በማህበረሰቡ ውስጥ የላቸውም።በዚህና ተያያዥ ጉዳዩች ላይ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚ/ር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አማኑኤል ህክምና እስፔሻላዝድ ሆስፒታል በመገኘት የአእምሮ ህክምና ነርስ ከሆኑትና በስራዉ ከ አስር አመታት በላይ ያሳለፉትን ሲስተር ጸሀይ ግርማን በማናገር የሚከተለዉን ምላሽ አግኝቷል፡፡

ሲስተር ጸሀይ በሆ/ሉ የሚገኙ በርካታ ሴቶች የሚስተዋሉባቸዉን የእእምሮ ህመሞች ሲገልጹ በርግጥ የእእምሮ ህመም የተለያዩ ዓይነቶች አሉት ለምሳሌ እስኪዚዮፍሬኒያ አለ፣ ባይፖላር ዲስኦርደር አለ፣ ዲፕሬሽን አለ ፡፡ ሌሎችም አሉ ፡፡እኛጋ የሚመጡት ሴቶች በብዛት ተጠቅተዉ የሚመጡት በባይፖላር ዲስኦርደር ነዉ ከወንዶችጋ ሲነጻጸር ማለት ነዉ፡፡ ይህ በሽታ ከስሙ እንደምረዳዉ በሁለት የስሜት (Mood ) ጽንፎች ታማሚዎችን የሚያመላልሰ ሲሆን ፣የታማሚዎቹ ሙድ ሲጨምር ማኒክ ( maniac) ሲሆኑ ሙዚቃ ከፍ አድርገዉ ሊከፍቱና ሊጨፍሩ ይችላሉ፡፡ ገንዘባቸዉን ሊያባክኑ ይችላሉ፡፡ ሰዉነታቸዉን አብዝቶ መኳኳል ማታተብ ከኖርማል ዉጪ በሆነ መልኩ ሊያበዙ ይችላሉ፡፡ የፍትወተስጋ ስሜታቸዉ ሊጨምር ይችላል፡፡ ከዚህ ስሜት ወጥተዉ ደግሞ ዲፕሬሽን (ድባቴ ) ዉስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ፣ እራሳቸዉን ማጥፋት ሊመኙ ይችላሉ እንዲሁም የበታችነት ስሜት ሊሰማቸዉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም የባይፖላር ህመምተኞች እነዚህ ሁለት ስሜቶች ሲፈራረቁባቸዉ ይስተዋላል፡፡

ሌላኛዉ ደግሞ ከስደት ከአረብ ሀገር የሚመለሱት ሴቶች ደግሞ የሚጠቁት በአብዛኛዉ በፖስት ትራዉማቲክ ስተረስ ዲሰኦርደር Post Traumatic Stress Disorder (PSTD)፡፡ ይህ ህመም ሴቶቹ በዐረብ ሀገራት ሳሉ ጥቃት ደርሶባቸዉ አስገድዶ መደፈር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን በማስታወስ እንደመባነን እያደረጋቸዉ ሲሰቃዩ ማለት ነዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከአረብ ሀገራት የመጡት በከባድ የአእምሮ ህመም ስኪዚዮፍሬኒያ (schiziophrenia) ሲያጠቃቸዉ ይስተዋላል፡፡ በተለይም ካታቶኒያ (catatonia) የሚባለዉ የስከዚዮፍሬኒያ ዓይነት ያጠቃቸቃቸዋል፡፡ በዚህ ዓይነቱ የአእምሮ ህመም ተጠቁ ማለት ደግሞ አይበሉም፣ አይጠጡም ፣እንቅስቀሴም የላቸዉም መድሀኒት ለመዋጥኳ አፋቸዉን ታግለን ከፍተን ነዉ የምናዉጣቸዉ፡፡ በቃ ድርቅ ብለዉ ነዉ የሚቀሩት ማለትም ተኝተዉ ከሆነ ተኝተዉ ተቀምጠዉም ከሆነ ተቀምጠዉ ማለት ነዉ፡፡

በሆስፒታሉ ስለሚሰጠዉ የህክምና አገልግሎት ሲገልጹም እኛጋ የሚተኙት ጤና ጥበቃ ባወጣዉ መስፈርት በአማካኝ ለ 32 ቀናት ብቻ ነዉ ፡፡ ከዚያም መድሀኒቱን ባሉበት ሁነዉ ይከታተላሉ፡፡ ተኘኝተዉ የሚታከሙት ታማሚዎች በሳምንት ሁለት ቀን በኬዝ ቲም ነዉ የሚታዩት ፡፡ ኬዝቲሙ ከተለያዩ የአእምሮ ህክምና ባለሙያዎች የያዘ ነዉ ማለትም ከአእምሮ ሀኪም ፣ከስነልቦና ባለሙያ የአእምሮ ህክምና ነርስ ከክሊኒካል ነርስ ከመድሀኒት ሰጪ እና ከማህበረሰብ ሳይንስ ባለሙያ ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች እንደሙያቸዉ በሽተኛዉን ያክማሉ፡፡ በየዕለቱ ደግሞ በነርስ ሕክምናና መድሀኒታቸዉን ይወስዳሉ ፡፡ ከሚሰጣቸዉ ህክምና ባሻገር ሆስፒታሉ ሞዴስ፣ፓንትና ፒጃማ በተሟላ መልኩ ያቀርብላቸዋል ብለዋል፡፡

የአእምሮ ህመምተኛ በመሆናቸዉ ስለሚደርስባቸዉ በደል ሲያብራሩ ሴት የአእምሮ ህመምተኞች ሴት ስለሆኑ ብቻ ሆስፒታል ከመምጣታቸዉ በፊት በአብዛኛዉ ወሲባዊ ጥቃት ሊደርስባቸዉ ይችላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በኤች አይ ቪ ኤድስ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ያልተፈለገ እርግዝና ሊገጥማቸዉ ይችላል፡፡በህብረተሰቡ በኩል ደግሞ አድልዎና መገለል ሲደርስባቸዉ ይስተዋላል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ደግሞ ባሎቻቸዉ ስለሚፈቷቸዉ ትዳራቸዉ ሊፈርስና ልጆቻቸዉ ሊበታተኑ ይችላል በማለት ገልጸዉታል፡፡

ሲስተር ጸሀይ በመከላለሉ ረገድ መደረግ ስላለበት ጉዳይ ሲገልጹ ሴቶች በአእምሮ ህመም እንዳይያዙ ለመከላከል በባህል በአኗኗራቸዉና በማህበረሰባዊ ተጽዕኖዎች ሳቢያ በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን በተለያየ መልኩ መቀነስ በዋነኛነት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ለሴቶች የተለያዩ ዕድሎችን ማለትም የመማር፣ የመስራትና በኢኮኖሚ የማደግ ዕድሎችን ከወንዶች እኩል ማዳረስ አስፈላጊ ነዉ በማለት አጠቃልለዋል፡፡

መስከረም 3/2011 (የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር)

12/09/2018
well done. great Job.
27/08/2018

well done. great Job.

Announcement: Undergraduate Scholarship Oppurtunity for talented youth with disabilities and disadvantages.

"Transformation towards sustainable and resilience society for all" "ሁሉን አቀፍ ጠንካራና ዘላቂ ማህበረሰብ እንገንባ"
04/12/2017

"Transformation towards sustainable and resilience society for all"
"ሁሉን አቀፍ ጠንካራና ዘላቂ ማህበረሰብ እንገንባ"

“በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቆም የወንዶች አጋርነትን ማጠናከር” “ Leave no one behind: Ending Violence Against Women and girls”
27/11/2017

“በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቆም የወንዶች አጋርነትን ማጠናከር”
“ Leave no one behind: Ending Violence Against Women and girls”

በአመራርነት ክህሎት ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ--------------------------------------------------------------------------በጤና ጥበቃ ሚኒስ...
23/11/2017

በአመራርነት ክህሎት ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
--------------------------------------------------------------------------
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከጤና ስርዓት ማጠናከር ልዩ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከሁሉም ክልሎችና ከጤ/ጥ/ሚኒስቴር ዋናው ግቢ ለተውጣጡ መካከለኛ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአመራርነት ክህሎት ዙሪያ በአዳማ ከተማ ሪፍት ቫሊ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ በስልጠና ማብቂያው ላይ የመዝጊያ ንግግርና አቅጣጫ የሰጡት በጤ/ጥ/ሚ/የሴ/ወ/ጉ/ዳ/ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ያምሮት አንዱዓለም አመራርነት ትዕዛዝ ማስተላለፍና ማስፈጸም ብቻ ሳይሆን ግንባር ቀደም መሆንና ለበታች ሰራተኞች ስራን ስርቶ ማሳየትና ውሳኔ አሰጣጥ ላይም ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡ ሰልጣኞችም ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በስራ ቀይረው ከትላንቱ በበለጠ ነገ የተሸለ አመራር መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fmoh WYA Directorate Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram